Translate

Friday, January 16, 2015

ኢትዮጵያ አለች ወይ? – ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

dr-dagnachew-Assefa 
አንድ የተማረ ሰው ከአዲስ አበባ ወጥቶ ወደ ሌላ ክልል ሄዶ ስራ ሲሰራ ደሞዙ ተቆርጦበት ወይም ዘግይቶበት ሰለ መብቱ
ቢጠይቅ የሚሰጠው ምላሽ እኔዴውም ከአላገራቹህ መጥታቹህ ስራ ስላገኛቹህ ልታመሰግኑ ይገባል ይባላሉ። አሁን ያለንበት ደረጃ አሥከፊና አስቸጋሪ ነው። እነዴውም አሁን እየጠየቅን ያለነው፣ አገራችን አለች ወይ ነው? ኢትዮጵያ አለች ወይ? ልክ ከአዲስ አበባ ወጣ ስትል ከየት ነው የመታኽዉ ትባላለህ። ልክ ሌላ አገር የሄድክ እስኪመስልህ። ምንም አይነት ‘ፕሮቴከሽን’ የሌለባት አገር ሁናለች።
መጀመሪያ የጠነሰሱት ቢህል አሁን እያበበ ነው። የአገሪቱ ሁኔታ ‘ኢዝ አት ስቴክ’ (is at stake)። አንተ ትቀልዳለህ ሶማሊያ፣ ጋምቤላ ተወው፥ እዚህ አምቦ እንኮ የኔ ተማሪወች ስራ ተቀጥረው የእኛ ተማሪወች እስኪመጡ ብቻ ነው ስራ ሊኖራችሁ የምትችሉ ነው የተባሉት። አንተ ትቀልዳለህ! አገር የለንም ነው እንኮ የምልህ። ይህ ከሗላ ኪሴ አውጥቼ የምንገርህ እንዳይመስልህ ልጄ። 62 (ስልሳ ሁለት) አመቴ ነው። ያለው እውነታ ይህ ነው። አገር የሚባል ነገር አብቅቷል። አዝናልሁ። ግን ያለው ሁኔታ ይህ ነው። ህገ መንግስቱ ዜጋ የሚባል ‘ቮካቡላሪ’ የለውም። እኛ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ነው የሚለው። አንድ ሰው በግልሰብ በዜግነት ስለ መብት የሚያወራበት ሁኔታ የለም። በጣም በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው። ወጣ ካልክማ አንተ እንዴት መጣህ? ይልሃል። ቱሪስት ነህ ወይስ ምንድን ነህ? ይልሃል። ከየት ነው የመጣህ ነው እንኮ የምትባለው። የሚገርም ጉድ እንኮ ነው የፈላብን።
‘አካዳሚክ ፊርደም’ የሚለውን ‘ኮምፒሊትሊ’ አውጣው። ሁሉም ፕሮፌሰር፣ ሁሉም አስተማሪ አንገቱን ደፍቶ ዛሬ ነገ ያዙኝ ብሎ የሚኖርበት አገር ነው ዩኒቨርሲት ማለት ኢትዮጵያ። እነግራሃለው። የፈልጉትን ይበሉ እነግረሃለው። ይሄ ነው ያለው። ስለ ሰቆጣ የጻፈው የህግ አስተማሪ ደብዳቤ ነው የተጻፈለት እንዲባረር። ያውም እሱ የብአዴን አባል ነው ምናምን ነገር። ‘አካዳሚክ ፍሪደም’ የሚባል ‘ቮካቡለሪወም’ የለ። ድሮ ቀረ።
አሁን ሳምንት ምን አለኝ ‘ቸርማኑ’ እና እኛ እንመርጥና እነሱ ‘ሪኮሜንድ’ ያደርጉልናል። ‘ቼርማን’ አንመርጥም። ‘ዲን’ አንመርጥም። ካድሬወች ነው የሚመርጡልን። ምን አለፋህ። አንድ ዩኒቨርሲቲ ‘አድሚሽኑን’ (admission) ያስረከበ ዩኒቨርሲቲ ‘አካደሚክ ፍሪደም’ አለኝ ይላል እንዴ? በትዛዝ እንከሌን ተቀበሉ እነከሌን አተቀበሉ የሚባል ዩኒቨርሲቲ ‘አካዳሚክ ፊሪደሙን’ ተወው አልኩህ። እርሳው እሱን። ይገባሃል የምልህ? ‘አድሚሽኑን’ ያስረከበ ዩኒቨርሲቲ ‘አካደሚክ ፍሪደም’ አለ ብሎ ሊያወራ አይችልም።
መከፋፈልን እንደ ጸጋ የወሰደ ስርዓት እኮ ነው። ምን ትጠብቃለህ እስኪ ንገረኝ። “የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኳን ደስ ያላቹህ። ብሄር ብሀረሰቦች ሆናቹህ ነው እኮ የሚለው ዘፈኑ ሁሉ። አንተ ነገሩን እንዴት ነው የምታየው። አገር የለም። ህግ የለም። እየጠፋን ነው። ምን ትላልለህ? ስለመብት ታወራለህ እንዴ። የእኛስ፣ የተማሪወች ማህበር አለ አይደል እንዴ ካድሬወች ነው እኮ ‘ራን’ (run) የሚያደርጉት። ሲቪል ማህበራት የሚባል ነገር የለም። ወይ ጠፈተዋል ወይ ተካተዋል።

No comments:

Post a Comment