በመላው ኦሮሚያ እንዲሁም በአማራው ክልል በተለይም በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ውስጥ ውጥረት ውስጥ የገባው ኢሕ አዴግ መንግስት ጦሩን ወደ ኤርትራ ድንበር ካስጠጋና እንደዚሁም ደግሞ በኦሮሚያ በ8 ዞኖች ከፋፍሎ ወታደራዊ አስተዳደር ካወጀ በኋላ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሕዝብ አመጽ ይነሳል በሚል ምክንያት የተለያዩ ዝግጅቶችን በመሰረዝ ላይ ይገኛል::
Translate
Saturday, February 27, 2016
የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን መከላከያ ሰራዊት በሰሜኑ በኩል የሚያደርገዉ ዉጊያ እና ሰራዊቱ።
ሰበር ዜና ! !
የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን መከላከያ ሰራዊት በሰሜኑ በኩል የሚያደርገዉ ዉጊያ እና ሰራዊቱ።
መላዉ ኢትዮጵያዊያንን በሐይልና በጉልበት ሲገዛ የነበረዉ ህዝባዊ ጠላት ወያኔ አሉኝ የሚላቸዉን የመከላከያ ሰራዊት አባልት በኤርትራ ላይ ለማዝመት ሁለት ዋነኛ አላማዎ ችን ለሰራዊቱ አስቀምጧል
የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን መከላከያ ሰራዊት በሰሜኑ በኩል የሚያደርገዉ ዉጊያ እና ሰራዊቱ።
መላዉ ኢትዮጵያዊያንን በሐይልና በጉልበት ሲገዛ የነበረዉ ህዝባዊ ጠላት ወያኔ አሉኝ የሚላቸዉን የመከላከያ ሰራዊት አባልት በኤርትራ ላይ ለማዝመት ሁለት ዋነኛ አላማዎ ችን ለሰራዊቱ አስቀምጧል
ዓረና_መድረክ የጠራው ሰለማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በህወሓት መሪዎች ታገደ።
ዓረና_መድረክ የጠራው ሰለማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በህወሓት መሪዎች ታገደ።
ዓረና_መድረክ በኣራት ኣንገብጋቢና ኣስቸኳይ መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ክልላዊና ሃገራዊ ርእሰ ጉዳዮች ኣስመልክቶ ለ20 / 06 / 2008 ዓ/ም በመቐለ ከተማ የጠራው ሰለማዊ የተቓውሞ ሰልፍ የህወሓት መሪዎች ኣግደውታል።
ሰልፉ ከኤርትራ በመጡ ታጣቂዎች ታግተው ስለተወሰዱ ወጣቶች መታገት፤ የህግ ልእልና እንዲከበር፤ በረሃብ እያለቁ ስላሉ ወገኖቻችንና የኦሮምያ ክልል ስለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞና እየተወሰደ ያለው ግድያና እስር ቆሞ መንግስት ከሚመለከታቸው እንደ መድረክ የመሰሉ ፖለቲካዊ ድርጅቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ድርድር እንዲጀምር የሚጠይቁ ኣጀንዳዎች ናቸው።
ህወሓቶች ለእገዳው የሰጡት ምክንያት፦
Friday, February 26, 2016
የሕወሓት ጦር ኦሮሚያን በ8 ቀጠናዎች ከፋፍሎ በሕዝቡ ላይ እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑ ተጋለጠ
(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሞ ሕዝብ እንቅስቃሴ 4ኛ ወራት እያስቆጠረ ነው:: ቀደም ሲል የኦሮሞ ሕዝብ ቁጣ እየተቀጣጠለ ሲሄድ ክልሎ ከኦህዴድ አስተዳደር እጅ ወጥቶ በቀጥታ በሕወሓት መሪዎች; የደህነነት ኃይሎች እና ወታደሮች እንዲመራ መደረጉን ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ስትዘግብ ነበር::
“በመጨረሻም ፍትሕ ከጎናችን ትቆማለች”
(በቀለ ገርባ)
ነሐሴ 21/2003 ከምሠራበት ቦታ በስልክ ተጠርቼ በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ ከሚጠራው የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተወስጄ ከአንዲት ትንሽ ጨለማ ክፍል ውስጥ ከተወረወርኩ በኋላ በማግስቱ አራዳ ወረዳ ፍ/ቤት ቀርቤ የሃያ ስምንት ቀን የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆብኝ ተፈቅዶላቸው፣ ያም ሲያልቅ እንደገና ሌላ ቀጠሮ ተጠይቆ ተፈቅዶላቸው፣ የማይመለከቱኝን ጥያቄዎች ስጠየቅና ስመልስ ቆይቼ ጥቅምት 3/2004 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቤ የክስ ወረቀት ደርሶኝ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተልኬ እነሆ እስከዛሬ ድረስ ዞን አንድ ቅጣት ቤት ተብላ በምትጠራው ቤት እገኛለሁ፡፡
Amnesty International Report 2015/16 – Ethiopia
Members and leaders of opposition parties as well as protesters were extrajudicially executed. General elections took place in May against a backdrop of restrictions on civil society, the media and the political opposition, including excessive use of force against peaceful demonstrators, the disruption of opposition campaigns, and the harassment of election observers from the opposition. The police and the military conducted mass arrests of protesters, journalists and opposition party members as part of a crackdown on protests in the Oromia region.
ለበዕውቀቱ ሥዩም፡- የንግሥተ ሳባ ጥበብን ፍለጋ ጉዞዋ የወሲብ ረኻብ የወለደው ጉዞ አልነበረም!!
በዲ/ን ኒቆዲሞስ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለን ነበር በመጀመሪያ ጊዜ ከበዕውቀቱ ሥራዎች ጋር የተዋዋኩት፡፡ በወቅቱ ካልተሳሳትኩ በዕውቀቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ካምፓስ ተማሪ እያለ ‹በራረሪ ቅጠሎች› በሚል ርዕስ ከደርዘን የሚልቁ ጣፋጭና አከራካሪ ወጎችን በአንድ ላይ ጠርዞ ለአንባብያን ያቀረባቸው መጣጥፎቹ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትንና ተደናቂነትን እንዲያተረፍ አድርጎት እንደነበር አይዘነጋም፡፡
በዚህ መጽሐፉ በዕውቀቱ በተለይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ያለውን የዘር ሽኩቻ፣ የርዕዮተ ዓለም ቅኝት፣ የዘመኑን የብሔር ፖለቲካዊ ቀውስ፣ ተማሪዎች ዶርም ያለውን አስቂኝ፣ አዝናኝና አሳዛኝ ገጠመኞችን- ራሳችንን በቅጡ እንድናይና ቆም ብለን እንድጠይቅ የሚያደርጉን መረርና ከረር ያሉ እውነቶችን ከቀልድና ከተርብ፣ ከአሽሙርና ከአግቦ ጋር እያዋዛና እያዛነቀ የተረከበት መጣጥፎቹ አሁንም ድረስ በብዙዎች በናፍቆት ተደጋግመው የሚነበቡ ናቸው፡፡
አዲስ አበባ ላይ ያልተሳካላቸው የህወሓት አገዛዝ ፌደራል ፖሊስ አዛዦች ባህር ዳር ላይ በድጋሚ ስብሰባ አካሂደው የባሰውን ተበጣበጡ፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
አዲስ አበባ ላይ ያልተሳካላቸው የህወሓት አገዛዝ ፌደራል ፖሊስ አዛዦች ባህር ዳር ላይ በድጋሚ ስብሰባ አካሂደው የባሰውን ተበጣበጡ፡፡
የፌደራል ፖሊስ አመራሮቹ ከእሁድ የካቲት 13 እስከ 16 2008 ዓ.ም ድረስ ነው በባህር ዳር ከተማ ምንም አይነት አዎንታዊ ውጤት ያላመጣ ውይይት ለማድረግ የሞከሩት፡፡ በስብሰባው ላይ “ባልተማሩ የህውሓት ታጋዮች አንመራም… ” የሚል ተቃውሞ ተነስቷል፡፡
በልዩ ልዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ የጠብመንጃ ጉልበት ተጠቅሞ ፀጥ የማስኘትን የአገዛዙን የፀና አቋም በሚመለከት ደግሞ በአዛዦች መካከል እስከ አምባጓሮ የዘለቀ አለመግባባት ተከስቶ ነበር፡፡ “ወደ ህዝባችን እንዲተኮስ ትእዛዝ አንሰጥም…“ በማለት በግልፅ ተቃውሟቸውን ያሰሙ በርካታ የፈዴራል ፖሊስ አመራሮች ነበሩ፡፡
