Translate

Wednesday, May 15, 2013

የባህር ዳሩ ገዳይ ጉዳይ፤ ኮስተር ያለ ወሬ


የፌስ ቡክ ወዳጆቼን ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና የኢትዮጵያ መንግስት የባህር ዳር ግድያን አስመልክቶ ምን ብለው ይሆን… የሚለውን ጠይቄ ነበር፡፡ ብዙዎቹ ያመለጠኝን ሲነግሩኝ ሌሎቹም ደግሞ በቀጣይ ኢቲቪ በጉዳዩ ላይ ሊያወራ የያዘውን ቀጠሮ ነገሩኝ፤ እኔም አድብቼ ጠብቄ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን አየሁት፤
21እንደተለመደው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሆነ የማጭበርበር ነገር ይታይበታል፡፡ ለምሳሌ የገዳዩ አስከሬን ከአባይ ወንዝ ውስጥ ሰጥሞ በመከራ ነው ያገኘነው ሲሉ አሰማን፡፡ የገዳዩን ፎቶ እንዳየነው ግን ውሃ የነካውም አይመስልም፡፡ ታድያ ጋዜጠኛው… ማንም ሊጠይቅ የሚችለውን ጥያቄ መግለጫ የሚሰጡትን ሰውዬ  ለምን አልጠየቀም ብለን ብንጠይቅ፤  የሆነ ማጭበርበር እንዳለ እንረዳለን፡፡

ኢቲቪ የህዝቡን ቁጣ ለማቅረብ ሞክሯል፡፡ በተለይም “ሰውዬው ያንን ሁሉ ህዝብ ሲፈጅ ጓደኞቹ የሆኑት ፖሊሶች እንዴት ዝም አሉት… እኛ ከስንት ጠላት ይጠብቁናል ያልናቸው ፖሊሶች አንድ ሰው በአደባባይ ይሄንን ሁሉ ሰው ሲፈጅ ዝም የሚሉ ከሆነ እየጠበቁ ያሉት ህዝቡን ነው ማለት እንደምን ይቻላል…” ብሎ የተቆጣው የባህር ዳር ህዝብ ተቆራርጦም ቢሆን ሀሳቡ በኢቲቪ ሲቀርብ አይተናል፡፡  በዚህም ኢቲቪን ማመስገን ባይቃጣንም ሁለት ከአስር ውጤት እንሰጠዋለን፡፡ (ኢቲቪዬ በርትተህ ስራ እና ውጤትህን አሻሽል ብለንም እናበረታታለን)
አሁን በቅርቡ “ወደፊት ምን መሆን ይፈልጋሉ” ሲባሉ “ጠቅላይ ሚኒስትር ብሆን ደስ ይለኛል” ብለዋል፤ ተብለው የሚፎገሩት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል የሚል ነገር ሰምቻለሁ… ባለፈው ጊዜ ኦባማ አንድ ቀውስ ወደ ሃያ የሚጠጉ ተማሪዎችን ፈጀ የተባለ ጊዜ እንባ እየተናነቃቸው ወደ መድረክ ብቅ ብለው፤ “ከዚህ ግድያ ጀርባ ምን እንዳለ ባስቸኳይ እናጣራለን… ለዚህም የሚሆን ልዩ ሀይል አሁኑኑ ይቋቋማል…” ብለው ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት እንደሰጡት አሳይተውን ነበር፤ አቶ ሃይሌ ግን ቢሯቸው ሆነው እንደ አይናፋር አፍቃሪ በደብዳቤ ሀዘናቸውን ገለፁ ሲባል የሰማን ሁሉ በዚህ በዚህ እንኳ ምናለ እነርሱን ቢመስሉ… ብለን ጠይቀናል፡፡
በአንዳንድ ወዳጆቻችን ዘንድ ደግሞ ዜናው የተሰራበት ሁኔታ በጣም ሆድ የሚያስብስ ነው፤ አንድ ነገር ሲፈጠር ዘሎ ዘር መቁጠር እንዴት ያለ መረገም ነው፤ “ተጠርጣሪው የሌላ ብሄር አባል ነው፤” የሚል ዘገባ ሰምቻለሁ፤ ለመሆኑ ሌላ ብሄር ማነው… ለመሆኑ ይሄ ሰውዬ የየትኛውስ ብሄር አባል ቢሆን የፈፀመው ብልግና ብሄሩን ይገልጻልን… እንኳንስ የብሄሩን እና የቤተሰቡ መለጫ ሊሆን ይችላልን… በፍፁም አይመስለኝም፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ከሰውዬው እኩል ተጠያቂ መሆን ያለበት አካል ለእንዲህ ያለው ቀውስ መሳሪያ ያስታጠቀው መንግስት ነው እንጂ ብሄሩ፤ ዘመዶቹ ዌም ቤተሰቦቹ አይደሉም፡፡  ጉዳዩን ወደ ብሄር እና ቤተሰብ ማጠጋጋት ሰውዬው ካጠፋው የሚበልጥ ሌላ ጥፋት ነው….!
በድጋሚ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ፡፡
በድጋሚ ይሄንን ሰውዬ ያስታጠቀ መንግስት ሌሎቹንም ቀውሶች ያስፈታ እላለሁ፡፡
በነገራችን ላይ (ይለን ነበር መስፍኔ….)
በነገራችን ላይ፤ በዛ ሰሞን ቦሌ መንገድ ላይ የቀድሞ ሚስቴ ነበረች ብሎ እናቷን አቁስሎ እርሷን የገደለው ሰውዬም ያስታጠቀው መንግስት ነው፡፡
ስለዚህም ድምፃችንን ከፍ አድርገን መንግስት ሆይ አስለከመቼ ገዳዮቻችንን ታስታጥቃለህ…?.በማለት ኮስተር ብለን መጠየቅ ይገባናል፡፡
Abetokichaw

No comments:

Post a Comment