ዘረፋ የአምባገነኑ ወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናትና አገልጋዮቻቸው የወቅቱ ቀዳሚ ተግባር እየሆነ ነው ተባለ
ዘጋቢያችን ባስተላለፈልን ሪፖርት ሰሞኑን በኦሮሚያ በየዓመቱ በሚከበረው ለአባ ገዳ ስርአት ላይ ከህዝብ የተሰበሰበውን ገንዘብ በአካባቢው የሚገኙ የወያኔ ባለስልጣናት መቀራመታቸው ታውቋል። ቀደም ብሎ እንደሚታወቀው በጉጂ ኦሮሞ ባህል አንድ አባገዳ ስልጣን በተረከበ በስድስተኛው አመት ጉማታ ወይም ስጦታ ከህዝቡ የሚሰበስብ ሲሆን ስልጣኑን የሚያስረክበው ደግሞ በስምንተኛው አመት በመሆኑ ፣ ለሁለት አመታት የሚሰራበትን ገንዘብ፣ እህል ወይም የቤት እንስሳ ከህዝቡ በስጦታ መልክ ይቀበላል።
ይሁን እንጂ በዚህ አመት አባገዳው ጉማታውን ለመሰብሰብ ዝግጅት በሚጀምርበት ጊዜ የቦረና ዞን የወያኔ አገዛዝ ግልገሎች ከአሁን በሁዋላ ጉማታው መሰብሰብ ያለበት በመንግስት ነው በሚል ሽፋን የጉማታ ሰብሳቢዎች በተለያዩ አካባቢዎች መዋቀራቸውና የወያኔ ሆድ አደር ባለስልጣናቱም ከህብረተሰቡ እየዞሩ በአባገዳው ስም የሰበሰቡትን እጅግ በርካታ ገንዘብ ፣ ለአባገዳው ሳይሰጡ የተወሰነውን ለበላይ አለቆቻቸው የተወሰነውን ለራሳቸው ማድረጋቸውን፣ ዘጋቢያችን የአካባቢዉን ነዋሪዎች ዋቢ በማድረግ በላልከልን ዘገባ ላይ አመልክቷል።
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ወደስልጣን ወምበር ከመጣበትና ከመምጣቱም በፊት ባሉት ጥቂት የማይባሉ አመታት ውስጥ አልጠግብ ባይ የወያኔ ሆዳሞች በዝርፊያ ስራ ተጠምደው እንደሚገኙ በስፋት ሲዘገብ እንደቆየ ይታወሳል። በተለይም ዘረፋው በመከላከያ ውስት ጎልቶ እንደሚታይ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡ ሲሆን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዝን ኢሳት በሰሞኑ ዘገባው ሳሞራ የኑስ በቄራ መብራት ሀይል አካባቢ በ80 ሚሊዮን ብር ዘመናዊ ህንጻ ማሰራቱን በፎቶ ግራፍ አስደግፎ አቅርቧል። የሳሞራን ህንጻ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችም መከራየታቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
ይህን ቅጥ ያጣ ዝርፊያ አስመልክቶ ዘጋቢያችን ያናገራቸው አንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እንደገለጹት በሃገር ሃብት ላይ ልቅና ሃላፊነት የጎደለው ዘረፋ እየተካሄደ ለመሆኑ አንዱ ማስረጃ ሳሞራ የኑስ በጎን እንዲህ አይነት ዝርፊያ ባደባባይ እየፈጸመ በሚገኝበት ሁኔታ መከላከያ ሚኒስቴር በወር 10 ሺ ዶላር የሚከፍልበት በልዩ የደህንነት መሳሪያዎች በየሚጠበቅ መኖሪያ ቤት ውስጥ የመኖሩ ጉዳይ ነው። ሳሞራ የኑስ ብቻ ሳይሆን አብዛኞቹ የህወሀት ጄኔራሎችም በቦሌ ክፍለ ከተማ በውድ ዋጋ የተገነቡ ህንጻዎች አሏቸው። እናም ኢትዮጵያዊያን ይህ ዝርፊያ፣ ግፍና በደል አንድ ቦታ ላይ እንዲቆም ካላደረግን ፍጹም ሊታጠፍ የማይቻል ጥፋት ላይ እንደርሳለን ብለዋል።
No comments:
Post a Comment