ኢሳትን እንደገና ወደ አየር ለመመለስ የተደረገው ጥረት ከዛሬ ዕሁድ መጋቢት 25/2008 ( እ/ኤ/አ April 3/2016) ጀምሮ ፍጻሜ በማግኘቱ የሙከራ ስርጭቱ ቀጥሏል ኢሳትን ለማፈን የሚንቀሳቀሰው ሃይል አሁንም በአፈና ሙከራው እንደሚገፋ ቢጠበቅም፥ እነርሱ ለማፈን ካላቸው እልህ በላይ እኛም ለነጻነት ቆርጠን የምንሰራ በመሆናችን ፈተናው ቢቀጥልም በማናቸውም ሁኔታ ኢሳት ወደኋላ እንደማይመለስ ማረጋገጥ እንሻለን።ይህንን ሁሉ ፈተና እየተጋፈጥን እንድንቀጥል ጉልበት የሆነን በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እና በሃገር ቤት ያለው ወገናችን የነጻነት እና የፍትህ ርሃብ በመሆኑ አሁንም ድጋፋችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እያቀረብን አዲሱ ሳተላይት የሚከተለው መሆኑን እንገልጻለን።
Satellite: Tel Star T12
Transponder TXP K33
15 Degrees West
Downlink Frequency: 12550
Symbol Rate: 4.411
QPSK,DVB-S 3/4
Transponder TXP K33
15 Degrees West
Downlink Frequency: 12550
Symbol Rate: 4.411
QPSK,DVB-S 3/4
ይህ አዲስ ሳተላይት በናይል ሳት አቅጣጫ በመሆኑ የአረብ ሳት ተጠቃሚዎች የሳተላይት መቀበያ ሳህኑን (ዲሹን) ማንቀሳቀስ አይጠበቅባችሁም።ሆኖም በጥራት ማየት ካልቻላችሁ ሳህኑ ላይ ተጨማሪ LNB መግጠም ይኖርባችኋል።
የኢሳት አስተዳደር
No comments:
Post a Comment