Translate

Monday, November 4, 2013

የሀይሉ አማራጭ፣ የኤርትራ ድጋፍና ተቃውሞው

ከዳኮታ ጥናት መአከል

የኛ ነግር መልሶ መላልሶ ሆኗል። በገራችን አቆጣጠር በ1960ዎቹ የተማሩና የነቁ ወጣቶች አቢዮት ማካሄድ በጀመሩ ጊዜ የተነሱ ልዩነቶች አንዳንዴ ቅርጻቸውን በመጠኑ ይቀይሩ ይሆናል እንጂ ዛሬም ድረስ ባንድ ወይ በሌላ በኩል  የልዩነትና የፍዳችን ምንጭ ሆነው ቀጥለዋል። እነዚህ ልዩነቶች  መረቀቂያዎች፤ መጣያያዎች ቢያመች መገዳዳያዎቻችን ናቸው።   ችግር የሆነው ጎራ ለይተው በነበሩ ፖለቲከኛች  የሀሳብ ልዩነቶቹ መፈጠራቸው ወይ መኖራቸው አልነበረም። ወይ ልዩነት የተፈጠሩባቸው አገራዊ ቁም ነገሮች ስህተተኛነትና ወይ አላስፈላጊነት ኖራቸው አይደለም። ትናንትናም ሆነ ዛሬ ምንአልባትም ነገም ችግር የሚሆነው  ምንም አይነት ልዩነት ላይ በረጋ ሁኔታ መነጋገር፤ ልዩነትን ማቻቻል፤ አብሮ የሚያሰራና በጋራ የሚያታግል  ማድረግ አለመቻሉ ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ ችግር ከአርባ አመታት በሗላም ያሳየው  መሻሻል እዚህ ግባ የማይባል ነው። ዛሬም ድረስ ቡድንም ሆነ ግለሰብ ልዩነት ታየበት ማለት አለቀ ጠላት አድርገው የሚፈርጁ ፖለቲከኞችና ድርጅቶች በገፍ አሉን። ያኔ ትግሉን በዋናናት የመሩትና ፖለቲካውን የተወኑት ዛሬም ወሳኔ ሰጪዎች በሆኑበት እዚህ ችግር ውስጥ መዳከራችን ብዙም አይገርምም።

ያኔ አስገራሚ ከነበሩት ልዬነቶች አንዱ በከተማ በሚኖር ህዝባዊ አመፅ እና ከገጠር ከሚጀምር የሀይል አማራጭ  የሚለው የትግል አማራጮች ላይ የነበረው ልዩነት ዋንኛው ነው። አስገራሚ የሚያደርግው መራር የሆነ ትግል ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ደርግን አይነት ሀይል አስቀምጠው በትግል አይነት ልዩነት ምክንያት መተባበር ሳይችሉ ቀርተዋል።  ይባስ ብለው ከሌሎች ጋር አይደለም የድርጅት አንድነታቸውን መጠበቅ እንኳ አቅቷቸው  የተነሱበትን አላማ ከግብ ሳያደርሱ መቅረታቸው  ነው።
ዛሬም በተመሳሳይ ትንሽ የቅርፅ ልዩነት አድርጎ  የሀይሉ አማራጭ ወይ የህዝባዊ እንቢተኝነት ያካተተ የሰላማዊ ትግል የሚሉት ሁለት አማራጮች የልዩነት መሰረቶቻችን ሆነዋል። በእርግጥም እነዚህ የትግል አማራጮች መሰረታዊ የሆነ ልዩነት አላቸው። ወዲያም ብናደርገው ወዲህ ግን ሁለቱም የትግል አይነት ናቸው። ትግሎች ናቸው። ሁለቱም መራር የሆነ መሰዋትነት የሚያስከፍሉ ናቸው። ዛሬ ከደርጉም የባሰ ፈላጭ ቆራጭ ለአገርና ለህዝብ ደንታ የሌለው ሀይል አናታችን ላይ እየጨፈረ ባለበት ሁኔታ በድጋሚ የትግል አይነት ልዩነት ሰማይ እሲከነካ ሲጮህ መስማታና በመረረ  ስሜት አንዱ ሌላውን ሲቃወም ማየት በእጅጉ የሚያሳዝን ነው።
ያኔም ሆነ ዛሬ  ትግል ያስፈልጋል ላለ፤ ሊታገል ለቆረጠ አካል የትግል አማራጮች ላይ የሚነሱ  ልዩነቶች ጎራ ለመለየትና ለመቆራቆዧነት ያላቸው ጠቀሜታ ስለተፈለገ እንጂ የማይቀናጁ፤ የማይደጋገፉ፤ ሊተባበር የማይችል ወይ መጨረሻ ላይ የሚያስገኙትን ውጤት ተመሳሳይና የሚጠቅም እንዲሁም ሁሉ የሚስማማበት ማድረግ ስለማይቻል አልነበረም። ዛሬም ቢሆን በጭራሽ አይደለም።
እዚህ ላይ ዛሬ ያለን ልዩነት ወይ የምናቀርበው ተቃውሞ ለምን የሀይሉን አማራጭ ምርጫ ተደረገ የሚል አይደለም። ለምን? መነሻውን ኤርትራ አደረገ የሚል ነው።  ይህ ማስቀየስ ነው የሚለ መከራከሪያ መነሳቱ አይቀርም። አጢኖ ለተከታተለው ግን የሀይሉ አማራጭ ላይ የሚነሱ ተቃውሞዎች  የመሳርያውን ትግል እናዳታደርጉ የሚሉ ሆነው በተጨማሪ ሌሎች  ምክንያቶች የሚጨመሩበት ነው። ምን  ሲደረግ ከኤርትራ የሚለው  በቀላሉ መጮህ የሚችልና ለልዩነትና ለመቆራቆዣ የተሻለ ስለሚሰራ አገልግሎት ላይ የዋለ የሚመስልበት ሁኔታ ነው ያለው።  የዚህ ፅሁፍ አላማም ወናው መቆራቆዣ ምክንያት እንዳልሆነ ብናውቅም ለምን ከኤርትራ የሚለው ላይ የሚታየንን ለማለት ነው።
ካነሳን አይቀር  ግን በተለያየ ጊዜ ሁሉንም አይነት የትግል አይነቶች ላይ የሚነሱ ተቃውሞዎችን በተመለከተ ሞግተናል። የሀይሉን አማራጭ  ወይ ለምን መሰረቱን ከኤርትራ አደረገ በሚል ሲነሱ የነበሩ ተቃውሞዎችን ስንሞግት የመጀመርያችን አይደለም። ከዚህ ቀደም የአርበኞች ግንባርን የትግል ምርጫ በመደገፍ የተነሳውን ተቃውሞ ትክክል አይደለም፤ አይጠቅምም፤ በበቂ ምክንያታዊም አይደለም ብለናል። የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሰላማዊና ህጋዊ ትግሉን ሲያጣጥልና አይሰራም ሲል ነበር።   በጊዜው ትከክል አይደለም አይጠቅምም ብለናል። በነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም አገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶች በምርጫ ለመሳተፍ ሞመከራቸውንም ጨምሮ። የህዝባዊ አመፁ አይሰራም ለማለት ምክንያት ሲደረድሩና ሲቃወሙ የነበሩ እንደነበሩ አንባቢ ያስታውሳል። ዛሬ የሚሞቱለት ይህ የትግል አይነት ነው!!። አሁን ደግሞ  የፖለቲካውን ድባብ ሞልቶ ያለው የሀይሉ አማራጭ አይሰራም የሚለው ጩህት ነው።
ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ ከሀይሉ አማራጭ ውጪ ያሉት የበዙት የትግል ሙከራዎች  ዜጎች ዝም ማለቱ አላስችል ሲላቸውና ምሬቱ ሲበዛባቸው በራስ አነሳሽነት የሚየደርጓቸው ናቸው ማለት ይቻላል። በእርግጥ በአገር ውስጥ በሚገርም ሁኔታ አሁን ላይ ተቀይሯል። በውጪ ቀድሞ በታቀደና ስረአት በያዘ መንገድ  በድርጅቶች የሚመራን ትግል ላሁኑ የቅንጦት ነው ብለን  እንተወው። አንዳቸውም አይነት እስካሁን የተደረጉ ትግሎች  ያለ ትችት፤ ማንቋሸሽና  አይሰራም ትንታኔ ሳይቀርባባቸው የተሞከሩ ግን አይደሉም።  ሰላማዊና ህጋዊ ትግል ማድረግ መሞዳመድ ነው። ያላግባብ የታሰሩ ይፈቱ ብሎ መሰለፍ  ከብትነት ሆኖ እበት ላይ መጮህ ተደርጎ ይገለፃል። የሻማ መብራት ማድረግ ፊርማ ማሰባሰብ ልመና ነው። ህዝባዊ እንቢተኛነት ማሰብ ህዘብን ማስጨረስና አገር ለማፈራራስ ነው። መፃፍ መቸከችክ ነው። ተሰባስቦ ስላገር ጉዳይ መምከር ስራ ፈትነት ነው። የመሰራያውን ትግል የሚሞክር ሁሉ  ነገ አንባገነን ለመሆን ስለፈለጉ ነው። ማቆሚያ የለውም።
እነዚህን አይነት ቅጥ አንባራቸው የጠፋ ተቃውሞዎችን በተደጋጋሚ በመሞገት የየድርጅቶቹን  በየትግል አይነቶቹ ላይ በየጊዜው የተያዙ አቋሞች፤ ለዚህ የሚደረደሯቸውን ምክንያቶችን ባዶነት፤ ተቃውሞው የሚቀርብበትን የመረረ ስሜት  አያይዘን  ስንመለከት እኛ እየታየን ያለው ስእል አስፈሪ ነው። በእርግጥ ይህ ጉዳይ  ፖለቲካው አካባቢ ተሰሚና ተፅኖ አድራጊ ግለሰቦችንና  አንዳንድ ስብስቦችንም ይመለከታል።  በተናጠል በተለያየ ጊዜ በተሞከሩ የትግል አይነቶች ላይ ሁሉ የተያዙ አቋሞችን ተከታትለን አደራጅተን  ደምረን የመጨረሻ ውጤታቸውን ስናሰላ የደረስንበት ውጤት ያንዳንዶቹ ” አትታገሉ” የሚመስልበት ሁኔታ አለ። እውነትነት የለውም  ያለ ዜጋ ካዛሬ ጀምሮ መከታታል  ይችላል። በኛ እምነት እስከዛሬም ይህ ችግር ግልፅ ብሎ ያልታየው ሁሌም ያንዱ የትግል አይነት  ተቃዋሚ ሲሆኑ ለአፍ የሌላው አይነት የትግል አይነት ወና ደጋፊ ስለሚሆኑ ብቻ ነው። ባንዱም ላይ  ፅናት ያለው አቋምና ትግል ሲያካሂድ ግን አይታይም። ሰላሳመዊ ትግል ላይ ሲወራ የመሳርያ ትግል ደጋፊ ይሆናሉ። ስለ ፊርማ ማሰባሰብ ሲነሳ ወጥቶ ጉርባ ለጉርባ መተናነቅ ነው የምን ፊርማ ነው  አቋም ይሆናል።  ስለሰላማዊ እንቢተኛነት ትግል ሲነሳ፤ በኢትዮጵያ ሁኔታ አይሰራም  ብለው መፀሀፍ ሊወጣው የሚችል ምክንያት ይደረድራሉ። እነዚህ አይነት ሁኔታዎችን ስለምናውቅ ነው ምን ሲደረግ ከኤርትራ  የሚለው ተቃውሞ ላማጮህ ቀላል ስለሆነ የተመረጠ ሆኖ የሚሰማን።
ምን ሲደረግ ከኤርትራ?።
መሰረቱን ኤርትራ ያደረገውን የመሳርያ ትግል አምርረው እየተቃወሙ ያሉ ክፍሎች የሚያነሷቸውን መከራሪያዎች ጠቅለል አደርጎ በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል።
1-አንድነቷ የተጠበቀ ጠንካራ ኢትዮጵያ እንድትኖር የኤርትራ( የሻቢያ) መንግስት አይፈለግም ወይ ሊፈልግ አይችልም።
ኤርትራ የኢትዮጵያ አንድ ክፍለ ሀገር ነበረች።ትርጉም የሚሰጡ ልዬነቶች ማውጣት በሚያስቸግርና  ሁለንተናዊ ሊባል በሚችል አንድ አይነት ህዝቦች  ነን።  ይህን መካድ   ቢቻልም መደበቅ አይቻልም።  እዚህ ታሪካዊ ሁኔታ ላይ የደረስነው ግን መራራ ከሆነ ጦርነትና ሰላም ማጣት በዛም በዚህም ወገን ቁጥሩ ስፍር የሌላቸው ዜጎች አልቀው ነው። ይህ መራራ ጦርነት የቆየ ታሪክ አይደለም። ዛሬ በሂወት ያለና ለማገነዛብ የደረሰ  የበዛው  ኢትዮጵያዊም ሆነ ኤርትራዊ ዜጋ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ በዚህ ሂደት አብዝቶ ተጎድቶበት ነው። ጠቅላላ ሂደቱንም ጠንቅቆ ያውቃል። ቁስሉንና መጎዳቱን ለመጠገን  ያላሰለሰ ስራን ብቻ ስይሆን ጊዜን የሚፈልግ ችግር ነው።
ባጠቃላይ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጉዳይ መጥፋት የሚችለው የመጨረሻ ደረጃ ድረስ ጠፍቷል። መልካም ግንኙነታችንና አንድነታችን ሊጎዳ የሚችለው ደረጃ ድረስ ተጎድቷል።  በብዙ ውጫዊም ሆነ ሀገራዊ ስህተቶችና ተፅኖዎች ኤርትራ ዛሬ እራሷን የቻለች ነፃ አገር ሆናለች። ለዚህ ታላቅ አገራዊ ጥፋት በተዋረድ ባለድርሻዎች ብዙ ቢሆኑም  በአጥፊነት ዛሬ ቀጥቅጦ እየገዛን ያለውና እንግዳ የሆነ  የመንግስት ባህሪ ያለው የወያኔ ስርአት ባለ ትልቁ ደርሻ ነው። ከሂደቱም ከየትኛውም ወገን በተለየ  ዛሬም ድረስ በሁሉም ዘርፍ እያተረፈበትና ስልጣን ለመቀጠል እየተጠቀመበት ያለውም ይህ ክፍል ነው።
ለነጻነት መራራ ትግል ያካሄደው የኤርትራ ነጻ አውጪ አላማውን አሳክቶ ዛሬ ነጻ አገር መስርቷል።  እንደውም የኤርትራ መንግስት ነው። አደራጅቶ ረድቶ አዲስ አበባ ያስገባው አካል ጋር ከቢፊቱ በባሰ የመረረ ጦርነት ውስጥ በድጋሚ ገብተው ዛሬ ፀበኞች ናቸው። በመሬት ላይ ያሉና በቀላሉ የሚታዩ እነዚህን የመሰሉ ብዙ ሁኔታዎችን ለሚያወቅ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በእርግጥም የኤርትራ መንግስት አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማየት ይፈልጋል ብሎ ለመቀበል የሚከብድ  ነው። ይፈልጋል  ብሎ መከራከሩም በጭራሽ  ቀላል አይሆንም። እኛም ይፈልጋል ብለን አንከራከርም።  ነግር ግን በተጨባጭ መሬት ላይ ወርደው እዚህ ጉዳይ ላይ ለመስራት ከሞከሩ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ከምንስማው ምስክርነት  የኤርትራ መንግስት አይፈልግም ብሎ በሙሉ ልብ ደፍሮ ለመናገምር የሚቻልም አይመስለንም። ያም ሆነ ይህ ግን ትግሉ ላይ እርዳታን መቀበል አለመቀበል እንደየ ድርጅቶቹ አቋም ሊያካሂዱት እንደሚያስቡት ትግልና ትግሉን እንደሚያካሂዱበት ጠቅላላ ሆኔታ  ሊለያይ ይችላል። ለማንኛውም አይነት ኢትዮጵያዊ ድርጅት ግን በነዚህ ሁሉ ችግሮች ውስጥ ከኤርትራ መንግስትና ህዘብ ጋር  ግንኙነት አያስፈልግም ማለት ቅሽምና ነው። ያላሰለሰ ግኑኙነት፤ የተቻለወን ያህል መቀራረብና ተሰታፎ ሁሌም መኖር አለበት።
እኛ የምናቀርበው  መከራከርያ እየደረሰብን ያለው ጭቆናና መበደል አምርሮ ለመታገል በቂ ምክንያት ነው። በመሳርያ የሚደረግንም ትግል ይሻል። ወይ የሀይሉን አማራጭ  እንደ አንድ የትግል አማራጭ ያካትታል የሚለውን መነሻ ያደርጋል።  ከዚህም ላይ ተነስቶ  ከላይ የተነሳውን ጥያቄ አገላባብጦ በመጠየቅ ይጀምራል።  የኤርትራ{የሻቢያ} መንግስት  ሲጀመር መፈለግ አለበት ወይ?። አንድነቷ የተጠበቀ ጠንካራና የበለጸገች ኢትዮጵያ እንድትኖር መፈለግና መታገል የማን ሀላፊነት ነው?። እንዴት ነው የኤርትራ መንግስት ወይ የኢሳያስ ሀላፊነት የሆነው?። በተመሳሳይ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታና ትግሉን በምናካሂድበት ነባራዊ ሁኔታ ትግሉ ላይ ከኤርትራ  እገዛን ለማግኘት የኤርትራ መንግስት  አንድነቷ የተጠበቀና ጠንካራ አገር እንድትሆን መፈለጉ ቅድመ ሁኔታ መሆን አለበት ወይ?። እርዳታውን ነው የምንፈልገው ወይስ እኛ ላገራችን ያለን እርአይ ወይ ፍላጎት ላይ ተገዥነቱንና መስማማቱን ማሳየቱን ነው?
