JONAS TAMERU ( OSLO NORWAY )
ለሁለት አስርተ አመታት በኢትዮጲያና በህዝቦቿ ላይ ነግሶ በማን አለብኝነት አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ በሁሉም ያገሪቱ አቅጣጫዎች ሰላማዊውን ህዝብ ለሞትና ለስደት እንዲሁም ለእስር ሲዳርግ የነበረው አምባገነኑ የህውሃት ዘረኛ ቡድን የመለስ ዜናዊ ሞት ተከትሎ በይስሙላ ምርጫ ያስቀመጠው አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የዚሁ ዘረኛ ቡድን ደቀ መዝሙር ሆኖ በነሱ በመቃኘት ተፈጥሮአዊ ባህሬያቸውን ወርሶ አሁንም በሃገራችን ስርዓቱ ካለው እኩይ ተፈጥሯዊ ባህሪ አንፃር የናፈቅነውንና የተመኘነውን ነፃነትም ሆነ ለውጥ ሳይመጣ እነሆ ሌሎች ንፁሃን ሲገደሉና ሲሰደዱ እንዲሁም ሲታሰሩ አየን ሰማን፡፡
ለብዙሃን ዜጎች ህይወት መጥፋት፣ መሰደድና በየእስር ቤቱ መታጎር ተጠያቂ የሆነው አምባገነኑ የወያኔ ቡድን እንዲሁም ስርዓቱ በተለይ ሃገር ሲያፈርሱ፣ ሲመዘብሩና ደሃውን የህብረተሰብ ክፍል ሲየፈናቅሉና በችጋር ሲቆሉ የነበሩት የህወሃት መስራቾች በዘፈቀደ ባገኙት አጋጣሚ እዚህ ምስኪን ህዝብ ላይ አፋቸውን ማላቀቃቸውን መዘባበታቸው የተለመደ ቢሆንም የወያኔ ጠ/ሚንስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተለያየ አጋጣሚ በስርዓቱ መገናኛ ቡዙሃን ቀርበው የሚሰጡት አስተያየትም ሆነ የሚናገሩት እጅግ የወረደና ስነምግባር የሌለው ዲስኩር ሰውየው በራሳቸው ሳይሆን ስርዓቱ እንደፈለገ እንደሚዘውራቸው ፍንትው አርጎ የሚያሳይ ነው፡፡
ጥቂት የማይባል የህብረተሰብ ክፍል ለዝች ዘመናትን በግፍና በመከራ ላሳለፈ ሃገርና ህዝብ የመጣል ተብሎ በታሰበው ወይም በመጣው አዲሱ መሪ ላይ ጭላንጭል ተስፋ ሰንቆ ቢቆይም ተስፋ አሰቆራጭ ሁኔታ የተፈጠረው ብዙም ግዜ ሳይፈጅ መሆኑ ተስፋ አድርጎ የነበረውን ተስፈኛ አሁንም የመከራው ቀንበር መፈታት ሳይሁን አለመላላቱን ያየነው አዲሱ ጠ/ሚንስትር ሃ/ማርያም ደሳለኝ ከሀ እስከ ፐ የሟች ቅጂ መሆናቸው እየተስተዋለ ሲመጣ ነው፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ የወያኔ ስርዓት በዙሪያው የሚሰበስባቸውና ወደ ስልጣን የሚያስጠጋቸው ሰዎች ምን አይነት አመለካከትና ስብእና ወይም ሀገራዊም ሆነ ህዝባዊ ስሜት አላቸው ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ሊቅ ወይም ነብይ መሆን የሚጠበቅብን አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም የህውሃት ወያኔ ቡድን ይችን ሃገር በገዛበት ሁለት አስርተ የግፍና የመከራ ዘመን ውስጥ በራሳቸው የሚተማመኑትን፣ በሃሳብ ደረጃ አምባገነኑን ስርዓት የሚሞግቱትን በተለይ ለሃገርና ለህዝብ የሚጠቅም ፅንሰ ሃሳብ የሚያንፀባርቁትን የሃገር ሃብት ምሁራን ሲገድል፣ ሲገፋና ሲያሳድድ በግፍ ሲያስር ዘመን ማሳለፉ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በአመለካከት የተለዩትን አብረውት በትግል ሜዳ የነበሩትንም ሁሉ ሳይቀሩ ሲያሶግድ፣ ሲያስርና ሲያሳድድ መኖሩ በህይወት ያሉ የቀድሞ የህውሃት ሰዎች ምስክር ናቸው፡፡ ይህንን ከተረዳን አቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝ በዚህ ስርዓት ተመርጠው እንዴት እዚህ ደረሱ የሚለውን ለማወቅ ከላይ እንደጠቀስኩት ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡
በሁለተኛ ደረጃ አቶ ሃ/ማርያም በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ተፅእኖም ይሁን ወያኔ የህዝብ ይሁንታ ለማግኘት ቁልፍ የሆኑ የስልጣን ቦታዎችን ይዞ ከፊት አስቀድሞ መንበረ ስልጣኑን ቢሰጣቸውም ምንም የመወሰን አቅም የሌላቸው ወያኔ ለሽፋን ያስቀመጣቸው መሆናቸውን ያየንባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው፡፡የሳቸውም በራስ ያለመተማመን መንፈስና የስብእናችው ጉዳይ ታክሎበት በይዘትም ሆነ በፅንሰ ሃሳብ የዘረኛው አምባገነን ስርዓት ቅኝት መሆናችው በተደጋጋሚ ከሚሰሩት ስራ ለማየት ችለናል፡፡ የእሳቸው እራሳቸውን ያለመሆን ችግር አንድም እርምጃ ወይም ውሳኔ ለይስሙላ በተሰጣቸው ስልጣን እንደማይፈፅሙ የሚያሳየን ብዙ ማሳያዎች ቢኖሩም ለአብነት ያህል አንዱን ልጥቀስ፡፡ ከወራት በፊት የአውሮፓ የፓርላማ የልኡካን ቡድን በኢትዮጲያ ውስጥ ያሉትን የህሊና እስረኞች በተለዪም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፣ጋዜጠኛና መምህርት እርእዮት አለሙ፣ እንዲሁም ወጣቱን ፖለቲከኛ አንዶለም አራጌና ሌሎችንም የፖለቲካ እስረኞች ለመጎብኘትና ስላለው ሁኔታ ከእስረኞቹ ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት በህጋዊ መንገድ አዲስ አበባ በመገኘት በተያዘላቸው ፕሮግራም መሰረት እኚሁ የወያኔን ሹመኛ ጠ/ሚ ሃይለማርአም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው ስለመጡበት አላማና ተነጋግረው በማግስቱ በተያዘላቸው ፕሮግራም መሰረት እስረኞችን ለመጎብኘት ቃሊቲ ያመራሉ ሆኖም እዛ ያጋጠማቸው የማይታመን ነገር ነበር፡፡ የህንን የአውሮፓ ፓርላማ ልኡካን ቡድን የቃሊቲው እስር ቤት አዛዥ እንደማያቃቸውና የመጡበትንም ተልእኮ እንደማይፈፅሙ አስረግጦ ነግሮ ይመልሳቸዋል፡፡ ልብ በሉ ጠ/ሚ ታብይው እንኚህን ዲፕሎማት ተቀብሎ አሰተናግዿል ስለመጡበትም ጉዳይ ጠንቅቆ ያቃል እናም ይሁንታውን ሰቷቸዋል ሆኖም በአለቆቹ በህውሃት በኩል የልኡካን ቡድኑ ጉብኝት እንዲሰረዝ ሆነ፡፡ ይህ ማለት ጠ/ሚ ተብዬው በራሱ አንዳችም የመወሰን ስልጣን እንደሌለውና በጥቂት የስርዓቱ ሰወች እንደሚነዳ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡
ሰውየው ኢትዮጲያንና ህዝቧን የሚመሩት ከአለቃቸው በውርስ ባገኙት የሳቸው ባልሆን ባህሪ ብቻ ሳይሆን ይችን ሃገር መዝብረው በደለቡና በሰቡ የህውሃት ሰዎች በርቀት መቆጣጠሪይ ስለሆነ ከህዝብ ሳይሆን ከነኚሁ የሃገርና የህዝብ ጠላቶች ክብርና ሞገስ ለማግኘት ሆዳምና ከራሱ ባለፈ ስንዝር የማያስብ ጥርቅም በሞላበት ፓርላማ ተብይ ውስጥ በሙት መንፈስ እየተመሩ መኮረጅ የቻሉትን ያህል ሲተውኑ፣ ተልኳቸውን በድል ለመወጣት ሲወራጩና ሲሳደቡ፣ እንዲሁም ህዝብ ክብር የሚሰጣቸውን የህሊና እስረኞችንና የነፃነት ታጋዮችን ሲዘልፉ፣ ከቃላት አጠቃቀምና አስተያየት ጀምሮ የሳችው ባልሆነ ስብእና የሚያደርጉት ትእይንት በሳችው ደረጃ ካለ ከተማረና ከዚህ ዘመን ስልጡን ሰው የሚጠበቅ አይደለም፡፡
ሰሞኑን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የታየው የሰውየው ባህሪ ምንም ጠብ የሚል ነገር ያልተገኘበት እንደውም ባዶ ነታቸው የጎላበት ነበር፡፡ እንዳየነው አርቆ ከማሰበና ከብስለት ጋር ያልተዋሃደ እጅግ ተራና የወረደ መግለጫ ሰውየው የተሞሉትን ያህል እንደተነፈሱ የሚያሳይ ነው፡፡ ህገ- መንግስቱ በሚፈቅደው መልኩ ያውም እጅግ በጣም በጠበበ ምህዳር ለመብት፣ ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሕዝቡን ዘርፈ ብዙ ችግር አንስተው የሚታገሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች በዚህ መንገድ መግለፅ አሁንም ወደፊትም በሕዝብ ሊነሱ የሚችሉ ዘርፈ ቡዙ ችግሮች ያለበት ስርዓት ለከት በሌለው ልቅነት በዚህ መጠን መመፃደቅ ሕዝብን ከመናቅና ከማዋረድ እንደማይተናነስና ዋጋም እንደሚያስከፍል ከስነምግባር ውጪ የሆኑት ጠ/ሚ የገባቸው አይመስልም፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ !! ሞት ለወያኔና ለሆዳሞች!
No comments:
Post a Comment