Translate

Thursday, April 28, 2016

በጋምቤላው ጭፈጨፋ የደ/ሱዳን ሹመኞች እጅ መኖሩን አንድ የአገሪቱ የጦር ጄ/ል አጋለጡ

“ ባለሰልጣኑ በጋምቤላው ጭፍጨፋ ዙሪያ አካፋን አካፋ ብለው መጥራት ይገባቸዋል” ሌ/ጄኔራል ዲቪድ ያ ኡ ያ ኡ
ኢትዮጵያ ዛሬም ለባእዳኖቹ ምቹ አልጋ ፣ለልጆቿ ግን ቀጋ የመሆኑዋ ጉዳይ እያነጋገረ ነው
ከሳምንት በፊት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልላዊ መስተዳደር በሚገኙ የኑኢር ማህበረሰብ ላይ ከጎረቤት ደ/ሱዳን አንደመጡ የሚነገረላቸው እጅግ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና የደ/ሱዳን የመከላከያ ሰራዊቱን የድምብ ልብስ ያጠለቁ መሆናቸው የተነገረላቸው የሞራሌ ጎሳ ተወላጆች በ 10 የኑዊር መንደሮች ላይ በከፈቱት የጅምላ የተኩስ እሩምታ ከ 200 በላይ ሰዎች ህይወትን በመቅጠፍ ከ100 በላይ ጨቅላ ህጻናትን ደግሞ አፍነው በመወሰድ ፣ከ 2ሺህ በላይ የቀንድ ከበቶቻቸውን በመዝረፋቸው ሳቢያ በበርካታ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊናኦች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ሃዘን እና ቁጭት መቀሰቀሱ አይዘነጋም።

