Translate

Thursday, November 28, 2013

ከሳዑዲ የተመለሱ 7000 በላይ ኢትዮጵያዊያ በአደገኛ ሁኔታ የመን ውስጥ…

በግሩም ተ/ሀይማኖት 
በባህር ተሻግረው በየመን በኩል ያንን እልህ አስጨራሽ በረሃና ፈተና አልፈው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የገቡ ኢትዮጵያዊያን ከአበሀ፣ ከሚስ ምሽት፣ ናጂራንና አሲር… ከመሳሰሉት የመን ድንበር አቅራቢያ ያሉ የሳዑዲ ከተማዎች ላይ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን እየገቡ ነው፡፡ ጅዳ ሄደው ወደ ሀገራቸው ለመግባት የማይችሉ በመሆኑ የመን መግባት አማራጭ ሆኖባቸዋል፡፡
ምክንያቱም ወደ ጅዳ ለመሄድ በየቦታው ሊፍጸምባቸው ወይም ሊገጥማቸው የሚችለውን ችግር በማሰብ ነው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያዊያ ወደ የመን የገቡት በሁለት መንገድ ሲሆን አንደኛው ከላይ እንዳልኩት ያላቸው አማራጭ በመሆኑ ባሳቸው ፍላጎት ሲሆን ሁልተኛው እና ወደ 3000 የሚጠጉትን ግን የሳዒዲያ መንግስት የመናዊያኑን እንደ ቆሻሻ በጭነት መኪና አምጥቶ ድንበር ላይ ሲገለብጣቸው አብሮ የጫናቸው ናቸው፡፡


እነዚህ የሳዑዲ መንግስት አምጥቶ የገለበጣቸው ራሱ በሁለት መንገድ ይከፈላሉ፡፡ ድንበር ድረስ እንሂድ ብለው ለምነው የተጫኑ መኖራቸውን ካናገርኳቸው ልጆች ተረድቻለሁ፡፡ ሁለተኞቹ የሳዑዲ ፖሊሶች አፍነው ጭነዋቸው የሚያመጧቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከጅዳ ታፍነው የተጫኑ ሁለት ልጆች በስልክ አግኝቻለሁ፡፡ እርጉዞች የተደበደቡ የተደፈሩ ሁሉ ህዝቡ፣ መንግስት እንዳዳያቸው ተብሎ ወደ የመን እንደተጣሉ ነው ያናገርኩት ልጅ የገለጸልኝ፡፡


ሀረድ የሚገኘው IOM (International organization of migrant) ካምፕ እየተቀበላቸው ሲሆን በአሁኑጊዜ በፊት MSF( medical san frontan) ያዘጋጀውን ካምፕ IOM እየተጠቀመበት ስለሆነ እሱንም ከፍተውታል፡፡ ቢሆንም ይህ ቦታ ከሳዑዲ እና የመን ድንበር ከ 100 ኪ.ሜ በላይ ርቀት ስላለው ይህን ሁሉ መንገድ በእግር መጓዝ ግድ ብሏቸዋል፡፡ ያም ቢሆን መንገዱ በሰላም እንዳያልቅ መካከል ላይ አፋኞች ከሳዑዲ ገንዘብ ይዘው ነው የሚመጡት በማለት የተለያየ ጉዳት እያደረሱባቸው ነው፡፡ ዘርፈው፣ ደብድበው፣ ደፍረው ለፖሊስ ስለሚያስረክባቸው እንዲሁም መንገድ ላይ በቁጥጥር ስር ስለሚያውላቸው በአሁኑ ሰዓት ሰነዓ ኢሚግሬሽን (ጀዋዛት) እስር ቤት ከ3200 በላይ እንደሚገኙ አይቻለሁ፡፡


ባለፈው እርብ በወርሃዊ ፕሮግራማችን መሰረት እስረኞች ለመጠየቅ ስንሄድ 2700 አካባቢ ኢትዮጵዊያን ስደተኞች እስር ቤቱን አጣበውት ነበር፡፡ አሁን ግን ከ3200 በላይ በመሆናቸው እስር ቤቱ ሞልቶ ጊቢው ውስጥ እና ከጊቢው ውጭ ሁሉ ፈሰው ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ወገኖች በርሃብ እንዳይሞቱ ሁላችንም ማድረግ ያለብንን ማድረግ አለብን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሳዑዲ ላለው ስደተኛ በኢሳት ቴሌቪዥን አሰባሳቢነት የተጀመረው ነገር ከሳዑዲ ሸሽተው የመን ለሚገቡትም በርሃብ ሊያልቁ ነው እና ትኩረት እንዲደረግበት ጥያቄዬን አቀርባለሁ፡፡ በይበልጥ ሰሞኑን ወደ ቦታው በድጋሚ ሄጄ ማየት ስለምፈልግ ያለውን ሁኔታ አሳውቃለሁ

No comments:

Post a Comment