Translate

Sunday, February 10, 2019

በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን



በሌብነት የተጠረጠሩት በረከት ስምኦንና ታደሰ ካሣ አርብ በባህር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በዕለቱ ሁለቱም ግለሰቦች ያሉባቸውን ችግሮች ያስረዱ ሲሆን በተለይ በረከት ስምዖን በእስርቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲል ማማረሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ኮምፒውተር ያስፈልገናልም ብለዋል።

Tuesday, May 29, 2018

በአዲስ አበባ፣ አውሮፓና አሜሪካ ለ“ዘመቻ ዓቢይ” የስውር ምልመላ ተጀምሯል!

የ“ዘመቻ ዓቢይ” - አዝማቾችን ዓቢይ ያውቋቸዋል?



  • ኃይሌ ገብረሥላሴ መልማይ መሆኑ ታወቀ
የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዳላስ ሊያካሂድ ያሰበው ሰላሳ አምስተኛ የስፖርት ፌስቲቫል ከወዲሁ እጅግ ጥንቃቄ በሚያሻው ጉዳይ ተወጥሯል። የጎልጉል የመረጃ አቀባዮች እንዳሉት በአገር ውስጥ፣ በአሜሪካና በአውሮፓ የሕዝብ ግንኙነት የሚሠሩ ክፍሎች በምሥጢር እየተመለመሉ ነው። ኃይሌ ገብረሥላሴ አገር ውስጥ ሆኖ ይህንኑ የምልመላ ሥራ እየሠራ ነው። አነጋጋሪ የሆነው ይህንን ዘመቻ የሚያከናውኑት ክፍሎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ እውቅና ይኑራቸው አይኑራቸው አለመታወቁ ነው።

Wednesday, April 4, 2018

ቀጣዬ 100 ቀናት!(ኤርሚያስ ለገሰ)

Ermias Legesse, author and ESAT TV and Radio contributor
መንደርደሪያ
የትግራይ ነፃ አውጪ በገጠመው ሕዝባዊ ማእበል፣ እንዲሁም የሕዝቡን ተቃዉሞ በተከተለበት ጫና ዶክተር አቢይን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት አምጥቷል። የዶክተር አቢይ ወደ ፊት መምጣት በብዙ መልኩ የተደበላለቀ ስሜቶችን ፈጥሯል። በህውሓት ደጃፍ ከፍተኛ ቁዘማና ንዴት የፈጠረ ሲሆን በለውጥ ፈላጊው ዘንድ የተከፋፈለ አስተያየቶች በመስተናገድ ላይ ናቸው። በተለይም ዶክተሩ በበአለ ሲመቱ እለት ያቀረበው ንግግር የብዙ ኢትዬጲያውያንን አንጀት ቅቤ ያጠጣ ነበር። በታሪካዊነቱም ተመዝግቧል።

Sunday, March 18, 2018

ዛሬ ልወቅስ ነው፣ ራሴን ጨምሬ…

መሳይ መኮንን
Waldeba monastery priests, political prisoners in Ethiopia.
ዛሬ ልወቅስ ነው። ራሴን ጨምሬ በጽሁፍ ጅራፍ ልጋረፍ ነው። በእውነት ይህን ጽሁፍ ስሞነጫጭር ውስጤ በእልህና ቁጭት ድብን እያለብኝ ነው። በዚህም አሰብኩት። ወደዚህም ወሰድኩት። አገለባብጬ ተረጎምኩት። ዝምታችን ከፍርሃት በቀር ምክንያታዊ አልሆንልህ አለኝ። መቼም የትግራዩ አገዛዝ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ የሞራል ልኬታችን ፈሩን ስቷል። የህሊና ፍርዳችን ተዛብቷል፡፡ ሰው የመሆን ሚዛናችን ጎድሏል።

Tuesday, March 13, 2018

የነዳጅ አቅርቦት ማስተጓጎል ዘመቻ()

