Translate

Thursday, February 28, 2013

የሳጅን ዘመድኩን ዛቻ እና ትርጉሙ



ባለፉት ሳምንታት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፈለ ከተማዎች የወያኔ መንግስት ፓሊሶችና ደህንነቶች በሙስሊሙ ወገኖቻችን መኖሪያ ቤቶች በመዘዋወር ዝርፊያ የተቀላቀለበት አሸባሪ ብርበራና ፍተሻ ሲያካሄዱ ሰንብተዋል። ይህ ብርበራ በአይነቱ ፍጹም ከሆነ የወሮባላ ተግባር የተለየ እንዳልሆነ የደረሰባቸው፣ ያዩና የሰሙ ሁሉ የሚመሰክሩት ነው።
የፍርድ ቤት ትእዛዝ ለይስሙላ እንኳን ያልያዙ ጭንብል ያጠለቁ ፓሊሶችና ደህነነቶች ጨለማን ተገን በማድረግ በር እየበረገዱ በመግባት ቅዱሳን መጸሃፍትን፣ ሞባይልን፣ ቴሌፎኖን እና ወርቅ በግፍ መዘረፋቸውን ሰለባዎቹ አረጋግጠዋል። ይህ በእነዚህ ንጹሃን ሙስሊም ወገኖች ላይ ከተፈጸመው ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ማስደንገጫ ተጨማሪ መሆኑ ነው።
የእነዚህን አሳዛኝ ግፈኛ ተግባር የሰማው የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዜናውን በየካቲት 14 ቀን 2005 አ.ም ምሽት ዘግቦ ነበር። በዚህ ዘገባ ላይ የቪ.ኦ.ኤው ጋዜጠኛ የሰለባዎቹን ምስክርነትና አስተያየት ብቻ ማቅረብ ተገቢ ያልመሰለው ፕሮፌሽናሉ ጋዜጠኛ፣ ሚዛናዊ ዘገባ  ለማቅረብ ድርጊቱ ተፈጸመባቸው ወደተባሉት ክፍለ ከተማዎች የፓሊስ አዛዦች መደወል ነበረበት። ይኼኔ ነበር ጋዜጠኛው ሳጅን ዘመድኩንን ያገኘው። ይህን የመንግስት ወንጀል እንዲያስተባብሉ እድል የተሰጣቸው ሳጅን ዘመድኩን የሰጡት መልስ ሰዋዊ ሳይሆን አውሬያአዊ   ነው ማለት ይቻላል።

ከኢህአዴግ ጋር ቅርበት እንዳላችው የሚታሙት ብፁዕ አቡነ ማቲያስ 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸው ይፋ ሆነ


የአሜሪካው ሲኖዶስ ምርጫውን እንደማይቀበለው በመግለጫው አሳውቋል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛ የፓትርያርክ ምርጫ ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ተከናወነ፡፡ ቀደም ሲል የሟቹ ብፁዕ አቡነ ጳውሎስን ሞት ተከትሎ በአዲስ አበባና በአሜሪካ ባሉት ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የተቋረጠው እርቀ ሰላም እንዲቀድም የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ሳይሳካ በመቅረቱ ከአዲስ አበባው ቅዱስ ሲኖዶስ ጳጳሳት መካከል 6ኛ ፓትርያርክ እጩዎች ይፋ በተደረገው መሰረት ብፁዕ አቡነ ማቲያስ 6ኛ ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸው ይፋ ሆኗል፡፡
በእጩነት ከቀረቡት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታ ዳውሮ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ህዝቄል የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ጸሐፊ እና ብፁዕ አቡነ ማቲያስ የኢየሩሳሌም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንደነበር ለምርጫው የተዘጋጀ የግል መኀደራቸው አመልክቷል፡፡
በእጩ አቀራረብ ዙሪያ በርካታ አነጋጋሪ ጉዳዮች በጳጳሳት መካከል መፈጠሩና ከዕጩዎች መካከል አሁን ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸው ይፋ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘ-ኢየሩሳሌም አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ናቸው፤ስለዚህ እጩዎች ውስጥ መካተት የለባቸውም የሚል ተቃውሞ ቀርቦባቸው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

Wednesday, February 27, 2013

“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት “የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ


(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ

Imageሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።

ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለበት! አዎ ዕዳ አለበት!!


ከተመስገን ደሳለኝ

እንደ ጉርሻ
በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ነው (ምንአልባት የሀይለማርያም መንግስት ሪፎርም /ማሻሻያ/ የማድርግ ዕቅድ ካለው በዚሁ ሊጀምር አስቦ ሊሆን ይችላል፤ አሊያም እንደተለመደው እስረኛ በመልቀቅ የፖለቲካ ማሻሻያ እንደተደረገ ለማስመሰል ይሆናል)፡፡ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄርም በብዛት ከሚለቀቁት እስረኞች ጋር አብረው እንደሚፈቱ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለበት! አዎ ዕዳ አለበት!!
አጀንዳችን…
ዛሬ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የእነእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ፍትህ ሚንስቴር የመሰረተው ክስ ሲታይ ውሎአል፡፡
እስክንድር ከዚህ ቀደም ‹‹የታሰርኩት በግፍ ስለሆነ ንብረቴን አትውረሱ ብዬ አልከራከርም፤ ዛሬውኑ ልትወስዱት ትችላላችሁ›› በማለት ያልተከራከረ ሲሆን፣ የአበበ በለውን ንብረት በሚመለከት በሌለበት ታይቷል፡፡ የአንዱአለም አራጌ ባለቤት ደግሞ በስሟ የተመዘገበው መኪና መወረሱ አግባብ እንዳልሆነ በጠበቃዋ አቶ ደርበው ተመስገን አማካኝነት ተከራክራለች፡፡

የጁኔይዲ ሳዶን ወደ ኬኒያ መሰደድ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ምላሽ ሰጠ


“ጁኔይዲ ሳዶ በወንጀል አልተከሰሱም፤ እንደማንኛውም ዜጋ የመውጣትና የመግባት መብት አላቸው”

የፌዴራል ፖሊስ

junedin
(ሰንደቅ ጋዜጣ) የቀድሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ጁኔይዲ ሳዶ በጎረቤት ሀገር ኬኒያ በመሰደድ የፖለቲካ ጥገኝት መጠየቃቸውን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀለኛ ስለመሆናቸው የማውቀው ነገር የለም ሲል ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፀ።
አቶ ጁኔይዲ ሳዶ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሃቢባ መሐመድ በሽብር ተግባር ተሳታፊ ናቸው በሚል ጥርጣሬ በፌደራል አቃቤ ሕግ መከሰሳቸውን ተከትሎ በአዳማ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ላይ ተገምግመው ከስራ አስፈፃሚነታቸው መሰናበታቸው ይታወቃል። ይህን የፖርቲውን ውሳኔ ተከትሎ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውም ተሰናብተዋል። ከዚህ ተከታታይ ውሳኔዎች ጋር በተያያዘ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመከሰስ መብታቸውን በማንሳት ክስ ይመሰርትባቸዋል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ይህ ሳይፈፀም ሰሞኑን ከሀገር መውጣታቸው ተሰምቷል።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የውጪና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ዘሚካኤል አነጋግረናቸው በሰጡን ምላሽ፤ “ጁኔይዲ ከሀገር ሊወጡ ይችላሉ ተብሎ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሲደረግ የነበረ ክትትል አልነበረም። እኛ አቶ ጁኔይዲ የምናውቀው እንደማንኛውም ሰው ነው።”

