አንደኛ: የመለስ ራዕይ ወደ ሥላሴ መቃብር ይወርዳል። HD ከዚህ በኋላ ” ታላቁ መሪያችን” ብሎ እንዳይናገር ከአርከበ ትእዛዝ ይደርሰዋል።
ሁለተኛ: አዜብ መስፍን የስዬ አብርሃ እጣ ፈንታ ሊደርሳት ይችላል። እርግጥ ዘብጥያ ማውረዱ ዞሮ ዞሮ የኤፈርት ዝርፊያ እና ሌብነት ላይ ስለሚሽከረከር ለስብሃት በጣም ከባድ ይሆንበታል። አርከበም ቢሆን በሌብነት ከሴትየዋ የሚስተካከል በመሆኑ እስሩን ላይደግፈው ይችላል።
ሶስት: የሕውሓት ካድሬዎች ለሁለት ሊሰነጠቁ ይችላሉ። በተለይ ከሌብነቱ በላይ “የባድመ ጉዳይ” በልዩነት ጐልቶ መውጣት ከቻለ አባይ ወልዱ፣አዜብ እና ሳሞራ የኑስ በካድሬው ዘንድ ተቀባይነት ሊኖራቸው ይችላል ። ለስብሓት ነጋ የባድመ ጉዳይ ከባድ ፈተና ይሆንበታል።
አራት: በረከት ስምኦን ዳግም የመልቀቂያ መልቀቂያ ያስገባል። አርከበ እና ደብረፂዮን በትግርኛ ይስቁበታል። ስብሃት ነጋ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ( ከአምላኩ አጠገብ) መቃብር ይምስለታል። በረኸት እንደተለመደው አፍንጫውን እየጐተተ ” ቀድሞ ወደ መቃብር ማን እንደሚሄድ እንተያያለን!!” በማለት ይዝታል ።
አምስት: አርከበ እቁባይ ወይም ወንድሙ አሊያም በስብሃት ነጋ እና በአርከበ ኔትወርክ ውስጥ ያሉ የሕውሐት ባለሥልጣናት ኤፈርትን ይቆጣጠሩታል። ደብረፂዮን በፌዴራል ደረጃ ቁልፍ ሥልጣኑን መልቀቁ ለህውሓት አደጋ ስለሚሆን የድርጅቱን ም/ሊቀመንበርነት መያዙ በቂው ሊሆን ይችላል።
ስድስት: የአዜብ መስፍን፣ አባይ ወልዱ፣ የበረከት እና ሳሞራ የኑስን ቆሽጤ ለማሳረር ተጋዳሊት ፈትለወርቅ “ሞንጆሪኖ” ( የአባይ ፀሐዬ የቀድሞ ሚስት) በፊት መስመር የመምጣት እድል ይኖራታል። ሳሞራ በአስቸኳይ በጡረታ ሊገለል ይችላል። በርካታ ጄኔራሎችም ሊባረሩ ይችላሉ።
No comments:
Post a Comment