Translate
Sunday, September 22, 2013
በኢህአዴግ ቀይ መስመር ላይ የተደረገ ታሪካዊና ውጤታማ ሰለፍ
የሰልፊ አጀማመር ልክ እንደባለፈው ነበር ልዩነቱ የሰአቱ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ የዛሬው 3፡45 ሲሆንየጀመረው የባለፈው ከሶስት ሰአት በፊት ለጉዞ ተነስቶ ነበር፡፡የባለፈው ሰልፍ ላይ መጀመሪያ ላይ የአካባቢው ህብረተሰብ የለሁበትም አይነት የሞላበት የፍርሀት ስሜት የተንጸባረቀበት የነበረ ሲሆን የዛሬው ግን የዛ ፍጹም ተቃራኒ ነበር፡፡በአካባቢው የነበሩ ጥቂት የማይባሉ ፖሊሶች ላይ ሳይቀር ይነበብ የነበረው ስሜት ደግ አደረጋችሁ ፈጣሪ ከእናንተ ጋር ይሁን አይነት ነበር፡፡
ብዙ ሰው ወደ መሀል ለመግባት አሁንም ድፍረት በማጣት የተሸማቀቀበት ሁኔታ ቢታይም በስሜት በመኪናም ሆነ በእግር ላይ የነበረው መንገደኛ ፊቱ ላይ ይታይ ከነበው ሁኔታ የሰልፉ አካልና ደጋፊ እንደነበረ ማወቅ ይቻላል፡፡ የዛሬ ሰልፍ ለየት የሚያደርገው ኢህአዴግ በጉልበቱ ያሰመረውን …የአትለፉ..መስመር ላይ የተካሄደ በመሆኑ ነው፡፡እኔ እንዳልኳች፣እንዳዘዝኳችሁ በዚህ ግቡ በዚህ ውጡ አንቀበልም ፣የምንመራው ህግን ብቻ በምንገብ ከኢህአዴግ ጋር የፊት ለፊት መፋጠትጥ የተካሄደበት ሰልፍ፡፡
ሰልፉ ላይ እንደሰማሁት ከፈለጋችሁ ጃንሜዳ ሂዱ እንጂ መስቀል አደባባይ አትችሉም መባላቸው ሰማያዊ ፓርቲዎች ሲናገሩ ነበር፡፡------ሰልፍ የት እንደምናደርግና ለምን እንደምናደርግ የምንወስነው በህጉና በህገመንግቱ መሰረት በማስፈራራትና በጉልበት በሚሰጠን ህገወጥ መመሪያ አይደለም፣አደባባዮች የህዝብ ናቸው ፣መስቀል አደባባይ የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ የአንድ ፓርቲ ንብረት አይደለም ---ብለዋል አንድ የፓርቲው አመራር፡፡ እንዲሁም … ፣ሰልፉ በዚህ ሁኔታ በመካሄዱ ሰማያዊ ፓርቲ የኢህአዴግ ህገወጥ መስመር ለአለም ህዝብ አሳይቷል፣የጠሚ ደሳለኝ ሀ/ማሪያም አመራርም ለፍትህና ለዲሞክራሲ ያለው ንቀት ብዙ መንገደኛ ፣የአካባቢው ህዝብ በተገኘበት፣ የሀገርውስጥና አለምአቀፍ ሚዲያዎች ባሉበት በተግባር አጋልጧል---ብለዋል፡፡
በግሌ በዛሬው ሰልፍ ላይ በመሳተፌ የዚህም ፎቶ አንድ አካል በመሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡እርግጠና ነኝ በሂደት ተሰላፊ ብቻ ሳይሆን እንደ ዛሬዎች ጎበዝና ጀግና የሰልፍ መሪዎች ለምሳሌ እንደእነ ብርሀኑ ተክለ ያሬድ የምሆንበት ቀን እናፍቃለሁ፡፡
ሌላው በጣም ደስ ያለኝ ግን በጣም ያልጠበኩት በሰማያዊና በአንድነት ፓርቲ ወጣቶች መካከል ያየሁት የመተሳሰብና የመተባበር መንፈስ ነው፡፡በአካል ልዩናቸው በሀሳብ ግን አንድናቸው ፣አንዱ ውሀ ሲያጠጣ ሌላው ይኮተኩታል፣አንዱ ሲያጭድ ሌላው ይሰበስባል የሚባለው ነገር የታየኝ መሰለኝ፡፡የዛሬ በሰማያዊ አደባባይ በደረገው የማያዊ ሰልፍ ላይ የተደረገው የትብብርና የትግል መንፈስ የዛሬ ሳምንት አንድነት በጠራው (መስከረም 19/2006) ሰልፍ ላይ ጎልቶና ልቆ እንደሚታይ ተስፋ አደረግላሁ!!
በዛሬው ጉዳይ ብዙ ብል ደስ ይለኝ ነበር አንድ ነግ ብቻ ባክል፣ ያች የኢህአዴግ የአትለፉ መስመር የተደፈረባት---በህግ እንጂ በጉልበት አንገዛም፣ በህግ አምላክ የተባለባት ቦታ …ሰማያዊ አደባባይ ---ብትባል ደስ ይለኛል፣፣ብሶት የወለደው ፣በኢህአዴግ ላይ የበላይነት የተገኘበት፣በአለምፊት ማንነቱን የተጋለጠበት አደባባይ!! አሁንም የሕግ የበላይነት ይከበር!! ድምጻችን ይሰማ!!!ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
የኢትዮጵያዊነት ድምጽ-Ethiopiawinet
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment