በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞችን ይዛ ወደ ላምቤዱሳ ደሴት በማቅናት ላይ የነበረች አንዲት ጀልባ  እሳት  ተቀስቅሶባት  በመስጠሟ 92 ሰዎች ሞቱ ።
በጀልባዋ ላይ የተቀሰቀሰውን እሳት ለማምለጥ ስደተኞቹ ወደ ባህር መዝለላቸውና  ጀልባዋም መስጠሟ  ተነግሯል ። 150 የሚጠጉ ሰዎችን ህይወት ማትረፍ  እንደተቻለ ፖሊስ አስታውቋል ።
200  የሚሆኑ  ስደቶች  ግን እስካሁን  የደረሱበት  ያልታወቀ ሲሆን ፥  የሟቾች ቁጥርም አሁን ከተጠቀሰው  በላይ  ሊሆን  እንደሚችል ተገምቷል ።
ከስደተኞቹ መካከል  የሚበዙት  ኤርትራውያንና  ሶማሊያውያን ሲሆኑ ፥ አንድ ህፃንና  አንድ ነፍሰ ጡር ሴትም  ይገኝተውበታል ።
በአሁኑ ወቅት  የሜዲትራኒያን ባህር የተረጋጋ ሁኔታ ያለው በመሆኑ  በየእለቱ አፍሪካውያን ስደተኞችን የያዙ ጀልባዎች በደቡባዊ የጣሊያን  የባህር ዳርቻ  እንደሚደርሱ  ነው የሚነገረው ።
ሆኖም ስደተኞቹን የሚጭኑት ጀልባዎች ጤንነት አሳሳቢ በመሆኑ  አሳዛኝ ክስተት በአከባቢው  እየተደጋገመ መጥቷል ።
የመንግስታቱ  ድርጅት  የስደተኞች ጉዳይ ደርጅት እንደሚለው  በዚያ  አከባቢ  ችግር ባለባቸው ጀልባዎች በመሰፈራቸው በየዓመቱ በተንሹ 1  ሺህ 500 የሚሆኑ  ስደተኞች ባህር ላይ  የቀራሉ ።
ምንጭ ፦  ቢቢሲ
 
No comments:
Post a Comment