Translate

Tuesday, January 13, 2015

መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ የተሳካ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

Tatek Assefa's photo.ምርጫ ቦርድ በታዛቢነት በጉባኤው አልተገኘም
በጥቅምቱ ጠቅላላ ጉባኤ በመልቀቂያ የተሰናበቱት አቶ አበባው መሃሪ ጥሪ ቢደረግላቸውም አልተገኙም
ለአሜሪካ ሬድዮ የአማርኛ እና የጀርመን ሬድዮ የዐማርኛ ድምፅ ዘጋቢዎች ጥሪ ቢደረግም አልተገኙም
425 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተገኝተዋል፡፡
መኢአድ በሁለት ወራት ውስጥ ሁለተኛውን የተሳካ ጠቅላላ ጉባኤውን ጥር 3/2007 ዓ.ም አካሄደ፡፡ጉባኤው ከመላው ሀገሪቱ በተሰበሰቡ ቁጥራቸው 425 በሚሆኑ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በተገኙበት የተካሄደው ምርጫ ቦርድ ከጥቅምት 28-30/02/2007 መኢአድ ያደረገውን የተሟላ ጠቅላላ ጉባኤ አልተቀበልኩትም በማለቱ ምክንያት ነው፡፡ምርጫ ቦርድ የመኢአድን የጥቅምቱን ጉባኤ አለቀበልም ያለበት ምክንያት ተከትሎ ዛሬ በተደረገው ሁለተኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ምርጫ ቦርድ በታዛቢነት እንዲገኝ ቢጋበዝም አልተገኘም ፡፡ ለምን አንዳልተገኝ ምክንያቱ ባይታወቅም ከመኢአድ ለምርጫ ቦርድ በታዛቢነት እንዲገኘ ጥሪ የደረገለት መሆኑ እና መልክቱም በፖስታ ቤት እና በስልክ እንዳነጋገሯቸው ተረጋግጧል፡፡ የጠቀሱት የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ አቶ ተስፋየ መላኩ ጠቅላላ ጉባኤው መጀመር ከነበረበት ጊዜ 30 ደቂቃ ዘግይተው የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የእለቱን ጉባኤ አስጀመሩ፡፡ አያይዘውም ጉባኤው ዘግይቶ ሊጀመር የቻለው ከምርጫ ቦርድ ተወካይ እስኪመጣ እየተጠበቅ መሆኑን እና አሁን በስልክ በተነገራቸው መዕልክት ምርጫ ቦርድ የጥር 3/2007 ዓ.ም ጉባኤ የሚካሄደውን የመኢአድን ጉባኤ ለመታዘብ ፈቃደኛ አለመሆኑን ለጉባኤው ነግረው መድረኩን ለመኢአድ ፕሬዘዳንት ለአቶ ማሙሸት አማረ አስረከቡ፡፡
አቶ ማሙሸት አማረ ወደ መድረክ ሲወጡ በከፍተኛ ጩህትና ጭብጨባ ጉባኤው ተቀበላቸው፡፡እርሳችም ከመድረክ ለተደረገላቸውን የክብር አቀባበል አመስግነው መኢአድ የሚደረግበትን የፖለቲካ ሴራና ደባ ተረድታችሁ በአስቸኳይ ና ድንገተኛ ጥሪ ከአራቱም የሐገሪቱ ማዕዘናት ለተሰበሰባችሁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የከበረ ምስጋና ይገባችኋል በማለት ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡
ዋና አጀንዳቸውን ለቤቱ ያስተዋወቁት በሚከተለው የመግቢያ መዕልክታቸው ነው፤ መኢአድ በመመሪያው መሰረት እና በጠቅላላ ጉባኤ አባለት ጥያቄ የውስጥ ችግሩን በእርቅ ለመፍታታት ጥቅት 28/02/07 የላዕላይ ም/ቤቱ እና ጥቅምት 29-30/02/07 ዓ.ም አስቸኳ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄዷል፡፡
በጉባኤውም ፤ሁሉም የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተገኘተዋል፤ ዋና አጀንዳ የነበረው ውስጥ ችግሩን መፍታት ነበር ፤ የጉባኤው ውሳኔም የመኢአድን የወደፊት የስራ አመራር እቅድ ማጽደቅ እና ትክክለኛ የመኢአድ አመራር አባላትን መምረጥ ነበር፤በዚህ ጉባኤ ላይ ሁለት የምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች ተገኝተው ነበር፡፡ታዛቢዎቹም ምዕላተ ጉባኤውን ቆጥረው የቃለ-ጉባኤ ስነ-ሥርዓቱን አረጋግጠው ጉባአው ሊጀመር እንደቻለ አቶ ማሙሸት አስታውሰዋል፡፡ ጉባኤውም የአመራሩን የውስጥ ችግር ጥቅምት 28 አይቶ በ29/02/07 ለሚካሄደው የጠቅላላ ጉባኤ መርቶት ነበር፡፡ይህንንም የጉባኤ ውሳኔ የምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች ታዝበዋል፡፡የውስጥ ችግሩም በጠቅላላ ጉባኤው በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን የቦርዱ ታዛቢዎች ተመልክተዋል፡፡