ታዲያ ከዚሁ ሰሞነኛው የጋምቤላው ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አሰተያየቶች እየተሰነዘሩ ሲሆን የተወሰኑ ወገኖች በጭፍጨፋው ላይ የደ/ሱዳን የመከላከያ ጦር እጁ እንደነበረበት የሚናገሩ ሲሆን በተቃራኒው ጎራ “ በጭፍጨፋው ላይ የተሳተፈው የደ/ሱዳን ስራዊት ሳይሆን ለስረቱ ቀረብ ያሉ የ አካባቢው ፖለቲከኞች ናቸው “የሚሉ ወገኖች ከደ/ሱዳን ባለሰልጣናት ዘንድ ብቅ ብቅ ማለታቸው ታውቋል። ይህንን (የሁለተኛውን )ሃሳብ ከሚያቀነቅኑት መካከል የደ/ሱዳን ዲሞክራቲክ ሙቭመንት (SSDM/SSDA) ዋና ሊቀመንበር የነበሩት ሌትናል ጄነራል ዲቪድ ያኡ ያኡ የሰሞኑን የጋምቤላውን ጭፍጨፋን በጸኑ ያወገዙ ሲሆን ጥቃቱን አድራሺዎቹ ሊኪዋንጋሎ ከተባለ አካባቢ ከሚገኙ ኒያርጀኒ፣ዎጎን፣ማንያታካ፣ቶልቶል እና ማንታይድ ከተባሉ መንደሮች በሚገባ የተደራጁ እንደሆኑ እና ይህ ክልል ደግሞ በአሁኑ ወቅት የቦማ ግዛት ሃገር ገዢ (ገቨርነር )የሆኑት ባባ ኒዳን የትውልድ ስፍራ ሲሆን አኚሁ ሃገረ ገዢው ከዚህ ቀደም ከነዋሪው ሕዝብ ጋር ስላላቸው ቁርኘት በተመለከት ሌ/ ጄ/ል ዲቪድ ሲገልጹ” ሃገረ ገዢው ቀደም ሲል ፒቦር የተባለች ከተማን ለመውረር ሕዝቡን የዘመናዊ የጦር መሳሪያ ባለቤት በማድረግ እና ጥይቶችን በገፍ በማቀበል ጥቃት ለመፈጸማቸው በግላጭ የሚታወቅ ሲሆን ይሄው የጦር መሳሪያ እ ወታራዊ ቁስ ሰሞኑን ጋምቤላ ወስጥ በኑኢር ልጆች ላይ ለተፈጸመው አሳቃቂ እና ተግባር ላይ ውሏል” ሲሉ የ ደ/ሱዳን ባለሰልጣኑ (የሞራሌ ተወላጆችን ያሰታጠቁ የአካባቢውን ሹምን) ቁጥር አንድ ተያቂ ናቸው ሲሉ ወንጅለዋቸዋል።
የቦማ ግዛት ሃገረ ገዢው ከዚህ ቀደም በእልቂቱ ላይ የ ደ/ሱዳን ጦር እጆች ሰለመኖራቸው በተመለከት የሰጡትን ትችት በተመለከት ጄ/ል ዲቪድ ሲናገሩ “ እኛ አማጺያኖች ከወቅቱ ከጁባ መንግስት ጋር ስራዊታችን ኣንዲጣመር እና እርቀ ሰላም እንድናደረግ መንገድ በጠረገችልን አገር ( በ ኢትዮጵያ እና በሕዝቧ) ላይ የጦር መሳሪያ በጭራሽ አናነሳም ። ይልቁንም ለዚሁ የሰበ ጡራን ፍጅት እና ሰቆቃ ተጠያዊ የሆኑት የቦማ ግዛት ገዢው ባባ ኒዳን ለተፈጸመው ወንጀል ሃላፊነቱን እንዲወስዱ፣ አካፋንም አካፋ በሎ መጥራት (ወንጀለኞቹን የማጋለጥ እና ለፍርድ የማቅረቡ እርማጃን )መማር አለባቸው፣ ባለሰልጣኑ ተራ እና መሰረተ ቢስ ውንጀላቸውን ትተውም በግፍ ታፍነው የተወሰዱት 108 በላይ ኢትዮጵያዊያን ህጻናት እና የተዘረፉት የቀንድ ከብቶች ለህጋዊ ባለቤቶቻቸው (ለጋምቤላ ማህበረሰብ )ይመለሱ ዘንድ ከአካባቢው የጎበዝ አልቆች ጋር በግላጭ መነጋገር አለባቸው ።” በማለት ጄ/ል ዲቪድ ለሃገር ገዢው፣ ለ ባባ ፣የተማጸኖ መልእክት ለከዋል ። የቀደሞው ስራዊታቸንም “እጁ ከደሙ ንጹህ ነው” ሲል ትከላክለዋል።
ላለፉት ሁለት አመታት በአርሰ በርስ ጦርነት የታመሱት ት ፣ለበርካታ ሰላማዊ ዜጎች መሞት እና መሰደድ ምክንያት የሆኑት የደ/ሱዳን ዋንኛ ፖለቲከኞች ፕ/ቱ ሳልቫ ኪርር እና እስከ ትላንትናው እለት ድረስ ጋምቤላ እና አ/አ ውስጥ ሲዝናኑ ቆይተው በአለማቀፉ ማህበረሰብ ጫና እና ግፊት ወዳፈራረሷት የደ/ሱዳን መዲና የሆነቸው ጁባ ለመሄድ የተገደዱት ዶ/ር ሪክ መክችር የምክትል ቦታውን ዳግም እንዲይዙ የተደረገ ሲሆን ሁለቱ ፖለቲከኞች (ሳልቫ ኪርር እና መክቻር ) በአሁኑ ወቅት ሰለ ወንበራቸው እና ሰለ ራሳቸው መጻኢ ተስፋ ማሰብ እና ማሰላሰል አንጂ በእነርሱ ጦስ ሳቢያ ለተሰደዱ ከ200 ሺህ በላይ ዜጎቻቸውን ላሰጠለለች ከዚያም አልፎ ባለፈው ሳምንት በጋምቤላው የጃዊ የሰደተኞች ጣቢያ በተፈጠርው ድንገተኛ የመኪና ግጭት ሳቢያ የሁለት የደ/ሱዳን ሰደተኞች ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ ከ 10 በላይ ሰላማዊ ኢትዮጵያዊያኖች በአካባቢው አጠራር (ደገኞች/የመሃል አገር ትወላጆች ) ላይ የደረሰው የብቀላ እና ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ ሳቢያ የህይውት መጥፋትን በተመለከተ (አንዲያውም በወቅት ዶ/ር ማክችር ድርጊቱ ሲፈጸም በከተማ ውስጥ ነበሩ ይባላል) ፣ ከዚያ በመለጠቅ የሞራሌ ጎሳዎች ባለፈው ሳምንት በእነርሱ ሹማምንቶች የተጥቅ ደጋፍ ታግዘው በ208 ላይ ሰላማዊ የጋምቤላ ነዋሪዎች ላይ ስለ ተፈጸመው ጭፍጨፋ እስከ አሁን ድረስ ጠጠር ያለ የማውገዝ እና ፈጣን እርምጃ የመወሰድ እንቀሰቃሴ ያለማድረጋቸው ጉዳይ “ኢትዮጵያ ድሮም ሆነ ዛሬ ለ ባእዳኖች የሞቀ አልጋ ፣ለልጆቿ ግን የቀጋ እሾህ ነች”የሚለው ብሄል በበዙዎች አይምሮ ውስጥ ሰሞኑን ዳግም እንዲመላለስ አድርጎታል።
ይህ ማለት ደግሞ ዛሬ በአንዳንድ አገሮች እንደምናየው እና ወግኖቻቸን እንደሚያበሻቅጧቸው “ሰደተኞች አገራችንን ለቀው ይወጡልን ዘመቻ አይነት እናካሄድ “ማለት ሳይሆን በኢትዮጵያ መሬት የሚገኙ የትኛውም አገር ሰደተኞች የአገሪቱን እና የህዝቧን ክብር እና ባህል በማይነካ መንገድ እንዲሰተናገዱ ፣ አደብ የሚያሰገዛ እና ለሰደተኞች ሲባል የዜጎቹንም ህይውት በግፍ እና በከንቱ የማይቀጭ ፣ ክብራችውን እና መብታቸውን የማይደፈጥጥ መንግስት፣የህግ አስከባሪ ሃይል ይኑር ። እንዲሁም ህዝባዊ ስር አትም ይዘርጋ ማለት ነው።
Tamiru Geda's photo.

No comments:

Post a Comment