አንድ አስተያየት፤ ህውሀት ተኮር


Abe Tokchaw

ሞት ይርሳኝ እና የህውሃት ወዳጆቼን እንኳን ለየካቲት 11 አደረሳችሁ ሳልላቸው የካቲት 21 ሊሆን አይደል እንዴ!? በሉ አሁንም የካቲት ራሱ ሳይወጣ “እንኳ አብፃኩም” ልበል። እኔ የምለው ይሄ ስንተኛ አመት ነው ማለት ነው… በዛ ሰሞን ስታትስቲክስ መስሪያ ቤት ስሰራ አንድ አባት ዕድሜያቸውን ስጠይቃቸው…” አይ ልጄ የእኔ እድሜ ሩቅ ነው… ቢጠሩትም አይሰማ!” እንዳሉኝ አይነት ህውሀትም እድሜው በጣም እየራቀ ሄዷል። በዚህ ቢጠሩት በማይሰማ ሩቅ ዕድሜ ምን ያህል ስራ እና ምን ያህል ሴራ እንዳከናወነ ግምገማው ይቁጠረው።
በበኩሌ የህውሃትን እምቢ ባይነት እና ታጋይነት አደንቃለሁ። አንድ ማህበረሰብ ጭቆና አለብኝ ብሎ ካመነ፤ እና ተዉኝ አትጨቁኑኝ ቢል የሚሰማው ካጣ “ዘራፍ” ብሎ ማምረሩ የአባት ነው። ችግሩ አትጨቁኑኝ ብሎ ዘራፍ ያለው መልሶ ጨቋኝ ሲሆን ነው እንጂ!
ይህው ዛሬም የደርግ ስርአት ህውሃትን እንደፈጠረው ሁሉ፤ የኢህአዴግ/ ደርግ ስርአት ደግሞ፤ አርበኞች ግንባርን፣ ኦነግን፣ ኦብነግን፣ ደህሚትን እና የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይልን ፈጥሯል።  ሁሉም በየ አቅጣጫው ነፍጥ አንግበው “ና በለው… ና!” እያሉ ከግዙፉ የኢህአዴግ ሰራዊት ጋር እየተፋለሙ እንደሆነ በተለያየ ግዜ እየሰማን ነው።

ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር!


ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር!

ማስለቀቂያ ካልተከፈለ – ኩላሊት ለገበያ
tigist gebre

ጠ/ሚ ኃ/ማርያምን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው?

 
hailemariam_desalegn_6በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በቅርቡ ከተላለፈው ‘‘ጅሃዳዊ ሃራካት’’ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ የወንጀልና የፍትሃብሔር ክስ ሊመሰረት ነው። ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ባሻገር በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሬቴድ) እና በፌዴራል ፖሊስ ተመሳሳይ ክስ ይመሰረትባቸዋል።
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናቱ እና የተጠቀሱት ተቋማት ላይ ክስ የሚመሰረተው ሰሞኑን ‘‘ጃሃዳዊ ሃራካት’’ በሚል በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ደርጅት የቀረበው ዘጋቢ ፊልም በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር ያሉትን ተጠርጣሪዎች መብት ሲጣስ መከላከል ባለመቻላቸው፣ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀማቸው፣ በሕዝብ ሐብት ያለአግባብ በመገልገላቸው፣ የተሰጣቸውን የሕዝብ አደራ ባለመወጣታቸውና በሃይማኖት ጣልቃ በመግባታቸው የወንጀልና የፍትሐብሔር ክስ ይመሰረትባቸዋል። ክሱን የሚመሰርቱት በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ባሉት ተጠርጣሪዎች ጠበቆች አማካኝነት ሲሆን ክሱም በሁለት ደረጃ ተከፍሎ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል።

የፍርሃትና ስም ማጥፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ


ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
2011፡ የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ሰም ማጥፋት
በዲሴምበር 2011 ‹‹ኢትዮጵያ የደም ሃገር ወይም የንቅዘት (ሙስና) ሃገር›› በሚል ርእስ የኢትዮጵያን ሁለት ገጽታ በማመዛዘን አንድ ጦማር አስነብቤ ነበር፡፡ በዚያን ወቅትEthiopia The Politics of Fear in the police states ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በተባለው ተቋም ተቀምጦ የነበረው ገጽታ ያሳየው ኢትዮጵያ ለም መሬቶች በተንኮል በተጠቀለለ ስውር ደባ እየተቸበቸቡ እንደነበር ነው፡፡በዘገባው ላይ ተቋሙ ለኢትዮጵያ ያሰፈረው ነጥብ (10 ከሙስና የፀዳ ማለት ሲሆን 0 ደግም በሙስና ንቅዘት ያጨማለቀው ማለት ነው) ኢትዮጵያ 2.7 ነበር ያገኘቸው፡፡ በሙሰና ከታወቁት የኣለም ሃገሮች ዋነኛዋ ኢትዮጵያ ናት ይል ነበር::  የግሎባል ፊናንሻል አንተግሪት ድርጅት ደግሞ ባለፉት ፲ ኣመታት ከኢትዮጵያ 11.7 ብልዖን  ያሜርካን ብር በሀገወጥ መንገድ ከኣገሪቷ ወጥቶአል ብሎ ዘገቦ ነበር::

Tuesday, February 26, 2013

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!


ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!

በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)
ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር  የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው  ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡

የደህንነት መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ከአገር እንዳይወጡ አዘዘ

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ 15 የትኬት እና 30 የኤርፖርት ሰራተኞችን ከስራ ካባረረ በሁዋላ ከአገር እንዳይወጡ አገደ። ከአየር መንገድ የውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሀብታሙ ጫኔ፣ ዳንኤል ገበየሁ፣ ኢማን ያሲን፣ ኤደን ካሳየ፣ ቤዛ ኤፍሬም፣ ይገርማል ታደሰ፣ ሰለሞን ይብራህ፣ ክንፈ ሚካኤል ሽጉጤን ጨምሮ በርካታ ሰራተኞች ከስራ የተባረሩ ሲሆን ፣ አየር መንገዱ ለደህንነት እና አሚግሬሽን መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ ሰራተኞቹ ከአገር እንዳይወጡ አሳግዷል።
ሰራተኞቹ ከአገር እንዳይወጡ ሲታገዱ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች መካከል ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ ለማዋጣት ፈቃደኛ አለመሆን፣ የድርጅቱን ሚስጢራዊ መረጃዎች የአገር ጠላት ለሆኑት የሽብርተኞች ሚዲያዎች ለኢሳት እና ለፍትህ ጋዜጣ መስጠታቸው፣ እንዲሁም የባለራእዩን መሪ የአቶ መለስ ዜናዊን ራእይ ለማሳካት በሚል የተነደፈውን የስድስት ቀን የነጻ የስራ አገልግሎት እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን የሚሉት ይገኙበታል። የሰራተኞቹ ፓስፓርት ቁጥር ለኢሚግሬሽንና ደህንነት ክፍል በመላኩ ሰራተኞች ከአገር ለመውጣትና ራሳቸውን ለማዳን አልቻሉም።

Monday, February 25, 2013

ከእሁድ እስከ እሁድ


ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
junedin reporter


“ጁነዲን ሳዶ ሳዑዲ ገብተዋል”
የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱት አቶ ጁነዲን ሳዶ ወደ አረብ አገር ማምራታቸውን አውቃለሁ ሲሉ አንድ ጎልጉል ተከታታይ ተናግረዋል።

የቡዳዎቹ ሠፈር የትኛው ነው? ወልደማርም ዘገዬ


የቀድሞው ኢትዮጵያዊ የአሁኑ ኤርትራዊ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድኃኔ “ኤርትራ እንደ እናት አገር፤ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም” በሚል ርዕስ በአውሮጳውያኑ የዘመን አቆጣጠር ጥር ወር 2013 የጻፉትን ጥናታዊ ዘገባ በፍላሼ አሰንብቼ ዛሬ ጧት ቁርሴን አወራረድኩበት፡፡ ኤርትራ ለእርሳቸው የምታስጨንቀውን ያህል ኢትዮጵያም – ባለቤት ያጣችዋ ከርታታዋ ኢትዮጵያም ለእኔ እንደእናት ሀገር ታስጨንቀኛለችና የተሰማኝን ልናገር ብዕሬን አነሳሁ፡፡
ግን በዚህች የተረገመች ሀገር – በዚህ የዜጎች መብት ክፉኛ በሚረገጥባት ሀገር የመብራት መጥፋት በየደቂቃው ስለሚከሰት በምፈልገው ፍጥነት መጨረሴን እጠራጠራለሁ፡፡ አንዳንዴ በቀን ለቁጥር ለሚያታክት ጊዜ ያህል መብራት ይቆራረጣል፤ አሁን ድርግም ይልና ከደቂቃዎች በኋላ ሊመጣ ይችላል፤ የምትሠራውን ቅጥ ያሳጣብሃል – በልጆቼ አነጋገር ‹ሙድህን ይሠርቅብህ›ና ልትሳነፍ ባስ ሲልም ልትጽፍ ያሰብከውን ከነጭራሹ ልትተወው ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ በኛ መንደር በቀደም ዕለት የጠፋ ከ27 ሰዓታት በኋላ ትናንት ማታ ነው መብራት የመጣልን፡፡ ስልኩም ውኃውም እንደዚሁ ነው፡፡ የቤት ስልክ ከሚሠራበት ጊዜ የማይሠራበት ይበልጣል፡፡ የአንዱን ሊጠግኑ ሲመጡ የሌላውን አበላሽተው ሊሄዱ ይችላሉ – ጠርተሃቸው በመቁሽሽ እንድታሠራቸው፡፡ ውኃ ወር እስከወርም ላታገኝ የምትችልባቸው አጋጣሚዎች አሉ፡፡

ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል


#Ethiopia #StopCensorship

From  Zone 9  blog
ለምዕራባዊያኑ የመጨረሻ  ወር በሆነው ዲሴምበር ወር መጀመርያ በሀገረ አሜሪካ ኢትዮጵያዊውን ጦማሪ እና እስክንድርነጋን ለማሰብ የተዘጋጀ መድረክ ነበር፡፡ በመድረኩ ላይ ስለ እስክንድር ነጋ የተናገሩት ተዋናይ ሊዬቭ ሽሬ የይበር እና ጸሐፊ ካርል በርንስቴይን ነበሩ፡፡ በርንስቴይን  ከ40 ዓመታት በፊት የዋሽንግተን ፖስት ዘጋቢ ሆኖ በሚሠራት ወቅት ከባልደረባው ቦብ ዉድወርድ ጋር በመሆ ን በአሜሪካ መንግስት ታሪክ ትልቅ የተባለውን እና የዋተርገቱ ቅሌት በመባል ሚታወቀውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ያሳተፈ የሙስና ቅሌት አጋልጠዋል፡፡ በነዚህ ሁለት ዘጋቢዎች ታሪካዊ ማጋለጥ ምክንያት በወቅቱ አሜሪካን በፕሬዝዳንትነት ይመሩ የነበሩት ሪቻርድ ኒክሰን ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ሆኗል፡፡
የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሳሌ ተደርጋ የምተጠቀሰው አሜሪካ በወቅቱ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ አቅም የሚያንሳት ሀገር አልነበረችም፡፡ የፖለቲካ ባህሏም (በጥቅሉ) ተጠያቂነትን የሚያበረታታ እና ሙስናን የመሰሉ ተግባራትን አፀያፊ አድርጎ የሚቆጥር ነበር/ነው ማለት ይቻላል፡፡

የመናገር ነጻነት ዘመቻው ለህወሃት መራሹ መንግስት ምኑ ነው?


From Borkena blog/ ቦርከና

ሰሞኑን የዞን 9 አባላት የብሎጋቸውን በኢትዮጵያ መከልከል ተከትሎ ከክፈቱልን ያለፈ ፤ መሰረታዊ ሊባል የሚችል ዘመቻ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ጀምረዋል፡፡ በዚህ ደረጃ ምላሽ መስጠቱ እና መጠቀም የሚቻለውን መድረክ ተጠቅሞ የችግሩን ጥልቀት ለማመላከት መሞከር ጥሩ ነው። ነገር ግን የመጻፍ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እየተጠየቁ ያሉትን ቡድኖች(‘ፎርማሊ’ ካወራን መንግስት ናቸው -ያውም ፈላጭ ቆራጪ) ባህሪ  ግምት ውስጥ በማስገባት፤ ዘመቻው እነዚሁ ቡድኖች አምነትውበት በማናለብኝነት የወሰዱትን ርምጃ ከማስቀየር ይልቅ በስነ ልቦናቸው ለተቀረጸው የትምክህት እና የበላይነት አስተሳሰብ ሃሴት የሚሰጥ ሆኖ ስለተሰማኝ ለነሱ ትምክህት ሃሴት ላለማዋጣት ስል በዚህ በዘመቻ አልተሳተፉኩም።
እንኳንስ የመናገር ነጻነት አይደለም ለእምነት ነጻነት ጀርባቸውን ሰጥተው የክስርቲያኑን የእምነት ተቋማት በቁጥጥር ስር አድርገው ሙስሊሙንም እንዲሁ እምነቱን ለመንጠቅ ቤት ለቤት ጭምር አሰሳ የገቡ ሰዎች ናቸው፡፡

ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት


ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)

25.02.2013
የዘረኛው የህውሃት ስርዓት በነፃ አውጪ ስም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም ከዛም በፊት የሚከተለው የተሳሳተ ሃገር መገነጣጠሉንና ቤሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ መስጠቱንtplf rotten apple መመልከት የተለመደና የቀን ከሌት ክንውናቸው መሆኑ በሃይል ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የሚታይ እውነታ ነው፡፡
ከምስረታው ጀምሮ ይዞት የተነሳው የኢትዮጲያን ሉዋላዊነት የማፍረስና የመበተን አላማውን መተግበር የጀመረው የሻቢያ አሽከር በመሆን ለሃገር አንድነትና ክብር ዘብ የቆመውን የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት በመውጋት ሃገራችን ያለ ባህር በር እንድትቀርና በኢትዮጲያዊነት የታነፀውን ዘመናዊ የወታደር ሃይል በትኖ በምትኩ የአንድ ብሄር የበላይነት የሚታይበት፣ ቤሄራዊ ስሜት የሌለው፣ በአለቆቹ ከመታዘዝ ውጪ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀት ያልዘለቀው ጀሌዎቻቸውን በህዝብ ላይ አንግሰው ያሻቸውን ሲገሉ፣ የሻቸውን ሲያስሩ እንሆ አሁን ያለንበት ደርሰናል፡፡

Sunday, February 24, 2013

የደም እንጀራ


ከቴድሮስ ሐይሌ (TADYHA@GMAIL.COM)

“የጤፍ መወደደድ ምክንያቱ ቀድሞ ሊመገብ የማይችለው አርሶ አደር እንጀራ መብላት በመጀመሩ ነው’’ በማለት የተናገረው የሙት ራዕይ ለማስፈጸም ሽር ጉድ እያለ የሚገኘው የከተማ ልጆች በቁሙ የሞተ ሲሉ የሚሳለቁበት ሃይለማርያም ደሳለኝ ፓርላማ ለተባለው የወያኔው አውጫጭኝ የቀድሞ አለቃው መለስ ዜናዊ ስኳርን በተመለከተ በአንድ ወቅት የተናገረውን ምንም ሳይገለበጥ ለጤፍም ችግር መመለሱን ባለፈው ሰሞን ሰምተናል። መጽሃፉ ሙታንን ለሙታን ተዋቸው እንዲል የበድን ጣዖት አምላኪ ወያኔና ጭፍሮቹን ለግዜው እንተዋቸውና ይህንን የሕገ አራዊት አገዛዝ እታገላለሁ የሚለውና በሃገሩ የመኖር ነጻነት አጥቶ የተሰደደው በተለይም በምዕራቡ ሃገራት የሚኖረው ኢትዮጽያዊ ዲያስፖራ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በቀጥታ በሃገር ውስጥ ያለውን ደሃ ወገኑ ላይ ከባድ የኑሮ ክብደት ጫና ሲፈጥር በአንጻሩ የወያኔውን አገዛዝ በውጭ ምንዛሪ እየደጎመ ጥቂት የአገዛዙ ግብርአበር ነጋዴዎችን ኪስ ሲያደልብ ከምናስተውልባቸው የንግድ ዘርፎች ውስጥ ከሃገር ቤት በቀጥታ በአይሮፕላን ተጭኖ ለንግድ የሚቀርበው የእንጀራ መጠን ከቀን ወደቀን እየደገ መምጣቱ ማየት ካስፈለገ በየሃበሻው ሱቅ ያለውን አቅርቦት መታዘብ በቂ ነው።

Saturday, February 23, 2013

ጊዮን ሆቴል የተጠናቀቀው የኦህዴድ ድራማ!!


ግለሰብ የሚጠመዝዘው “የህዝብ” ወኪል

opdo1
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ወገኛ ድርጅት ነው። “ሲያደርጉ አይታ” እንደሚባለው እንደ ኤፈርት አይነት ታላቅ የንግድ ኢምፓየር ከፈተ። ስሙንም ቱምሳ ኢንዶውመንት አለው። ቱምሳ የድርጅት ቅርጽና መልክ ተበጅቶለት ስራ ጀመረ። በበረሃ ትግል ወቅት በነበረን ሃብት መሰረትነው ለማለት ቀዳሚዎቹ የኦህዴድ ምልምሎች ሳንቲም አዋጡና ወደ ተግባር ገቡ።

ምረጡኝ ብዬ አላልኹም፤ ምረጡኝ ብዬ አላውቅም


ምረጡኝ ብዬ አላልኹም፤ ምረጡኝ ብዬ አላውቅም

545593_451547511583315_918352971_n
■ፓትርያሪክ እንድሆን የመንግስት ባለሥልጣን አላግባባሁም
■ ‹ካህናትና ምእመናን ለቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ብለው ብቻ ማሰብ፣ ይገባቸዋል›› –
■የፓትርያሪክ ምርጫ መንፈሳዊ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ፕትርክናውን ለማግኘት ማሰብና መሞከር ሕግም አይፈቅድም፡፡ ይህ የሥልጣን ስግብግብነት ነው፡፡/ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል/
አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሞተ ሥጋ ከተለዩ ስድስት ወራት ተቆጠሩ፡፡ ከፓትርያርኩ ኅልፈት በኋላ በሕገ ቤተ ክርስቲያን በተደነገገው መሠረት ስድስተኛው ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክነት ተሠይመው ቤተ ክርስቲያኒቱን በማገልገል ላይ ናቸው፡፡

ጁነዲን ሳዶ ኢህአዴግን ከዱ


የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ አገር መክዳታቸውን ዲብርሃን ኢትዮቻናል የሚባለውን የመንግስት አፈቀላጤ ጋዜጣ ጠቅሶ ዘገበ።እንደ ዘገባው አቶ ጁነዲን ጥገኝነት የጠየቁት ኬንያ ነው።
ባለቤታቸው በሽብርተኛነት ተፈርጀው የተከሰሱባቸው አቶ ጁነዲን ሳዶ በኦህዴድ “የመደብ ትግል” ግምገማ ከድርጅቱ አመራርነታቸው መወገዳቸው ይታወሳል። በተለያዩ የስራ ሃላፊነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ጁነዲን ባለቤታቸው ነጻ መሆናቸውን ገልጸው ለተለያዩ ሚዲያዎች ጽሁፍ ማሰራጨታቸው ይታወሳል።

Ethiopian Minister Junedin seeks Asylum in Kenya

EthioChannel,  pro regime “private” Saturday Newspaper has today reported that top ruling party official and “the Minister of Civil Service” has sought asylum in neighboring Kenya. A political scientist with a close knowledge of the former Minister that De Birhan talked to said that Junedin’s family couldn’t confirm the Report and that he was not contactable.
Junedin Sado’s wife, Habiba Mohammed, is one of 29 people facing terrorism charges related to protests by Muslims. Junedin last year published a letter in the same newspaper defending his wife and criticizing the federal prosecutor’s charges. In the letter, Mr. Junedin said that he had approached the Saudi Arabian Embassy in his personal capacity to raise money to build a mosque to fulfil the wishes expressed in the will of his late mother. The money recovered from his wife, Mr. Junedin said, was meant for the mosque and not to fund terrorist activities.Habiba was charged  in October 2012 with funneling money from the Embassy of Saudi Arabia to Islamist terror groups, at a hearing at the Ethiopian Federal High Court.

Friday, February 22, 2013

መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል


መስፍን ወልደ ማርያም

Publication1-150x150በአለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ችግሮችን መፈልፈያ መሣሪያ ሆናለች፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት ይዘናቸው (ምናልባትም አቅፈናቸው ማለት ይሻል ይሆናል) ስንንከባለል የቆዩ ችግሮች ሞልተውናል፤ እያሰብን እነዚያን የቆዩ ችግሮቻችንን በመፍታት ፋንታ ሌሎች አዳዲስ ችግሮችን እየፈለፈልን የተቆላለፉና የተወሳሰቡ፣ ውላቸው የጠፋ ችግሮችን ፈጥረናል፤ እየፈጠርንም ነው፤ አሁን በመፈጠር ላይ ያለው አዲስ ችግር እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚል ነው፤ እስቲ እንመልከተው፡፡
በሩቁ እንጀምር፤ እስላማዊ መንግሥታት ያቋቋሙ አገሮች አሉ፤ አንዳቸውም ሰላም የላቸውም፤ እስላማዊ ቡድኖች በምርጫ አሸንፈው ሥልጣን የያዙ አሉ፤ ለምሳሌ በቅርቡ በአረብ አገሮች በተጀመረው የፖሊቲካ እድገት ለውጥ በቱኒስያና በግብጽ እስላማዊ ቡድኖች አሸንፈው ሥልጣን ይዘዋል፤ በዚህም ምክንያት በቱኒስያና በግብጽ የለውጥ ጥያቄ አገርሽቶ አንደገና ሰዎች እየሞቱ ነው፤ በነዚህና በሌሎችም አገሮች የሚገኙት ወጣቶች የሚፈልጉት የሰው ልጆች ሁሉ መብቶች የሚከበሩባቸውና በሙሉ የግለሰብ ነጻነት የተረጋገጡባቸው አገሮች እንዲኖራቸውና በእኩልነት ኩሩ ዜጎች ሆነው እንዲኖሩ ነው፤

ጠቅላይ ሚኒስት ሃይለማርያም ደሳለኝና ጸጋዬ በርሄ ለሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ማስጠንቀቂያ ሰ



ለስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ እየተደረገ በሚገኘው ቅድመ ዝግጅት፣ የየራሳቸውን ‹ምርጥ› ይዘው የቡድን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉ አካላትን ያስተባብራሉ ለተባሉ ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት መንግሥት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተሰማ፡፡ ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸው ሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት÷ የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እና የምሥራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኀይለ ማርያም ደሳለኝ
ለሐራዊ ምንጮች የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ለሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸው ሰኞ፣ የካቲት 11 ቀን 2005 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተጠርተው ሲኾን፣ ያነጋገሯቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ኀይለ ማርያም ደሳለኝና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አማካሪ አቶ ጸጋዬ በርሄ ናቸው፡፡ ባለሥልጣናቱ÷ የፓትርያሪክ ምርጫው ቤተ ክርስቲያኒቱ ባጸደቀችው የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ መሠረት ብቻ መፈጸም እንደሚገባው መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ ‹‹የራሳችኹን ሕገ ደንብ አክብራችኹ መሥራት ሲያቅታኹ በመንግሥት ላይ የሚቀርበውን ሰበብ ማስቆም አለባችኹ፤ በየካፌው፣ በየሬስቶራንቱ፣ በየሆቴሉና በየልኳንዳ ቤቱ እየተሰበሰቡ የሚመክሩትንና የምታስተባብሯቸውን ቡድኖችም መግታትና መቆጣጠር አለባችኹ፤›› የሚል ማሳሰቢያ መስጠታቸው ተነግሯል፡፡

የህወሀት ጉዞ የርስበርስ መበላላት ታሪክ ነው


ከትእዝብት አድማሱ

የዝንጀሮ መንገድ ቢከተሉት መጨረሻው ገደል ነው እንዲሉ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ – የህወሓት ታሪክ ዞሮ ዞሮ የእርስ በርስ መበላላትና የመናቆር ታሪክ ነው። በገዛ ወንድሙ ላይ መጨከን፣ የገዛ ወንድሙንtplf rotten apple ገድሎ አካኪ ዛረፍ ማለት፣ የገዛ ወንድሙን ገድሎ ጀግና ነኝ ማለት፣ በገዛ ወንድሙ ላይ በሐሰት መስክሮ ለጥቕምና ለስልጣን ሲባል አሳልፎ መስጠት፣
በንፁኃን ደም እየነገዱ የግል ስልጣንን ማደላደል የመሳሰሉትን አስነዋሪ ተግባራት ዛሬ ከአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝና አመራር የወረስናቸው ሰይጣናዊ አስተሳሰቦችና ፓሊሲዎች ናቸው። የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግሞ የህወሓት አረሜናዊ ባህርይ እንደ ኤይድስ በሽታ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየተዛመተ መምጣቱ ነው።

ሰበር ዜና – አስመራጭ ኮሚቴው ለዕጩነት የለያቸው አምስት ሊቃነ ጳጳሳት ታወቁ !!


ሰበር ዜና – አስመራጭ ኮሚቴው ለዕጩነት የለያቸው አምስት ሊቃነ ጳጳሳት ታወቁ !!

ሐራ ዘተዋሕዶ
  • ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል አልተካተቱም
  • ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው አጠራጣሪ ኾኗል
  • የፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱ ከዕጩዎች ማንነት ጋራ በአግባቡ ይረጋገጥ
  • ‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ››› /ሰሞንኛ አባባል/
የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ለዕጩ ፓትርያሪክነት አጣርቶ የለያቸውን አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ማቅረቡ ተሰማ፡፡ ከየካቲት ዘጠኝ ቀን ጀምሮ የዕጩዎች ልየታ ሲያካሂድ የቆየው አስመራጭ ኮሚቴው÷ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የአምስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ስም ዝርዝር፡-

ዘረፋ የአምባገነኑ ወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናትና አገልጋዮቻቸው የወቅቱ ቀዳሚ ተግባር እየሆነ ነው ተባለ


ዘረፋ የአምባገነኑ ወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናትና አገልጋዮቻቸው የወቅቱ ቀዳሚ ተግባር እየሆነ ነው ተባለ

ላለፉት ሃያ አንድ አመታት በኢትዮጵያዊያን ጫንቃ ላይ ተፈናጠው ያለምንም ረፍትና ሃፍረት ህዝብን እየዘረፉ የሚገኙት የዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናትና አጫፋሪዎቻቸው ዝርፊያውን በተባባሰ መልኩ እየቀጠሉበት መሆኑን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ዘገባ አመለከተ። እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ባሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለው ዘረፋ ከከፍተኛ ባለስልጣናት አልፎና ወደታችም በስፋት በመውረድ ቀደም ብሎ በድብቅ ይካሄድ የነበረው ዘረፋ በተባባሰ መልኩና ለህዝብም ግልጽ በሆነ መንገድ እየታየ መምጣቱ ታውቋል።
ዘጋቢያችን ባስተላለፈልን ሪፖርት ሰሞኑን በኦሮሚያ በየዓመቱ በሚከበረው ለአባ ገዳ ስርአት ላይ ከህዝብ የተሰበሰበውን ገንዘብ በአካባቢው የሚገኙ የወያኔ ባለስልጣናት መቀራመታቸው ታውቋል። ቀደም ብሎ እንደሚታወቀው በጉጂ ኦሮሞ ባህል አንድ አባገዳ ስልጣን በተረከበ በስድስተኛው አመት ጉማታ ወይም ስጦታ ከህዝቡ የሚሰበስብ ሲሆን ስልጣኑን የሚያስረክበው ደግሞ በስምንተኛው አመት በመሆኑ ፣ ለሁለት አመታት የሚሰራበትን ገንዘብ፣ እህል ወይም የቤት እንስሳ ከህዝቡ በስጦታ መልክ ይቀበላል።

የካቲትን የምንዘክረው ከሀገር በቀል ወራሪው ህወሃት ጋር በመፋለም ነው!!


የካቲትን የምንዘክረው ከሀገር በቀል ወራሪው ህወሃት ጋር በመፋለም ነው!!

ቀደምቶቻችንን የምናስታውስበት፣ ሀገራችንን ከጠላት ወራሪ እና አንድነቷን ለማስጠበቅ ያደረጉትን  ተጋድሎ ከምንዘክርበት እለት አንዱ የካቲት 12 ነው። በዚህ ግዜ ይህንን ታሪክ ገልብጦ ለማበላሸትና ለመጻፍ የሚጥረውን፣ የአሁኑን የግራዚያኒ ትንሽ ወንድም ሀገር በቀል ዘረኛ መንግስት  የሆነውን ህወሃት/ኢህአዴግን ሀይማኖት፣ ዘርና ጾታ ሳይለየን የምንታገልበት ሁነኛ ወቅት ላይ እንገኛለን።
የቀድሞዋ የአፍሪካ ሀገራት የነጻነት ተምሳሌት የሆነችው እማማ ኢትዮጵያ፤ ዛሬ ሀገር በቀል በሆኑ የዘረኛ መዥገሮች ስብስብ ተጣብቃ የአበው መሰዋእትነት ከንቱ ይሆን ዘንድ ወያኔዎች እየሰሩ ነው። ጥንታዊ ታሪክን በመፋቅ፣ ባልተደረገና ባልተፈጸመ ታሪክ ለመተካት ወያኔ/ኢህአዴግ እያንዳንዱን የአበውን የታሪክ ማህደር በማጥፋት፣ እንደ አቡነ ጴጥሮስ የመሳሰሉ የጀግኖችን ሀውልት አሻራ በማፍራረስ ርካሽ የሆነ ግዚያዊ የፖለቲካ  ጥቅም ማስገኛ ስራ ላይ በመሰማራት ሀገራችንን ወደኋለዮሽ እድገት እየጎተቷት ይገኛሉ።
ሁለቱን ገዳዮች የሚያገናኛቸው፤ የግራዚያኒ ወታደር አበው ለነጻነታቸው ለአንድነታቸው ሲያደርጉት የነበረውን ተጋድሎ ለማስቆም፤ የህዝቡን የትግል ሞራል ለመግደል የአዲስ አበባን ነዋሪ ቁጥሩ 30ሺ የሚሆን ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ ፋሽስትነቱን ለማሳየት ያደረገው ያልተሳካ ሙከራ ነው፡፡

Tuesday, February 19, 2013

Ethiopia: The Politics of Fear and Smear


by Alemayehu G. Mariam

2011: Dictatorship, corruption and the politics of fear and smear
In December 2011, I wrote a commentary entitled, “Ethiopia: Land of Blood or Land of Corruption?” contrasting two Dictatorship, corruption and the politics of fear and smear in Ethiopia portraits of Ethiopia. At the time, the portrait painted by Transparency International (TI) (Corruption Index) and Global Financial Integrity (GFI) showed Ethiopia as a land blighted by  systemic corruption. GFI reported that “Ethiopia, which has a per-capita GDP of just US$365, lost US$11.7 billion to illicit financial outflows between 2000 and 2009. In 2009, illicit money leaving the economy totaled US$3.26 billion, which is double the amount in each of the two previous years.” TI gave Ethiopia a score of  2.7 on the Corruption Index (on a scale of 0 – 10, where 0 means “highly corrupt” and 10 means “very clean”).

Make demands on Ethiopia’s leader


Make demands on Ethiopia’s leader


Carina Hägg
CARINA HÄGG (S)
CARINA HÄGG STOCKHOLM 20101103 Carina Hägg, politiker, riksdagsledamot för Socialdemokraterna Foto: Henrik Montgomery / SCANPIX Kod: 10060
Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn has recently been appointed Chairman of the African Union (AU). He succeeded five months ago the deceased Meles Zelawi (EPRDF), which ruled Ethiopia with an iron fist since dictator Mengistu Haile Mariam was overthrown 1991st Mengistu was responsible for about 30 000 people were killed and now lives in exile in Zimbabwe.
Ethiopia holds fascinating sights, culture and magnificent scenery. But there is reason to monitor how the current political landscape is drawn up.

Monday, February 18, 2013

አበበ ገላው ተጫማሪ የግድያ ዛቻ ደረሰው


(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተጨማሪ የግድያ ሙከራ ዛቻ እንደደረሰው በጎግል ቮይስ በኩል በድምጽ ማስረጃ አቀረበ። “አበበ ደምህን እንጠጣዋለን፤ ከኛ የትም አታመልጥም” ሲል አስፈራሪው ሰው ይሰማል። ይህን ተከትሎ አበበ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው “የህወሃቶች ዛቻ እና የዘረኝነት ፉከራ ቀጥሏል። እስከ አሁን ያልተገለጠላቸው ሃቅ እንኳን ዛቻ ሞት ከትግላችንም ሆነ ከቁርጠኛ ጉዞአችን ፈጽሞ አይገታንም። ነጻነት ወይንም ሞት ብሎ የተነሳን ህዝብ ማንም አንባገነን አያስቆመውም። እኔ ብሞትም በዛ በታላቅ አደባባይ ላይ የተናገርኩት እውነት ግን ፈጽሞ አይሞትም፣ ምክንያቱም በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ የታመቀ ሃቅ ነውና። ሃቅ ሲታፈን ፈንድቶ መውጣቱ ያለ እና ወደፊትም የሚኖር ነው።”

ቴዲ አፍሮ በስራው ተከብሮ ተሸለመ


(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)

teddy awarded


ቴዲ አፍሮ በስራው ተከብሮ ተሸለመ
ታዋቂ የሚባሉት የኪነት ባለሙያዎች በአብዛኛው የህዝብ አንደበት ከመሆን ይልቅ “አጫፋሪነትን” መርጠዋል በሚል በሚዘለፉበት ወቅት ላይ ከየአቅጣጫው ምስጋና፣ ውዳሴና አድንቆት የሚዘንብበት ቴዲ አፍሮ በስራው ተከብሮ ተሸለመ።

“ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”


“ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”

ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል
inspection panel and world bank
/ዜና ጎልጉል/ ኢህአዴግ ላይ ቀደም ሲል ሲቀርቡበት ከነበሩት ሪፖርቶች በተለየ ጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠሩ አስደንጋጭ መረጃዎች እንደወጡበት ተሰማ። መረጃው የኢህአዴግን አንገት የማነቅ ያህል እንደሚቆጠርና ለተግባራዊነቱ የተንቀሳቀሱትን አካላት “የአስተዋይነት” ትግል ውጤት እንደሆነ ተጠቁሟል።

በጂሃድ ሃረካት ፊልም ላይ ከ33ቱ ፔቲሺን ፈራሚዎች የተሰጠ መግለጫ


በጂሃድ ሃረካት ፊልም ላይ ከ33ቱ ፔቲሺን ፈራሚዎች የተሰጠ መግለጫ

jihad harakat
ንብረትነቱ የሕዝብ ቢሆንም አገልግሎቱ የኢህአዴግ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ የሆነው ኢቲቪ በሰሞኑ የፍርድ ቤት ዕግድ ወደጎን በመግፋት ከተለያዩ ፊልሞች በመቀነጫጨብ ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› በማለት ጉዳያቸው በፍርድቤት እየታየ ባለው በእሥር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ያነጣጠረ ፊልም በተደጋጋሚ አሰራጭቶ ተከታትለናል፡፡ (ሙሉን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)

የዋሾ መንግስት ጩኸት፣ ውሸት! ውሸት! ውሸት!


የዋሾ መንግስት ጩኸት፣ ውሸት! ውሸት! ውሸት!

ሉሉ ከበደ
ሰሞኑን ወያኔ የተለመደ የውሸት ድራማ ሰርቶ፤ ሲሞን በረከት በሚባል፤ የማያምር፤ የማያፍር የኤርትራ ሰው፤ ጭራሹን አማራ ነኝ ብሎ እንዲያታልል ወያኔ የቀጠረው ባእድEthiopian Muslims, we are all Abubeker የፕሮፓጋንዳ ሚኒስቴር፤ የሀሰት ፊልም ደራሲና የበላይ አዘጋጅ የሆነ ሰው፤ ሰርቶ ጨርሶ ያሳለፈውን “ጂሀዳዊ ሀረካት” በሚል ርእስ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት ከሚያደርገው ነገር የተለየ ባይሆንም፤ ቀጣይ የማናደድ ስራቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ አቅርበው ነበር። እንደድሮው አረፍተነገርና የስእል እንቅስቃሴ እየበጣጠሱ፤ ቆርጠው እየቀጣጠሉ፡ እየገጣጠሙ፤ ውሸት እየደራረቱ፤ ለራሳቸው ያሳምናል ብለው እንደመሰላቸው ለኢትዮጵያ ህዝብም ይመስለዋል ብለው በታመመ አእምሮ ስለሚያስቡ ለቀውታል።

ኢትዮጵያ፡ ከዚህ በኋላ ቀጣዩ ጉዟችን (ወይም መቆሚያችን) ወዴት ነው?


ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
በዴሞክራሲ የአንድነት ጎዳና ላይ?
በጁን 2012 ‹‹ኢትዮጵያ፡ በሕገመንግስታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና ላይ›› የሚል ጦማር አቅርቤ ነበር፡፡ ‹‹በርካታማ ሕበረሰቦች ከጭቆና ወደ ዴሞክራሲ ሽግግርን ሲያስቡና ሲንቀሳቀሱ፤ እንቅስቃሴያቸውን የሚገቱ በርካታ ፈተናዎች›› እንደገጠሟቸው በማስረጃ የተደገፉ ታሪካዊ እውነታዎችን ጠቅሼ ነበር:-
ከአረብ ‹‹መነሳሳት››ከታየው ልምድ በመነሳት ሕገ መንግስታዊ ቅድመ ውይይት እንደሚያስፈልግ ጠቁሜ አንዳንድ ሃሳቦችም ሰንዝሬ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግስት ፍለጋና የዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግስት ግቡ ዙርያ ጥምጥም መንገድ፤ አድካሚና ተስፋ ሞጋች ይሆናል፡፡ይም ሆኖ የማይቻል አይደለም………..ግጭትን አስወግዶ ሰላማዊ ሽግግርን ተግባራዊ ለማድረግ፤ተፎካካሪ አለያም በተናጠል ያሉት ሁሉ በአንድ ላይ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ ይሄ ደግሞ በዋናው ግብ ላይስምምነትንና መቻቻልን መግባባትን ይጠይቃል፡፡

አባት ያቆየውን በማፍረሱ የሚመፃደቅ ሰራዊት!


አባት ያቆየውን በማፍረሱ የሚመፃደቅ ሰራዊት!

ጌታቸው, ከኦስሎ
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
የሰሞኑ የአዲስ አበባ ከራሞት እና የቴሌቭዥን ጣቢያዋ የዜና ርዕስ ”የመከላከያ ሰራዊት ሳምንት” ተከበረ የሚል ነበር። በ አዲስ አበባም የኢትዮጵያ ሰራዊት” የደረሰበት የእድገት ድረጃ”
Ancient Ethiopian army
ጥንታዊው የኢትዮጵያ ወታደር
ተብሎ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የተሰሩ፣ የተገጠሙ፣ እየተባሉ የተነገሩ አውደ ርዕዮች ከመታየታቸውም በላይ በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ስታድዮም ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም በተገኙበት ኢህአዲግ ለመጀመርያ ጊዜ ወታደራዊ ትርኢት አሳይቷል። መቸም ማንም ዜጋ የሀገሩ ሰራዊት ጠንካራ መሆኑን እና ሃገርን የመጠበቅ አቅም እንዲኖረው ይመኛል። ይህ ሁሉንም የሚያስማማ ጉዳይ ነው።

Thursday, February 14, 2013

ግፍ ሲበዛ ማስፈራት፤ እስርም ሲበዛ ማሸማቀቁ ይቀራል


ግፍ ሲበዛ ማስፈራት፤ እስርም ሲበዛ ማሸማቀቁ ይቀራል

የወያኔ ልብ ወለድ “ደራሲዎች” ተደራሲ በሌለበት  አለም  ሆነው የገሃዱን  አለም  ነጸብራቅ  ያልሆነውን የቀን ቅዠታቸውን በመርዛማና በዶለደመ መቃቸው ዛሬም እንደትላንቱ በቆሸሸው ኢቲቪ አማካይነት የጥጋብ ግሳታቸውን ማግሳት ቀጥለዋል፡፡  እኛም ግሳታቸውን በተራበ አንጀት እነሆ ለ21 አመት እየተጋትነው አለን።
የወያኔ ዘረኞች ቀደም ሲል በግንቦት 7 እና በሌሎቸም ደርጅቶች ላያ ያነጣጠሩ አኬልዳማን የመሰሰሉ የዉሸት ድራማዎችን በማቀነባበርና ሀአዲስ አበባን እንደ ባግዳድ የእልቂት ቀጠና ሊያደርጓት ነዉ የሚል የሞት ዜና ለህዝብ በማሰማት የታጋዮችን ቅስም ለመስበርና  የህዝብን  የተነሳሳ የትግል ስሜት ለማቀዝቀዝ ከፍተኛ ሙከራ አድርገዋል።
እነዚህ ዘረኞች  በባህላችንም ሆነ በሀይማኖታችን እንዲሁም በኢትየጵያዊ ትውፊቶቻችን ላይ ሲያላግጡ ገና ከመጀመርያው በቃቸሁ በለመባላቸው ዛሬም እንደትናንቱ “የምን ትሆናላችሁ” ንቀታቸዉንና  ለህዝብና ለአገር ያላቸዉን ጥላቻ ትውፊቶች ያላቸውን ጥላቻና ንቀጅሃዳዊ ሃረካት፡ በሚል የዘግናኝ ፈልም እያሳዩንነው ። ጅሃዳዊ ሃረካትን ከአኬልዳማ የሚለየዉ ነገር ቢኖር፤ ጅሃዳዊ ሃረካት፡  ለዘመናት ተከባብረው በኖሩት የሀገራችንን  የእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ነው፤ ይህ የወያኔ ጭፍን ተግባር የሚያሳየን ወያኔ ስልጣኑን እስካራዘመለት ድረስ ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ተከባብሮ የኖረን ህዝብን፣ እምነትንና አገራችንንም ጭምር ለማጥፋት እንደማይመለስ ነው።

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያዎች በነዋሪዎች ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግድያ ይፋ አደረገ


የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያዎች በነዋሪዎች ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግድያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት በትናትናው እለት የስርጪት ፕሮግራሙ የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያዎች በነዋሪዎች ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግድያ ይፋ አድርጓል። ኢሳት ይፋ ባደረገው በዚሁ በምስል የታገዘ ዘገባ እንደተገለጸው በምእራባዊያን አቆጣጠር ማርች 16፣ 2012 በኢትዮጵያዋ የሶማሊ ክልል ፣ በጋሻሞ ወረዳ በክልሉ መንግስት የሚተዳዳሩት ልዩ ሚሊሺያዎች አንድ ወጣት ይገድላሉ። የወጣቱን መሞት ተከትሎ ከወረዳው ህዝብ የተውጣጡ ሰዎች “አሁንስ በቃ” በማለት ገዳዩን የሚሊሺያ አባል ተከታትለው ይገድሉታል። ይህን ተከትሎ የልዩ ሚሊሺያ ሀይሉ አባላት በተደጋጋሚ ወደ አካባቢው በመሄድ ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሴቶችን ሲደፍሩና ንብረት ሲዘርፉ መቆየታቸውን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ማጋለጣቸውን ዘገባው አውስቷል። እንደ ኢሳት ዘገባ “ህዝቡ በቃን” ብሎ እንዲነሳ ያደረገው ዋና ምክንያትም የግፉ ጽዋ ሞልቶ በመፍሰሱ መሆኑን ነዋሪዎች እንደሚናገሩ ታውቋል።
በማግስቱ ማርች 17፣ ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ ልዩ የሚሊሺያ አባላት ወደ ወረዳው ተመልሰው በመሄድ ሰዎችን ከቤት እያወጡ ሰዎችን ገደሉ። ኢሳት የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ እንደገለጸውና የአካባቢው ነዋሪዎች በፎቶግራፍ አስደግፈው በላኩት መረጃ ከቤታቸው እየተለቀሙ የተገደሉት ሰዎች ብዛት 23 ነው። የልዩ ሀይሉ ድርጊት ያስቆጣው የወረዳው ነዋሪ መሳሪያ አንስቶ ከልዩ ሀይሉ ጋር መታኮስ በመጀመሩ፣ 17 የልዩ ሀይል የሚሊሺያ አባላት ተገድለዋል። የህዝቡ ቁጣ ያስፈራቸው የልዩ ፖሊስ አባላት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል ብሏል። ይሁን እንጅ ውጥረቱ አሁንም ድረስ እንዳለ የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ ብሏል ኢሳት።

በአልቃይዳ ሰበብ ቻይናን መቆጣጠር


በአልቃይዳ ሰበብ ቻይናን መቆጣጠር

የኦባማ አስተዳደር መጪው የአፍሪካ ዕቅድ
us china
የአገራቸውን አጠቃላይ ሁኔታ እና መጪው ጊዜ ምን እንደሚመስል፤ የአገራቸውን የወደፊት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ … ሁኔታ እንዲሁም አሜሪካ በቀጣይ ዓመታት የምትከተለውን የአጭርና የረጅም ጊዜ የውጪ ፖሊሲ ዕቅድ በተመለከተ ለሁለተኛ ጊዜ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማክሰኞ ምሽት ለምክርቤቱ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ኦባማ በርካታ ጉዳዮችን ዳስሰዋል፡፡ አፍሪካና ቻይናም የንግግራቸውን ሙሉ ቀልብ የሳቡ ነበሩ ባይባልም ሳይጠቀሱ አልታለፉም፡፡ በተለይ ስለአፍሪካ እንዲህ ብለዋል፤-

ቀባሪ ያጣው የወያኔ/ኢህአዴግ የአገዛዝ ስረአትና ባለቤት የሌላት ኢትዮጵያ


ቀባሪ ያጣው የወያኔ/ኢህአዴግ የአገዛዝ ስረአትና ባለቤት የሌላት ኢትዮጵያ

ፊልጶስ
እንደ ወያኔ/ኢህአዴግዊ ሀገርንና ትውልድን የሚያጠፋ እኩይ አመለካከትና ምግባር ይዞ ተነስቶና ተሳክቶለትም የሚገዛ ከኢትዮጵያ ውጭ በአለም ላይ ያለ ሀገርም ሆነ የሚገዛ ህዝብ የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግ የገዛ ወገኑንና ሀገሩን በጠላትነት ፈርጆ፣ ታጥቆና ተደራጅቶ የሚወጋና የሚያፈራርስ የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግዊ አገዛዝም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊንን የማጥፋቱንና የመበታተኑን ምግባር እንዲያቆም እሽሩሩ የተባለና እየተለመነ ያለ የለም።…..

ሰበር ዜና፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የአርቡ ሕዝባዊ ትዕይንት ላይ ሁከት ለመፍጠር ያደረገው ሙከራ ከሸፈ


ሰበር ዜና፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የአርቡ ሕዝባዊ ትዕይንት ላይ ሁከት ለመፍጠር ያደረገው ሙከራ ከሸፈ

ድምፃችን ይሰማ
  • ሁከት ፈጣሪዎቹ በራሪ ወረቀቶች እንዲበትኑ ተልእኮ ተሠጥቷቸው ነበር
  • የድርጊቱ ዋነኛ ተዋናይ ዶክተር ሺፈራው እና የፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች ናቸው
ባለፈው ሳምንት መንግስት ሕገ መንግስቱንና የራሱን ፍ/ቤቱን ትዕዛዝ በመጣስ ያሰራጨው ‹‹ጂሀዳዊ ሃራካት›› ‹‹ፊልም››ን በመከተል ሙስሊሙ ህብረተሰብ ባለፈው ጁሙዓ በአንዋር መስጊድ ባካሄደው ከባድ ተቃውሞ ላይ መንግስት ሁከት ለማስነሳት ሙከራ አድርጎ እንደነበርና፤ ሙከራውም ሳይሳካ መክሸፉ ተሰማ፡፡ በእለቱ የመንግስት ባለስልጣናት ዶ/ር ሺፈራው፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሕመድ እንዲሁም የፌዴራል መጅሊስ ሀላፊዎች በጋራ ለመጅሊስ ተመራጭና በአዲሱ የአሕባሽ ማህበር ስር ለተሰባሰቡ ሰዎች አበል በማዘጋጀት አንድ ተልእኮ ሰጥተው ነበር፡፡ ይኸውም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ‹‹በጂሃዳዊ ሀረካት›› ፊልም ስለተቆጣ ዛሬ ትንሽ ነካ ብናደርገው ለብጥብጥ ወደኋላ አይልም የሚል ግምት በማዘል የተሰባሰቡት ሰዎች በራሪ ወረቀት በአርቡ የተቃውሞ ትዕይንት መሀል እንዲበትኑ ነበር፡፡

ህግ ካልሰራ ጉልበት አማራጭ ይሆናል


ህግ ካልሰራ ጉልበት አማራጭ ይሆናል

ከይኸነው አንተሁነኝ
የካቲት 13 2013
የሰው ልጅ ማህበራዊ ፍጡር ነው። ለመኖር በግል ከሚያስፈልጉት የምግብ፣ የአልባሳትና መኖሪያ ቤት ማሟላት በተጨማሪ ለቀን ከቀን እንቅስቃሴው እና አካባቢውን በተለየ መልኩ ለሱ እንዲመች አድርጎ ለማስዋብ ከሱ መሰል ሌሎች ሰዎች ጋር መተባበር የግድ ይለዋል። ሁሉንም ነገር በራሳችን የግል ጥንካሬና ችሎታ ብቻ መከወን ያለመቻላችን ሚስጥርም ጠፈጥሮአዊ ማህበራዊነታችን ነው። በእርግጥ ሌሎች እንሰሳትም በማህበር ይንቀሳቀሳሉ እንስሳዊ ፍላጎታቸውንም ያሟላሉ። እጅግ በጥልቀት በማሰብ ለምንቀሳቀሰው ለኛ ለሰዎች ግን ማህበራዊነት ከሁሉም በላይ ፋይዳው የገዘፈ ነው። ያንዳችን እንቅስቃሴ የሌላኛውን መንገድ እንዳያበላሸው ከሌሎች እንስሳት ይልቅ ቀርበን በመወያየት በመነጋገርና በመስማማት ለጋራ ጥቅም የጋራ ውሳኔ እናሳልፋለን። በዚህም መሰረት ትዳር ከመመስረት ጀምሮ ባካባቢያችን የምናቃቁማቸው እንደ እድር እቁብ፣ የሙያ ማህበራት፣ የደቦ ጊዜያዊ ትብብርና ሌሎችም መሰል ስብስቦች ያሉንን እለታዊ እንቅስቃሴዎች ለብቻችን ማሸነፍ ያለመቻላችን ችግር የፈጠራቸው ማህበራዊ መፍትሄዎች ናቸው።

Tuesday, February 12, 2013

ኢሕአዴግ ከመቻቻል ይልቅ መጃጃልን መረጠ


ከትዕዝብ አድማሱ

የሐራካት ፊልም ድራማ ህዝቡን ያስተባብሯል እንጂ አይለያየንም
ትግሉን ያቀጣጥለዋል እንጂ አንገት አያስደፋንም

ሰሞኑን ሁላችንም እንዳየነው ወጣት ሙስሊም ወንድሞቻችን ሕገ መንግስቱ የሰጠንን የእምነት ነፃነታችን ይከበር በማለት በሕጋዊ አገባብ መልስ እንዲሰጣቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው በሓሰት ላይ የተመሰረተ ሓራካት የሚል የፊልም ድራማ በኢትዮጵያ ተለቪዥን ላይ ሲታይ መሰንበቱ ይታወቃል። የፊልሙ ይዘት በሶስት ነጥቦች ከፍሎ ማየት ይቻላል። 1. ፊልሙ ምን አዲስ ነገረ አለው? 2. የፊልሙ አላማ ምንድን ነው? 3. ፊልሙስ እንዳሰቡት ግቡን መቷልን? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ቀጥለን እንመልከት።

1. የሙስሊም ሐራካት የፊልም ድራና ምን አዲስ ነገር አለው?

ፊልሙ አዲስ ነገር የለውም። እንደዚህ ዓይነት በውሸት ላይ የተመሰረተ ማደናገሪያ ድራማ ማቅረብ የተለመደ፣ በተለይም ህወሓቶች ከተፈጠሩበት ቀን ጀምረው እስካሁን ድረስ በተለይም ምርጫ ሲቃራብ፣ የሚፈልጉትንና የሚጠረጡሩትን ሰው በእጅ አዙር ለመምታት፣ የህዝቡን ቀልብ ለመቀየር፣ የፓለቲካ ተቃዋሚዎችን ለማስደንገጥና ወኔ ለመስለብ ሲሉ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሙት የስነ ልቦና ጦርነትና ዘመቻ ነው። ለምሳሌ ወደ ዛሬው ድራማ ከመሄዳችን በፊት ህወሓቶች ስልጣን ከያዙ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከፈፀሙት አሰቃቂ ድርጊቶች ውስጥ ቆንጥረን የሚከተሉትን እንመልከት፡-

Thursday, February 7, 2013

የወያኔ ጀሃዳዊ ሀረካት ድራማ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄ እንደማያዳፍነው ተገለጸ


የወያኔ ጀሃዳዊ ሀረካት ድራማ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄ እንደማያዳፍነው ተገለጸ

ህዝብን ርስ በርስ በማጋጨትና በማዋጋት ራሱን በስልጣን ኮርቻ ኮፍሶ ለዘመናት መጉዋዝ የሚፈልገው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ ከትናንት በስቲያ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ እንደፈለገው በሚጫወትባቸው ሚዲያዎቹ ያስተላለፈው ጀሃዳዊ ሃረካት ድራማ በኢትዮፕያዊያን እየተጣጣለና እየተወገዘ መሆኑን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ዘገባ አመለከተ።
እንደዘጋቢያችን ሪፖርት በሃገር ውስጥ በሰላማዊ ትግል እየተንቀሳቀሰ ያለው አንድነት ፓርቲ  ” በ‹‹ጀሃዳዊ ሃረካት›› ትረካ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄ ማዳፈን አይቻልም!” በሚል ርእስ  መግለጫ፣  ማውጣቱ ታውቁአል። አንድነት በዚሁ መግለጫው በገዢው ፓርቲ ድርጊት ማፈሩንና ማዘኑን ገልጾ የከትናንት በስቲያ አዲስ ድራማው  ገዥው ፓርቲ  ዜጎች በማንኛውም መንገድ የሚያነሱትን ጥያቄ በግልጽና በውይይት መፍታት ያለመፈለጉ ግልጽ ሀገራዊ አደጋ እየሆነ መምጣቱ እየታየው ነው  ብሉአል። በመቀጠልም  ”ኢትዮጵያን የምታክል ትልቅ ሀገር እያስተዳደረ ባለ አገዛዝ” ማዘኑን ገልጾ  በኢትዮጵያ ሕዝብ ግብር የሚተዳደረው ነገር ግን የገዥው ፓርቲ መሳሪያ በመሆን የሕዝብ  ጥያቄዎችን ለማፈን ተባባሪ መሳሪያ ሆኖ እያለገለ ያለው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ‹‹ጀሃዳዊ ሃረካት›› በሚል የተሰናዳና እንደተለመደው የሙስሊሙን ህዝብ ጥያቄን ለማዳፈን የተዘጋጀ አይነት ትረካ ሲያቀርብ የመጀመሪያው አለመሆኑን አስታውሷል።
በበረከት ስምኦንና በጓደኞቹ ተቀነባብሮ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሊቀርብ ሲል በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የታገደዉ “ጂሀዳዊ ሀረካት” የሚባል ፊልም እገዳዉ በተሰማ በሰአታት ውስጥ በወያኔ ባለስልጣኖች ግፊት ተነስቶ ፊልሙ በኢቲቪ የታየ መሆኑን በስፋት መዘገቡ ይታወሳል።

Wednesday, February 6, 2013

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በአሜሪካ በሚገኙ አባቶች ሲኖዶስ ላይም ሊዘምት ነው


የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በአሜሪካ በሚገኙ አባቶች ሲኖዶስ ላይም ሊዘምት ነው

ሐራ ዘተዋሕዶ

  • አራተኛውን ፓትርያሪክ ጨምሮ ሦስት አባቶች ተተኩሮባቸዋል
  • ጠ/ቤ/ክህነቱ ለዶክመንተሪው ስርጭት ከብር መቶ ሺሕ ብር በላይ መክፈሉ ተነግሯል
የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙ አባቶች ላይ ያነጣጠረ ዶኩመንተሪ ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተሰማ፡፡
‹‹የነውጥን ጎዳና የመረጡ የሩቅ አገር ናፋቂዎች›› በሚል ርእስ መቀናበሩ የተነገረለት ይኸው ዶኩመንተሪ÷ በዋናነት፣ በአራተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ እና አቡነ መቃርዮስላይ የሚያተኩር ነው ተብሏል፡፡Letest Ethiopian Orthodox Church
ዝግጅቱ ለአንድ ሰዓት ከ30 ደቂቃየሚዘልቅ ሲሆን በሁለት ተከታታይ ክፍል እንደሚቀርብ ተገልጧል፡፡ የዝግጅቱ ዓላማ/ፋይዳ÷ በውጭ በስደት የሚገኙ አባቶችን ‹‹የኋላ ማንነት እና የወቅቱን አቋም ማጋለጥ››፣ በዚህም ቀጣይ አካሄዶቻቸውን ‹‹ተቀባይነት ማሳጣት›› እንደኾነ ተመልክቷል፡፡
አራተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ÷ ከምንኲስና እስከ ፕትርክና የነበራቸው ጉዞ፣ ለፕትርክና የበቁበት መንገድ እና ከቀድሞው ሥርዐተ መንግሥት ጋራ የነበራቸው ግንኙነት በዝግጅቱ የተካተተ ሲሆን በተለይም በጎንደር ሥርዐቱ በዜጎች ላይ ፈጽሞታል በሚለው በደል ነበራቸው የሚለውን ተሳትፎ በማተት ይወነጅላቸዋል፡፡