ለአነባበብ ይረዳ ዘንድ ጽሁፌን ከመጽሃፉ እያጣቀስኩ ለመልሱ ከራሴ እና አስረጅ ይሆናሉ ካልኳቸው ዋቢ ማስረጃዎች ጋር አድርጌ የራሴን እነሆ እላለሁኝ።
ይህ ጉዳይ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የትግሪኛ ፕሮግራም ላይ አረጋዊ በርሄ እና ስብሃት ነጋ ቀርበው የተወያዩበት/የተከራከሩበት እና እና ስለ መጽሃፉ በተለይ እኛ ከአገር ውጪ ያለን ኢትዮጵያውያን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማንበት ጭብጥ ነው -የአክሱም ስልጣኔ ጉዳይ።
ከመጽሃፉ እጠቅሳለሁ:-
<< በርካታ ተመራማሪዎችና ጸሃፊዎች “አክሱም አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ የአማራ ነዋሪዎች ወዳሉበት ደቡባዊ ክፍል ስለመስፋፋቷ የጽሁፍ ማስረጃዎች የሉም። እንደኢትዮጵያ(አማራ) አባባል ሳይሆን የአክሱም ታሪክ ከሁሉ በላይ የደቡብ ኤርትራና የሰሜን ትግራይ ታሪክ ስለ መሆኑን(sic) ማስረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህ በተጨማሪ አማራ የአክሱም አፄአዊ ግዛት አካል የነበረ ስለመሆኑ ምንም አይነት ታሪካዊ ጥቁምታ የለም: