Translate

Friday, January 30, 2015

ጥሩ ነው አገር መሆን ! ጋሸ አዳሙ ዘ ብሔረ አዲስ አበባ

(አሌክስ አብርሃም)
ልክ ከምሽቱ አራት ሰዓት …!! የሰፈራችን ታዋቂ ሰካራም ጋሽ አዳሙ እየዘፈነ እየፎከረ እየተሳደበ እና እየተራገመ …. የምሽት ጭርታ የተጫጫናት ሰፈራችንን የዝምታ ድባብ ገፈፈው ….‹‹ እ ያ ን ዳ ን ድ ሽ ›› ሲል ገና 
‹‹ጋሽ አዳሙ መጣ ..›› ተባብለን የቴሌቪዥን ድምፅ ለመቀነስ ተራወጥን
‹‹ኧረ ቀስ ቡናውን እንዳትደፉት›› እየተባልን ….በቃ ጋሽ አዳሙን ለመስማት መንደርተኛው በሙሉ ማታ ማታ በየቤቱ ሁኖ ጆሮውን ያቆማል …ጋሽ አዳሙም እንደሚሰማ ያውቀዋል መሰል ድምፅ እስከምንቀንስ ጠብቆ ….እያንዳንድሽ …..ብሎ ይቀጥላል …. አይዛነፍም ሰዓቱ ልክ አራት ሰዓት ላይ ነው ሰፈራችን የሚደርሰው !
‹‹ እኔ የምለው …ይሄ ሰፈር በጊዜ መብራቱን አጠፋፍቶ ለሽሽ የሚለው ምን ነክቶት ነው ….ወይስ የሌላውም ሰፈር እንቅልፍ ወደዚህ ሰፈር ተግዟል ! …. እንቅልፍ ብቻ …. ደህና ህልም እንኳን አታልሙ እንቅልፍ ታባክናላችሁ …. ሃሃሃሃሃ ....የማላውቅ መሰለሽ እያንዳድሽ ጋሽ ተሸ ቤት ህልም ልታስፈች ስትመጭ ‹‹ ሱዳን ስሄድ አየሁ … ዱባይ ስሄድ አየሁ ›› አሁን እስቲ ማን ይሙት ሱዳንና ዱባይ እንኳን በህልም በዜና ስማቸው ሊነሳ ይገባ ነበር ….ህልማችን ከጊዜ ወደጊዜ ወርዷል …. የህልም ግሽበት ! አሁን በዚህ በሚመጣው ምርጫ ‹‹ህዝቡን ደህና ነገር እንዲያልም አደርጋለሁ ›› የሚል ፓርቲ ካለ እመርጣለሁ ሃሃሃሃሃሃ! …

የተበላው እቁብ (ምርጫ 2007) እና እኔ ባይተዋሩ…

ethiopian election 2015አቤንኤዘር ጀምበሩ (አዲስ አበባ)
ጥር 11/07 ዓም ቦታው አፍንጮ በር፣ ከዩሀንስ፣ ከጊዬርጊስ እና ቀጨኔ መድሃኒያለም ታቦቶች ለከተራ ወደ ጃንሜዳ ሲተሙ የሚጋጠሙበት ቦታ። እልልታው ፣ጭፈራው፣ መዝሙሩ ፣ የሐገር ባህል ልብስ፣ ዱላ ፣ሸንኮራ ፣ጠጠር መጣያ ከሌለው ህዝብ ጋር አብረው ሽኝቱን አድምቀውታል ። ከሁሉ ከሁሉ ድምጽ ግን ከጀርባዬ የቆሙ እናት ጮሆ ውስጥ ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ ። መቼ ነው ምልጃ እና አግዚኦታ የሚያልቀው? “አምላኬ ወጣቶችን ጠብቅ፣ ምርጫውን በሰላም አጠናቀው ፣ደም መፍሰስን አንተ በቃ በል ፣ ልጆቻችንን ጠብቅ፣ ተለመነን … ” ፣ ሁሉ አንቅስቃሴ ፣ ሁሉ አዲስ ነገር ፣ ሁሉ አዲስ ሐሳብ የስጋት ምንጭ እንደምን ይሆናል? ስጋትን ወደ መልካም አጋጣሚነት መቀየር አይቻልም?
የቤታችን በር በአማካኝ ሶስት ጊዜ ትንኳኳለች፣ ሰሞኑን አህዟን በእጥፍ አሳድጋ ስድስት ጊዜ መንኳኳት ጀምራለች። ምክንያት ብትሉ ያካባቢያችን ምርጫ አስፈፃሚዎች “ካርድ ወሰዳችሁ፣ ውሰዱ ፣ማን አልወሰደም ፣ መቼ ተወሰደ …” እያሉ ይመጣሉ።

የአንድነትና የመኢአድ ቢሮ በፖሊስ ተከቧል

Police surrounded UDJ's office in Addis Ababa
(ነገረ-ኢትዮጵያ) የአንድነት ለፍትሕና ዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ቢሮ በፖሊስና በደህንነት መከበቡን አቶ አስራት አብርሃ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ቢሮው በደህንነትና በፖሊስ በመከበቡ አባላት መውጣትና መግባት እንደማይችሉ የገለጹት አቶ አስራት ‹‹ውጭ ያለነው ወደ ውስጥ እንዳንገባ ተከልክለናል፡፡ ውስጥ ያሉትም መውጣት አይችሉም፡፡›› ብለዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችና አባላት እንዳይወጡና እንዳይገቡ የከለከሉት ደህንነትና ፖሊሶች የከበባውን ምክንያት እንደማይናገሩ አቶ አስራት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቢሮው በፖሊስና በደህንነቶች በመከበቡ አመራሮችና አባላቱ ወደ ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጭ መውጣት እንደማይችሉ ተግልጾአል፡፡

Thursday, January 29, 2015

የህወሃት ምስጥራዊ የምርጫ አሰራር ሲጋለጥ

ምስጥራዊ የህወህት የምርጫ አሰራርን የሚያጋልጡ የመንግስት ባለስልጣንና ካድሬን በማነጋገር ሳዲቅ አህመድ ከትንታኔ ጋር የሚያቀርበዉን ክፍል አንድ ፕሮግራም ይከታተሉ።


Audio Player

Ethiopian election 2015

ምርጫ ቦርድ፣ ቦርዱን ያከብራሉ ያላቸውን በእነ ትግዕስቱ አወሉ ለሚመራው አንድነት እና በእነ አቶ አበባው መሀሪ ለሚመራው መኢአድ ዕውቅና ሰጠ፡፡

ጥር ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እና የቦርዱ ጸሀፊና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነጋ ዱፊሳ በጋራ ዛሬ ጥር 21 ከቀኑ 10፡00 ሰኣት በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ በእነአቶ በላይ ፍቃዱ የሚመራው አንድነት፤ የፓርቲውን ደንብና የምርጫ አዋጁን የጣሱ ተግባራትን እንደሚያከናውን፣ ፓርቲው ያካሄደውን ጉባዔ ለሰባት ወራት ሳያሳውቀው መቆየቱን፣ የቀድሞ ፕሬዚደንት ከሃላፊነታቸው የተነሱት ሕጉን ጠብቆ አለመሆኑን፣ ፓርቲው ለሁለት ሲከፈል ቦርዱ ልዩነታቸውን በጋራ ለጠቅላላ ጉባዔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ቢጠይቅም ፈቃደኛ ሆነው አለመገኘታቸውን ጠቅሰዋል።

Wednesday, January 28, 2015

ያልተቀደሰው ጋብቻ!! ኢህአዴግ፣ ፋና፣ ኢብኮ፣ ምርጫ ቦርድ (ጌታቸው ሺፈራው)

በአንድ ወቅት ኢህአዴግ «የሚወዳደረኝ ተቃዋሚ ጠፋ» ብሎ ቀልዶ ነበር። በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ተበታትነው የነበሩት ተቃዋሚዎች ቅንጅትን ፈጥረው 1997 ምርጫ ላይ ሲያሸንፉት ደግሞ ቀልዱን ረስቶት ወደ ምርጫ የሚያመራውን መንገድ ሁሉ ለመዝጋት መታተር ያዘ። የፀረ ሽብር፣ የፕሬስ፣ የሲቪክ ማህበራት….አዋጆች «ከእኔ ጋር ለመወዳደር አቅም የላቸውም።» ይላቸው የነበሩትን ተቃዋሚዎች ወደ ምርጫ የሚያመሩበትን መንገድ የሚዘጉ መሰናክሎች ሆኑ። ያም ሆኖ ግን በእነ ኢዴፓ፣ የአየለ ጫሚሶው «ቅንጅት»ና መሰል ፓርቲዎች በመታጀብ ምርጫን ለይስሙላነት መጠቀሙን ቀጥሏል። በዚህ ሂደት ውስጥ ሳያሸንፍም ቢሆን አሸንፈሃል የሚለው «ምርጫ ቦርድ» ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ይሰራል። ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ያልሆነውን ኢህአዴግን ብቸኛ አማራጭ አድርገው የሚያቀርቡት ኢቲቪና ፋና አሉ። ሚዲያና ምርጫ ቦርድ ኢህአዴግ በተቃዋሚዎች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች በማንሳት ተቃዋሚዎችን በህዝብ አይን ማሳነስ ዋነኛ ስራቸው ሆኗል። በተለይ ምርጫ በተቃረበ ቁጥር ኢህአዴግ፣ ፋና፣ ኢብኮ፣ ምርጫ ቦርድ ሆነው በአንድነት በተቃዋሚዎች ላይ መዝመታቸው የተለመደ ነው።

የሰላም በሮች ሲዘጉ የሁለገብ ትግል ስልት በሮች ይከፈታሉ!!!

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ አማካይነት እየደረሰበት ያለውን በደል ለሕዝብ ለማሰማት ጥር 17 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ጂንካና ሸዋ ሮቢት የተቃውሞ ሰልፎችን ጠርቶ ነበር። በተለይ በአዲስ አበባው ሰልፍ ላይ የተገኙ ወገኖቻችን ለህወሓት ፍጹም ታማኝ በሆነው የፓሊስ ክፍል ያለርህራሄ መደብደባቸው እና የተቃውሞ ሰልፉም በጉልበት መበተኑ ነፃነትና ፍትህ ናፋቂውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሳዘነ ብቻ ሳይሆነ ያስቆጨ ጉዳይ ነው። በመላው ዓለም በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተለመደውን ድንጋይ ውርወራ እንኳን ሳይከጅሉ፤ የፓሊሶችን ሰብዓዊ ርህራሄ ለማግኘት “ፓሊስ የኛ ነው” እያሉ እየዘመሩ በፓሊስ ተደበደቡ። ሴቶችና አዛውንት ብቻ ሳይሆን ተላላፊ መንገደኞች እንኳን ከፓሊስ ዱላ አላመለጡም። ከሁሉም በላይ የሚዘገንነው ደግሞ የ 7 ወራት ነብሰ ጡር ሴትም በፓሊስ መመታትዋና ሆዷ መረገጡ ነው። ይህ እኩይ ተግባር የሚፈጥረው ቁጭት በህወሓት ላይ ብቻ አያበቃም። ትዝብቱ ለፓሊስም ተርፏል። ይህ የጭካኔ ተግባር ለፍትህና ለነፃነት በሚደረገው ትግል የሕዝብ አጋር ይሆናል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የፓሊስ ሠራዊትን የሚያዋርድ ነው። ደካማ እናቶችን፣ አረጋዊያንን፣ ባዶ እጃቸውን ተቃውሞ እያሰሙ ያሉትን ወጣቶችንና ነፍሰጡሮችን በጭካኔ መደብደብ ለራሱና ለሥራው ክብር ለሚሰማው ፓሊስ ውርደት ነው፤ የሞት ሞት ነው። የኢትዮጵያ የፓሊስ ሠራዊት አባላት ተግባራቸው ያሳፍራቸዋል፣ ይቆጫቸዋል፤ ቁጭታቸውንም ይህን ትዕዛዝ በሰጡ አለቆቻቸው ላይ በግልም ሆነ በተደራጀ መንገድ በሚወስዱት እርምጃ እናያለን ብሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ ያደርጋል።

Monday, January 26, 2015

የኢትዮጲያ ፖለቲካ መልኩን የሚቀይርበት 11ኛው ሰዓት ላይ ደርሷል!

የኢትዮጲያ ፖለቲካ መልኩን የሚቀይርበት 11ኛው ሰዓት ላይ ደርሷል!

መግቢያ መውጫ አሳጥቶ፤ የወንድ በር እንኳን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን በማን አለብኝነትና በትምክህት ስነልቦና ተወጥሮ በአፈና ጅራፉ ሲገርፈን ፀጥ ብለን የምናይበት የፈሪ ልብ፤ መጠን ያለፈውን የጭቆና ቀንበር የምንሸከምበት ጫንቃ የለንም፡፡
አዎን ኢህአዴግ የደም መስዋዕትነት የከፈልኩበትን ስልጣን በቀላሉ አለቅም በሚል የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርግ ሁሉ እኛም ጓዶቻችን የታሰሩበትን ትግል እና ፓርቲ ወደጎን ትተን የትም አንሄድም፡፡ አንዱአለም አራጌ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሀ ደስታ፣ አግባው ሰጠኝ እና ሌሎቹም የታገሉለትን አላማ ከግብ ሳናደርስ ወደኋላ ማለት የለም፡፡

በትንሹ የምንነግራችሁ ነገር ቢኖር… ይህ እየሆነ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው!

11111
ጥቁር ሽብር …በኢትዮጵያ ምድር! (ዳዊት ከበደ ወየሳ እንደዘገበው)
(ኢ.ኤም.ኤፍ) በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት ድጋፍ የሚደረገው የአሸባሪነት ተግባር እንደቀጠለ ነው። በከተሞች አካባቢ በህግ ሽፋን ዜጎች በአሸባሪነት ተፈርጀው ይታሰራሉ። ወደ ገጠር ስንሄድ ደግሞ፤ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ጥያቄ በጠራራ ጸሃይ ተገድለው፤ ለአስከሬናቸው እንኳን ክብር ሳይሰጥ በአደባባይ ህዝብ እንዲያያቸው እና እንዲሸማቀቅ ይደረጋል። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እጅግ ዘግናኝ የሆነ ጥቁር ሽብር እየተከናወነ ያለው፤ በዜጎች ላይ ነው። በፍርድ ቤት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ሳይሆን፤ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ነን በሚሉ ሰዎች ድጋፍ የሚከናወን ነው – እንዲህ ያለው ግድያ።

Sunday, January 25, 2015

የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ

ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)
በመጀመርያ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ደጋፊና ተደጋፊ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን በሙሉ ጠሯቸው። ሰበሰቧቸው። እንዲህም አሏቸው። “ወደ ደደቢት አብራችሁን ትሄዳላችሁ፤ እዛ እንደደረሳችሁም አመጣጣችንንና አካሄዳችንን በደንብ አድርጋችሁ ታጤናላችሁ። ከዚያ ስትመለሱ ሁሉንም ነገር ለህዝቡ ትናገራላችሁ።…”       
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሃገር መሪ ሆነው የሚሰሩት እኝህ ሰው መልዕክታቸውን በዚህ አላበቁም። አይናቸውን ፈጠጥ፤ ጉሮሯቸውንም ጠረግ-ጠረግ አደረጉና ንግግራቸውን ቀጠሉ “ስለረጅሙና መራራው ትግላችን፤ ከጅምራችን እስከ አያያዛችን የታዘባችሁትን ሁሉ ንገሩን። ጥሩውንም ይሁን መጥፎውን ነገር ሳትደብቁ ተናገሩ።…”
serawit fikre
ድምጻዊው በዝማሬ፣ ጸሃፊው በድርሰት፣ ተዋንያኑ በተውኔት ስለ ህወሃት የአርባ አመት ጉዞ እንዲመሰክሩ የተሰጠች ትእዛዝ መሆንዋ ነው። አጭር፣ ግልጽ እና ቀጭን መልዕክት ነበረች።

የስርዓቱን አረመኔያዊ እርምጃ እናወግዛለን! -‬ ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

10945537_586148308186795_6023333897633994809_nየ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አብሮ ስለመስራትና ሌሎቹም ትብብሩን እንዲቀላቀሉ በየጊዜው የሚወተውተው አገራችን በዚህ ዘመን በማይመጥን አምባገነንና የጭካኔ ስርዓት ውስጥ የምትገኝ መሆኑን በመረዳቱ ነው፡፡ ይህ የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነንና ጨካኝ ስርዓት ህዳሩ 27/28 2007 ዓ.ም የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በወጡት አመራሮቻችን፣ አባላቶቻችን፣ ደጋፊዎቻችንና በየጎዳናው የተገኙት ንፁሃን ላይ ከፍተኛ ድብደባና የጅምላ እስር በመፈፀም ስርዓቱን ለመታገል የተነሳነበትን አላማ ትክክለኝነት አረጋግጦልናል፡፡
በዛሬው ዕለትም ገዥው ፓርቲ በፓርቲያቸው የውስጥ ጉዳይ ገብቶ የሚፈፅመውን ደባ፣ ምርጫ ቦርድንና የህዝብ ሚዲያን ተጠቅሞ ፓርቲውን ለመከፋፈልና አሳንሶ ለማሳየት የሚያደርገውን እኩይ ተግባር በመቃወም ሰልፍ የወጡ የአንድነት አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና የፓርቲው ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው ቤተ ክርስትያን አካባቢ የነበሩ አዛውንት ምዕመናንን ሳይቀር በመደብደብ ጭካኔውን ዳግመኛ አሳይቶናል፡፡ ፖሊስ በትዕዛዝ በአንድነት አባላት ላይ ከፍተኛ የጭካኔ እርምጃ ወስዷል፡፡ አብዛኛዎቹንም በጅምላ አስሯል፡፡

Saturday, January 24, 2015

እንኳን ደህና መጡ ወደ ወያኔ 2007 የምርጫ ጨዋታ!

እንኳን ደህና መጡ ወደ ወያኔ 2007 የምርጫ ጨዋታ!

የወያኔው ቋሚ ተሰላፊ ምርጫ ቦርድ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ምርጫ ውስጥ እንዳይገቡ ቢከለክል ምርጫ ተብዬው ጨዋታ ሊኖር አይችልም፣ ስለዚህ ወያኔን በምርጫው ወቅት የሚያጫውቱት ቡድኖች ስለሚያስፈልጉ አንዳንዶችን ያሳትፋል።

“የአንድነት በር ለመዝጋት በሚታትሩት ልክ፣ ሌላ ትልቅ ይህችን ሀገር ወደ አደጋ የሚወስድ በር ይከፍታሉ” አቶ ግርማ ሰይፉ /የአንድነት ም/ፕሬዝደንት/


udj_udj12አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ጥር 8 ቀን 2007 ዓ.ም ቀበና በሚገኘው ጽ/ቤቱ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እንዳይፈጠር ምርጫ ቦርድ ታሪካዊ ስህተት እየፈፀመ ነው ሲል መግለጫ ሰጥቷል።
ፓርቲው እንዳለው፤ ቦርዱ በሕግ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ከመወጣት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ ያለውን ወገንተኝነት በምርጫው ሂደት ዋዜማ በይፋ እያረጋገጠ ይገኛል። አሁንም ቦርዱ ወሰነ ተብሎ በሚዲያ የተገለፀው እንዲሁም ለፓርቲያችን በጽሁፍ የተሰጠው “በአስራ አምስት ቀን ውስጥ በጋራ ጉባዔ አድርጉ” የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ በተደጋጋሚ ፓርቲያችንን ደንብ እንዲያከብር እየጠየኩ ነው በማለት ከደንብ ውጭ እንድንሰራ የአዛኝ ቂቤ አንጓች ሆኗል ሲል ከሷል። የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ የመጥራት ኃላፊነት ያለበት የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ወይም ደግሞ በአባላት ጥያቄ የጠቅላላ ጉባዔ አባላትን አንድ ሦስተኛ ፊርማ አሰባስበው በኦዲትና ኢንስፔክሽን ትዕዛዝ መሆኑ በግልፅ እየታወቀ ከፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ ውጭ በ15 ቀን ውስጥ ጉባዔ ጥሩ የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ ከገዢው ፓርቲ ጎን ተሰልፎ እየተጫወተ አንድነትን ከጨዋታ ለማስወጣት ካልሆነ ሌላ ምንም ትርጉም ልንሰጠው አንችልም። ይህ ደግሞ ቦርዱ እየሰራ ያለውን ታሪካዊ ወንጀል ይፋ የሚያደርግ ነው ብሏል።

Friday, January 23, 2015

ጣሚ ታገል ሠይፉ ቃለ-ምልልስ

ገጣሚ ታገል ሠይፉ በዚህ ቃለ-ምልልስ ላይ ከተናገራቸው:-

1) "...በወንድማማቾች ጠብ አንዱን ባንዱ ላይ ጀግና ማለት እምነቴ አይደልም.... ወደ ደደቢት ከሄደው የአርቲስቶች ቡድን ጋር 

ያልሄድኩትም በዚህ ምክንያት ነው"

2) "...ኪነ-ጥበብን ገለውታል...ይህ መንግስትን ዋጋ ያስከፍላል..."

3) "አሁን (ኪነ-ጥበብን) የሞሉት ገንዘብን በአቋራጭ ማግኘት: ሴትን ልጅ ወደ አልጋ መውሰጃ አቋራጭ መንገድ" የሚያደርጉ 

ናቸው




Wednesday, January 21, 2015

ምርጫ ቦርድ፣ ማጭበርበሩን ያቁም!

(አስገደ ገ/ስላሴ ከመቀሌ)

election 2007

በሕወሓት አመራርና አጃቢዎች የተፈበረከው ምርጫ ቦርድ ባለፉት 20 አመታት ለ4 ጊዜ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ምርጫ አካሂዷል። ሁሉም ምርጫዎች ግን የዴሞክራሲ መስፈርትን የሚያሟሉ እንዳልነበሩ ዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ጭምር አረጋግጠዋል።
በ2007 ዓ.ም የምርጫ ውድድርም ሕወሓቶች፣ በዚሁ አመት ሃቀኛ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ጭራሹን ላለማሳተፍ፣ ለአመታት ያህል የቤት ስራ እየሰሩ ቆይተዋል፡፡ ለዚሁ አላማ ግቡን ለመምታት አስቀድመው እጅግ ብዙ ብቁ ምሁራንን እና ወጣት የፖለቲካ አመራሮችን “ለስልጣናችን አስጊ ናቸው” በማላት በሀሰት ወንጅለው አስረው በማሰቃየት ላይ ይገኛሉ። ብዙ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች አባላት ላይም ስጋት ፈጥረዋል፤ ከትምህርትና ከስራም አፈናቅለዋል። ፓርቲዎችን ለመበታተን ብዙ ሰርጎ-ገቦችን በማስረፅ አለመተማመን በመፍጠር፣ እንዲከፋፈሉ ለማድረግ ብዙ ገንዘብ ረጭተዋል።

ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?

የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሰሞኑን ሥጋቱን ይፋ ሊያደርግ ነው!

hrw media freedom


* ኢህአዴግ አሸነፈ፤ ፋና መሰከረ!

ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተመልካች (Human Rights Watch) በያዝነው ሳምንት ማገባደጃ አካባቢ በኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነትን አስመልክቶ አጠቃላይ ዘገባ እንደሚያወጣ ተሰማ፡፡
ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ መረጃውን ያቀረቡና ከዘገባው ጋር ተዛማጅነት ክፍሎች እንደተናገሩት የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ይህንን ዘገባ ያጠናቀረው በተጨባጭ ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ሰለባ የሆኑትን በሚዲያው መስክ የተሰማሩትን በማነጋገርና የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ በመሰብሰብ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Tuesday, January 20, 2015

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

ዜጎች የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ጥሪ አቅርቧል

9 parties1

• “ምህዳሩ ካልተስተካከለ ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረውም ቢሆን ከምርጫ ልንወጣ እንችላለን”

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር “በነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ” ዘመቻው ነፃነትን የማስመለስ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡ ትብብሩ ዛሬ ጥር 12/2007 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አፈና እና ጫና እያደረጉ ቢሆኑም ነፃነትን ለማስመለስ የያዘውን ግብ ለማሳካት ወደኋላ እንደማይል ገልፀዋል፡፡ “የኢህአዴግ ጨካኝነትና የምርጫ ቦርድ አጋፋሪነት ሊቀጥል ይችላል” ያሉት የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሆኖም የትግሉ አላማ ኢህአዴግን ማጋለጥ በመሆኑ የሚያስፈልገውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ትግሉን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ “ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ ጥሪ ስናደርግ የፖለቲካ ምህዳሩ ተስተካክሏል እያልን አይደለም፡፡ እኛ አሁንም እያነሳን ያለነው የትግል ጥያቄ ነው” ያሉት የትብብሩ ም/ል ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ የትብብሩ የትግል አላማ ይህን የተዘጋ ምህዳር ማስከፈት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በጨረፍታ!

andargachew new picture
ግዛቸው አበበ
ከሁለት ሳምንት በፊት በዕለተ-እሁድ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፖሊስ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ፣ እንደገና ከአራት ቀናት በኋላ በእለተ ሐሙስ በድጋሚ የታየው፤ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን የሚመለከተው ፕሮግራም፤ ጃኬትና ሸሚዝ ሳይቀር እየተቀያየረ ተበጣጥሶ የተገጣጠመ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ነበር፡፡
ይህ ፊልም የቀረበው፡- “በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ ሰቆቃ አይፈጸምም” ለማለት ተፈልጎ መሆኑ ይታወቃል። በእውነት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች፣ የምርመራ ማዕከላትና በደህንነት ጽሕፈት ቤቶች ውስጥ ግፍና ሰቆቃዎች አይፈፀሙም ወይ? ለሚለው ጥያቄ እውነተኛውን መልስ መስጠቱ ነው። ሌላው ቢቀር በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ቀርበው በምርመራ ማእከላትና እስር ቤቶች ውስጥ ሰቆቃና ግፍ እየተፈጸመባቸው መሆኑን የገለጹ በጣም ብዙ ሰዎች ስላሉ መለስ ብሎ መመርመር ተገቢ ነው። በኢትዮጵያ ምድር አድራጊና ፈጣሪ የሆነው ሕወሓት፣ ለዓላማው ብሎ መሳሪያ አንግቦ የታገለ ድርጅት ነውና አቶ አንዳርጋቸውን በሚዛናዊ ዐይኑ እንደሚያይ ተስፋ አደርጋለሁ።

Monday, January 19, 2015

(ይናገራል ፎቶ) ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ኤርትራ በርሃ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ታጋዮች ጋር

የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ኤርትራ ከሚገኙ የኢትዮጵያውያን ታጋዮች ጋር ቆይታ አድርጓል:: ጋዜጠኛው እዚያው የሚገኙትንና ብረት አንስተው አሁን ያለውን የሕወሓት አስተዳደር ለመጣል ከሚታገሉት ታጋዮች ጋር የተነሳውን ፎቶዎች ይናገራል ፎቶ ስንል አቅርበንላችኋል::

የኢሕአዴግ የደህንነት መዋቅር መናጋቱን ምንጮች ጠቆሙ::

by MINILIK SALSAWI »

Image
ተቃዋሚ ሃይሎች ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ሰብረው በመግባት ስርአቱን ማፍረስ ያለባቸው ወቅት ነው::
Minilik Salsawi : ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን የፖለቲካ የምጣኔ ሃብት እና የማሕበራዊ ቀውስ እና ውጥረት ተከትሎ የባለስልጣናት አረመረጋጋት ታክሎበት በገዢው መደብ የተዋቀረው የደሕንነት ተቋም መናጋቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ የላኩት መረጃ ጠቁሟል::

ኢትዮጵያና የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ. ም (ገብረመድህን አርአያ፣ አውስትራሊያ)

ኢትዮጵያና የካቲት 11 ቀን 1967 በሚል ርእስ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ማቅረብ ተገቢ ነው ብዬ ተነሳሁ። የማቀርበውም ባጭሩ የሚከተሉትን በተመለከተ ይሆናል፤ የየካቲት 11 ቀን 1967 ዓላማ፤ ፖሊሲው፣ ለማን እና ለምን እንደተፈጠረ።
The Tigrayan People's Liberation Front (TPLF)
ቅድመ የካቲት 1967 ዋናው አስኳሉ የተፈጠረው፣ ማሕበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) በ1965 አካባቢ በቀ. ኃ. ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ነው። በትምህርት ላይ የነበሩ የትግራይና የኤርትራ ተማሪዎች ተሰብስበው ያቋቋሙት ማህበር ነው። ይህ ማህበር እንደተፈጠረ የወሰድው አቋምና የሚከተለው ፖሊሲ፣ በረቀቀ መንገና ጥናት ጸረ ኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት፣ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት፣ ፍቅርና ስላም ለማፍረስ የወጠነ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ኹከትና ብጥበጥ እንዲፈጠር የወሰነ በባእዳን የተፈጠረ ማህበር ነው። ማገብት ገና በረሃ ሳይወጣ ያዘጋጀው ፖሊሲው፣ ኤርትራና ትግራይ ነፃ የነበሩ ሃገራት ሲሆኑ በአማራው መንግሥት ቅኝ አገዛዝ ስር የወደቁ ናቸው የሚል ነው። አማራው የትግራይ ህዝብ ድመኛ ጠላት ስለሆነ ከሚኖርበት መሬት ዘሩን ማጥፋትና፣ በማንኛውም ጊዜ ህብረተሰብአዊ እረፍት እንዳያገኝ እናደርገዋልንም የሚል ፖሊሲ ነው።

“አእምሮዬ አልዳነም!”

ዖጋዴን! - የገሃነም ደጅ

martin ogaden

“በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ቶርቸር (አካላዊ ስቃይ) የሚፈጸምባቸው ጩኸታቸው ይሰማኛል፡፡ የቃሊቲ ማጎሪያ ውስጥ የታሰሩ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ንጹሃን ዜጎች፣ ስቃይ አሁንም ከፊቴ አለ፤ የሚሞቱት ሰዎች ሊረሱኝ አይችሉም፤ የእስር ቤቱ ጠረንና ሽታ ይከተለኛል፤ በአካል ደህና ብመስልም አእምሮዬ ግን አሁን ድረስ ሰላም የለውም” በማለት የስዊድን ጋዜጠኛ ማርቲን ሺብዬ በተለይ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ተናገረ፡፡

Sunday, January 18, 2015

Exposed: Prof. Constantinos Berhe has two fake degrees


By Abebe Gellaw
A lengthy Addis Voice investigation can reveal that Dr. Constantinos Berhe, a professor of public policy at the Addis Ababa University (AAU) and a key operative of the ruling TPLF-led regime, obtained two fake degrees from a bogus university. After claiming for many years to have earned an MA degree from Oxford University and a PhD from University of California (?), the “professor” finally admitted to AV that he got a Masters of Business Administration (MBA) and a PhD from American Century “University” (ACU).
Costy.jpgThe bogus university (formerly Century University), which claims to be based in Albuquerque, New Mexico, is a diploma mill that sells fake degrees online.In the course of our investigation, this reporter contacted ACU as a prospective graduate student and was offered MBA and PhD degrees for “graduation” within six weeks with a price tag  of $4000.  He was also granted a bogus scholarship with a total “value” of $15,225 despite the fact that the degrees and transcripts are worthless.
The offer was made by ACU’s CEO and administrative director, Allen Mirzaei (aka Ali Mirzaei).

Friday, January 16, 2015

ባለጌና ውሻ በቤቱ ይኮራል

የመጻፍ ፍላጎት በጭራሽ አልነበረኝም፡፡ ይሁን’ይ ዛሬ እንደወትሮው አላስችልህ አለኝ፡፡ መጻፍ የማልፈልገው መጻፍን በመጥላት ሣይሆን የሀገራችን ችግር ከመጻፍም፣ ከማንበብም፣ ከመመልከትና እጅን አጣምሮ በመቀመጥ በቁጪት ከመብከንከንም በእጅጉ ያለፈ በመሆኑ ነው፡፡ አዎ፣ ጊዜው የወሬና የሀተታ ሣይሆን የተግባር መሆን ይገባዋል – ልብ ላለው(2)፡፡ ብዙዎች – እኔንም ጨምሮ – ላለፉት ሃያ ምናምን ዓመታት በከንቱ ኃይላችንን መጨረሳችንን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ እነሱ ላይሰሙ ጆሯቸውን እንደዘጉና ዐይናቸውን እንደጨፈኑ፣ እኛም መለያየታችንና ሥልትአልባነታችን ላያርመን በግትርነት እንደተጓዝን ግማሽ ምዕተ ዓመት ሊጠባ የቀሩት በጣት የሚቆጠሩ ዓመታት ብቻ ናቸው – ሚሌኒየማዊ ከፍተኛው ዕድለቢስነት፡፡
wendimagegn Gashu
ዛሬ ያለመናገር የራስ በራስ ማዕቀቤን ያስነሣኝ በወንድማገኝ ጋሹ ቤተሰብ ላይ በወያኔ የተወሰደው “ለስላሳ” እርምጃ ነው፡፡ የሕጻናቱ አምላክ ጠብቋቸው እንጂ ወያኔን ምንም ነገር ከማድረግ የሚያግደው አንዳች ምድራዊ ሕግ የለም፡፡ ይህ የታወቀ እውነት ይመስለኛል፡፡ ወያኔ የበቀል አባት፣ የክፋት አቅማዳ፣ የመድሎና ዘረኝነት አጋፋሪ፣ የጭካኔ ምንጭና የውሸት ንጉሠ ነገሥት ነው፡፡

ኢ/ር ይልቃል ጌትነትና ሌሎች ሁለት የፓርቲ አመራሮች ምስክርነታቸውን ሰጡ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ስለሺ ፈይሳ እና የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት ቀርበው የተከላካይ ምስክርነታቸውን ሰጡ፡፡
ህዳር 27 እና 28/2007 ዓ.ም በ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ተዘጋጅቶ በነበረው የአዳር ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ በራሪ ወረቅት ሲበትን ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሲሳይ ዘርፉ በፌደራል አቃቤ ህግ በቀረበበት ክስ ተከላካይ ምስክር ሆነው የቀረቡት የፓርቲ አመራሮቹ፣ አቶ ሲሳይ ባለፈው ታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም የአቃቤ ህግ ሁለት ምስክሮች ቀርበው በተከሳሽ ላይ ምስክርነት በመስጠታቸውና በዕለቱ ዳኛው በበራሪ ወረቀቱ ላይ የተጠቀሰውን ‹‹የኢህአዴግ መንግስት ያፍናል፣ ያጭበረብራል፣ ይገድላል…›› የሚለውን በመጥቀስ ድርጊቱ ወንጀል ስለሆነ ተከሳሹ መከላከል አለበት ማለቱን ተከትሎ የመከላከያ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ተከሳሹ አቶ ሲሳይ ዘርፉ ‹‹…‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ› ለመላው ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ሁሉ….ተብሎ የተጻፈበት በራሪ ወረቀቶች ለህብረተሰቡ ሲያከፋፍል እጅ ከፈንጅ በመያዙ በፈጸመው የሐሰት ወሬን በማውራት ህዝቡን ማነሳሳት ወንጀል…›› በሚል ነው ክስ የቀረበበት፡፡

ኢትዮጵያ አለች ወይ? – ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

dr-dagnachew-Assefa 
አንድ የተማረ ሰው ከአዲስ አበባ ወጥቶ ወደ ሌላ ክልል ሄዶ ስራ ሲሰራ ደሞዙ ተቆርጦበት ወይም ዘግይቶበት ሰለ መብቱ
ቢጠይቅ የሚሰጠው ምላሽ እኔዴውም ከአላገራቹህ መጥታቹህ ስራ ስላገኛቹህ ልታመሰግኑ ይገባል ይባላሉ። አሁን ያለንበት ደረጃ አሥከፊና አስቸጋሪ ነው። እነዴውም አሁን እየጠየቅን ያለነው፣ አገራችን አለች ወይ ነው? ኢትዮጵያ አለች ወይ? ልክ ከአዲስ አበባ ወጣ ስትል ከየት ነው የመታኽዉ ትባላለህ። ልክ ሌላ አገር የሄድክ እስኪመስልህ። ምንም አይነት ‘ፕሮቴከሽን’ የሌለባት አገር ሁናለች።

Thursday, January 15, 2015

ከፍተኛ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ጀኔራሎች ስርዓቱ በላያቸው ላይ የሚፈፀመውን ተግባር በመቃወም ወደ ጠቅላይ ሚኒስተር ደብዳቤ መላካቸው ተገለፀ፣

generals of ethiopia
ከመከላከያ እስታፍ አፈትልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በከፍተኛው የመከላከያ ሰራዊት እርከን ሲሰሩ የቆዩ ከፍተኛ መኮነኖች ሌተናል ጀኔራል አበባው ታደሰ፥ ሌተናል ጀኔራል ሰዓረ መኮነን፥ ሜጀር ጀኔራል ሞላ ሃይለማሪያም፥ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በላያቸው ላይ እየፈፀመው ያለውን ተግባር ትክክል አይደለም በማለት በዚህ ሳምንት ወደ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የቅሬታ ደብዳቤ እንደፃፉ ለማወቅ ተችሏል፣

Wednesday, January 14, 2015

በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7፣ ለፍትህ፣ ዴሞክራሲና የነጻነት፣ ንቅናቄ መሀል የተደረገውን ውህደት በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣

በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7፣ ለፍትህ፣ ዴሞክራሲና የነጻነት፣ ንቅናቄ መሀል የተደረገውን ውህደት በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በዛሬው ዕለት፣ ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7፣ ለፍትህ ለዴሞክራሲና የነጻነት፣ ንቅናቄ፣ ድርጅቶች፣ ተዋህደን “አርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ”፣ በሚባል ሥም መጠራት መጀመራችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስናበስር፣ እጅግ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ባለፉት በርካታ አስርተ አመታት፣ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለነጻነት፣ መብትና አንድነት፣ ከፍተኛ ትግል ሲያካሂድ ቆይቷል። በአደረገውም ትግል እጅግ ከፍተኛ መስዕዋትነት ከፍሏል። ለከፈለው ከፍተኛ ዋጋ የሚመጥን ግን ምንም ዓይነት ውጤት አላገኘም። እንዲያውም ከጊዜ ወደ ጊዜ የመብት ረገጣው፣ አድሎው፣ ማስፈራራቱና ማዋከቡ ተጠናክረው መቀጠል ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ልትቀጥል የማያስችል ከፍተኛ የመበታተን አደጋ አንጃቦባት ትገኛለች ።
በሀገራችን ላይ ላንጃበበው ከፍተኛ የመበታተን አደጋ ምክንያት የሆነው በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ የአምባገነን ቡድን ነው። ይህ ዘረኛ አምባገነን ቡድን በሀገራችን ታሪክ በሥልጣን ላይ ከመጡ የገዥ ሃይሎች ጋር ሲወዳደር ሀገርን ለከፍተኛ አደጋ በማጋለጥ፣ ሕዝቧን በማወረድ፣ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ዕኩይ ሃይል መሆኑን በበርካታ ተግባራቶቹ ያለ ምንም ጥርጣሬ አረጋግጧል።

Tuesday, January 13, 2015

የኢትዮጵያ ምርጫ መቆመሪያ ተቋም ገመና በዳንኤል ተፈራ

ያሳለፍነው ሳምንት በሕወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ተሰልተው፣ ታስቦባቸው ይፋ ከተደረጉና አሻንጉሊቱ ምርጫ ቦርድ እንዲፈጽመው በህወሃት ሰዎች ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጥቶት ገቢራዊ እንዳደረገው የሚጠረጠረው የፖለቲካ ጉዳይ ይፋ የተደረገበት ነበር፡፡ ይሄው ጉዳይ በአይረቤ ሰበብና በምክንያት አልባ ሁነት ግን ዳግም ከቤተ-መንግስት በወጣ ትዕዛዝ በሚመሰል መልኩ አንድነት እና መኢአድ ወደ ምርጫ ፍክክሩ እንዳይገቡ አይን ያወጣና የሰዎችን የስልጣን ብልግና ባጋለጠ መልኩ መግለጫ የሰጡበት ነው፡፡

የኢህአዴግ ካድሬዎች የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ


‹‹በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ዘመቻ ተከፍቷል››
ብአዴን/ኢህአዴግ በምስራቅ ጎጃም ዞን ‹‹የምርጫ ግብረ ኃይል›› በሚል አደረጃጀት የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ አቶ ሳሙኤል አወቀ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የብአዴን ካድሬዎች በምስራቅ ጎጃም በተለይም ደብረማርቆስ ከተማ ላይ ቤት ለቤት እየዞሩ ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ በሚቀሰቅሱበት ወቅት የምርጫ ካርድ አልወስድም የሚሉ ዜጎችን ‹‹አልወስድም ስትል ፈርም›› እያሉ እያወከቡ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ‹‹የምርጫ ግብረ ኃይል›› በተሰኘው መዋቅር የምርጫ ካርድ እንደማይወስዱና እንደማይፈርሙ ስለሚገልጹት ዜጎች ከሌሎች መረጃ በመጠየቅ ለማስፈራራት እየሞከሩ መሆንን ገልጸውልናል፡፡
ከዚህም ባሻገር ካድሬዎቹ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ለምርጫ ጽ/ቤት አቅጣጫ እንደሚሰጡ፣ የምዝገባ ሰነዶችም በእነሱ እጅ እንደሆኑና የምዝገባ ሂደቱን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተግልጾአል፡፡ ካርድ የማቅረብና የመመዝገብ ኃላፊነት የምርጫ ቦርድ ስራ ሆኖ እያለ ሞጣ አካባቢ የምርጫ ካርድ አለቀ ሲባል በብአዴን ካድሬዎች ትዕዛዝ ከጎዛመን ወረዳ የምርጫ ካርድ ወደ ሞጣ መላኩን በመጥቀስ ብአዴን/ኢህአዴግ ምርጫ ቦርድን ተክቶ እየሰራ መሆኑን ኃላፊ ገልጸዋል፡፡

መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ የተሳካ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

Tatek Assefa's photo.ምርጫ ቦርድ በታዛቢነት በጉባኤው አልተገኘም
በጥቅምቱ ጠቅላላ ጉባኤ በመልቀቂያ የተሰናበቱት አቶ አበባው መሃሪ ጥሪ ቢደረግላቸውም አልተገኙም
ለአሜሪካ ሬድዮ የአማርኛ እና የጀርመን ሬድዮ የዐማርኛ ድምፅ ዘጋቢዎች ጥሪ ቢደረግም አልተገኙም
425 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተገኝተዋል፡፡
መኢአድ በሁለት ወራት ውስጥ ሁለተኛውን የተሳካ ጠቅላላ ጉባኤውን ጥር 3/2007 ዓ.ም አካሄደ፡፡ጉባኤው ከመላው ሀገሪቱ በተሰበሰቡ ቁጥራቸው 425 በሚሆኑ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በተገኙበት የተካሄደው ምርጫ ቦርድ ከጥቅምት 28-30/02/2007 መኢአድ ያደረገውን የተሟላ ጠቅላላ ጉባኤ አልተቀበልኩትም በማለቱ ምክንያት ነው፡፡ምርጫ ቦርድ የመኢአድን የጥቅምቱን ጉባኤ አለቀበልም ያለበት ምክንያት ተከትሎ ዛሬ በተደረገው ሁለተኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ምርጫ ቦርድ በታዛቢነት እንዲገኝ ቢጋበዝም አልተገኘም ፡፡ ለምን አንዳልተገኝ ምክንያቱ ባይታወቅም ከመኢአድ ለምርጫ ቦርድ በታዛቢነት እንዲገኘ ጥሪ የደረገለት መሆኑ እና መልክቱም በፖስታ ቤት እና በስልክ እንዳነጋገሯቸው ተረጋግጧል፡፡ የጠቀሱት የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ አቶ ተስፋየ መላኩ ጠቅላላ ጉባኤው መጀመር ከነበረበት ጊዜ 30 ደቂቃ ዘግይተው የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የእለቱን ጉባኤ አስጀመሩ፡፡ አያይዘውም ጉባኤው ዘግይቶ ሊጀመር የቻለው ከምርጫ ቦርድ ተወካይ እስኪመጣ እየተጠበቅ መሆኑን እና አሁን በስልክ በተነገራቸው መዕልክት ምርጫ ቦርድ የጥር 3/2007 ዓ.ም ጉባኤ የሚካሄደውን የመኢአድን ጉባኤ ለመታዘብ ፈቃደኛ አለመሆኑን ለጉባኤው ነግረው መድረኩን ለመኢአድ ፕሬዘዳንት ለአቶ ማሙሸት አማረ አስረከቡ፡፡

Monday, January 12, 2015

የአርቲስት አስቴር በዳኔና ሳሞራ ፍጥጫ በደደቢት በረሃ

…አርቲስት አስቴር በዳኔ ከተቀመጠችበት ወደፊት ወጥታ ማይኩን ስትጨብጥ ፍርኃት ቢጤ እንደወረራት ከመጀመሪያው ያስታውቃል፡፡ ‹‹በጣም ነው የሚያስፈራው፤›› በማለት የጀመረችውን አስተያየቷን የያዘችውን ማስታወሻ እያነበበች አስተያየት መስጠት ቀጠለች፡፡
‹‹ይህንን ዕድል ተመቻችቶልን በቴሌቪዥን ስናየው የኖርነው ታሪክ ለማየት ስለቻለን እጅግ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ በፊት የነበረኝ ያልተጨበጠ አመለካከት በመረጃ የተደገፈ ሆኗል፤›› በማለት ሐሳቧን ቀጠለች፡፡ ‹‹እውነትን መናገር እወዳለሁ፡፡ የሐሳብ ነፃነትም አለ፡፡ በእርግጥ የፖለቲካ ሰው አይደለሁም፤›› በማለት ታዳሚዎችን ፈገግ ያሰኘች ሲሆን፣ በሒደትም የፍርኃቷ መጠን እየቀነስ የመጣ ይመስላል፡፡
‹‹ዛሬ ባልናገረው የሚቆጨኝ የተከፈለው መስዋዕትነት እጅግ በጣም ከባድ እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ በጆሮ ስሰማው ደርግ ተደምስሶ ታጋይ እንዲህ ሆኖ ሲባል ከሁለቱም ወገን የተሰዉት በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ የሞቱት፣ እግራቸው የተቆረጠ፣ ዓይናቸው የጠፋ ስላሉ ለሁለቱም ‹ጠላት› የሚለው ቃል ተገቢ አይመስለኝም፡፡ የወንድማማቾች ደም በመፍሰሱ ቤተሰቦቻቸው ዘንድ ሄደን ስናይ ልብ የሚሰብር ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የጦርነትና የትግል ታሪክ ዘመኑ የፈጠረው ነው፡፡ በወቅቱ መንግሥታዊ ለውጥ ለማምጣት የትጥቅ ትግሉ አማራጭ አልነበረውም፡፡ አሁንስ?›› አርቲስት አስቴር ትንፋሿን ዋጥ በማድረግ ቀጠለች፡፡

ትናንት ከዉጭ ወራሪዎች የታደገን መከላከያ ሠራዊታችን ዛሬም ከአገር ዉስጥ ወራሪዎች ይታደገናል

አስተዋዩ የኢትዮጵያ ህዝብ እድገቱን ለሚመኙ አስተዋይ መሪዎች እለታደለምና ደሃ ነዉ፤ ረሀብተኛ ነዉ አልተማረም ወይም ኋላ ቀር ህዝብ ነዉ ማለት ይቻል ይሆናል፤ ሆኖም የኢትዮጵያ ህዝብ ያሰኘዉን ያክል ቢደኸይ ወይም ኋላ ቀር ቢሆን ለነፃነቱ፤ ለአንድነቱና ለግዛት አንድነቱ መከበር ያለስስት ደሙን የሚያፈስ ጀግና ህዝብ ነዉ። ይህ ጀግንነት ደግሞ አንደተረት በአፍ ተነግሮ የሚያበቃ ሳይሆን በመተማ፤ በአድዋ፤ በማይጮዉ፤ በወልወል፤ በፊልቱና በጎዴ የጦር ሜዳዎች ሊወጉትና ሊወሩት የመጡ ጠላቶቹ ጭምር የመሰክሩለት የታሪክ ሐቅ ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከጀግንነቱ ጋር አርቆ አስተዋይና ታጋሽ ህዝብ ነዉ፤ ሆኖም ይህንን ህዝብ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ በተከታታይ የገዙት የገዢ መደቦች ጀግንነቱን ለራሳቸዉ ክብርና ዝና ታጋሽነቱን ደግሞ ለስልጣን ዘመናቸዉ ማራዘሚያ አድርገዉ የመከራ ዘመን እያስቆጠሩ ኖረዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ታጋሽ ህዝብ ቢሆንም እርግጫዉና ጭቆናዉ በበዛበት ቁጥር አምርሮ የሚነሳ ለገዢ መደቦች የማይመች ቁጡና እልህኸኛ ህዝብ መሆኑንም በተከታታይ አሳይቷል። ይህንን ደግሞ በ1966 ዓም ከዳር ዳር ባቀጣጠለዉ ህዝባዊ አብዮት በ1983 ዓም ደግሞ በአራቱም ማዕዘናት ባካሄደዉ ህዝባዊ አመጽ አሳይቷል። ሆኖም አብዮቱንና ህዝባዊ አመጹን ከትግል ሜዳ እስከ ፖለቲካ ስልጣን አደባባዮች ድረስ አቀነባብሮ የሚመራ የተደራጀ ህዝባዊ ኃይል ባለመኖሩ የኢትዮጵያ ህዝብ የታገለላቸዉ የትግል ዉጤቶች ሁሉ የአምባገነኖች መጠቀሚያ ሆነዉ ቀርተዋል።

ኦኬሎ አኳይ እጅና እግራቸውን ታስረው ጨለማ ክፍል መታሰራቸው ተገለጸ እስክንድር ነጋ ከቤተሰብ ውጭ ጠያቂ ተከልክሏል

okello a

የቀድሞው የጋንቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ እጅና እግራቸው ታስሮ ጨለማ ክፍል መታሰራቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
አቶ ኦኬሎ ቂሊንጦ በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚታወስ ሲሆን ከሰሞኑ የርሃብ አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ በእስር በሚገኙበት እስር ቤት እጅና እግራቸውን ታስረው ብቻቸውን ጨለማ ክፍል እንዲገቡ እንደተደረጉ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ቂሊጦ ማረሚያ ቤት እስረኞችን ሊጠይቁ ሄደው እንደነበር የገለጹት ምንጮች፣ እዚያው በእስር ላይ ካሉ ሰዎች አቶ ኦኬሎ ያሉበትን ሁኔታ መረዳታቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የ18 አመት እስር ፍርደኛው ታዋቂው ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ከቤተሰብ ውጭ ሌላ ሰው መጠየቅ እንደተከለከለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)

Sunday, January 11, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ ይቅርታ እንደማይጠይቅ አስታወቀ


ሰማያዊ ፓርቲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤትን እስከ ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በጽሑፍ ይቅርታ ይጠይቅ በማለት የተላለፈው ውሳኔ ከሕግ አግባብ ውጪ ስለሆነ ተቃውሞውን በመግለጽ ይቅርታ እንደማይጠይቅ አስታወቀ፡፡

Saturday, January 10, 2015

“ጥምቅት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርት መልበስ አይቻልም” – ኢህአዴግ

“ጥምቅት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርት መልበስ አይቻልም” – ኢህአዴግ

blue shirt

በተለይ ምርጫ ሲደርስ ቀለማዊ ነክ ነገሮችን በጣም የሚያስፈራው ህወሃት/ኢህአዴግ በመጪው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ሰማያዊ ቀለም እንዳይታይ መከልከል መጀመሩ ተዘግቧል፡፡ የደኅንነትና የፖሊስ አባላቱን በማሰማራት በግልጽ ማስጠንቀቂያ እየሰጠ ያለው ኢህአዴግ ለዘመናት በቆየው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ የጨመረው ባለ ሰማያዊ መደብ ኮከብ በበዓሉ ላይ እንዳይታይ አብሮ ካልከለከለ በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማነት የሰየመውን የኢህአዴግ ዓርማ መቀየር አለበት በማለት አንዳንዶችተሳልቀዋል፡፡ በሰማያዊ መደብ ቢጫ ኮከብ ያለውን የኢህአዴግ ዓርማ በቲሸርት በማሰራት “ለኢህአዴግዬ ያልሆነ … ይበጣጠስ” በማለት “አምረውና ደምቀው” በበዓሉ ለመታየት ያሰቡ ካድሬዎቹና አፈቀላጤዎቹም በዚህ ጉዳይ ላይ አመራር ካልተሰጣቸው “ከኑግ የተገኘ …” የመሆን ዕጣ እንዳይደርሳቸው “ያስፈራል” ተብሏል፡፡

Friday, January 9, 2015

ወያኔ/ኢሕአዴግ የሚያቆነጃጀው ምርጫ 2007 ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብቷል::

አንድነትና መኢአድ የውስጥ ችግራቸውን ካልፈቱ በምርጫ ላይሳተፉ ይችላሉ::የሚል መግለጫ ምርጫ ቦርድ ም/ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር በራዲዮ ፋና መስጠታቸውን ተከትሎ;የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ስብሰባን ረግጦ መውጣቱን አስታኮ በመጭው ምርጫ ላይ ውጥረት ማጥላቱን መረጃዎች ሲጠቁሙ በሌላ በኩል መድረክ እና ኢዴፓ የግንቦቱ ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች አሉን በማለት ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር መደራደር(መወያየት)እንደሚፈልጉ እየተናገሩ ይገኛል::belay
ምርጫ ቦርድ እያለ ራሱን የሚጠራው ኢሕአዴጋዊ ተቋም አንድነት እና መኢአድ በህገ- ደንባቸው መሰረት ውስጣዊ ችግራቸውን እንዲፈቱ በቦርዱ ቢነገራቸውም ችግራቸውን ሊፈቱ አልቻሉም እያለ ሲከስ መስመራቸውን ስተዋል ብሎ እንዳመጣለት በመወንጀል በምርጫ ሊሳተፉ እንደማይችሉ ቢናገሪም የፓርቲዎቹ አመራሮች ግን ምርጫ ቦርድን በመቃወም አስፈላጊ የሚባሉ ፖለቲካው እርምጃዎችን እና ውሳኔዎችን እንደሚያደርጉ አስጠንቅቀዋል::

ለጥምቀት ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለበስ ተከለከለ • ህዝብን ያነቃቃሉ የተባሉ መንፈሳዊ ጥቅሶች መጠቀም አይቻልም ተብሏል

semayawi(ነገረ ኢትዮጵያ) የክርስትና እምነት ተከታይ ወጣቶች ጥምቀት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርቶችን እንዳይለብሱ መከልከላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን ጀምሮ እስከ ጃንሜዳ አካባቢ የሚኖሩ ወጣቶች በተለያዩ ማህበራት ስር ለጥምቀት በዓል ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ የገለጹት ምንጮቹ ከዝግጅታቸው መካከል ቲሸርት አሳትሞ መልበስ አንዱ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ሆኖም ወጣቶቹ ለጥምቀት በዓል የተለያዩ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች የታተሙበት ሰማያዊ ቲሸርት ማሳተማቸውም ተከትሎም ደህንነትና ሲቪል የለበሱ ፖሊሶች በየ ቤታቸው እየዞሩ ‹‹ጥምቅት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርት መልበስ አይቻልም፡፡›› እያሉ እያስጠነቀቁ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በነገው ዕለትም ካድሬዎች ከፈረንሳይ ሌጋሲዮን እስከ ጃን ሜዳ አካባቢ የሚገኙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ስብሰባ መጥራታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ ህዝብን ያነቃቃሉ ከሚል ስጋት አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በቲሸርት ላይም ሆነ ሌላ ለጥምቀት በዓል ላይ በማድመቂያነት በሚውል ነገር ላይ ማተም እንደማይቻል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ወጣቶቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለጥምቀት በዓል ማድመቂያነት እንዳይውሉ ከተከለከሉት ጥቅሶች መካከል ‹‹የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚያብሄር ትዘረጋለች፣ የአባቶቻችን ርስት አንሰጥም….›› የመሳሰሉት ይገኙበታል ተብሏል፡፡ እነዚህን መንፈሳዊ ጥቅሶች መጠቀም እንደሚያስቀጣም ደህንነትና ፖሊሶች የበዓሉ አዘጋጅ ወጣቶችን አስጠንቅቀዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ እና አማራ ተዋጊዎች መካከል ሰፈረ (ከዚያስ?)

ዳዊት ከበደ ወየሳበሰሜን ጎንደር, አርማጭሆ አውራጃ ልዩ ስሙ "ገ'ጨው" በተባለው ስፍራ የመከላከያ ሰራዊት ከትላንት ጀምሮ እንዲሰፍር ተደርጓል:: ማዶ እና ማዶ ሆነው እየተዋጉ ባሉት የትግራይ ወታደሮች እና በአማራ ህዝብ መካከል መከላከያ ሰራዊት ከሰፈረ በኋላ ጦርነቱ አሁን ለጊዜው ጋብ ብሏል:: የቀድሞ የህወሃት ወታደሮችን ሁመራ ላይ በማስፈር አካባቢውን ለራሱ ያደረገው ህወሃት - አሁን ደግሞ በአርማጭሆ መስፋፋት በመጀመሩ ነው - በአካባቢው ከሚኖረው የአማራ ህዝብ ጋር ግጭቱ የተቀሰቀሰው::

ሰሞኑን ግጭቱ ከመባባሱ በፊት የአማራው ህዝብ ተዋጊዎች - ህወሃት በአጭር ጊዜ ውስጥ አካባቢውን ለቅቆ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር:: ሆኖም የህወሃት ወታደሮች አካባቢውን ለቅቀው ባለመሄዳቸው በተለይ በማይ'እምቧ በርካታ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ - ህወሃት አባላት ሞተዋል:: በወያኔዎቹ ላይ የደረሰው አደጋ ያስደነገጣቸው እና ወደ አርማጭሆ ያመሩት ሌሎች የህወሃት አባላት - ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ጦርነት ሲያደርጉ ነበር የከረሙት:: በዚህ ጦርነት የሞቱት ሰዎች ቁጥር በትክክል ባይታወቅም የተኩስ ልውውጡ ከፍተኛ ነበር:: አሁን የመከላከያ ሰራዊት በሁለቱ ወገኖች መካከል ከሰፈረ በኋላ ግን ጦርነቱ ለጊዜው ጋብ ብሏል:: ሆኖም ሁለቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች - ማለትም የህወሃት እና ብአዴን አመራሮች ውስጥ ውስጡን እየተናቆሩ ናቸው::

መሳይና ፋሲል ታገቱ (ሄኖክ የሺጥላ)

አገቱኒ የምትለውን የግዕዝ ቃል በመጀመሪያ በመዝሙረ ዳዊት ላይ ነው ያየሁዋት ፣ መዝሙር (3)፣ እንዲህ ነበር ሰንጠር ብላ የገባችው ።
ESAT-Eritrea-300x152ወተንሳእኩ እስመ እግዚያብሔር አንስአኒ
አይፈርህ እመ አእላፍ ሕዝብ
ዕለ አገቱኒ ወቆሙ ላዕሌየ ።
ትርጉሙም ….
እግዚያብሔር አንቅቶኛልና እና ነቃሁ
ከአእላፍ ሕዝብ ከከበቡኝም አልፈራም ።
ስለዚህ ( አገቱኒ =ከከበቡኝም ) ማለት ይሆናል ። መያዝም አቻ ቃል ነው ።
ከዚያ ወዲያ ታዋቂው ቦጠሊቀኛ ፣ መምህር ፣ ተመራማሪ ፣ እኔ ደሞ ነብሴ እስኪጠፋ የምወዳቸው ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ለ መጽሃፋቸው አርዕስት አድርገውት ። አዎ አገቱኒ እና መታገት መንፈሳቸውን አንድ ያደረጉልኝ መሳይ መኮንንና ፋሲል የኔ-ዓለም ናቸው ። በመታገት !መስይና ፋሲል ግን ዛሬ መታገታቸውን አብስረዋል ።

Thursday, January 8, 2015

Meron Getinet አትሂድ እና Girum Zenebe Suraphel Wondimu “ሃገሬን በ


መታረም የሚገባዉ ማነዉ? ርዕዮት አለሙ ከቃሊቲ እስር ቤት

በግል የህትመት ዉጤቶች አማካኝነት በሀገሬ ዉስጥ የምመለከታቸዉን ችግሮች ለህዝብ ማቅረብና እንደዜጋም መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸዉን ሀሳቦች መጠቆም ከጀመርኩ አምስት አመታት አለፉ፡፡ የመጀመሪያ ፅሑፌን ያዘጋጀሁት ” “ስህተቶችን” ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶችና የስህተት ማረሚያ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ እንደነበረ አስታዉሳለሁ፡፡ በዚህም ፅሑፍ የፕሬስ፣የፖለቲካፓርቲዎች ምዝገባና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የተመለከቱ አዋጆች የወጡበት ምክንያትና እንደሀገር የሚያሳድሩትን ተፅእኖ ለመዳሰስ ብሎም ኢህአዴግ ከስህተቶቹ እንዲታረም ለመምከር ሞክሬያለሁ፡፡
የኢህአዴግ ሰዎች በአንድ የገዢዉ ፓርቲ ልሳን በሆነ ድረገፅ አማካኝነት የማስጠንቀቂያ ይዘት ያለዉ ምላሽ መስጠት የጀመሩት ከላይ ከጠቀስኩት የመጀመሪያ ፅሁፌ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በአዲስፕሬስ ጋዜጣ ላይ በአዘጋጅነት ተቀጥሬ መስራት ስጀምር ግን ሁኔታዉ እየባሰ መጣ፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም አዳማ ላይ ከተለያዩ ሚዲያዎች ለተዉጣጣን ጋዜጠኞች የሰጠዉን ስልጠና ከተካፈልኩ በኋል ከስልጠናዉ ጋር በተያያዘ ለህትመት ያበቃሁት ፅሁፍ ኢህአዴጎችን በእጅጉ አስቆጣቸዉ፡፡ በመሆኑም ወደቢሮአችን ተደዉሎ ከኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የተደወለ መሆኑ ከተገለፀ በኋላ ለጽሑፌ ምላሽ የላኩ በመሆኑ በፍጥነነት እንድናወጣዉ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጠን፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ ነው ወይስ የኋሊት ጉዞ እያሳየ ነው?

የህዝቡስ ኑሮ ተሻሽሏል ወይ? ወይስ ጥቂቶች የደለቡበት ሁኔታ ነው የሚታየው?

arrows-up-down


ዶ/ር ዳንኤል ተፈራና ዶ/ር ፀሀይ ለኢሳት ጋዜጠኛ ለአቶ ፋሲል የኔ ዓለም ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ለሰጧቸው መልሶች የቀረበ አስተያየት ከፈቃዱ በቀለ
መግቢያ
በቅርቡ ሁለት በአሜሪካን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኢኮኖሚስቶችን የኢሳት የቴሊቪዝን ጋዜጠኛ የሆነው አቶ ፋሲል የኔ ዓለም ኢትዮጵያ ከውጭ የምትበደረው ብድር መጠን እያደገ ስለመምጣቱና ስለኢኮኖሚው አጠቃላይ ሁኔታ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በመጋበዝ በመሰላቸውና በሚታያቸው፣ እንዲሁም ከተማሩት የኢኮኖሚ ትምህርት አንፃርና ከዕምነታቸው በመነሳት ለተደረገላቸው ጥያቄ አስተያየት ለመስጠት ሞክረዋል። ፕሮፊሰር ዳንኤል ዕዳንንም ሆነ፣ የሚሰሩትን ፕሮጅክቶች ወደ ፊት ሊገኝ ከሚችለው ውጤትና አትኩሮ ቅድሚያ መስጠት የሚገባውን፣ ነገር ግን የሚታለፈው አንገብጋቤ ጥያቄ ሊያስከትል የሚችለውን  አሉታዊ ውጤት በንጽጽር መልክ ለማሳየት ሲሞክር፣ ዶ/ር ፀሀይ ደግሞ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ቢሰሩ ጥቅማቸው እንደሚያመዝንና ለዕድገትም አስፈላጊ መሆናቸውን ለማመልከት ሞክሯል።

Wednesday, January 7, 2015

ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን!!!

በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የፌደራል ፓሊስ በእሁድ ታህሣሥ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አቅርቦት ነበር። ይህ የ10 ደቂቃዎች ምስል ለቁጥር በሚያታክት ብዛት ተቆራርጦ የተቀጣጠለ በመሆኑ አቶ አንዳርጋቸው ምን ተጠይቆ ምን እንደመለሰ ማወቅ አይቻልም። ስለሆነም በንግግሩ ይዘት ላይ አስተያየት መስጠት ይናገረው አይናገረው በአልታወቀ ጉዳይ ማብራሪያ መስጠት ይሆናል።  ስለዚህም፣ በንግግሩ ይዘት ላይ ጊዜ ከማጥፋት ህወሓት አንዳርጋቸው ጽጌን አሁን ማቅረብ ለምን እንደፈለገ መተንተን ይበልጥ ጠቀሜታ  አለው ብሎ ግንቦት 7 ያምናል።
አሁን ህወሓት በውስጥም በውጭም ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባበት ጊዜ ነው፤ በራሱ በድርጅቱ ውስጥም ሰላም የለም። ህወሓት የትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር እንደሆነ አድርጎ በመቁጠር መላዋን ኢትዮጵያን ለመዝረፍና ለማጥቃት እንደ መንደርደሪያ፤ በሌላኛው የኢትዮጵያ ክፍል ተቃውሞ ሲበዛበት ደግሞ እንደ መደበቂያ ዋሻ ሲጠቀምበት የነበረው ጊዜ አብቅቶ የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ ማመጹ በግልጽ በተግባር እየታየ ነው። በርካታ የትግራይ ልጆች በህወሓት ላይ ነፍጥ አንስተዋል፤ ከፊሎቹ ደግሞ በሰላማዊ ትግል ህወሓትን ማስወገድ ይቻላል ብለው በክልላቸውም ከክልላቸውም ውጭ ከህወሓት ጋር ፍልሚያ ገጥመዋል። ህወሓት መሠረቴ ነው ከሚለው የትግራይ ክልል ፈጽሞ ሊነቀል የሚችል መሆኑ ግልጽ ምልክቶች እየታዩ ነው። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ከትግራይና ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያገናኘው የአማርኛና የትግርኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም መጀመሩ የህወሓት ሹማምንትን ናላ ያዞረ እርምጃ ሆኗል።

Tuesday, January 6, 2015

የምርጫ ቦርድ ምክትል ሃላፊ አንድነትን እና መኢአድ በምርጫው መሳተፍ እንደማይችሉ ገለጹ

የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ፣ አንድነት እና መኢአድ በምርጫ እንዳይሳተፉ መታገዳቸውን ለፋና ራዲዮ ገለጹ። የአንድነት አመራሮች ወደ ምርጫ ቦርድ ሄደው የምርጫ ቦርድን ዉሳኔ በጠየቁ ጊዜ ቦርዱ ነገ ማክሰኞ እንደሚሰበሰብና ቦርዱ እንደሚወስን ቢነገራቸውም፣ ቦርዱ ሳይሰበሰብ ምክትል ሃላፊው፣ ቀደመው በራዲዮ፣ የመኢአድ እና የአንድነት ፓርቲ እንደይሳተፉ መግለጻቸው፣ ከወዲሁ በሕወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ የተወሰነና ተግባራዊ የሚሆነው ይሄ ዉሳኔ ይሆናል በሚል እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ።

ከሬዲዮና ከቴሌቪዥን በተጨማሪ ድረገፆችን ለመቆጣጠር አዲስ ህግ ተዘጋጀ

በኢንተርኔት የሚሰራጩ ፅሁፎችን, ምስሎችንና ቪዲዮዎችን ለመቆጣጠር ታስቧል 
የግል የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈርሰው ከመንግስት ቻናል እንዲከራዩ ለማድረግ ታቅዷል

የሬዲዮና የቴሌቪዥን ስርጭቶችን ለመቆጣጠር ከስምንት ዓመት በፊት በታወጀው ህግ ላይ አዳዲስ ቁጥጥሮችን የሚጨምርና እንዲሁም የኢንተርኔት ስርጭቶችንና ድረገፆችን የሚያካትት ህግ ተዘጋጀ.
ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ጋር ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ውይይት የተካሄደበት ረቂቅ ህግ , ነባሩ አዋጅ ውስጥ የሰፈሩ የባለቤትነትና የፈቃድ አሰጣጥ ቁጥጥሮችን የሚዘረዝር ሲሆን; በኩባንያ መልክ እንጂ በግለሰብ የሬዲዮ ወይም የቴሌቪዥን ድርጅት ማቋቋም እንደማይቻል ይጠቅሳል. የዝምድና ወይም የጋብቻ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ለብቻቸው ባለአክሲዮን የሆኑበት ኩባንያ ፈቃድ እንደማይገኝም ተደንግጓል.

ስንቴ፣ በስንቱ እንታለላለን? - በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

ከብዙ ዓመታት በፊት ሪፖርተር ጋዜጣ የኢሳይያስ አፈወርቂና የድርጅቱ አቀንቃኝ ነበረ፤ ዛሬ ከሌሎች ብዙዎች ጋር በመቃብር ውስጥ ያለው የመጀመሪያው የሪፖርተር መጽሔት በሙሉ ውዳሴ ኢሳይያስ አፈወርቂ ነበር፤ የሞተው መለስ ዜናዊ እያለ የሪፖርተር መጽሔት ኢሳይያስን በመጀመሪያ እትሙ ሲያወድስ ነበር፤ በቅርቡ ደግሞ ደፋሩ የወያኔ አባት ስብሐት ነጋ ለኤርትራ ያለውን ልዩ ፍቅር በሚያስገርም ሁኔታ ገልጾ ነበር፤ ለኤርትራ ቆመን እንዋጋለን አስከማለት ደርሶ ነበር፤ መለስ ዜናዊ በልዩ ጥበቡ መጀመሪያ ኤርትራን ባዕድ አደረገ፤ ቀጥሎም ጠላት አደረገ፤ ክፉ ጦርነት ተደረገ፤ በጦርነቱ ያሸነፈ የለም፤ በፍርድ ግን ኤርትራ አሸነፈች ተባለ፤ ፍርዱ ዋጋ-ቢስ ቦሆንም!

Monday, January 5, 2015

የግንቦት 7 ሕዝብ ግንኙነት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ስለ አዲሱ የአንዳርጋቸው ቪዲዮ ተናገሩ (ያድምጡ)

የግንቦት 7 ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ የ ዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ የህወሓት አገዛዝ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ያሰራጨውን ፊልም ጉዳይ በተመለከተ ከህብር ሬዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል:: ያዳምጡት::

< ...በአንዳርጋቸው ላይ የተለያዩ የፕሮፖጋንዳ ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩ አስቀድመን አውቀናል ።በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደተናገረ ይታወቃል። ይሄኛው ቪዲዮ ከዚህ ቀደም አገዛዙ ካሳያቸው ሁሉ መናኛ ነው አስገድደው እንደሚያናግሩት የታወቀ ነው።ይሄ ስርዓት በሰቆቃ የተገነባ ነው...የኢትዮጵያ ሕዝብ ከግንቦት ሰባት እና አብረውት ከሚሰሩት ሁሉ የሚጠብቀው ነገር አለ። የትግላችን የመጨረሻ እርምጃ ላይ ደርሷል...ለጠላታችን ግን መጣንልህ ...>>

ዛሬ የወያኔው ፖሊስ ስለለቀቀው የአንዳርጋቸው ጽጌ አዲስ ቪድዮ ዙሪያ የተሰጡ አስተያየቶች

የሕወሓት አስተዳደር ፖሊስ ዛሬ ስለአንዳርጋቸው አዲስ ቪድዮ ለቋል:: በየሶሻል ሚዲያዎችም መነጋገሪያ ሆኗል:: በዚህ ዙሪያ ከሶሻል ሚዲያዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ስለቪድዮው ሰብስበናል ያንብቧቸው:-
andargacew Tsige
የጆሜክስ ካሳዬ አስተያየት:-
ሌባና ፖሊስ የሚባለው የገዢው አገልጋይ የሆነው የፌዴራል ፖሊስ ፕሮግራም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ቪዲዮ በማሳየት አሜሪካን የሚያስንቅ የምርመራ ሥልት አለን እንደ ሌባ ሻይ ሳንገርፋቸው ይናዘዛሉ በማለት የድፍረቱን (የድድብናውን) ልክ ሊያሳየን ሞክሯል፣ ይህ መራር ቀልድ በአስቀያሚ የማዕከላዊ ምርመራ ሂደት ውስጥ ያለፉትንና ቶርቸርን ያስተናገዱት ጓደኞቼን ሳስብ ድፍረቱ አሳምሞኛል ፤ጓደኞቼም በማዕከላዊ ቆይታቸው የታዘቡት ጥፍራቸው የተነቀለባቸውን ተማሪዎች ሳስብ እነዚህን መርማሪዎች እና ጋዜጠኞች በፍትህ አደባባይ አገኛቸው ዘንድ ዘወትር እናፍቃለሁ፤
ፕሮግራሙ አሜሪካን ሊያብጠለጥል የፈለገበት እና የጠቀሰወው ሰሞነኛው የቶርች ሪፖርት ኢትዮጵያም ተሳታፊ መሆኗን እንዳጋለጠ ዘንግተውት ይሆን ብዬ አልጠይቅም አንዴ ምንም አያመጡም አያውቁም ተብለን ተንቀናልና (ሕዝብን ከመናቅ ካለሆነ ከምን ይመነጫል?)፡፡

Sunday, January 4, 2015

“እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም” አብርሃ ደስታ

“እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም” አብርሃ ደስታ

"በሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሰው ማሳበድ ይፈልጋሉ" ኦኬሎ አኳይ
abraha and okello


ከቂሊንጦ እስር ቤት ከሚገኙት መካከል የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አብርሃ ደስታና የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ኦኬሎ አኳይ፣ ስለ እስራቸው ሁኔታ እንዲህ ይላሉ:: በቅድሚያ አብርሃ ደስታ:-

Thursday, January 1, 2015

ወያኔ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ የህዝቡን ሰላም ለማደፍረስ ስለሚያደርገው እንቅስቃሴ›› መረጃ ስጡኝ በሚል ለህዝቡ ቅጽ እያደለ ነው

(ነገረ ኢትዮጵያ) የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› መረጃ እንዲሰጡት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅጽ እያከፋፈለ መሆኑ ታወቀ፡፡
ምንም እንኳ በቅጹ ላይ ዜጎች ስለ ሰማያዊ ‹‹ጥሩና መጥፎ›› አስተያየት እንዲሰጡ ቢልም መጀመሪያ ላይ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› ሲል ፓርቲው የህዝብን ሰላም እያደፈረሰ ነው ሲል ፈርጆታል፡፡
ቅጹ ከተሰጣቸው መካከልም አንድ የኮልፌ ቀራኒዮ ነዋሪ ቅጹን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ሲል ለኢትዮ ምህዳር የላከ ሲሆን ‹‹ይህንን አስገራሚ ቅጽ እንድንሞላ በአንድ ክ/ከተማ በተገኘንበት ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢው ሁሉ ታደለ፡፡ ታዲያ ሁሉም ቅጹን ወስዶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ እኔም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ለጋዜጣችሁ ዝግጅት ክፍል ልኬዋለሁ፡፡ አይገርምም ሕገ-መንግስት የሚፈቅደው ሰላማዊ ሰልፍ አንቀጽ በመንግስት አስፈጻሚዎች ሲጣስ›› በሚል አስተያየታቸውን አስፍረዋል፡፡