Translate

Thursday, September 26, 2013

የሀይማኖት አቋም የእድገት መመዘኛ መስፈርት እንዲሆን ተወሰነ የሀይማኖት አቋም የእድገት መመዘኛ መስፈርት እንዲሆን ተወሰነ

Bereket_simon

መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ በረከት ስምኦን በተመራው የኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ውይይት ላይ ፣ የሀይማኖት አክራሪነት ከምርጫ 97 ቀጥሎ ከፍተኛ ፈታኝ አደጋ እንደሆነ ከተገለጸና ውይይት ከተካሄደ በሁዋላ የአገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ የሀይማኖት ጉዳይን እንደ አንድ የእድገት መመዘኛ መስፈረት እንዲተገብር ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በጉባኤው ላይ የሐይማኖት አክራሪነት የመንግስትን ተቋም በማፈራረስ እና ተከታዮቹ ነፍጥ አንስተው መስዋእት እንዲሆኑ በማነሳሳት ከፍተኛ የሆነ አደጋ ይፈጥራል ሲሉ አቶ በረከት ተናግረዋል፡
በኢትዮጵያ ታሪክ በዩዲት ጉዲት እና በግራኝ አህመድ ዘመን በከፍተኛ ሁኔታ የደረሰውን የመንግስት ውድመት ዳግመኛ ሊፈጥር የሚችል አዝማሚያ አለው ሲሉ የተናገሩት አቶ በረከት፣ ይህንን በተማረው ህብረተሰብ እየታየ ያለውን በመንግስት ላይ ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ ለመቋቋም ያስችል ዘንድ፣ በማንኛውም ሁኔታ በህዝብና በመንግስት ተቋማት ውስጥ መዝሙር ማዳመጥ ፤ የሐይማኖትን መልእክት የሚያንፀባርቁ ማንኛውንም ሃሳብ መለጠፍ ፤ መስበክ፤ የሞባይ መጥሪያ ድምጽ ማድረግ ፈጽሞ መከልከሉን ገልጸዋል።
መንግስት አክራሪነትን በአጭር ጊዜ ድምጥማጡን ሊያጠፋ የሚችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው ሲሉ የገለጹት አቶ በረከት፣ የኢህአዴግ ህልውና አደጋ ውስጥ የጣሉትን ሃይሎች ማፈን እና ማኛውንም መንገድ በመከተል መገደብ የሚቻለው የኢህአዴግ አባላትን በየደረጃው አሰልጥኖ ማሰተግበር እና የሐገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ ስርዓት የውጤት መመዘኛ አንድ መሰፈርት በማድረግ የሰራተኛውን ህልውና ጥያቄ ውስጥ በመክተት ነው ሲሉ አክለዋል።
የሐገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሀይማኖት ጉዳይን የሰራተኛው አንዱ መመዘኛ በማድረግ ለቅጥር ፤ለእድገት እና ለዝውውር መስፈርት አድርጎ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሰራ የ2006 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ ተቀርጹዋል፡፡

No comments:

Post a Comment