Mesay Mekonnen, ESAT journalist
መሳይ መኮንን
ቄሮ ቃሉን አያጥፍም። ባለፉት ሁለት ዓመታት በቄሮ ተጠርቶ ያልተሳካ የአድማም ሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ከነበረ አላስታውስም። ከሁሉ የሚደንቀኝ በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት፡ የኦሮሚያን ክልል ከዳር እስከዳር ባናወጠው ህዝባዊ እምቢተኝነት በቄሮዎች እጅ ህይወቱን ያጣ ሰላማዊ ሰው አለመኖሩ ነው። የሚጠራው አድማ፡ የሚካሄደው ዘመቻ፡ የሚወሰደው እርምጃ የአገዛዙን የማፈናና የመግደል አቅም ከማላሸቅ ያለፈ የትኛውንም የህብረተሰብ ክፍል ለጉዳት የዳረገበት አጋጣሚ አልተፈጠረም። በእውነት የቄሮዎች ትግል እነመሀተማ ጋንዲ የእንግሊዝ የቅኝ ግዛት ዘመን እንዲጨልምና ከነግሳንግሱ ከምድር ገጽ እንዲጠፋ ያደረጉበትን አስደናቂ የእምቢተኝነት ትግል የሚያስታውስ ነው።

በእርግጥ ቄሮዎች ዛሬ ላይ ላቀጣጠሉት እምቢተኝነት እርሾው ቀደም ተብሎ የተዘጋጀ መሆኑን እዚህ ላይ መጥቀስ ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ አገዛዝ ቤተመንግስት ከገባ ጀምሮ ትግል ነበር። በተለያዩ አካላት ሲደረግ የነበረው እልህ አስጨራሽ የነጻነት ተጋድሎ በቅብብሎሽ እዚህ ዘመን ላይ ደርሷል።

Saturday, March 10, 2018

“የክርስቲያን አገር በሆነችው ሙስሊሞች ሊነግሡባት ነው” ህወሓት ለአሜሪካ እንደራሴዎች


  • የአስራ ሰባት ታዋቂ ኦሮሞ ሙስሊሞችን ስም ለማስረጃነት አቅርቧል
  • ከዝርዝሩ ውስጥ የዶ/ር አቢይ አህመድ ስም ይገኝበታል
ህወሓት ከፊቱ የተጋረጠበትን የፖለቲካ ቀውስና ቀውሱን ተከትሎ ከጌቶቹ የተነሳበትን ተቃውሞና ግፊት አቅጣጫ ለማስቀየር ሃይማኖትን የተንተራሰ ስልት ተግባራዊ ማድረጉ ተሰማ። የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ አገሪቱን ለእስልምና አክራሪ አሳልፎ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ህወሓት በወኪሉ በኩል ስም ዘርዝሮ አቅርቧል።

Thursday, March 1, 2018

ህወሓት፡ የHR 128 ፍርሃቻ እና የማግኒትስኪ ሕግ

ከዚህ በፊት በአሜሪካ ምክርቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በረቂቅ ሕግነት ከቀረቡት መካከል ህወሓት/ኢህአዴግ HR 128 እጅግ ፈርቶታል። ይህንን ረቂቅ ሕግ ለማክሸፍም የውትወታ (ሎቢ) ሥራ ከመሥራት ጀምሮ የአሜሪካ ባለሥልጣናትንና የፖለቲካ መሪዎችን በ“አልሻባብ ምስራቅ አፍሪካን ይወራል” ድራማ ለማስፈራራት ተደጋጋሚ በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካለትም። ላለፉት በርካታ ወራትም (በቅርቡ ወደ አሜሪካ የመጡትን እነ ወርቅነህን ጨምሮ) ሊያሳምኑ ይችላሉ የሚላቸውን ሹሞቹን በመላክ ረቂቅ ሕጉ በተግባር እንዳይውል የአሜሪካ ባለሥልጣናትንን – ጊዜ ስጡን፣ ሁሉን እናስተካክላለን፣ … የመሳሰሉ ተማጽንዖዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። በግምባር ቀደምትነትም የህወሓት ወዳጅ የሆኑት ሴናተር ኢንሆፍ ህወሓት/ኢህአዴግን ለመታደግ ኢትዮጵያ ድረስ እስኪሄዱ ያደረሰ የውትወታ ሥራ ተካሄዷል።

Tuesday, February 27, 2018

“ታሪክ ራሱን ቧልት በሆነ መንገድ ሲደግም!”

ኤርሚያስ ለገሰ
Ermias Legesse, author and ESAT TV and Radio contributor
አንድ safegurding Tegaru lives በሚል ስያሜ የሚጠራ  ካድሬ ” ደኢህዴን ከኃይለማርያም ወደ ሽፈራው ሽጉጤ ያደረገው ለውጥ የጥልቅ ተሃድሶ እድገት ነው፣ ወይንስ ከድጡ ወደ ማጡ ነው?” በሚል ያነሳሁት ጥያቄ ላይ አስተያየት ሊሰጥ ወደ ገፄ መጥቶ ነበር።  ከላይ ከተጠቀሰው ኮካ በተጨማሪ በለውጥ ሀይል ዙሪያ ያሉ ወገኖች ” ሲራጅ ፈርጌሳ የደኢህዴን ሊቀመንበር ሆነ ብለህ ነበር!” የሚል ጥያቄ ስላነሳችሁልኝ ሁኔታውን ትንሽ ልበልበት። በትግራይ ነፃ አውጪ ደጃፍ ታሪክ እራሱን ስለሚደጋግሞ መለስ እያሉ ማስታወሱ ሳይበጅ አይቀርም። ከላይ የተጠቀሰው አይነት ሾርት ሜሞሪ ያላቸውን ኮተታም ካድሬዎች አፍ ማዘጋት የሚቻለው በዚህ መልኩ ነው። በሚያገኙት መረጃ ወደ ሰው ይመለሳሉ ብሎ ተስፋ ማድረግ ታማኝ እንዳለው ” እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም!” ቢሆንም እባብነታቸውን እንዳይረሱ ያደርጋቸዋል። እናም እንደሰሞኑ በጅምላ ግድያ በርሜላቸውን እስኪሞሉ አድብተው እንዲቀመጡ ያደርጋቸዋል።

Thursday, February 22, 2018

ወርቅነህ ገበየሁ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን ህወሃት ወስኗል

ክንፉ አሰፋ
Workneh Geeyehu, Ethiopia's Minister of Foreign Affairs.
ወርቅነህ ገበየሁ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን በህወሃት ተሹሟል። ይህ ከታማኝ ምንጭ የደረሰን መረጃ ነው። መረጃው እንደሚጠቁመው፤  እነ ዶ/ር ደብረጽዮን  ሹመቱን ያጸደቁለት፤ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ  ገና በስልጣን ላይ እንዳሉ ነበር። የህወሃት ሰዎች “የኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ሃገሪቱ አሁን የገባችበትን አስከፊ ችግር ይፈታል”  የሚል ቅኝት ይዘው ወደ ምዕራቡ አለም እንዲሰማሩም ተደርጓል። 

Monday, February 19, 2018

የጠቅላይ ተጠቅላይ ጨዋታ

ኤርሚያስ ለገሰ
Image result for ermias legesse
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀጥሎ የኢትዬጲያን የፓለቲካ አየር የሞላው የሚቀጥለው " ጠቅላይ/ ተጠቅላይ" ማን ይሆናል የሚለው ነው። ይህንን ጉዳይ ሰዎች በተለያዩ አቅጣጫዎች ይመለከቱታል። በተለይም በማህበራዊ ድረገጾች ካሉት ፍትጊያዎች አንዱ በዚህ ዙሪያ ያለው እሰጣ ገባ ሆኗል። በአንድ በኩል ስርነቀል የስርአት ለውጥ ለማምጣት እየታገልን ባለንበት ሰአት በዚህ አነስተኛ አጀንዳ ዙሪያ ለምን ጊዜያችንን እናጠፋለን የሚሉ ብዙዎች ናቸው። በሌላ በኩል ከራሳቸው እምነት፣ ጥቅም እና ፍላጐት በመነሳት " እከሌ ጠቅላይ መሆን አለበት!" የሚለውን የሚገፋም አልታጡም።

Sunday, February 18, 2018

የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ህወሀት ክፉኛ ቆስሏል። ከእንግዲህ በመንግስትነት የመቆም እድል የለውም። ኳሷ በኢትዮጵያውያን እግር ስር ገብታለች።

Mesay Mekonnen, ESAT journalist
መሳይ መኮንን
ያለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልልቅ ክስተቶች የተሰተናገዱበት ነው። ተስፋና ስጋት፡ ብርሃንና ጽልመት፡ አንድነትና መነጣጠል፡ ከፊታችን ተደቅነው ጉዟቸንን እንድናሳምር፡ መንገዳችንን እንድንመርጥ፡ አካሄዳችንን እንድናስተካክል፡ እድል እጣፈንታችንን እንድንወስን ከሚያስችለን ዋናው ምዕራፍ የተጠጋን ይመስላል። የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ህወሀት ክፉኛ ቆስሏል። ከእንግዲህ በመንግስትነት የመቆም እድል የለውም። ኳሷ በኢትዮጵያውያን እግር ስር ገብታለች። የጊዜ ጉዳይ ነው። በጣም ጥንቃቄ የሚያስፈግበት ወቅት ላይ ነን። ጥሞና ያስፈልገናል።
አዎን! እስረኞች ተፈተዋል- የሚቀሩ ቢኖሩም። አቶ ሃይለማርያም ስልጣን ለቋል- ስልጣን ባይኖረውም። አስቸኳይ አዋጅ ተደንግጓል- ለውጥ ባያመጣም። ህዝባዊ ትግሉ ተጠናክሯል- በፈረቃ መሆኑ ባይቀርም። ይህ ሁሉ የሆነው በዚህ ሳምንት ውስጥ ነው። በኢትዮጵያ የ27 አመታት የትግራይ ነጻ አውጪ የአገዛዝ ዘመን እንደዚህ ሳምንት ክስተቶች በፍጥነት ተደራርበው የመጡበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። እነኚህ ክስተቶች ወዴት ይመሩናል? በእርግጥ ቁልፍ ጥያቄ ነው።
የእስረኞች መፈታት

የትግላችን መጨረሻ ነፃነታችን ብቻ ነው! (የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል)

የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል
Ethiopians demonstration against the Amhara eviction
የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል ከፈጣሪ በታች የምንመካበት የኢትዮጵያ ህዝብ ክንዱን አስተባብሮ ስለነፃነቱ በጋራ በመቆም ለነፃነቱ ገፋፊዎች ባሳየው ማንነቱ አንገታችንን እንድናቀና ስላደረገን ምስጋናችን ከልብ የመነጨ ነው።

Wednesday, February 14, 2018

“ሁሉንም ባለድርሻዎች ያካተተ የሽግግር መንግስት ሂደት” አቶ ንአምን ዘለቀ

ሁሉንም ባለድርሻዎች ያካተተ – ማለትም የፓለቲካ ሃይሎች፡ የሲቪክ ማህበረሰቡን፡ ታዋቂ ምሁራንን፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሚገኙበት ማንንም ያላገለለ የብሔራዊ ዉይይትና ከዚህም የሚወጣ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ሂደት
  • ሁሉንም ባለድርሻዎች ያካተተ – ማለትም የፓለቲካ ሃይሎች ፡ የሲቪክ ማህበረሰቡን፡ ታዋቂ ምሁራን ፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሚገኙበት ማንንም ያላገለለ የብሔራዊ ዉይይትና ከዚህም የሚወጣ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ሂደት ብቻ ነው ተቀባይነት የሚኖረው፡፡

Tuesday, February 13, 2018

የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባርና የወያኔ ድርድር በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተቃጣ ሴራ!

ከዶ/ር ዲማ ነገዎ፣ ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው እና ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ
Ogaden is the unofficial name of the Somali Region of Ethiopia
ከታማኝ ምንጮች እንደተረዳነው በወያኔና በኦብነግ መካከል ሲካሄድ የቆየው ውይይት በመጠናቀቅ ላይ ነው:: በናይሮቢ ተጀምሮ በዱበይ ከተማ ሲካሔድ ቆይቶ አሁን እንደገና ወደ ናይሮቢ ተመልሶ ፍፃሜ ላይ መድረሱን ምንጮቻችን ገልፀዋል:: ይህ ሤራ ወያኔ ኢትዮጵያን ረግጦ  ገዝቶ ለመኖር ካልቻለ ኢትዮጵያን ሽብር  ውስጥ  ከቶ ትግራይን ለመገንጠልና የትግራይን ሪፑብሊክን ለማቋቋም ያለውን ግልፅ አቋም በተግባር እየተረጎመ መሆኑን ያሳያል::

Sunday, February 11, 2018

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ህወሀት ከኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ጋር በኬኒያ ሸምጋይነት ድርድር ጀምረዋል።

 በመሳይ መኮንን
Ogaden National Liberation Front
የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ህወሀት ከኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ጋር በኬኒያ ሸምጋይነት ድርድር ጀምረዋል። የሶማሌ ክልል ፕሬዛዳንት አብዲ ኢሌና በሶማሊያ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ተወካይ ጄነራል ገብሬ የህወሀትን መንግስት ወክለው በድርድሩ እየተሳተፉ መሆናቸው ተገልጿል። የሚጠበቅ ነው። በዚህን ወቅት፡ የህዝብ ንቅናቄ ሲጠነክር፡ ፖለቲካዊ ትኩሳት ሲጨምር የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ከሚወስዳቸው የተለመዱ እርምጃዎች አንዱ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባርን ደጅ መጥናት ነው። ድርድር።

Thursday, February 8, 2018

ፋሽስታዊው የሕወአት አገዛዝ የቆመበትን ኢኮኖሚያዊ ምሰሶዎች ለማሽመድመድ አለም አቀፍ የሃዋላ ተአቅቦ ዘመቻ አካል እንሁን!!

በነአምን ዘለቀ
Ethiopians Remittance Embargo.
ከፋሽስቱ የወያኔ አገዛዝ ጋር በሚደርገው ሁለገብ ትግል ስልቶች መካከል የኢኮኖሚያዊ ጦርነት (Economic Warfare) አንዱ ነው። ስርአቱ የቆመበትን ምሰሶ የማዳከም የኢኮኖሚያዊ ጦርነት ስልቶች እንዱ የሃዋላ ተአቅቦ ነው። የሃዋላ ተአቅቦ ለአጠቃላይ ትግሉ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግና ስርአቱን ለማዳከም ያለው ሚና ከፍተኛ ነው።

ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!

የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል።

Monday, February 5, 2018

የንግድ ስርአቱና “የቲም ለማ” ግኝት!

ኤርሚያስ ለገሰ
#1: መግቢያ
በአቶ ለማ መገርሳ ሊቀመንበርነት የሚመራው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአዳማ የ10 ቀን ዝግ ስብሰባ ለማድረግ ተቀምጧል። በዚህ ስብሰባ ላይ የተለያዩ ድርጅታዊ፣ ክልላዊ፣ አገራዊ እና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በመመርመር ታላላቅ ውሳኔዎችንና የቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ በግምገማው ቃል አቀባይ ተነግሯል። የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ እና የግምገማው ቃል አቀባይ አቶ ሐብታሙ ሐ/ ሚካኤል ለየኦሮሞ ብዙሃን መገናኛ ( OBN) በሰጠው መረጃ መሰረት ግምገማው በአሁን ሰአት ወደ አቢይ አጀንዳዎች ተሸጋግሯል።
Lemma Megersa, with his team, was in Bahir Dar.
Lemma Megersa
ከእነዚህ አቢይ አጀንዳዎች መካከል በአገሪቱ የንግድ ስርአት ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑ ቃል አቀባዩ ተናግሯል። የንግድ እንቅስቃሴው ስልጣንን ተገን በማድረግ በተወሰኑ አካላት ተይዞ የኦሮሚያን ኢኮኖሚ እያቀጨጨው መሆኑ በጥልቀት መታየቱን ገልጿል። ስልጣንን መሰረት በማድረግ በተወሰኑ አካላት የሚለውን በቀይ ብዕር አስምሩልኝና ወደ ቃል አቀባዩ መግለጫ እንመለስ። አቶ ሐብታሙ ለOBN በሰጠው መግለጫ ላይ፣
” የአገሪቱ የንግድ ስርአት ከአድሎነት የፀዳ ነወይ? የንግድ ስርአቱ በፍትሐዊነት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል እኩል ተጠቃሚ እያደረገ ነወይ? ወይንስ የተወሰኑ አካላት ብቻ ከድንብር ድንበር እየተዘዋወሩ እንደፈለጉት ተጠቃሚ የሚሆኑበት ነው? በሚለው ጉዳይ ላይ በጥልቀት ተወያይተናል። በአገሪቱ የንግድ ስርአቱ ውስጥ ትልልቅ ችግሮች አሉ። ስልጣንን ተገን በማድረግ በተወሰኑ አካላት ተይዞ ያለ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ አራማጆች ላይ ታግለን መስመር እንዲይዙ በማድረግ ረገድ ምን እንደምንመስል ፈትሸናል” ብሏል።

Friday, February 2, 2018

“የህውሓት የአዲስ አበባ ልዩ ዞን!” እና የ HD አዲሱ ዲስኩር

በኤርሚያስ ለገሰ
መንደርደሪያ አንድ:- 1998 
Ermias Legesse, author and ESAT TV and Radio contributor
የመለስ ትሩፋት ባለቤት አልባ ከተማ መፅሐፍ ” የአዲስአባ ፓለቲካ ምህዳር” በሚል ርእስ ስር በገፅ 252 ላይ የሚከተለውን ትለናለች፣

Sunday, January 28, 2018

ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ጆሮና አይኔ ወሎ ላይ ተተክሎ ሰንብቷል

መሳይ መኮንን
ከወልዲያው ጭፍጨፋ፡ ከቆቦዎች አይበገሬነት እስከመርሳዎች ጀግንነት፡ ክስተቶችን እዚያው አጠገባቸው እንዳለ ሆኜ ነበር ስከታተል የቆየሁት። ስሜቴ ከወዲህ ውዲያ ሲላጋ፡ ቅጭም ሲል፡ በሀዘን ሲመታ፡ ደግሞም በጀግንነታቸው ልቤ ሲሞቅ፡ ወዲያኑም በሚደርስባቸው የግፍ በትር ውስጤ ሲደማ፡ በሞታቸው ኩምትር ስልበወርቃማ መስዋዕትነታቸው ስጽናና፡ እንዲሁ ላይ ታች ስል ሰነበትኩ። አሁንም ከዚያው ነኝ። ከወልዲያ ምድር፡ ከቆቦዎች መንደር፡ ከሮቢት ሰፈር፡ ከሀራ ገበያ፡ ከጎቢዬዎች ሀገር፡ ከመርሳዎች መንደር፡፡ የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም የሚለው አባባል አይገባኝም። ወሎን ባላውቀውም ይናፍቀኛል።
Mesay Mekonnen, ESAT journalist
መሳይ መኮንን (የኢሳት ጋዜጠኛ)
ፖለቲካው ግሏል። ሙቀቱ ጨምሯል። ህወሀቶች መቀሌ ላይ የቀመሙትን መርዝ በእጅ አዙር ሊረጩት ተሰማርተዋል። የዘርዓይ አስገዶም ያልተጠና ዲስኩር የህወሀቶችን ቀጣይ አካሄድ እርቃኑን ያጋለጠው ሆኗል። አንጻራዊ የህዝብ ድምጽ በማሰማት ቀና ማለት የጀመሩትን የኦሮሞ ብሮድካስት ኔትወርክና የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅትን ወደ ቀድሞ አገልጋይነታቸውና በቀቀንነታቸው ለመመለስ በህወሀት አማካኝነት የተዘጋጀውና እነዘርዓይ የተላኩበት ዘመቻ ድባቅ ሲመታ ለመታዘብ ችለናል። አፋቸው ተሎጉሞ የከረሙት ወይም ከህወሀት አገልጋይነት መላቀቅ አቅቷቸው ህዝባቸውን ሲያሳዝኑ የምናውቃቸው እነንጉሱ ጥላሁን እንኳን አፍ አውጥተው፡ ወኔ አግኝተው፡ ድፍረት ተላብሰው ”በዘረኝነት ትዕቢት የተወጠረውን” ዘርዓይን እሳት እንዳየ ላስቲክ ኩምሽሽ ሲያደርጉት አይተናል።