አሁን እንደሚታየው ለመታገል ለቆረጠ ለማንኛውም ክፍል የሚቻለውን እገዛ ለማድረግ የኤርትራ መንግስት ፍቃደኛ ነው። የቆረጡ ድርጅቶች ያገኙትን እድል ተጠቅመው እየሞከሩ ነው። እነሱ ሲያማርሩ አልሰማንም። በተመሳሳይ የተከፈተውን እድል እንጠቀም  ብለው የተከለከሉ ኢትዬጵያዊ ድርጅቶች የሉም። ወይ አለን ሲሉ አልሰማንም። የብዙዎቹ ድርጅቶች የእስከቅርብ ጊዜ የትግል  ምርጫ የሁለገብ  ትግል ነው። ሁለገብ ትግል የሀይሉንም አማራጭ ይጨምራል። ታዲያ አይደለም በሀይሉ አማራጭ ለሚታገል የህዝባዊ እንቢተኛነቱም ሆነ ለሰላማዊ ታጋይ  እገዛን ለመቀበል በሚያመቸው ሁኔታ ሆኖ ከኤርትራ ነው ብሎ ድጋፍን መግፋቱ ተገቢ ነው ወይ?።
ሌሎች አማራጮችስ ኖረው ቢሆን ከኤርትራ በኩል የተዘረጋው የእርዳታ እጅ ለምን ይገፋል?። የሚሻለው ዝም ብሎ አሜሪካና አውሮፓ መሰረትን አድርጎ እስከሁን ያደረግነውን አይነት የምንፈልገውን ውጤት በፈለግነው ፍጥነትና ጥራት ሊያመጣ የማይችል ትግል ስናደርግ መቀጠል ነው ወይ? ። አንድነቷ የተጠበቀ ጠንካራ ዲሞክራሲያዊት አገር እንድትኖረን አይደለም ትግሉ ላይ ሊያግዙንስ   የሚፈልጉ አገሮች ባካባቢያችን ወይ በዚህ ጊዜ በአለም ላይስ አሉ ወይ?። እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን አውጥተን አብሮ መልስ ለመስጠት ከተሞከረ። እኛም ሆንን ማንኛውም ጥሩ አሳቢ ዜጋ ምን ሲደረግ ከኤርትራ የሚለውን  የኤርትራ መንግስት ላገራችን ቀና አመለካከት ላይኖረው ይችላልና ምንም አይነት እገዛውን እንግፋ የሚል ውሳኔ ላይ መደረስ በቀላሉ የሚቻለው አይመስለንም። ወይ ይህ ፖለቲካል ውሳኔ ትክክል ሆኖ ሊታየው አይችልም።
እውነት ለመናገር የደርግ መንግስት ስልጣን ላይ ቢሆን ምን ሲደረግ ከሻቢያ{ ከኤርትራ} የሚለው  ለውሳኔ ቀላል ነበር። ዛሬ ስልጣን ላይ ስላሉት የትግሬዎች መንግስት ስናወራ  ግን ሴጣናዊ ስለሆነ ጨፍጫፊነታቸው፤ ትናንት በአገራችን ሉአላዊነት ላይ ስለፈፀሙት ጥፋት ወይ በአብሮነታችን ላይ ስላጠፉት ጥፋት ብቻ  በጭራሽ አይደለም።  ተጠናክሮ ስለቀጠለ፤ ዛሬ በዚች ሰአት ነገም እንዲሁ በሚኖራቸው እድሜ ከፍፃሜ ለማድረስ ከጊዜ ጋር እየተሽቀዳደሙ እየፈጸሙ ስላሉት አገራዊ ጥፋት ነው። ባግባቡ አቅደውበት፤ ተዘጋጅተውበት አሰልስው እየሰሩበት ስላለ ግዙፍ የሆነ ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር የማጥፋት እኩይ ተግባር ነው። በቶሎ ልናስቆማቸው ካልቻልን ውጤቱ እጅግ አስፈሪ ስለሆነ በሗላ መፍትሄ እንፈልግለት ብንል እንኳ መፍትሄ ስሌለው ወይ በቀላሉ ልንሰራለት ስለማይቻለን እጅግ አሳሳቢ ስለሆነ አገራዊ ቸግር ነው የምናወራው።
ከኤርትራ በጭራሽ አይሆንም ተብሎ የሚደረደሩ ምክንያቶችን በሙሉ ትግሉ ላይ ሊያግዙን ፍቃደኛ ቢሆኑ ኖር ከኬንያ በስተቀር በምንጎራበታቸው አገራት ላይ በሙሉ ላይ ብንጠቀመው እንደወረደ በተሻለ ሁኔታ ምክንያታዊ የሚሆን ነው። ደቡብ ሱዳንንም ጨምሮ። ሁሉም እንደ ኤርትራ የኛ የሚሉትን ወስደው የጨረሱ አይደሉም። ሁሉም  የይጋባናል ጥያቄ አገራችን ላይ ገና  አላቸው። ብዙዎቹ ታሪካዊ የምንለውን የጠላትነት መስፈርትም ያሟላሉ።
2-  መሰረታቸውን ኤርትራ ያደረጉ ድርጅቶች አገራዊ ጥቅማችንን በማስጠበቅ ረገድ አናምናቸውም።
የዚህ ተቃውሞ የመጀመርያው መነሻ ኤርትራ የገቡ ድርጅቶችን ባህሪ የሚመለከት ነው። ዋና ምክንያት ብዙዎች ብሄር ተከል ናቸው የሚልነው። ያም ሆኖ ትግሉ ላይ አጋር ሊሆኑ ይገባቸው ከነበሩ ድርጅቶች እነዚህ ክፍሎች ላይ ከሚሰማው እጅግ ያየለና የመረረ ተቃውሞ የሚሰማው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ላይ ነው። አብዝቶ ተቃውሞ የሚሰማበት ግንቦት ሰባት አገር አቀፋዊ እንቅስቃሴ ነው። የብሄር ስብጥራቸው ከየትኛውም ድርጅት የተሻለና ብዙ አባላቶቹ ወጣቶችና  በአገራቸው ፍቅር የተቃጠሉ የአንድነት ስብስቦች ናቸው። የአርበኛ ግንባር አይነት አገር አቀፋዊ ድርጅቶችም ኤርትራ ውስጥ አሉ። ታዲያ አለመታመኑ ከየት የመጣ ነው።  