ከተመስገን ደሳለኝ
እንደ ጉርሻ
በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ነው (ምንአልባት የሀይለማርያም መንግስት ሪፎርም /ማሻሻያ/ የማድርግ ዕቅድ ካለው በዚሁ ሊጀምር አስቦ ሊሆን ይችላል፤ አሊያም እንደተለመደው እስረኛ በመልቀቅ የፖለቲካ ማሻሻያ እንደተደረገ ለማስመሰል ይሆናል)፡፡ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄርም በብዛት ከሚለቀቁት እስረኞች ጋር አብረው እንደሚፈቱ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡

አጀንዳችን…
ዛሬ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የእነእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ፍትህ ሚንስቴር የመሰረተው ክስ ሲታይ ውሎአል፡፡
ዛሬ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የእነእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ፍትህ ሚንስቴር የመሰረተው ክስ ሲታይ ውሎአል፡፡
እስክንድር ከዚህ ቀደም ‹‹የታሰርኩት በግፍ ስለሆነ ንብረቴን አትውረሱ ብዬ አልከራከርም፤ ዛሬውኑ ልትወስዱት ትችላላችሁ›› በማለት ያልተከራከረ ሲሆን፣ የአበበ በለውን ንብረት በሚመለከት በሌለበት ታይቷል፡፡ የአንዱአለም አራጌ ባለቤት ደግሞ በስሟ የተመዘገበው መኪና መወረሱ አግባብ እንዳልሆነ በጠበቃዋ አቶ ደርበው ተመስገን አማካኝነት ተከራክራለች፡፡
ፍርድ ቤቱም ለውሳኔ የፊታችን ሚያዚያ አስር ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል (በእኔ ግምት ቀጠሮው እንዲህ የራቀው መጋቢት አስራ ስምንት ቀን እነእስክንድር የጠየቁት ይግባኝ የመጨረሻ ውሳኔ ስለሚሰጥበት ከዛ በኋላ የንብረቱን ጉዳይ ለመጨረስ ይመስለኛል)
የሆነ ሆኖ ዓቃቢ ህግ የእስክንድር ንብረት ተብለው ከቀረቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣ በባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ስም የተመዘገበ የቤት መኪና፣ እንዲሁም የእስክንድር እናት ንብረት የሆነ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤትን ለመውረስ ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት በእናቱ ስም የተመዘገበውን ቤት እንደተወው ገልጿል (አዲስ ታይምስ መፅሄት የእናቱ ቤት ዝርዝር ውስጥ መግባቱ ተገቢ አለመሆኑን ደጋግማ መግለጿ የሚታወስ ነው)፡፡
ይህንና ዓቃቢ ህግ በእስክንድር እናት ስም የተመዘገበውን መኖሪያ ቤት ከሚወርሳቸው ዝርዝር ውስጥ በማውጣቱ ምንም አይነት ምስጋና የለኝም፡፡ ምክንያቱም እንኳን ንብረታቸው ተከሳሾቹም ምንም ጥፋት ያላጠፉ ንፁሀን ናቸው ብዬ ስለማምን፡፡ ስለዚህም አሁንም እንዲህ እላለሁ፡- ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለብህ! አዎ እዳ አለብህ!! ንፁሀን ወንድሞቻችንን ይቅርታ ጠይቀህ እስክትለቅልን ድረስ!!!
No comments:
Post a Comment