ECADF – በባህርዳር ከተማ አንድ የፌደራል ፖሊስ (ወያኔ) ንጹሃን ዜጎችን እንደጨፈጨፈ የሀገሬው ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው። ማንኛውም ጋዜጠኛ ይህንን ለማጣራት የሚከብደው አይደለም። በርካታ መረጃዎች ድርጊቱ ከተፈጸመበት ምሽት ጀምሮ ሲደርሱን ቆይተዋል። የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) አሳቃቂውን ጭፍጨፋ በተመለከተ በቀጥታ የሀገሬውን ነዋሪዎች ማነጋገር ችሏል።
ይህ በዚህ እንዳለ አንጋፋው የኢትዮ-ሚድያ ድረ-ገጽ ግድያውን የፈጸመው “Ethiopian Unity and Freedom Force (EUFF)” (የኢትዮጵያ አንድነትና የነጻነት ሀይል) በመባል የሚጠራ የሽምቅ ተዋጊዎች ቡድን ነው በማለት ዘግቧል። ድረ-ገጹ ዘግይቶ እንዳደሰው ዜና ከሆነ ደግሞ ከሟቾቹ መካከል ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናት ይገኙበታል (የተባሉት ባለስልጣናት በስም አልተጠቀሱም) ኢትዮ-ሚድያ የመረጃውን ምንጭ ያደረገው ይህንኑ ግድያውን እንደፈጸመና ሀላፊነቱንም ወስጃለው ያለውን ቡድን ነው። ዘገባው በከፊል እንዲህ ይነበባል፣
The Ethiopian Unity and Freedom Force (EUFF), a rebel group that has been targetting the ruling EPRDF party officials and their businesses, claimed responsibility for the deadly attack. EUFF said the names of the officials killed and wounded would be released soon.
ለመሆኑ “EUFF” በመባል የሚታወቀው የአርበኞች ቡድን ማን ነው? ተዋጊዎቹስ እነማን ናቸው? የቡድኑን ቃል-አቀባይ መድረስ ይቻል ይሆን? ይህ ቡድን የራሱ የሆነ ልሳን አለው? ድረ-ገጽ ይኖረው ይሆን? በርካታ ጥያቄዎችን ማንሳት የሚቻል ቢሆንም ማን መልሱን እንደሚመልስ ማወቅ ግን አስቸጋሪ ነው።
በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው እስካሁን ከ16 በላይ ሰዎች ከወያኔው ታጣቂ በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል። ምናልባትም ቆስለው ከተረፉት መካከል የሚሸነፉ ካሉ ደግሞ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል።
የወያኔ/ኢህአዴግ ባለስልጣናትና በቁጥጥራቸው ስር ያሉ የመገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን አስመልክቶ የሚያሰራጯቸው መረጃዎችም እንዲሁ ግራ የተጋቡና ወይንም ደግሞ ሆን ብለው ግራ ለማጋባት የሚመስሉ አይነት ናቸው።
አያሌው ጎበዜ የክልሉ ፕሬዝዳንት (አብዛኛው ህዝብ ስልጣኑ ከተላላኪነት ያለፈ አይደለም ብሎ ያምናል) ሰላማዊ ሰዎችን የጨፈጨፈው የመንግስታቸው አንጋች እንዳልተያዘና በጸጥታ ሀይሎች እየታደነ መሆኑን ሲገልጹ፣ ሌላኛው ሹም ደግሞ ቀበል አድርጎ “ገዳዩ ሊያዝ ሲል ዘሎ አባይ ወንዝ ውስጥ ገባ” ይላል። እንዲህ እንዲህ ሲሉ አረፋፍደው በመጨረሻ ፊቱ በደም የተበከለና የፌደራል ፖሊስ ዩኒፎርም የለበሰ አስክሬን ቃሬዛላይ አድርገው “ይሄው ገዳዩ አሁን ተገኘ” በማለት ደመደሙት።
ይህ ሁሉ መዘባረቅ እና ማዘበራረቅ ለምን አስፈለገ? እወነተኛ የህዝብ ወገን ጋዜጠኞች ሰላማዊ ዜጎች በቄያቸው ለምን እና በማን እንደተጨፈጨፉ ያሳውቃሉ ብለን እናምናልን።
No comments:
Post a Comment