Translate

Sunday, November 26, 2017

“ዘጭ እንቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ” በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

No automatic alt text available.
ታደለ መኲሪያ
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ፣ ክኢሳቱ ጋዜጠኛ ማንአላቸው ስማቸው ጋር ስለ መጽሐፉ “ዘጭ እንቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ” ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ተከታትያለሁ፥ ይህን መነሻ በማድረግ አቶ አቻምየለህ ታምሩም “ንግግሩ ታሪክ መዝግቦ ከያዘው እውነት ጋር ይቃረናል“ በሚል ሐሣብ ይዘው ቀርበዋል፥ እኔም መላ መጽሐፉን አላነበብኩትም፥ ሆኖም የፕሮፌስሩን ያለፉ ሥራዎችን በከፊል አንብቤለሁ ፤ ለ52 ዓመታት በኢትዮጵያ ጉዳይ አንኳር አንኳር የሆኑ ሐሣቦችን ሲያቀርቡ ከማስታውሰው ሁለት ለኣብነት ልጥቀስ፣ በእኛ አቆጣጠር፣ 1964 ዓ.ም ነበር፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የወረዳና የአውራጃ ኣስተዳዳሪዎቹን እንዲመርጥ ያቀረቡት ሐሣብ እስከዛሬም እውን አልሆነም፥ በ 1970 ዓ ምህረትም፣ ስድስት ኪሎ ግቢ ነበር፤ አንድ ካድሬ እየተደረደረ መጥቶ ”ፕሮፌስር ብሎ ተጣርቶ ንቃት አለ፣ ውይይት ኣለ፥” ሲላቸው፣“ ለራስህ ንቃ “ብለውት ሄዱ፥ በወቁቱ አካባቢው በፍረሃት ድባብ ተውጧል፣ ፥ በላይ የሚባል የዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ከአራት ኪሎ አስተምሮ ሲወጣ ቀበሌዎች ተከታትለው ከሰድስት ኪሎ መግቢያ ደጃፍ ላይ በኢህአፓ ስም ነፃ እርምጃ ወስደውበታል፣ ግቢው ተሸብሯል፣ ካድሬው ከነበሩት ሰዎች ሁሉ መርጦ ወደ ፕሮፌስር መሰፍን ወልደማሪያም መሮጡ አድኑኝ ይመስላል። ግርግሩ ለፕሮፌሰሩ ቁብ አልሰጣቸውም፥ እነዚህ ሁለት ክስተቶች በተለያዩ ሥራዓቶች ሰለነበሩ ስለ ፕሮፌሰሩ የሚሉት ቁምነገሮች አላቸው ። ወደ ተነሣሁበት ሐሣብ ልመልሳችሁ፥

“ዘጭ እንቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ” በኢሳት ለቀረበላቸው ቃል መጠየቅ አቶ አቻምየለህ ታምሩ ፥ ፕሮፌስር መስፍን ወልደማሪያም ታሪክ አዛብተዋል በሚል የፍየል ወጠጤ መሰል ቅላጼ በኦዲዎ ተለቆ አድምጯለሁ፥ አቶ አቻምየለህ ታምሩ፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያምን ታሪክ አዛብተዋል፣ የሚሉት ሐምሌ 30 ቀን 1966 ዓ ም የወጣውን የ ሕገ መንግሥት ረቂቅ መሠረት አድርገው ነው፥ አቶ ተክለጻዲቅ መኲሪያ ስለ ሕገ ረቂቁ በማስታውሻቸው ያሰፈሩትንና ዶክተር ተፈራ ደገፌ ‘MINUTES OF AN ETHIOPIAN CENTURY 333_338’ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር፣ 1989 ዓ ም የፃፉትን እንደማስረጃ አቅርበዋል፥
“ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፣ በኢሳቱ ቃል ምልልሳቸው በጠቅላይ ሚንስትር እንዳልካቸው መኮንን ንግግር March 30, 1974 እ ኤ ኣ በ30 ታዋቂ ወነዶች ብቻ፣ ተከፍቶ ሥራውን የጀመረው፣ የሕገ መንግሥት አርቃቂ ጉባዔ ያዘጋጀው አዲሱ ረቂቅ ሕገ መንግሥት፣ ለሕዝብ የበለጠ ሥልጣን ስለሚሰጥ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስላልወደዱት ወደቀ፥” ወረድ ብለው፣ በንግግራቸው “ረቂቅ ሕገ መንግሥቱ ውድቅ እንዲሆን የተደረገው (ኋላ ላይ)የመጡት መንግሥቱ ኃይለማርያም ስላልወደደውም ነውም ብለዋል፣ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪም አስተያየት፣ “ረቂቅ ሕገ መንግሥቱ ያልጸደቀው መንግሥቱ ኃይለማርያም ስላልፈለገው ነው።” የሚል ብቻ ቢሆን ኖሮ የሰጡት አስተያየት፣ ጉዳይ ዙሪያ በታሪክ ተመዝግቦ ከሚገኘው እውነት ጋር የሰጡት አስተያየት አንድ ዓይነት ስለሆነ ባነሱት ጭብጥ ዙሪያ ጥያቄም ሆነ አስተያየት ሊነሳባቸው አይችልም ነበር።
አቶ አቻምለህ ታምሩ ልዑል ራስ እምሩ፣ ደጃዝማች ከበደ፣ ተከለፃዲቅ መኲሪያ፣ አቶ በላቸው አሥራትን ጃኖሆይ ኢዮቤልዎ ቤተ መንግሥት አስጠርተው፣“ በቶሎ የሚታረመውን አርማችሁ ለፓርማ ቀርቦ ይታውጅ።” እዚህ ላይ ልንረዳ የምንችለው ጉባዔው ያረቀቀው፣ ረቂቅ ሕገ መንግሥት ላይ የንጉሡ ጣልቃ ግብነት አልነበረበትም ማለት ይቻላል? እስቲ አቶ አቻምለህ ታምሩ እንደዋቤ ከጠቆሙን የዶክተር ተፈራ ደገፌ መጽሐፍ ውስጥ የተገለጸውን እንዳለ ላቅርብ፣1. ” While the monarch still sat at the palace, we had succeeded in stripping him of all his executive, legislative and judicial powers.” 2. ” The draft constitution stated that the emperor was to be a symbol of unity as a constitutional monarch.”
”ንጉሡ በዙፋናቸው ላይ እያሉ ሕግ አስፈፃሚው፣ ሕግ አውጭውንና የ ሕግ ተርጓሚ ሥልጣናቸውን ገፈፍናቸው።“ በሁለተኛው ላይ የተቀመጠው ንጉሠ ነገሥቱ የአንድነት መልክት መሆኑ ንግሡም በሕግ የተገደበ መሆኑን ነው። አቶ አቻምለህ ታምሩ የሚነግሩን ይህ ረቂቅ ሕገ መንግሥት እንዲያልፍ ንጉሡ ፈቅደው ነበር ነው የሚሉን? ሁለት ነገር እዚህ ላይ ላቅርብ፣ በ1953 ዓ ምህረትም ሆነ 1966 ዓ ም የመፈቀለ መንግሥት ሙከራ ሲደረግ ከዘውዱ ጋር ምንም ችግር አልነበረም። ደርጉ ለንጉሠ ለንጉሥቴ ታማኝ ነኝ ይል የነበረው ሰንበት ብሎ ለዘውዱ ታማኝ ነኝ በሚል ለወጠው፥ የንጉሡን የልጅ ልጅ አማሃ አሰፋው ወሰን ዘውዱን ይረከብ ጥሪ አቀረበ፥ ጊዜ ለመግዛት ሆነ ሕዝብ ለማወናበድ መሆኑን የሚታወቅ ነገር የለም፥ ሕገ ረቂቅ አውጪ ጉባዔ ስብስብ ውስጥ ለደርጎች መረጃ አቅራቢ ሻለቃ እንደነበር አቶ አቻምለህ ታምሩ በጠቀሱት በ ዶክተር ተፈራ ደገፌ በመጽሐፍ 333᎐338 ገጽ ይገኛል። እንግድህ በኮሚሽኑ አባላት መካከል የትኛው ወግ አጥባቂ፣ የትኛው ተራማጅ እንደሆነ ለደርጎች ይደርሳቸዋል፥ በጊዜው የንጉሡ ያለመለወጥ ለደርጎች ግልጽ ነበር። የእንዳልካቸው ሹመት “የጉልቻ መለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም” በሰፊ በሕብረተሰቡ ውስጥ ተስትጋባ፣ እንደሌሎች በንጉሥና በንግሥት እንደሚመሩት ሀገራት ሕገ ረቂቅ እንዲዘጋጅ ቢያው ጁ ኖሮ ቢያስ ንጉሡ ፍቃደኝነት ቢያሳዩ ወታደሩ ከሕዝብ በላይ አይደለምና በመጣበት መንገደ ይመለስ ነበር።
ታዲያስ ፕሮፌስር መስፍን ወልደማርያም ንግግር በአንድ ወቅት በተከሰተው ክስተት ላይ ተምርክዘው አይደለም፥ በየጊዜው ንጉሡ ሥልጣናቸው ለሕዝብ እንዲያካፍሉ ተጠይው አሻፈረኝ ማለታቸው ግልጽ ነው። “ አዲሱ ረቂቅ ሕገ መንግሥት ለሕዝብ የበለጠ ሥልጣን ስለሚሰጥ ቀደማዊ ኃይለ ሥላሴ ስላልወደዱት ወደቀ” አቶ አቻምለህ ታምሩ ሳንሱር ያልነካውን ሰላሳዎቹ የነደፉትን በዝር ሳያሳዩን አቶ ተከለፃዲቅ መኲሪያ ጃኖሆይ ዘንድ አራት ራሳቸው ሆነው ካሳለፉት ሕገ ረቂቅ ውስጥ አንድ ሰበዝ መዘው ሙሉዋ ባልሆነ ነገር ላይ መተቸት ይበልጥ ያሳስታል። አቅሙም እውቀቱም ኖሮ የ ፕሮፌስር መስፍን ወልደማርያምን ሥራዎችን አበጥረን፣ ፈትገን ፣ ሸክሸከን ቆልጭ ባለመንገድ ለትውልድ ብናቀርበው የእውቀት ድፍድፍ አለው። ፕሮፌሰሩ አይተቹ የሚል ቅጣት ያህል እምነት የአለኝም ” ዘጭ እንቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ“ መጽሐፍ እጃች ሲገባ እንገናኝ፣ ሰላም ሁኑ፣ ነበድገሊዎ!
ታደለ መኲሪያ
taddelemarye@gmail.com

No comments:

Post a Comment