Translate

Wednesday, February 14, 2018

“ሁሉንም ባለድርሻዎች ያካተተ የሽግግር መንግስት ሂደት” አቶ ንአምን ዘለቀ

ሁሉንም ባለድርሻዎች ያካተተ – ማለትም የፓለቲካ ሃይሎች፡ የሲቪክ ማህበረሰቡን፡ ታዋቂ ምሁራንን፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሚገኙበት ማንንም ያላገለለ የብሔራዊ ዉይይትና ከዚህም የሚወጣ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ሂደት
  • ሁሉንም ባለድርሻዎች ያካተተ – ማለትም የፓለቲካ ሃይሎች ፡ የሲቪክ ማህበረሰቡን፡ ታዋቂ ምሁራን ፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሚገኙበት ማንንም ያላገለለ የብሔራዊ ዉይይትና ከዚህም የሚወጣ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ሂደት ብቻ ነው ተቀባይነት የሚኖረው፡፡ ሰፊው የኢትዮጵያው ህዝብ ይህ ነው የማይባል የህይወት መስዋእትነት በመክፈል ከፋሽታዊው የህወአት ስርአት ጋር እየታገለ፣ እየተጋተረ የሚገኘው ወደ ሀቀኛ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የሚያደርስ ፡ ሙሉ መብቶችና ነጻነቶችን የሚጎናጸፍበትን ስርአታዊ ለውጥ ለማምጣት እንጂ የወያኔን የበላይነት የሚያስቀጥል ወይንም ስርአቱን ጠጋግኖ ለማቆየት ለሚደረግ የተለያዩ መከራዎች እንዲጠለፍ አይደለም።
  • የሕወአትን የበላይነት የነገሰበትን ስርአት ጠጋግኖ ለማስቀጠል የሚደረጉ ጥረቶች አገዛዙ የገባበትን ጥልቅ የፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ሊፈቱ የሚችሉ አለመሆናቸው ብቻ ሳይሆን የስርአት ለውጥ እየጠየቀና ከፍርሃት ወጥቶ ሞትን በማሸነፍ ከወያኔ ፋሽስታዊ ነፍሰ ገዳዮች ጋር በመጋፈጥ ላይ የሚገኘው የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የአፋር፣ የደቡብና ሌሎችም ማህበረሰቦች በጥቅሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚቀበሉት ዘላቂና እሰተማማኝ መፍትሄ አይሆንም፣ – ኦሄድድ በቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወስዳቸው እርምጃዎች የሚበረታቱና የህዝቡን ጥያቄዎች ውስን በሆነም መልኩ እየመለሱና የሕወአትን የበላይነት እየተፈታተኑ በመሆናቸው ለሚፈልገው ለውጥ ጥሩ ጅምር ነው ብለን እናምናለን።
  • የአግ 7 በብዙ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚደረጉ የህዝብ ትግሎች ውስጥ አለ፣ ክፍለጦሮች ፣ ብርጌዶች፡ መድፍና ታንኮች ይዞ ግን አይደለም፣ እግ7 የህዝቡን ትግል የሚያግዙ በርካታ ልዩ ልዩ የትግል ስልቶችን በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፣ ትግሉ ግን በቀዳሚነት የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ነው። – ከደሚት ጋር በ አግ7 ያወጣው የጋራ መግለጫ በጣም አስፈላጊም ፣ ወቅታዊም ነው፣ የትግራይ ህዝብ፣ የትግራይ ምሁራን፡ ልዩ ልዩ ሃይሎች ከዘራፊው ፋሽስታዊ የህወአት ጨካኝ ቡድን መነጠል ብሎም የትግሉ አካል እንዲሆኑ ተደጋጋሚ ጥሪ ማድረግ የውያኔን አጥፍቶ መጥፋት አገር እፍራሽ እካሄድ ለማምከን ለሀገሪቱ ሰላም፣ እንድነትና፣ የወደፊት እጣ ፈንታ ወቅታዊና በጣም እስፈላጊ ነው።

No comments:

Post a Comment