በመጨረሻም ስብሰባው እንደተለመደው ያለምንም ውጤት ተበትኗል፡፡ ከስብሰባው በኋላ 4 የፌደራል ፖሊስ አመራሮች ስርአቱን ከድተዋል፡፡ ከአራቱ መካከል አንዱ ኢንስፔክተር ፀጉ ይሰኛል፡፡ አራቱም መኮንኖች እስካሁን የት እንደደረሱ የታወቀ ነገር የለም፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) የህወሓት አገዛዝ የህዝቡን ትኩረት ለማስቀየር የጦር ኃይሉን ኤርትራ ድንበር አካባቢ ከወዲያ ወዲህ በማተራመስ ጦርነት የሚከፍት በመምሰል የተለመደ የማስመሰል ተግባሩን በማከናወን ላይ ነው፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
የህወሓት አገዛዝ የህዝቡን ትኩረት ለማ(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
የህወሓት አገዛዝ የህዝቡን ትኩረት ለማ(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
የህወሓት አገዛዝ የህዝቡን ትኩረት ለማስቀየር የጦር ኃይሉን ኤርትራ ድንበር አካባቢ ከወዲያ ወዲህ በማተራመስ ጦርነት የሚከፍት በመምሰል የተለመደ የማስመሰል ተግባሩን በማከናወን ላይ ነው፡፡
Thursday, February 25, 2016
ኣድርባይ በበዛበት ዘመን ታማኝ ለኣላማው ፥ ታማኝ ላ’ገሩ ( ሄኖክ የሺጥላ )
ስለ ኢትዮጵያዊነት የማውቀን ፅፌያለሁ ፥ እፅፋለሁ ። ሃገር ማለት እንዲህ ማለት ነው ብዬ በኣጭር ቋንቋ መግለፅ ግን እስከዛሬ ኣልቻልኩም ፥ ወደፊትም ኣልችልም ፥ ለመቻልም ኣልሞክርም ! ምክንያቱም ሃገር የሚለው ሃሳብ ከመንፈስነትም ፥ ከእምነትም ፥ ከምንነትም በላይ ነውና ። ሃገር እንደ ኣንድ ትልቅ የሰውነት መሃፀን ነውና ፥ ረቂቅም ነውና ።
«ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ
ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ »
ያለው ባለ ተባ ብእሩ በድሉ ዋቅጂራ ለዚያም ኣይደል ?
ሃገሬን ሳስብ ፥ የሃገሬ ጀግኖች ትዝ ይሉኛል ፥ የሃገሬ ጠላቶች በቁጭት ጥርሴን እንዳፋጭ የሚያደርጉኝን ያህል ፥ ለሃገሬ ጠበቃ ሆነው የሚሟገቱላት ፥ የሚሞቱላት ሰዎች ሳስታውስ ደሞ ጉልበት ኣገኛለሁ ፥ ለመንፈሴ ስንቅ ፥ «ለመንገዴ መብራት » የሚሆነኝ በነዚህ ሰዎች ልብ ውስጥ የተፃፈው ማንነት ነው ። እርግጥም ሃገር ውስብስብ ነው ቃሉ ።
ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ »
ያለው ባለ ተባ ብእሩ በድሉ ዋቅጂራ ለዚያም ኣይደል ?
ሃገሬን ሳስብ ፥ የሃገሬ ጀግኖች ትዝ ይሉኛል ፥ የሃገሬ ጠላቶች በቁጭት ጥርሴን እንዳፋጭ የሚያደርጉኝን ያህል ፥ ለሃገሬ ጠበቃ ሆነው የሚሟገቱላት ፥ የሚሞቱላት ሰዎች ሳስታውስ ደሞ ጉልበት ኣገኛለሁ ፥ ለመንፈሴ ስንቅ ፥ «ለመንገዴ መብራት » የሚሆነኝ በነዚህ ሰዎች ልብ ውስጥ የተፃፈው ማንነት ነው ። እርግጥም ሃገር ውስብስብ ነው ቃሉ ።
Wednesday, February 24, 2016
የህወሃት ልዩ ነፍሰ ገዳይ ሠራዊት አመሰራረት፣ የገዳይ ቡድኑ አጋዚ እና የእናት እንባ
የእግሊዝኛው ጽሁፍ አዘጋጅ – ዓለም ማሞ
የአማርኛው ተርጓሚ – ቢላል አበጋዝ
የአማርኛው ተርጓሚ – ቢላል አበጋዝ
“ፔንታጎን ያሰለጠናቸው የኢትዮጵያ ሠራዊት ፤ክፉውን አጋዚ የተሰኘውን ልዩ ኅይልም ይጨምራል።”
–ጄረሚ ስከሂል
ኢንተር- ሴፕት ኤንድ ናሽናል ሴኩሪቲ ለተባለው ጋዜጣ መስራችና ቃል አቀባይ ከአሜሪካ መንግስት ክፍተኛ ምክር ቤት የፍርድ ኮሚቴ ዘንድ ቀርቦ ከሰጠው የምስክርነት ቃል የተወሰደ ጥቅስ። ዲሴምበር 9 ፣2010
ታሪኩ እነሆ
ከእድሜዋ በላይ የጠናች መስላ ትታያለች።በአካል ያያት ስድሳ ዓመት ሞልቷታል ብሎ መገመት ይችላል።እውነቱ ግን አርባ ዓመትዋ ብቻ ነው።
“ወታደራዊው መንግስት ስልጣን ከመያዙ ሁለት ዓመት በፊት ነው የተወለድኩት” ትላለች ታሪክ እየጠቀሰች።የተጨማደደው ቆዳዋ፤ማዲያቷ እና ሽበትዋ መከራን ያሳለፈችን እናት ታሪክ ይናገራሉ።ያለፉት አስር ዓመታት በችግር የተሰቃየችባቸው ናቸው። “የበኩር ልጄን ከአስር ዓመት በፊት ቀበርኩ፤እኛ ተቃዋሚዎች አቸንፈን ድምጣችንን በቀሙን ጊዜ” አለች ወደ አድማሱ ቃኝታ ከተራሮቹ ሰው ብቅ የሚል እንደሁ ትጠብቅ ይመስል።
Monday, February 22, 2016
በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የቀረበው ሃሳብ በሕወሓት ውድቅ ተደረገ::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የወያኔን ትንፋሽ በጣረ ሞት የሸበበው የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ቀጥሏል::በተለያዩ ወረዳዎች የቀጠለው ተቃውሞ ሕዝቡ በወያኔ አገዛዝ የሚደረግበትን የፖለቲካ ጫና የኢኮኖሚ በደል እና ወታደራዊ እርምጃዎች በመቃውም ተቃውሞውን ለማሰማት አደባባይ የወጣ ሲሆን በየአከባቢው መንገዶችን በመዝጋት ለለውጥ ያለው ቁርጠኝነት በትግሉ እያሳየ ይገኛል::በተለየ ሁኔታ በሃረርጌ ጉራዋ በዳዋ አከባቢ እንዲሁም በበደኖ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን በዳዋ ያሉ ነዋሪዎች የአግኣዚ ሰራዊት ወደ በደኖ ዘልቆ ለመግባት ሙከራ ሲያደርግ ድልድዩን በመዝጋት የመግባት አላማውን አጨናግፈውበታል::
" የጥፋት ልጆችን እንዴት እንታገል"በኤርምያስ ለገሰ
ብዙ ሰዎች የወይዘሪት ሚሚ ስብሀቱ ስብእና ፊቱ ላይ እየተደቀነ ሴትየዋን እና በዙሪያዋ የተሰባሰቡ ትናንሽ ሰዎች የሚያቀርቡትን ፕሮግራም የመስማት ፍላጐት ያጣል። ርግጥም የእነ ሚሚ ፕሮግራም በቅዱስ መጵሀፋ " የአመጳ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ" እንደሚለው የሚፀነሰው በአደንዛዥ እጵ እና በስካር መንፈስ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት አብዛሀው በንቀት ፣ በመፀየፍ እና አቃሎ በመመልከት ቢያልፈው የሚያስገርም አይደለም። እውነትም እነዚህ የመንፈስ ድሀዎችን ማዳመጥ ጊዜ እንደማጥፋት ቢቆጥረው እና ትእግስት ቢያጣ ትክክል አይደለህም አይባልም።
Sunday, February 21, 2016
የቆሰለው አውሬ አገራችንን ይበልጥ ሳያቆስል በጊዜ እንነሳ! (አርበኞች ግንቦት7)
የንቅናቄያችን ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ተገኝተው ለኢትዮጵያውያን ባደረጉት ንግግር ወያኔ የቆሰለ አውሬ ሆኗል ብለው ነበር። ፕ/ር ብርሃኑ በንግግራቸው፣ የቆሰለ አውሬ በህይወት ለመቆየት ሲል ያለ የሌለውን ሃይል በመጠቀም ጥቃት በሰነዘረበት ግለሰብ ላይ የበቀል እርምጃ ከመውሰድ ወደ ሁዋላ የማይል በመሆኑ፣ ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበው ነበር። አውሬነት የጭካኔ ደረጃንና ሁዋላቀርነትን የሚያሳይ ገላጭ ቃል ነው፤ አውሬነት ወያኔ በህዝባችን ላይ ለሚፈጽመው ግፍ ጥሩ ወካይ ቃል ነው፤ ነገር ግን ወያኔ ከአውሬ አልፎ የቆሰለ አውሬ ሆኗል፤ አደገኛነቱም ጨምሯል።
ፕ/ር ብርሃኑ በትክክል እንዳሉት የወያኔ የጥቃት ኢላማዎች ወያኔን የሚታገሉት የነጻነት ሃይሎች ብቻ አይሆኑም። መላው የአገራችን ህዝብ በቆሰለው አውሬ ከመጎዳት አያመልጥም። በነፍስ ግቢና ውጪ መካከል የሚገኘው የቆሰለው አውሬ አፈር ልሶ ከቁስለቱ አገግሞ እንዳይነሳ ጥፋቱን እየተከላከሉ፣ ሞቱ የሚፋጠንበትን መንገድ መቀየስ ከእያንዳንዱ ዜጋ ይጠበቃል። የቆሰለ አውሬ ወዳጅ ጠላት መለየት የማይችል፣ ፊት ለፊት ባገኘው ላይ ሁሉ እርምጃ ለመወሰድ የሚንደፋደፍ በመሆኑ፣ ሁሉም ዜጋ የጥቃት ጥፎሮቹ እሱም ላይ እንደሚያርፉ በመገንዘብ አውሬውን ለማጥፋት መረባረብ ይኖርበታል።
Saturday, February 20, 2016
አ! ኳታሪ መዝናኛ በአዲስ አበባ! ኢትዮጵያውያኖች ለምን ኬክ አይበሉም? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
በአሁኑ ጊዜ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አውዳሚ በሆነ ረሀብ በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ!
የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ–ህወሀት) የመዝናኛ ሆቴል አልሚዎችን ከመካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገሮች እያፈላለጉ በመጋበዝ ላይ ይገኛሉ፡፡
Friday, February 19, 2016
ብርሃኑ ነጋ ለስልጣን ነው የሚታገለውን ? ( ሄኖክ የሺጥላ )
ብርሃኑ ነጋ ለስልጣን ነው የሚታገለው ለሚሉ ሰዎች ዛሬ የመልስ ምት መፃፍ ኣምሮኛል ። እንደሚከተለው ይቀርባል ።
ከጥያቄው እንነሳ
ብርሃኑ ነጋ ለስልጣን ነው ወይ የሚታገለው ?
ቀጥተኛ ያልሆነ መልስ « ኣዎ!» ብርሃኑ ለስልጣን ነው የሚታገለው።
በሻሸመኔ፣ በነቀምት፣ በአምቦ እና በጉደር ዛሬ ብቻ 16 ሰዎች ተገደሉ – በምስራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ ዛሬም ሕዝብ ከአጋዚ ጦር ጋር ተፋጧል
የ አጋዚ ጦር በነቀምት (Photo)
(ዘ-ሐበሻ) በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ አካባቢ በምትገኘው አባሮ መንደር የአጋዚ ጦር 4 ሰላማዊ ሰልፈኞችን መግደሉ ተሰማ:: የሕዝቡ ተቃውሞ በምስራቅ ሐረርጌ የተለያዩ ከተሞች እና ወረዳዎች እንደቀጠለ ነው::
Wednesday, February 17, 2016
የደም አፍሳሾች ሸንጎና የህወሃት የዘር ፍጅት አዋጅ በወልቃይት ጠገዴ ላይ
በጎሹ ገብሩ፣ አባይ መንግስቱ፣ ገብሩ ማማይ፣ ቻላቸው አባይ፣ አበራ አታላይ፣ አብዩ በለው
“ወልቃይት የትግራይ ነው ! የአማራነት ጥያቄው በዚህ የማያቆምና ተጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን…!”
አቶ አባይ ወልዱ
“የወልቃይት ጉዳይ ክልል አንድን እንጂ ማንንም አይመለከተውም፤ ውሳኔውም ሊሆን የሚችለው የክልል አንድ ብቻና ብቻ ነው፡፡”
ዶ/ር ደብረ ፂዮን ገ/ሚካኤል
“የወልቃይት አማራ መፍትሔ አፈላላጊ አካሉን በተደጋጋሚ አነጋግረናቸው በተፈቀደላቸው ህገመንግሥት ተጠቅመው መስራት ያልቻሉና ይልቁንም ከውጭ ካለው ፀረ ሰላም ኃይል ጋር በመሆን መንግሥትን በኃይል ለመናድ ከቆመ አካል ጋር እንደወገኑ፣ እኛንም የወያኔ ተላላኪዎች፤ ሆዳሞች፤ ቅጥረኞች እያሉ እየሰደቡን የሚገኙ ሲሆን፣ ከውጭ ያሉት ኃላፊዎቻቸውም በየሚዲያው እየቀረቡ የስድብ ናዳ ያወርዱብናል፤ በአውስትራልያና በአሜሪካ ትልልቅ ሰብሰባ እየጠሩ ሲያወግዙን እንደሚውሉ ደርሰንበታል፤ በተለይ አውስትራልያ ተጠርቶ በነበረው ሰብሰባ የኤርትራ ባለስልጣን በመጋበዝ ከኤርትራም በኩል እርዳት ሊደረግላቸው ቃል እንደተገባላቸው አረጋግጠናል። ድርጅታችን ህወሃትም ያማያዳግም ቅጣት ሊሰጣቸው ይገባል”
አቶ ፈረደ የሺወንድም
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ) የህወሓትን አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ሄሊኮፕተር ይዘው ከሀገር የወጡት እነ ሳሙኤል ግደይ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የህወሓትን አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ሄሊኮፕተር ይዘው ከሀገር የወጡት እነ ሳሙኤል ግደይ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው፡፡
የህወሓትን አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ሄሊኮፕተር ይዘው ከሀገር የወጡት እነ ሳሙኤል ግደይ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው፡፡
Tuesday, February 16, 2016
ሰልፈኞች ንብረትነቱ የሕወሓት የሆነ የነዳጅ መጫኛ ቦቴ አቃጠሉ – ወደ አ.አ. የሚያገናኙ መንገዶች በ20 አቅጣጫዎች በሰልፈኞች መዘጋታቸው ተሰማ
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ የስርዓቱን ንብረቶች ወደ ማውደም ተሸጋገረ:: ቀደም ባለ የዘ-ሐበሻ ዜና ም ዕራብ አርሲ ቀበሌ ጽህፈት ቤት መቃጠሉን የዘገብን ሲሆን አሁን በደረሰን መረጃ ደግሞ በምስራቅ ሸዋ ንብረትነቱ የትራንስ ኢትዮጵያ የሆነ የነዳጅ መጫኛ ቦቴ በሰልፈኞች ተቃጥሏል::
ሕወሓት በትግራይ ሕዝብ ስም ከፍቶት ሆንም ግን አንዳችም ቀን የትግራይን ሕዝብ ጠቅሞ የማያውቀው ኤፈርት ስር የሚገኘው ይኸው የትራንስ ኢትዮጵያ ንብረት ቦቴ በሰልፈኞች ከተቃጠለ በኋላ ወደዚያው ለመንዳት የሚፈልጉ ሹፌሮች ስጋቱ እንዳየለባቸው ለማወቅ ተችሏል::
Friday, February 12, 2016
ኃይሌ ገብረሥላሴ መካሪ ያጣባቸው 3 ነገሮች – ከኤርሚያስ ለገሠ
” ዲሞክራሲ -101″…”መካሪ አያሳጣህ!”
ተጳፈ ለሀይሌ ገ/ስላሴ
ተጳፈ ለሀይሌ ገ/ስላሴ
ይቺን አጭር ፅሁፍ ለመጫር የገፋፋኝ በዛሬው እለት አትሌት ሐይሌ ለአንድ የውጭ ሚዲያ የሰጠውን አስተያየት በማዳመጤ ምክንያት ነው። አላማዬ ሐይሌ የተናገረውን ሁሉ ለመቃወም አይደለም። ወይም አንዳንድ ” ልወደድ ባይ ደካማ” ሰዎች እንደሚያስቡት አትሌቱ የተጐናፀፈውን ዝና ለማጉደፍ አስቤ አይደለም።
ኦሮሚያ የመላው ኢትዮጵያዊ መላው ኢትዮጵያም የሁሉም ኦሮሞ ናት! ከጃዋር ሃሳብ የማልስማማበት እና የምስማማበትን ስለመለየት፤
ABEBE TOLA FEYISA
ኦሮሚያ የመላው ኢትዮጵያዊ መላው ኢትዮጵያም የሁሉም ኦሮሞ ናት!
ከጃዋር ሃሳብ የማልስማማበት እና የምስማማበትን ስለመለየት፤
ከጃዋር ሃሳብ የማልስማማበት እና የምስማማበትን ስለመለየት፤
የኛ ሀገር ፖለቲካ የቡዳ ፖለቲካ ነው እንዳሉት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አሁንም ድጋሚ ፖለቲካችንን ቡዳ ሊበላው ነው መሰል ጣት መቀሳሰር እና እነ እንትና እነ እንትና መባባል ልንጀምር ይመስላል… ምናባቱ እንግዲህ ካልደፈረሰ አይጠራም…
Thursday, February 11, 2016
አርበኛ ተጋይ ዘመነ ካሴ የአርበኞች ግንቦት 7 ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታና ወደ ኤርትራ በረሃዎች እየጎረፈ የሚገኘው ወጣት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መናርን በሚመለከት ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ የሰጡት አጭር ቃለ ምልልስ፡፡
ለኢትዮጵያውያን ምንም የሚቀር ሀገር የላቸውምን? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የደራሲው ማስታወሻ፡ የዚህ ሳምንት ትችቴ በኢትዮጵያ በጋምቤላ ካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ፒኤልሲ የተባለው ድርጅት መውደቁን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት ያቀረብኩት ትችት ተከታይ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 ዘ-ህወሀት 100 ሺ ሄክታር ለበጥባጩ የመሬት ተቀራማች ለሳይ ካራቱሪ ካስረከበ በኋላ በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ የኮንትራት ውሉን ሰርዟል፡፡
ከካራቱሪ አስደንጋጭ ውድቀት በኋላ ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ 725 ከ/ሜ ርዝመት ያለውን፣ እንዲሁም 250 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያለውን እና 600 ሺ ሄክታር ለም መሬት የሆነውን የኢትዮጵያን አንጡራ የግዛት ሉዓላዊነት ለሱዳን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ (ለሱዳን ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀውን የመሬት ስፋት ካርታ ለማየት ከዚህ ጋ ይጫኑ፡፡)
ዘ-ህወሀት ለሱዳን፣ ለካራቱሪ ወይም ደግሞ ለማንኛውም መሬት ተቀራማች ሸፍጠኛ ስለሚሰጠው የመሬት ድንበር የሕግ ጉዳይ ውጤት ትኩረት የለኝም፡፡ (ይቅርታ የድንበር ማመላከት ማለቴ ነው፡፡) ዘ-ህወሀት ለካራቱሪ ከ300 ሺ ሄክታር በላይ ሲሰጥ ምንም ዓይነት ጉዳይ አድርጌ አልወሰድኩትም ነበር፡፡ ካራቱሪ እ.ኤ.አ በ2011 ውድቀት እንደሚደርስበት እና እ.ኤ.አ በ2016 በአስገራሚ ሁኔታ እንደሚወድቅ ትንበያ ሰጥቸ ነበር፡፡
Tuesday, February 9, 2016
ብርሃኑ እንደ ቸርችል- እኛ እንደ እንግሊዞች (ነጋ አባተ- ከእስራኤል)
ነጋ አባተ- ከእስራኤል
ሰሞኑን ዶ/ር ብርሃኑ እንድ ግራምጣ የሚሰነጣጠቅ ሁሉም የየራሱን ጫፍ ነክሶ የሚያልመዘምዘው ንግግር በታዳሚያቸው ጆሮዎች ማዕዛው እንደሚናፈቀው የሃገሬ ጠጅ አንቆርቁረውታል ለስለስ ሸከር፤ ጣፈጥ መረር የሚል ቅኝት ግን ነበረው። የወደደውም ያልወደደውም ፈቅዶም ይሁን ተገዶ ብቻ ከሁሉም አቅጣጫ ታዳሚም አድማጭም ነበራቸው። በፈቃዱ የታደመው በጋለ ናፍቆት ሲጠባበቅ ሌላው ደግሞ ምን ሊል ነው በሚል የግዳጅ ቅምጫ ሬት ሬት እያለውና እየጎመዘዘው ማወራረዱ አልቀረም ሁሉም ግን እንደ አመጣጡ ታድሟል።
Saturday, February 6, 2016
የፉገራ ዜና ይከታተሉ
የፉገራ ዜና ይከታተሉ እየተዝናኑ የወያኔን ከልክ ያለፈ ውሸት ከመረጃ ጋር እያጣቀሰ ያስቃኘናል ተከታተሉት ገዢዎቻችን በተለያየ ግዜ እርስ በእርሱ የሚጣረዝ መለጫ ምን ያህል ባዶነታቸውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ተከታተሉት !!
Friday, February 5, 2016
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የምስክርነት ቃሉን ሰጠ
*‹‹የህሊና እስረኛ ነኝ›› እስክንድር ነጋ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በሽብርተኝነት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ 18 አመት እስር ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የመከላከያ ምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡
Thursday, February 4, 2016
በሐዋሳ ታቦር ትምህርት ቤት አሰቃቂ ግድያ በወያኔ ፖሊስ ተፈጸመ
በሐዋሳ ታቦር ትምህርት ቤት አሰቃቂ ግድያ በወያኔ ፖሊስ ተፈጸመ:: #Ethiopia #Hawassa
በደቡብ ኢትዮጵያ በሐዋሳ ከተማ በዛረው እለት ከጠዋቱ አራት ሰአት በታቦር ትምህርት ቤት አቅራቢያ አንድ ወጣት በፖሊስ ጥይት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሏል:: የወያኔ ፖሊሶች ‹‹ስለት ይዘህ ሰው አስፈራርተሀል›› በሚል በጥይት ደብድበው ገድለውታል;;
Wednesday, February 3, 2016
ሰውየው ---ብርሃኑ ነጋ ( ሄኖክ የሺጥላ )
አጭር ፍቅር
ሰውየው ሕልም አለው ። የአንደበቱ ርትዖነት ካለው የቃላት አጠቃቀም እና ልቀት ሳይሆን የሚመነጨው ከሃሳቡ ጠጣርነት እና ከቆመለት ትልቅ እውነት እንጂ !
ሰውየው ሕልም አለው ፣ ለዚያውም በሞቀ ቤት እና በቀዘቀዘ ቢራ ውስጥ በሚደረግ የሳይበር ጦርነት የሚጸና ሳይሆን ፣ የማሽላ እንጀራ እየበላ አፈር ላይ እየተኛ ፣ ከእባብ እና ገጊንጥ ጋ እየተታገለ ፣ በሞርታር እና በፈንጂ ወረዳ ውስጥ ውድ ነብሱን አቁሞ የሚሞትለት እጹብ ሕልም ።
ሰውየው ሕልም አለው ፣ ለዚያውም በሞቀ ቤት እና በቀዘቀዘ ቢራ ውስጥ በሚደረግ የሳይበር ጦርነት የሚጸና ሳይሆን ፣ የማሽላ እንጀራ እየበላ አፈር ላይ እየተኛ ፣ ከእባብ እና ገጊንጥ ጋ እየተታገለ ፣ በሞርታር እና በፈንጂ ወረዳ ውስጥ ውድ ነብሱን አቁሞ የሚሞትለት እጹብ ሕልም ።
Subscribe to:
Posts (Atom)