መታመንን በተመለከተ ሌሎችን አይታመኑም ለማለት መጀመርያ እራስ መታመንስ አይፈልግም ወይ? ።  አገራዊ መታመን በበዙ ዘርፈ በበዛ አገራዊ ቁም ነገሮች የሚለካ ይመስለናል።   ለእራስ ጥሩ የመጠርያ ስም መስጠት ብቻ ታማኝ አያደርግም። ሌሎችንም ለመከሰስም የሞራል የበላይነት አይሰጥም። ሌላው ቢቀር በሁኑ ጊዜ በመጀመርያ የተሻል ከልሆነም በትንሹ እንኳ የትግል አስተዋፆ ማድረግና፤ የህዝብንም ትግል ማገዝንም  በደንብ ይፈልጋል።
በእርግጥ ይህን አይነቱ ተቃውሞ ለምን ከብሄር ከተደራጅ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ መስራት ጀመራችሁ በሚል  ቀድሞ ብሎም ሲቀርብ ነበር። ግንቦት ሰባቶች ኤርትራ  ቀድመው  ገብተው ከሚንቀሳቀሱ ብሄር ተከል ድርጅቶች ጋር በእርግጥም ትብብር ፈጥረዋል። ይህ በተሰላ ሁኔታ ትግሉን መሬት ላይ ካሉ ድርጅቶች ጋር አስተባብሮ በቶሎ አሸናፊ ለማድረግ ያለመ እርምጃ መሆኑን ማንም አይጠፋውም። ከዚህም ባለፈ ግን ይኖራል ብለን የምንሰጋው አደጋ ላይ ፖለቲካዊ  መፍትሄ እየሰሩ እየሄዱ እንዳለ  ነው የሚያሳየው። በኛ እምነት ይህን አይነቱ እርምጃ የመፍትሄ ድርጅት ያደርጋቸዋል። የ21ክፍለ ዘመን ፖለቲካ እንደገባቸው ያሳያል። የተሻለ መታመንን የሚያሰጥም ነው። በርግጥም አግኝተውበታል።  መታመን ለማግኘት ችግሩ እንዳለ እያወሩ ምንም አለማድረግ ወይ በሌሎች የሚደረግ ማንኛውንም ሙከራ ቁጭ ብሎ በመቃወም መቼም ሊሆን አይችልም። ወይ መፍትሄው በዛ በኩል በለየለት ጎራ የለየ ክፍል ባለበት እዚህ ጋር ደግሞ ሌላ ጎራ ፈጥሮ አዋራው እስኪጨስ መሬት መርገጥ አይደለም።  ለዘለቄታውም ፋይዳ ያለው ግዴለም ባዳራሽ እናድርገው ባይሆን ጠረቤዛ እየደበደብን ይሻላል የሚለው አቀራረብ ነው።
ሌላው ከመታመን ጋር ተያይዞ የሚነሳው ኤርትራን በሚመለከት ያልተቋጩ  ጉዳዮች አሉን የሚል ነው። በግልፅ ባይቀመጥም የአሰብና የባድሜ አይነት የይገባናል ጥያቄዎች ናቸው። እነዚህ ያብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የይገባናል ጥያቄዎች ናቸው። የኤርትራ መንግስትም ተቃዋሚዎችን ሲረዳ እነዚህ ጥያቄውች መኖራቸውን አያውቅም ማለት ደደብነት ነው። ጥያቄው ያለው  እነዚህ ንብረቶች ዛሬ በማን እጅ ነው ያሉት የሚለው ላይ ነው። ታዲያ በሱ ቁጥጥር ስር ባሉ ንብረቶች ከሚረዳቸው ተቃዋሚዎች ጋር በነዚህ አገራዊ ጥቅሞች ላይ ለምን እንደሚደራደር አይገባም። ወይ ኢትዮጵያችን ላይ ያለው አገዛዝ የሚቆረቆርላቸው ጉዳዮች አይደሉም። ስላአሰብ ወይ ሰለባድሜ ከሆነ የኤርትራ መንግስት እንቅልፍ ማጣት ከወያኔ የተሻለ መቼም አይመጣም። ለምን ሌላ ተቃዋሚ ማደራጀት አስፈለገው? ስላጣን ላይ ያለው አገዛዝ ይዛችሁ ጥርግ በሉ ተቃዋሚዎችን አታደራጁብን እንጂ ብሎ ለመታረቅ የሚለምን ጉደኛ ነው። ለዘነጉት ለማስታወስ ትግል የሚካሄደው ከዚህ ክፍል ጋር ነው።
ሲጀመር በነዚህም ጉዳዬች ላይ ሆነ በሌሎች አገራዊ ጥቅሞች ላይ ኤርትራ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ለመደራደራቸው ምንም መረጃ በለሌለበት ገና ለገና  ይደራደሩ ይሆናል በሚል የሚቀርብ ከባድ የሆነና ግዙፍ የሆነ የውሸት ውንጀላ ነው።  በሌላ በኩል ስልጣን ላይ ያለው የኤርትራ  መንግስት ከማንም በተሻለ ጫካ ውስጥ ትግል ላይ ተሆኖ ስለሚደረግ ስምምነት ጥሩ ተሞክሮ ያለው ይመስለናል። ለታሪክና ለመወቃቀሻ ካልሆነ የማይፀና ስምምነት መሆኑኑ አሳምሮ ያውቃል። ብዙ የዚህ አይነት ስምምነቶችን ከተለያዩ ክፍሎች ጋር አድርጎ ነው ዛሬ ለስልጣን የበቃው። ለዚህም ነው ቀድመው ከገቡም ሆነ ከግንቦት ሰባቶችን ለመርዳት ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠው። ወይ ድርድር ውስጥ ያልገባው።
ለማንኛውም ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ምስክር ልንሆን እስከምንችለው ሲመሰረት ጀምሮ በማንኛቸውም አይነት አገራዊ ጉዳዩች ላይ እኛ አይደለንም ሌሎችም ህዝባዊ ውክልና ከህዝብ እስካላገኙ በአገር ጥቅሞች ላይ ለመደራደር አይችሉም ብሎ በግልፅ አስቀምጦ የተነሳ ድርጅት ነው። እዚህ ጉዳይ ላይ ጤያቄዎቹ ተደጋግመው ሰለሚጠየቁ ይህንኑ አስረግጠው አቋማቸውን ግልፅ አድርገዋል። ከመብዛቱ የተነሳ ሊያደርጉት ያሰቡት ትግሉ ላይ  ጎጂ ይሆናል በሚል ለኛ እስኪታሰበን።
መሰዋትነቱ የበዛበትን ውጫዊ የሆነን እርዳታ በገፍ የሚፈልገውን የሀይሉን አማራጭ ምርጫው ላደረገ ድርጅት ስማቸውን የዘነጋናቸው አባት በዚህ ቁም ነገር ላይ አስተማሪ ምክር ሰጥተው ሰምተናል። እኚህ አባት ኢሳት ላይ ከሲሳይ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የተናገሩት  ቃል በቃል ባይሆንም እንዲህ አይነት መልክት ነበረው። እየው የዚህ አይነት ትግል ላይ ስትሆን  በመሳርያውም በብሩም የሚረዱህ ጋር ስትቀርብ አንተ ስለምትፈልገው አይደለም እነሱ ስለሚጠቀሙበትና መስማት ስለሚፈልጉት ነው አሰማምረህ ጨመር ጨመር አድርገህ  የምትነግራቸው የሚል ነበር። ከቃለ ምልልሳቸው የረጅም ጊዜ ያርበኝነት ልምድ እንዳላቸው ተረድተናል። ከምሩ የሚታገልና ማሸነፍ የሚፈልግ እራሱን ከሁኔታዎች ጋር እያመሳሰለ ነው።
3- አለማቀፋዊና ክልላዊ ጂ. ኦ ፖለቲካዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ የግንቦት ሰባት አይነት ድርጅቶች መሰረታቸውን ኤርትራ ማድረጋቸው በሁኑ ጊዜ ጎጂ ነው አያዋጣም አይነት መከራከሪያዎች።
የበዙት መታገል እንደሚገባ የሚያምኑ፤ የመሳርያውም ትግል አስፈላጊ መሆኑን የሚቀበሉ።  ኤርትራ ላይ መሰረትን አድርጎ ለመንቀሳቀስ የሚደረገውን ሙከራ መሰረታዊ በሆነ ሁኔታ የማይቃወሙ ናቸው። ለጥንቃቄ ወገንታዊ በሆነ መንገድ ፍራቻቸውን የሚያቀርቡ ዜጎች ናቸው። በእርግጥ እስከጭራሹ የሀይሉን አማራጭ የሚቃወሙና ትግል እንዳይካሄድ የሚፈልጉም ይህን አይነቱን ምክንያቶች ለማስፈራርያነት ይጠቀሙበታል።
የኤርትራ መንገስት ሽብርተኞችን በመርዳት ይከሰሳል። ጉልበተኛ የሆኑ አገሮች አግልለውታል። በቅርብ ኬንያ ውስጥ የተፈፀመውን የሽብርተኞች ጥቃት ጨምሮ ሽብርተኛነት ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ እየተስፋፋ ነው። የምንታገለው ሀይል እንኳን የዚህ አይነት አጋጣሚ ተገኝቶ ባይኖርም ፈብርኮ ስልጣን ላይ በሚቆየው መንገድ መጠቀሙን ያውቅበታል።  ስለዚህም ለነፃነት ለምንታገል በመጪው ግዚያት አስቸጋሪ ሁኔታውች ከፊታችን ይጠብቁናል የመሳሰሉ ፍፁም እውነትነት ያለቸው ምክንያቶች ናቸው። እነዚህ ጉዳዬች ላይ ማለት የሚቻለው አልጋ በአልጋ የሆነ ትግል የለም። ትግል ማለት  አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታዎች ማሸነፍ ወይ አስቸጋሪ የሆኑትን ሁኔታዎች እንዲጠቅሙ አድርጎ መቀየር ነው።
ለዚህ ችግር ፍቱንና  ዋንኛው መዳኒት በሂወታቸው መሰዋትነት እስከመክፈል ድረስ ለኛ ነፃነት የቆሙ ዜጎቻችንን መቃወሙን ማንቋሸሹን ትተን  ሁለንተናዊ በሆነ ሁኔታ አብረናቸው እንዳለን ማሳየት ነው። አንዳንድ ድርጅቶች እንቢ ቢሉም ህዘብ የጀመረውን ድጋፍና አብረን ነን  በሚታይ መንገድ ደግሞ ደጋግሞ ማድረግ መቻሉ  ዋና መፍትሄ ሊሆን ይችላል።
ውሳኔያችን።
የተሻለ የትግል አማራጭ ነው ብለን አጠንክረን የምናምንበት የህዝባዊ እንቢተኛነት ትግል ነው። አገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ትግል ትኩረት መሆን አለበት አጠንክረን እናምንበታለን። አንዱ ምክንያት ግንቦት ሰባቶች በያዙበት መንገድ የሀይሉን አማራጭ የሞከረ ስላልነበረም ነው። ያም ሆኖ የትኛውንም አይነት ትግል መቃወም አይደለም ማገዝም ችግር ሆኖብን አያውቅም።  ለየትኛውም ክፍል ችግር መሆን አለበት ብለንም አናምንም። ምክንያቱም  የትኛዎቹም አይነት ትግሎች የማይቀናጅ፤ የማይደጋገፉ፤ ሊተባበር የማይችል ወይ መጨረሻ ላይ የሚያስገኙቸውን ውጤቶች ተመሳሳይና የሚጠቅም እንዲሁም ሁሉ የሚስማማበት ማድረግ የማይቻል ስላልሆነ ነው። ስለዚህም ነው የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል መመስረት ገና ከጅማሮው ጥይት መጮህ ሳይጀምር በአብዛኛው ህዝብ ማለፊያ እርምጃ ተደርጎ የተወሰደውና ድጋፍን የተቸረው። ለውሳኔ አስቸጋሪ በሆነው በዚህ ጉዳይ ላይ ህዝብ ግራና ቀኙን ሳያይ፤ በዚህ መረጃ በቀላሉ በሚገኝበት ዘመን ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ ላይ መረዳቱ ሳይኖረው ድጋፉን አልሰጠም። ስለዚህም መሰረታችሁን ከኤርትራ  አደረጋችሁ በሚል ምክንያት የከፋ መሰዋትነት የሚያስከፍለውን የሀይሉን አማራጭ የመረጡ ድንቅዬ ጀግና ዜጎችን ለማሰናከል የተያዘውን ጥፋት አጥብቀን እንቃወማለን። ለማንም አይጠቅምም ። የመጣው ይምጣ ብለው ጨክነው ቢገቡበትም የነዚህ ዜጎች ደህንነት ከኢትዮጵያዊ ከሆነው ዜጋ ሁሉ  እገዛንና ርብርቦሽ በቀጥታ ስለሚፈልግ የሰሞኑ ፖለቲካ አሳስቦናል። የኤርትራ መንግስት አንድነቷ የተጠበቀ ጠንካራ የሆነች ኢትዮጵያን  ፈለገም አልፈለገ  ትግሉ ላይ እገዛ ሊያደርግ ፍቃደኛ ነው። ፍቃደኝ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል። ትግሉ ካለበት ጠቅላላ ሁኔታ ማንኛውም የወያኔን ዘረኛ መንግስት በሀይል እታገላለው የሚል ክፍል ይህን አጋጣሚ መጠቀሙ ትክክለኛ ፖለቲካዊ እርምጃ አድርገን ወስደንዋል።
ዘላቂ የሆነው መፍትሄ
-የህዝብም ጥያቄ የሆነውና የሚወተውቱበት እኛም ደግመን ደግመን ደጋግመን ያሳሰብነው የመተባበር ጉዳይ ነው።  ዘርፍ ብዙ ጥቅሞቹንና ለብዙ ትግሉ ላይ ላሉብን ለዚህ አይነት ችግሮች መፍትሄነቱን በተለያየ አቅጣጫ የሳየንበት ታላቅ አገራዊ ቁም ነገር ዛሬም ደግመን አናነሳዋለን።  መተባበር ትግሉ ላይ ግድ ይላል።  መሰረታቸውን በውጪ ያደረጉ ድርጅቶች አገር ቤት እንዳሉ ድርጅቶች መተባበር አለባቸው። ትግሉን አቀናጅተውና ተጋግዘው የሚመሩበትን አንድ አይነት መድረክ መፈጠር አለበት። ሽግግር  መንግስት ይባል ፤ ጥምረት ወይ ትብብር  ችግር አይደለም። የሆነ አይነት ትብብር ይቁም። እኛ ቀላል መንገድ ሆኖ የሚታየን አንድ የጋራ መድረክ በማቆም መጀመሩ ነው። የማይቻል በጭራሽ አይደለም። ይህን ማድረግ እንዳለብን ችግርና መከራም ከባድም አይደለም። በጣም የዘገየንበትም ጉዳይ ነው።
ሁሌም ቢሆን ትብብር  የሚደረገው ልዩነት ባላቸው ክፍሎች ነው። እስከዛሬ በአለም ላይ የተደረጉ ትብብሮች ሁሉ የሚነግሩን ይህንኑ ነው። ከየት የመጣ ወይ ምን የሚሉት ብህል እንደሆነ የማይታወቅ  ለመተባበር  አንድ አይነት አላማ፤ ፍላጎናት መንገድ የምንከተል መሆን አለብን ይባላል። በጭራሽ አሳማኝ ያልሆነ አዳካሚ ምክንያት ነው።  ወይ ከዚህ በፊት የተሞከሩ ትብብሮች የፈረሱት ቀድሞም ልዩነቶች እያሉ ስለተባበርን ነው። አይደለም። አብሮ በመስራት በሂደት የሚነሱ ልዩነቶችን ማቻቻል ካለመቻል ነው። እንዲሁም ልዩነቶችን  አያያዝ ባለማወቅ ነው። ለዚህ ጥሩ ማስረጃው ትብብሮቹ አይደሉም ድርጅቶች እራሳቸው አንድነታቸውን ጠብቀው መቆም እያቃታቸው ነው። የተብብሩን ዋና አላማ ትግሉን እናድርገው። በትግል ሲታጀብ ትብብሩ ይፀናል። የጋራ የሆነ የትግል መድረክ ሲቆም በትግል አይነቶች ላይ የሚፈጠር አሰልቺ ጭቅጭቅ አይኖርም።
-የምንታገለው ወያኔን ለማሸነፍ ነው ወይስ  አንድን የትግል አይነት ከሌላው ተመራጭና አሸናፊ ለማድረግ ነው?። ይህን ወይ ያንኛውን የትግል አይነት ተመራጭና አሸናፊ ማድረግስ አይቻልም እንጂ ተቻለ ማለት ወያኔን ማሸነፍ፤ ወይ ትግሉን አሸናፊ ማድረግ የሚሆነው እንዴት ነው?። ትግሉን ትቶ ምርጫ ያደረገውን የትግል አይነት ተመራጭና አሸናፊ ለማደርግ ወይ እንዱሰ የድርሻውን ለማደረግ የሚፈጨረጨር ወገኑን አምርሮ ለመቃወም ያለ አቅሙን በሙሉ የሚጠቀም ታጋይ ነኝ ባይ እኛጋ እንጂ በአለም ላይ ኖር የሚያውቅ አይመስለንም። ሲጀመር ይህ የለውጥ ፈላጊ የእውነተኛ ታጋዬች አጀንዳ አይደለም።  በርግጠኛነትም ዋና ተዋናዮቹ ለውጥ ፈላጊዎችም አይደሉም። እነዚህን በትንሹ የመረጃና የመከታተል ስራ በመስራት ነቅሶ ማውጣት ይቻላል። እስከስካሁኑ ግን አላማቸውን አሳክተዋል። እየጎተቱ ንፅፅር ውስጥ ስለሚጨምሩን ይህን ወይ ያንኛውን የትግል አይነት እራሱን ችሎ እንዴት ውጤታማ ማድረግ እንደምንችል እንኳ በሰከነ ሁኔታ መሞከር አልቻልንም። በትንሹ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ስናስብ በምን መንገድ ብናደርገው ነው የተሻለ ውጤት የሚመጣው ብሎ መነጋገር አልተቻለም። የሀይሉ መንገድ ይዶልበትና የተቃውሞ ሰልፍ ይሰራል አይሰራም ክርክር ውስጥ በቀላሉ ይከቱናል።
የየትኛውም አይነት ትግል ላይ ከምር የሚሳተፍና እንዳሉበት ሁኔታ አስተዋፆ እያደረጉ ያሉ ዜጎች ሌላውን አይነት ጥረት ሊቃወም በጭራሽ አይችልም። ትግሉን በምናካሄድበት ያገራችን ተጨባጭ እውነታ ሁሉም አይነት ትግሎች እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ  የሚካሄዱ ስለሆነ ቢደረግም ተቃውሞው ወጋ ቢስ ነው በቀላሉ የሚሆነው።  ተቃውሞው በየትም አቅጣጫ ቢሰላ ትክክለኛም አይደለም። የቱንም አይነት ትግል ጠቅሞም አያውቅም። እስከስካሁኑ የትግል ጉዞ ደግመን ደጋግመን  እንዳየነው ይህን ወይ ያንኛውን የትግል አይነት ወይ እየሞከሩ ያሉ ክፍሎችን መቃወም ማለት መቶ በመቶ ምርጫችን የምንለውን ወይ እንደግፈዋለን የምንለውን ትግል በቀጥታ መጉዳት ነው። እንደግመዋለን በቀጥታ መጉዳት ነው። ይህ ሊሰመርበት ይገባል። በተደጋጋሚ የታየው ይህው ነው። እንደግፋላን እያልን ወይ የደገፍን እየመሰለን ስናኮላሽ የምር አድርገው ይዘውት መሰዋት እየሆኑ ያሉ ዜጎች እንዳሉ ማወቅ አለብን። ሀላፊነት ይሰማን።
-ድርጅቶቻች መድረክ ላይ የማይታዩትን ጨምሮ ውሳኔዎች ላይ ተፅኖ አድራጊ አባሎቻቸውን  መመርመር አለባቸው። ይታየን ከጀመረ ረጅም ጊዜ የሆነውና ያሳስበን የጀመረው ችግር የትኛውም አይነት የትግል አይነት ላይ ጭልምተኛ የመሆን አዝማሚያ ነው። ዛሬ ዛሬ  እየበዛ ጎልቶ የሚታይ እየሆነ ነው። ከትግሉ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ላይም ስህተቶች እንዲሁ።
ከድርጅቶቻችን የተለመደ ያሰራር ባህል አኳያ  በየድርጅቶቹ ያሉ ዋና ዋና ወሳኝ ሰዎች  አባላትና ደጋፊዎች ላይ የሚያሳድሩት ተፅኖ በእጅጉ የሚጎላ ነው። በዙ በቆዩበት ቁጥር ዝሆን እየሆኑ ነው የሚሄዱት። በጊዜው የታያቸው ወይ የያዙት ግንዜቤ ትክክልም ሆነ አልሆነ፤ የሚሰራም ሆነ የማይሰራ ሃሳባቸውን እንዴት በቀላሉ ተቀባይ እንደሚያደርጉ ልምድ ስላላቸው ሀይላቸው በየድርጅቶቹ ብርቱ ነው። ይህን ያልነው ድርጅቶችን ውስጥ የችግሩ መሰረት የአባላትና የደጋፊዎች አይነት በየድርጅቶቹ ላይ የሚፍጥሩት ተፅኖ ብሎ መውሰድ የሚያሳምን  ስላልሆነ ነው። ድርጅቶች አካባቢ ያለው ችግሩ ሰርጎ ገብ አይደለም። ቸግር የሆነው በልተሳካ የተደጋገመ የትግል ሙከራና ትግሉ ውስጥ ብዙ በመቆየት ምክንያት አሁን ምንም አይነት የትግል አይነትን ለመሞከር መፍራትና አለመፈለግ ነው። የትኛውም አይነት ትገል ውጤት ያመጣል ብሎ ማሰብ አለመቻል ነው። ባጠቃላይ ትግል መሰናክሎቹ፤ አደጋው፤ የሚያስክፍለው ወጋና የሚያስገኘው ውጤት ፍፁም መሆን አለበት ከሚለው አቅጣጫ ብቻ እየተቃኘ መካሄድ በጭራሽ አይችልም።

No comments:

Post a Comment