ለአምስት ቀናት የሚቆየው የበይነ መረብ ዘመቻ አንድነት ፓርቲ የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የጠየቀባቸውን ጉልህ ህገ መንግስታዊ መሰረታዊያን በማብራራት ህዝባዊ ንቅናቄውን በበይነ መረብ (online social media campaign) የሚያቀጣጥል ነው፡፡
በዚህ ዘመቻ የተለያየ ርዕዮተ አለም የሚከተሉ ሆኖም ህገ መንግስቱ እንዲከበር የሚጠይቁ የዴሞክራሲያዊ ኃይሎች አባላት፣ ነፃ የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት፣ የሀገሬ ጉዳይ ይመለከተኛል ለሚሉ ዜጎች፣ የመብት አራማጆች(አክቲቪስቶች) እና ህገ መንግስቱ እንዳይሸራረፍ የሚፈልጉ የኢህአዴግ አባላት እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል፡፡
ለበይነ መረብ ዘመቻው የተዘጋጁ የፕሮፋይል ምስሎችና የከቨር ምስሎችን በመቀየር እንዲሁም #millionsofvoices የሚለውን ሀሽ ታግ በመጠቀም የሚተላለፉ መልዕክቶቻችንን በማሰራጨት ለህገ መንግስት የበላይነት እንዲቆሙ በአክብሮት ይጠየቃሉ፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
ለሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት
ግብረ ኃይል
ለሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት
ግብረ ኃይል
No comments:
Post a Comment