ሁኖም ግን የመኢአድ የውስጥ ችግር አፈታት ሂደት ምንም ዓይነት የሕግም ሆነ የአሰራር ክፍተት እንደሌለበት እየታወቀ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም ያስተላለፈው መኢአድን የተመለከተው መግለጫ ከህግ እና ከአሰራር ያፈነገጠ ፍፁም ወገንተኝነትን የተከተለ በመኢአድ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የገባ ነው ብለዋል፡፡ ሁኖም ሰላማዊ ትግል ብዙ እልህ አስጨራሽ በመሆኑ ምርጫ ቦርድ የሚፈጽመውን የፖለቲካ ደባና ሴራ ለህዝባችን ማጋለጥ ተገቢ በመሆኑ የመኢአድ የጠቅላላ ጉባኤ አባለት በሁለት ወራት ውስጥ ብዙ መስዋትነት ከፍለው ለጥር 3/2007 አስቸኳይ ጉባኤ መገኘት በመቻላቸው አድንቀው አሁንም በዛሬው ጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ ቦርድ ያልተገኘው አንጋፈውን ድርጅት መኢአድን ከምርጫ ለማስወጣት በሚደረግ ሴራ ውስጥ ስለሆነ ሊሆን አንደሚችል በማሳወቅ መኢአድ ከግንቱ 2007 ዓ.ም በምርጫ ቦርድ እና በተለያዩ አካለት ፖለቲካዊ ውሳኔ ቢወጣ ሊከተል ስለሚችለው የትግል ስልት ወደፊት ቆም ብሎ ሊያስብ ይገደዳል በማለት አስረግጠው የተናገሩት የድርጅቱ ፕሬዘዳንት ከጠቅላላ ጉባኤው አባለት የማያባራ ድጋፍና ጭብጫባ ያጅባቸው ነበር፡፡
በመቀጠል ምርጫ ቦርድ የጥቅምቱን ጉባኤ እና የአመራር ምርጫ በራሱ ታዛቢዎች ተወክሎ ተከታትሎ አሁን ድጋሚ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ እስከ ጥር 4 ድረስ ያሳውቀኝ ባለው መሰረት ጉባኤው ይህንን ተረድቶ ሁለት ውሳኔዎችን ተወያይቶ እንዲወስን አሳሰቡ፡፡
ሁለቱ የዕለቱ ዋና ዋና አጀንዳዎችም ፤ባለፈው ጥቅምት 28-30/2007 የተደረገውን የመኢአድ አመራር እንደለ በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ማስቀጠልአ፤ወይም በዛሬው ጉባኤ አዳዳስ አመራር አባላትን መምረጥ የሚሉ ነበር ፡፡ በሁለቱም ሀሳቦች ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤው የጥቅምቱን የጠቅላላ ጉባኤ የአመራር ምርጫ እንዳለ ማሰቀጠል የሚለውን ሀሳብ በከፍተኛ የድምጽ ብልጫ አፅዲቋል፡፡ በዚህም መሰረት
1-አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ፕሬዘዳነት
2-ዶ/ር ታደወስ ቦጋለ የመኢአድ ተ/ም/ፕ/ት
3-አቶ እንዲሪያስ ኢሮ የመኢአድ ም/ፕ/ት
4-አቶ ተስፋየ መላኩ የመኢአድ ዋና ፀሀፊ ሁነው ይቀጥላሉ፡፡
በማንኛውም መንገድ የመኢአድን የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ሊለውጠው ወይም ሊሽረው የሚችለው የመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ ብቻ ነው፡፡አቶ አበባው መሃሪ ፀረ-መኢአድ አስተሳሰብ ካላቸው ቡድኖች ጋር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በታሪክ ይቅር የማይባል የባንዳነት ተግባር በመሆኑ በአስቸኳይ ጉዳዩን የሚከታተል ቡድን እንዲቋቋም ጠቅላላ ጉባኤው ወስኗል፡፡ጠቅላላ ጉባኤው ባለ አስራ አንድ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡ በመጨረሻም በጠቅላላ ጉባኤው በህግና በስነ-ስረዓት ከሚመራው በኢአድ ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴወች ፈፅሞ ተቀባይነት የሌላቸው ሲሆኑ በውጭም በአገር ውስጥ ያሉ የሚዲያ ተቋማት ይሕንን በመገንዘብ ብዙ መስዋትነት የተከፈለበትን አንጋፋውን ድርጅት ለማፈራረስ የተላላኪነት አጀንዳ አንግበው ከሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ጋር የሚያደርጉት ማንኛውም የመረጃ ልውውጥ መኢአድን አይወክልም ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment