Translate

Friday, May 15, 2015

ግንቦት 7ን በማስመልከት የወጣ የጋራ አቋም መግለጫ – አገራችንና ሕዝባቸን ማዳን ግባችን አድርገን በአንድነት አንሰራለን

አገራችንና ሕዝባቸን ማዳን ግባችን አድርገን በአንድነት አንሰራለን

Ginbot 7 Statement
የአንድነት፣ የመከባበር፣ የመቻቻል እና የነፃነት ምሳሌ የሆነችው አገራችን እኩይ አላማቸውን ለማሳካትና የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም በሚንከላወሱት የወያኔ ቡደን አገራችንና ሕዝባችን ከምንግዜውም በከፋ ደረጃ ላይ አድርሰዋታል።

ወጣቱ በአገሩ ላይ ተምሮና ሰርቶ የመኖር እድሉ ለወያኔው አገዛዝ ማደር አልያም አገሩን ጥሎ መሰደደ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ አገሩን ጥሎ የሚሰደደው ዜጋ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ለመሰደድ በሚያደርገው ጉዞ ምን ያህሉ በበርሃ እንደሚቀርና የአሳ እራት እንደሆነ የመገናኛ ብዙሃን በሰፊው ሲዘግቡት ቆይተዋል።
በተለያየ አገር በስደት ከሚፈልጉት አገር የደረሱትና የእለት ጉርሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ ደፋ ቀና በሚሉበት ሂደት ውስጥ በደቡብ አፍሪካ በቁማቸው በአሳት መቃጠል፣ በሊቢያ አይናቸው እያየ መታረድና በጥይት መደብደብ ሆኗል እጣ ፋንታቸው።
እናም አገርና ሕዝብ በእንደዚህ አይነት አስከፊ ሂደት መቀጠል የለበትም የወያኔም የግፍ አገዛዝ ሊበቀው ይገባል በሚል ቀደም ብለን ይህን በታኝ ስርዓት በትጥቅ ትግል እየተፋለምን ያለን ደርጅቶች እኛ አንድ ሆነን ሕዝቡን አንድ በማደረግ አገራቸንና ሕዝባችንን ነፃ ማውጣት የሚገባን ወቅት አሁን ነው በሚል ስርዓቱን ለማስወገድ በሚደረገው የትግል ሂደት በትብብር መስራት አለብን በሚል ውይይት ጀምረናል።
ወደፊት በሚኖረው የትግል ሂደት በትብብር፣ በጥምረት ብሎም በውህደት ለመስራት በውይይት ላይ የምንገኘው ድርጅቶች፡-
1. የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
2. የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ
3. የቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ
4. የአማራ ዴሞክራሲ ሃይል ንቅናቄ
5. አረበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ
ስንሆን ከሁሉም አስቀድመን አገራችንና ሕዝባችን ማዳን ግባችን አድርገን እንስራ በሚል መርህ በማንኛውም መንገድ አብረን መስራት አለብን ወደ ፊት ምንም አይነት ልዩነት ይኖረናል ብለን ባናምንም በሂደት ወደ አንድ የምንመጣበትን ሁኔታ እያመቻቸን አሁን ግን አገርና ሕዝብን የማዳኑን ስራ እንጀምር በሚል ውይይት እያደረግን መሆናችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መግለፅ እንወዳለን።
አምባገነኑም የወያኔ ቡድን እንዳለፉት ምርጫዎች ሁሉ በቅርቡ የሚደረገውን የይስሙላ ምርጫ ለማድረግ ደፋ ቀና እያለ ሲሆን በተለያየ አገራት በእናትህ፣ በአባትህ፣ በወንድምህ፣ በእህትህ ላይ ላይ እየደረሰ ላለው ዘግናኝ ግፍ እንኳን ወቅቱን ጠብቆ ተቃውሞውን ያልገለፀ ኢትዮጵያዊ ባህሪ የለሌው እኩይ ሥርዓት በመቃወም ረገድ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገህ ቢሆንም በተደራጀ ሁኔታ እየታገልን ከምንገኘው ተቃዋሚ ድርጅቶች ጎን በመሰለለፍ አስፈላጊውን አስተዋጽዖ እንድታደርግ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
አንድነት ሃይል ነው!!!
30/08/2007 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment