(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው የዘ-ሐበሻ ዘገባ የአባይ ጸሐዬ ሚስት ወ/ሮ ሳሌም ከበደ መታሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል:: ወ/ሮ ሳሌም ከቀድም ባለቤታቸው የወለዱትን ልጃቸውን ድረው መልሱን ሳይበሉ ዘብጥያ የወረዱ ሲሆን ባለቤታቸው አባይ ጸሐዬ የፖለቲካ ስልጣናቸውንና እርሳቸውን የሚደግፉ ሕወሓቶችን በማስተባበር ሚስታቸው እንዲፈቱ አድርገው የነበረ ቢሆንም ከሰዓታት ፍቺ በኋላ ወ/ር ሳሌም ዳግም ዘብጥያ መውረዳቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
Translate
Saturday, July 29, 2017
(ሰበር ዜና) በአባይ ጸሐዬ ትዕዛዝ ከ እስር ተፈተው የነበሩት ወ/ሮ ሳሌም ዳግም ታሰሩ * የፖለቲካ ስልጣናቸው ጉልበት አጥቷል
(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው የዘ-ሐበሻ ዘገባ የአባይ ጸሐዬ ሚስት ወ/ሮ ሳሌም ከበደ መታሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል:: ወ/ሮ ሳሌም ከቀድም ባለቤታቸው የወለዱትን ልጃቸውን ድረው መልሱን ሳይበሉ ዘብጥያ የወረዱ ሲሆን ባለቤታቸው አባይ ጸሐዬ የፖለቲካ ስልጣናቸውንና እርሳቸውን የሚደግፉ ሕወሓቶችን በማስተባበር ሚስታቸው እንዲፈቱ አድርገው የነበረ ቢሆንም ከሰዓታት ፍቺ በኋላ ወ/ር ሳሌም ዳግም ዘብጥያ መውረዳቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
ዋናዎቹ “መዥገሮች” ትንንሾቹን ነቀሉ!
ህወሓት/ኢህአዴግ በራሱ ጉባዔ (ፓርላማ)፣ በራሱ ባለሥልጣናት፣ በራሱ ፈቃድ፣ በራሱ በሚተዳደረው ሚዲያ፣ ፈቅዶም ሆነ ሳይፈቅድ በሚገዛለት ሕዝብ ፊት ይፋ ያደረገው የስኳር ፕሮጀክት ዝርፊያ በራሱ አስፈላጊ ርምጃ ለመውሰድ በቂ ሆኖ ሳለ ሙስናን በመታገል ስም እስካሁን መቆየቱ በራሱ አነጋጋሪ ነው፡፡ ምክንቱም አፈቀላጤ ነገሪ ሌንጮ እንዳለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ደሙን የሚጠጡት የበላይ ኃላፊዎች እነማን እንደሆኑ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነውና፡፡ ችግሩ ያለው ዋናዎቹን መዥገሮች ማን ይንቀላቸው የሚለው ላይ ነው፡፡
አዲሱ የአሜሪካ ምክርቤት ረቂቅ ሕግ በህወሓት ባለሥልጣናትና ቤተሰቦች ላይ ጭንቀት ፈጥሯል
ትላንት በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ የፀደቀው ረቂቅ ሕግ በህወሓት ባልሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ሥጋት፥ ፍርሃትና ጭንቀት መፍጠሩ ተሰማ።
Friday, July 28, 2017
የህወሓት መፈርከስ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያቀርባል !
Thursday, July 27, 2017
ነገሪ ሌንጮ፣ አቦይ ስብሃት በሙስናመታሰራቸውን ይንገሩን (ክንፉ አሰፋ)
የነጋዴዎች አድማ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ገዥው ፓርቲ ከየአቅጣጫው በመወጠሩ – የችግሩን ትኩረት አቅጣጫ ማስቀየር አለበት። የተለመደ የፉገራ ካርዳቸውን መዘዝ አድርገው ለዶ/ር ነገሪሌንጮ ሰጡዋቸው።
የስነ-ልቦና ጦርነት (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
ትልቁ የጦር ሜዳ የሰው ልጅ ጭንቅላት ነው። የብዙ ሰዎችን ጭንቅላት ያሳመነ አስተሳሰብ አሸናፊ መሆኑ የማይቀር ነው።ስለሆነም ጠላትን ለማሸነፍ በአስተሳሰብ በልጦ መገኘት ወሳኝ ነው። በአስተሳሰብ በልጦ ለመገኘት ደግሞ ምክንያታዊነት ብቻውን በቂ አይደለም። ከምክንያታዊነት በተጨማሪ ስሜቶችን (emotions) መቆጣጠር ይገባል።
አሸናፊ ስነልቦና ያለው ተፋላፊ ስሜቶቹን የሚቆጣጠር፤ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንኳን መንፈሱ የተረጋጋ ነው። ስለሆነም ለማሸነፍ አንተ በተረጋጋ የአዕምሮ ሁኔታ ላይ መገኘት ይኖርብሃል። በአንፃሩ ተፋላሚህ ደግሞ መዋከብ፣ መርበትበትና መደንገጥ ይኖርበታል። “ጠላትህ ማዋከብ” የስነልቦና ጦርነት ግብ ነው።
አምባገነን ሥርዓትን ማሸነፍ የሚቻለው የሥርዓቱ አራማጆች ወደ እብደት የተጠጋ የስነልቦና ቀውስ ውስጥ ሲገቡ ነው፤ ያኔ ውሳኔዎቻቸው ሁሉ የጭንቀት ይሆንና በስህተት ላይ ስህተት ይጨምራሉ፤ ከጭንቀት ብዛት የራሳቸውን ወዳጆች ሳይቀር ያጠፋሉ።
የስነልቦና ጦርነት በተለያዩ መንገዶች ሥራ ላይ ማዋል ይቻላል።
በዘራፊ አገር ወንጀለኛው ተራ ሌባ ነው፣ ዘራፊው ደግሞ ዳኛ (ጌታቸው ሽፈራው)
በዘራፊ አገር ወንጀለኛው ተራ ሌባ ነው። ዘራፊው ደግሞ ዳኛ። ዘራፊዎች የሚሰርቁት ህንፃ ነው። ዘራፊዎች የሚሰርቁት ሚሊዮን ነው። ቢሊዮን ነው። ይህም ሆኖ ዳኞች ናቸው። የጨዋታው ህግ አርቃቂ። የዘረፋ ህግ አዋቂ።
Wednesday, July 26, 2017
መስከረም ሳይጠባ እያንዣበበ ያለው አደጋ!
•~• Ermias Legesse Wakjira •~•
" በአፋን ኦሮሞ አማካኝቶ ማስተር ፕላኑን በጓሮ በር!" በሚል ርዕስ ከዛሬ አንድ ወር በፊት አጭር መጣጥፍ አቅርቤ ነበር። ይሔንን መጣጥፍ በድጋሚ እንዳስታውስ ያደረገኝ ዛሬ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ያቀረበውን ዜና ስመለከት የፈጠረብኝ አግራሞት ነው። የድርጅቱ ፅህፈት ቤት በድረገፁ ላይ " በኦሮሚፋ የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች በአዲሱ አመት ይከፈታሉ " በሚል አርስተ ዜና በፎቶግራፍ የተደገፈ ዜና አቅርቧል። ትምህርት ቤቶቹ መጠናቀቃቸውን ፣ በመጪው አመት ስራ እንደሚጀምሩ ፣ የትምህርት ቤቶቹ ብዛትና የፈጁት ገንዘብ፣ ለትምህርቱ የሚያስፈልገው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ መግለጫ የሚሰጠው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ነው። ያስገረመኝ ይሄኛው ክፍል ነው።
የኦሮሚያ የትምህርት ቢሮው መግለጫ በዚህ አላበቃም። ይልቁንስ ለትምህርት ቤቶቹ ርዕሰ መምህራን ፣ የአስተዳደር ሠራተኞች ፣ የጥበቃ እና ፅዳት ሰራተኞች ተሟልተውላቸው ተማሪዎችን ለመመዝገብ መዘጋጀታቸውን ይፋ አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪም በቀጣይ ጊዜያቶች በተቀሩት ስድስት ክፍለ ከተሞች በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ እና በግል ባለሐብቶች ተሳትፎ በኦሮሚፋ የሚያስተምሩ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ ተገልጿል። የትምህርት ቤቶቹ መገንባት በአዲስአበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ታዳጊዎች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲከታተሉ እንደሚያደርግ በዘገባው ተመላክቷል።
እንደ እውነቱ ከሆነ ይሄ ዜና አግራሞትን ከመጫሩም በላይ በአገዛዙ ማእቀፍ ስር ሕጋዊ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ከህጋዊነቱ ባልተናነሰ የአዲሳአባ የሚቀጥለው ጉዞ ካለፈው የሚከብድና የሚያስጨንቅ መሆኑን መገመት ይቻላል። አዲሳአባ ትከሻዋ ከሚችለው በላይ የችግር ጉድ ልትሸከም መዘጋጀቷን የሚያመላክት ነው። ዛሬ መዲናይቱ ላይ የነገሱትና በብቸኝነት የሚገዙት የትግራይ ነፃ አውጪዎች እና ተላላኪዎቻቸው ነዋሪውን እርስ በራስ ለማጨራረስ መዘጋጀታቸውን የሚጠቁም ነው። በመከባበርና በመፈቃቀር በአንድነት ተሰባስቦ ይኖር የነበረውን የአዲሳአባ ህዝብ በዘር ከፋፍሎ ለማጋደል በማሰብ የተጠነሰሰ ሴራ ነው። እርግጥም ሁኔታዎች እነሱ በፈለጉት መንገድ አልጋ በአልጋ ሆኖ ከቀጠለ የቀረበው ስጋት አየር ላይ የተንጠለጠለ ተራ ክስ ሳይሆን በቅርብ አመታት ውስጥ የሚከሰት ይሆናል።
Tuesday, July 25, 2017
መንግስት የገቢ ግብር እምቢታ አመፅን ለመግታት ዝግ ስብስባ ተቀምጧል
ዋዜማ ራዲዮ- ከኦሮሚያ የጨለንቆ ነጋዴዎች ተነስቶ ጊንጪ፣ አምቦና ወሊሶን ያዳረሰው የግብር በዛብን ስሞታ መልኩን እየቀየረ ባለፉት ሦስት ቀናት ወደ አዲስ አበባ ኮልፌ፣ ታይዋንና አጠና ተራ ተዛምቶ ቆይቷል፡፡ ኾኖም የግብር እምቢታ አመጹ በዚህ ፍጥነት ታላቁን የገበያ ስፍራ መርካቶን ያዳርሳል ብሎ የገመተ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡ ለብዙ ነጋዴዎች ያልጠበቁት ክስተቱ ኾኖ መገረምን የፈጠረው ይህ አመጽ ለመንግሥት ሹማምንትም ዱብ እዳ ሆኖባቸዋል፡፡
ከትናንት ጀምሮ ግምገማ የተቀመጡ የአስሩ ክፍለ ከተማ የድርጅት ኃላፊዎች አመጹን ማን አስተባበረው በሚለው ጥያቄ ላይ ከረር ያለ ግምገማ ያካሄዱ ሲሆን አዝማሚያዎችን ዐይቶ ማስቆም ሲቻል ይህ አለመደረጉ ትልቅ የመንግሥት ድክመት ሆኖ ተነስቷል፡፡
ትናንት ከቀትር ጀምሮ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮና የኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች በአንድነት በማዘጋጃ ቤት የካቢኔ አዳራሽ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የድርጅት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪዎች ራስ ኃይሉ ሜዳ በሚገኘው ቢሯቸው እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በስብሰባ ተሰንገው ማምሸታቸውን የዋዜማ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
የማዘጋጃ ቤቱን ስብሰባ ከተካፈሉ ምንጮች ዋዜማ እንደሰማቸው አመጹ ገፍቶ ከቀጠለ ቁርጥ ግብሩን የመክፈያ ጊዜ በተራዘመ ዓመታት እንዲሆን ከማድረግ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እስከማንሳት የሚሄድ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ከኃላፊዎች ፍንጭ መሰጠቱን ነው፡፡ ኾኖም እንዲህ ዓይነቱ ውሳኔ መንግሥት ሁኔታዎችን መቆጣጠር እየተሳነውና እየተዳከመ የመጣ ስለሚያስመስል የመጨረሻ አማራጭ እንደሚሆንና አሁን ዋናው ሥራ የእምቢታ አመጹን አስተባባሪዎች የመለየት ሥራ እንደሚሆን አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡ የዚህ ሥራ መጀመርያ የሚሆነው ደግሞ ነጋዴዎች ስሜታቸውን የሚተነፍሱባቸው መድረኮች በየወረዳው እንዲመቻቹላቸው ማድረግ፣ ቅሬታ አቅራቢዎችን በፍጥነት ማስተናገድ፣ በእምቢተኝነት የሚጸኑትን መለየት እንደሚሆንና ይህንንም የየክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች በአስተባባሪነት እንዲያስፈጽሙ ተወስኗል፡፡
ግብር አልገብርም ማለት መንግስት የለም ማለት ነው (መስቀሉ አየለ)
መስቀሉ አየለ
ለአበሻ ግብር መገበር ማለት ታክስ መክፈል ማለት አይደለም። ነገሩ ከዛ በላይ አልፎ የሚሄድ ውስብስብ መልዕክት አለው። ግብር በገንዘብ ብቻ የሚለካው ለፈረንጅ ነው። “አይ አም ኤ ታክስ ፔየር” ይላል። ለነሱ ሙሉ ለሙሉ የገንዘብ ጉዳይ መሆኑ ነው። ታክሱ በዝቶብኛል ብሎ ሲያስብ ለላንድ ሬቬኑ አንዲት ቁራጭ አፕሊኬሽን ፎርም ሞልቶ በመላክ ያስቀንሳል።
ሰበር ዜና – በጉጂ ዞን ከፍተኛ ውግያ ተነስቷል (ክንፉ አሰፋ)
በክንፉ አሰፋ
የአማሮ ህዝብ (ኮሬ ጎሳ) እና በጉጂዎች መካከል ከእሁድ (23 ጁላይ) ምሽት ጀምሮ ከባድ በሆነ የድንበር ግጭት መቀስቀሱን ወደ ስፍራው የተጓዙ እማኞች አረጋግጠዋል። ከሁድ ምሽት ጀምሮ በተነሳው የጎሳዎች ግጭት እስከአሁን ያልበረደ ሲሆን በግጭቱ ሳብያ በርካታ ቤቶች በመቃጠል ላይ መሆናቸውን ስፍራው ድረስ ስልክ በመደወል ለማረጋገጥ ችለናል።
Sunday, July 23, 2017
የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት (ክንፉ አሰፋ)
ክንፉ አሰፋ
የአስቸኳይ (የአፈና) ግዜ አዋጁ ገና አልተነሳም። በአዲሱ የግብር ትመና ሳብያ ከዳር እስከዳር የተነሳው ሕዝባዊ አድማ እና አመጽ ግን አዋጁን ውድቅ ያደረገው ይመስላል። አንድ ስርዓት ራሱ ያወጣው ህግ በህዝብ ሲሻርበት – ያኔ ነው ያበቃለት!
Saturday, July 22, 2017
የኢኮኖሚ ጦርነት (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ)
የህወሓት አገዛዝ ራሱን የኢትዮጵያ ሀብት ባለቤት አድርጓል። አገዛዙን ታማኝነትን በገንዘብና ሥልጣን ይገዛል። በአንፃሩ አገዛዙን የሚቃወሙ ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በኢኮኖሚ እንዲዳከሙና በድህነት እንዲማቅቁ ይደረጋል። በአሁኑ ሰዓት በአገራችን ማን ሀብታም፣ ማን ደግሞ ድሀ መሆን እንዳለበት የሚወስነው ህወሓት ነው። ማን ምን ያህል ግብር መክፈል እንዳለበትም የሚወስነው ህወሓትና የህወሓት ተላላኪ ድርጅቶች ናቸው።
በዚህም ምክንያት ጥቂት የህወሓት ባለሟሎች እና ከየክልሉ የመለመሏቸው አገልጋዮች ከዚህ በፊት በታሪካችን በማይታወቅ መጠን ሀብት አጋብሰዋል። እጅግ በጣም ጥቂቶች መቶ ሚሊዮኖችን ከመቁጠር አልፈው ቢሊዮኖች ላይ ደርሰዋል። በቁጥር እጅግ የበዛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ከቀድሞው በባሰ አስከፊ ድህነት እየማቀቀ ነው። ልመና፣ የጎዳዳ ተዳዳሪነት፣ ስደት፣ የአዕምሮ ጤና ጉድለት፣ ሥራ አጥነት፣ ረሀብና እርዛት . …. የአብዛኛው ኢትዮጵያው የዕለት ተዕለት ሕይወት መገለጫዎች ሁነዋል።
እዚህ ሀቅ ላይ ቆመን ስናየው ነው በአገዛዙ ላይ የኢኮኖሚ ጦርነት ማወጅ ፍትሀዊ መሆኑን የምንረዳው። በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ ልናደርጋቸው የሚገቡ በርካታ የኢኮኖሚ ጦርነት ስልቶች አሉ፤ ዋና ዋናዎቹን ከዚህ በታች እናቀርባለን።
አንድም ሦስቱም መረራ
በዘላለም ክብረት
አፍሪካ ከበደ ገና በአስራዎቹ የዕድሜ መጨረሻ ላይ ያለ ወጣት ነው፡፡ በጣም ተስፈኛ ነው፡፡ ሁሌም ለውጥ እንደሚመጣ መናገር ይወዳል፡፡ ለምን ስሙ ‹አፍሪካ› እንደተባለ ሲጠየቅ ደጋግሞ ወደ መምህር አባቱ ይጠቁማል፡፡ አባቱ ስድስት ልጆች እንዳላቸውና የመጀመሪያዋን ዓለም፣ ሁለተኛውን አፍሪካ፣ ሦስተኛውን ኢትዮጵያ፣ አራተኛዋን ኦሮሚያ፣ አምስተኛዋን ወለጋ እንዲሁም ስድስተኛዋን ደግሞ ሊሙ ብለው ስም እንዳወጡላቸው ለጠየቀው ሁሉ ፈገግ እያለ መናገር አይሰለቸውም፡፡ አፍሪካ በወጣትነት ዕድሜው የትውልድ ከተማው የምስራቅ ወለጋዋ ሊሙ ኮሳ ከተማ ውስጥ የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር መሆን ብዙ መዘዝ በሚያስከትልበት አገር አፍሪካ በተስፋ ጽሕፈት ቤቱን በራሱ ያቋቋመው ‹የአካባቢው ሰው አማራጭ እንዲኖረው› በሚል ሐሳብ እንደሆነና፤ ከፓርቲው የማረጋጋጫ ፈቃድ ተቀብሎ በጽሕፈት ቤቱ ጊቢ ውስጥ የኦፌኮን አርማ የያዘ ሰንደቅ ዓላማ ከክልሉና ከብሔራዊው ሰንደቅ ጎን የሰቀለ እለት በወረዳዋ የተፈጠረው ትርምስን እያስታወሰ ፈገግ ይላል፡፡ ‹‹አፍሪካ የመረራን ባንዲራ ሰቀለ›› በሚል የወረዳው አመራሮች ተሰብስበው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተወያይተው ለጥቂት ቀናት ከታሰረ በኋላ በፓርቲው ጥረት ተፈቶ ወደስራ እንደገና አንደተመለሰ ይናገራል፡፡ ‹‹የእኛ ጽሕፈት ቤት መክፈት በወረዳው አመራሮች ለሚበደሉ ሰዎች ትልቅ ተስፋ ሁኖ ነበር›› ይላል አፍሪካ፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች የመንግስት ሰራተኞች አለቆቻቸውን ‹‹አላሰራም የምትሉን ከሆነ አፍሪካ ጋር ሒደን እንሰራለን›› እያሉ ያስፋራሩ ነበር ይላል፡፡
ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ ህዝባችን እረፍት አይኖረውም! (አርበኞች ግንቦት7)
መልካሙ ታደግ, ከሮም
በሮም የተዘጋጀው 15ኛ የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል በወያኔ ኤምባሲና በትግራይ ልማት አቀናባሪነት እንደተዘጋጀ ፣ የፌዴሬሽኑም ኃላፊነት ሙሉ ለመሉ በወያኔ አገልጋዬች እንደተጠለፈ መረጋገጡ በተለያየ መንገድ ሲገለፅ ቆይታል።
አብዛኛው ሃገር ወዳድ የሃገሩና የህዝቡ ጨቋኝና ጨፍጫፊ የአገዛዝ ስርዓት ለመደገፍ በሮም ዝግጅቱ ላይ ላለመገኘት ወስኗል ።
ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ ህዝባችን እረፍት አይኖረውም! (አርበኞች ግንቦት7)
አርበኞች ግንቦት7
ባለፉት 26 ዓመታት በወያኔ ዘረኛ፣ ከፋፋይ፣ አፋኝና ገዳይ ፖሊሲ ስቃይ ያልደረሰበት ዜጋ አለ ከተባለ ያ ግለሰብ የአገዛዙ አባል መሆን አለበት። በወያኔ ፖሊሲ ህዝባችን ተገድሏል፤ አካለ ጎደሎ ሆኗል፣ ታስሯል፤ ተገርፏል፤ ተሰዷል። ህዝባችን በምድር ላይ ያለውን ስቃይና መከራ ሁሉ ተቀብሏል። ከዛሬ ነገ ይሻሻል ብሎ ተስፋ ሲያደርግ፣ ስቃዩ እየጨመረ፣ የህዝቡ የመኖር ህልውና አደጋ ውስጥ እየወደቀ፣ እንደ ህዝብ በጅምላ የሚጠፋበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ጥቂቶች የህወሃት ሽፍቶችና ግብረአበሮቹ፣ የማይጠረቃውን ቋታቸውን ለመሙላት ሲሉ ህዝቡን በአጥንቱ አስቀርተው አገሩን ሁሉ ለመውረስ ላይ እና ታች እያሉ ነው።
የመንግስት ሰራተኛው በአንድ ለአምስት ተጠርንፎ በኑሮ ውድነት ሲጠበስ ቆይቶ አሁን ግን የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ትግል ማድረግ ጀምሯል። አርሶአደሩ ሞፈሩንና ቀንበሩን እየሰቀለ፣ ጎተራውን አራቁቶ፣ ጥሪቱን አሟጦ ራሱን ለመከላከል እየተጋደለ ነው። “በብልጽግና ላይ ብልጽግናን አጎናጸፍነው” እየተባለ በእየለቱ የሚዘመርለት አብዛኛው ነጋዴ ደግሞ፣ ጥቂቶች ለበሉት እሱ እዳ እንዲከፍል በመታዘዙ ፣ “ በቃኝ” ብሎ ትግሉን ለኩሷል። ወያኔ አስፈራርቶ ለመግዛት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደ ጎን በመተው፣ ህዝባችን ከአቅጣጫው ትግሉን ማቀጣጠሉ ለወያኔ ያለውን ንቀት ብቻ ሳይሆን፣ ከእንግዲህ ወያኔንና ሰንኮፉን በአገራችን ምድር ለማየት እንደማይፈልግ ማሳያ ሆኖአል። ኩሩውና ጀግናው ህዝባችን ለወያኔ ያለውን ንቀት፣ የወያኔን የተጣመመ ህግ አልቀበልም ብሎ በማደም ብቻ ሳይሆን፣ የወያኔን የጥይት ጥቃት በመመከት ጭምር እያሳየ ነው። ጥይትና አፈና የማያንበረክከው ህዝባችን፣ ወያኔን ስልታዊ በሆነ ትግሉ ወደ ማይመለስበት መቃብር እየከተተው ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝባችን እየተገበራቸው ያለው የትግል ስልቶች፣ ነጻነት ወዳዱን ህዝብ ሁሉ የሚያኮራ፣ ገዳዮችን የወያኔ ጀሌዎች ደግሞ የሚያስበረግግ ነው።
ቀጣዮ የሽግግርሩ መንግስት አወቃቀር፥ሂደት እና አፈጻጸም እቅድ (ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ)
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
1. ከወያኔ ውድቀት በኋላ የሽግግር ጊዜ መንግስት ምን መምሰል አለበት?
2. የሽግግር መንግስት ዋና ዋና ስራዎች ምን መሆን አለባቸው?
3. የወደፊቱ ስርኣት ፓርላሜንታዊ ወይስ ፕሬዚዳንታዊ? ለምን?
3. በዘውግ የተደራጁ ፓርቲዎችና ሌሎች ድርጅቶች በምን መልኩ በሽግግርና በቋሚው መንግስት ይካተቱ?
4. የማህበረሰባችችን የሞራል መሰረት እንዴት እንገንባ? የሚሉትን እና ሌሎች ተመሳሳይ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ቁልፍ ጥያቄዎች ይዳስሳሉ። መልካም ንባብ!
2. የሽግግር መንግስት ዋና ዋና ስራዎች ምን መሆን አለባቸው?
3. የወደፊቱ ስርኣት ፓርላሜንታዊ ወይስ ፕሬዚዳንታዊ? ለምን?
3. በዘውግ የተደራጁ ፓርቲዎችና ሌሎች ድርጅቶች በምን መልኩ በሽግግርና በቋሚው መንግስት ይካተቱ?
4. የማህበረሰባችችን የሞራል መሰረት እንዴት እንገንባ? የሚሉትን እና ሌሎች ተመሳሳይ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ቁልፍ ጥያቄዎች ይዳስሳሉ። መልካም ንባብ!
Friday, July 21, 2017
‹‹በሴትነቴና በማንነቴ ላይ ተመስርተው ስድብና ማንቋሸሽ ፈጽመውብኛል›› ቀለብ ስዩም
#Ethiopia #HumanRights #KelebSeyoum
ስም፡- ቀለብ ስዩም
ዕድሜ፡- 28
አድራሻ፡- አማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ምዕራብ አርማጭሆ
አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት፣ ቃሊቲ እስር ቤት
ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረሻል ተብዬ ነው የታሰርሁት
በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- አርበኞች ግንቦት ሰባት ከተባለ የሽብር ድርጅት አመራሮች ጋር ግንኙነት በማድረግ ድርጅቱን ለመቀላቀል ልትጓዝ ነበር በሚል የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 7(1) በመተላለፍ በማናቸውም መልኩ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ መሳተፍ የሚል ክስ ነው የፌደራል አቃቤ ህግ ያቀረበብኝ፡፡
ዕድሜ፡- 28
አድራሻ፡- አማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ምዕራብ አርማጭሆ
አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት፣ ቃሊቲ እስር ቤት
ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረሻል ተብዬ ነው የታሰርሁት
በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- አርበኞች ግንቦት ሰባት ከተባለ የሽብር ድርጅት አመራሮች ጋር ግንኙነት በማድረግ ድርጅቱን ለመቀላቀል ልትጓዝ ነበር በሚል የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 7(1) በመተላለፍ በማናቸውም መልኩ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ መሳተፍ የሚል ክስ ነው የፌደራል አቃቤ ህግ ያቀረበብኝ፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
አርበኛ ታጋይ ብርሃኑ ጀግኔ
በዚህ በዛሬው የአርበኞች ማስታወሻ መርሃ ግብራችን ውስጥ አንድ ጀግና አርበኛን እናስተዋውቃችኋለን።
በ3 ሺህ ዘመን ታሪኳ ውስጥ ማህጸኗ መቼም ቢሆን የቁርጥ ቀን ልጆች ከመጸነስ፣ ከመሸከምና ከመውለድ አቋርጣ የማታውቀው እናታችን ኢትዮጲያ ዛሬም እንዲሁ ጀግና ወልዳልናለች። ይህ ጀግና አርበኛ የተፈጠረበትን፣የመጣበትን ዋና ተልዕኮ ፈጽሞ፣ ሩጫውንም ጨርሶ ወደማይቀረው አለም በክብርና በነጻነት ሄዷል።
በዚህ በዛሬው የአርበኞች ማስታወሻ መርሃ ግብራችን ውስጥ አንድ ጀግና አርበኛን እናስተዋውቃችኋለን።
በ3 ሺህ ዘመን ታሪኳ ውስጥ ማህጸኗ መቼም ቢሆን የቁርጥ ቀን ልጆች ከመጸነስ፣ ከመሸከምና ከመውለድ አቋርጣ የማታውቀው እናታችን ኢትዮጲያ ዛሬም እንዲሁ ጀግና ወልዳልናለች። ይህ ጀግና አርበኛ የተፈጠረበትን፣የመጣበትን ዋና ተልዕኮ ፈጽሞ፣ ሩጫውንም ጨርሶ ወደማይቀረው አለም በክብርና በነጻነት ሄዷል።
Thursday, July 20, 2017
አዲስ አበባ ወይብላ ማሪያም አካባቢ የሚገኙ ሱቆች ተዘግተው የሚያሳይ ፎቶ | ሽሮሜዳም በውስን ተዘጋግቶ ነበር
(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት መራሹ መንግስት በሕዝብ ላይ የጣለውን አግባብ ያልሆነ ግብር በመቃወም ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን መዝጋታቸውና በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች የሥራ ማቆም አድማ መደረጉን መዘገባችን አይዘነጋም:: በአዲስ አበባ ወይ ብላ ማርያም አካባቢ ሱቆች ተዘጋግተው የሚያሳዩ ፎቶዎች ደርሰውናል:: በሌላ በኩል በሽሮሜዳ አካባቢም በመጠኑ ሱቆችን የመዝጋት ተቃውሞ ተጀምሮ እንደነበር ምንጮች ገልጸው አንዳንድ ለሥርዓቱ ያደሩ ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን መክፈታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል:: እንደ ነዋሪዎች ገለጻ ከስርዓቱ ጋር ንክኪ ያላቸው እነዚህ ነጋዴዎች ከሕዝቡ ጋር የማይተባበሩ ሲሆን ሊደርስባቸው ለሚችለው ነገር ኃላፊነቱ የነሱ ነው ብለዋል::
Wednesday, July 19, 2017
ሆለታ ዝግ ሆና ዋለች – ወሊሶ ለ3ኛ ቀን ሥራ ማቆም አድማው ቀጥሏል * ተሳፋሪዎች ከአዲስ አበባ ወደ ወለጋና ሰሜን ሸዋ ለመሄድ ተቸግረዋል
(ዘ-ሐበሻ) አላግባብ ግብር ተጭኖብናል በሚል በሕወሓት መራሹ መንግስት ላይ “ግብር አንከፍልም” የሚል ሕዝባዊ ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ነው:: ዛሬ በሆለታ ከተማንግድ እና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ቆመው የዋሉ ሲሆን የመንግስት ኃይሎች በግድ ለማስከፈት ቢጥሩም እንዳልተሳካላቸው ለማወቅ ተችሏል::
ኅሊና እና መንገድ( ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)
...
አንድ ሰው ከሚያሳድዱት ሰዎች እየሸሸ ይሮጣል፡፡ ሊያመልጥ በሚችልባቸው መንገዶች ሁሉ እየተሹሎከሎከ ተጓዘ፡፡ ሰዎቹ እንዳያዩት ሊደበቅባቸው በሚችሉ አማራጮች ሁሉ ተፈተለከ፡፡ በስተ መጨረሻ እግሩ ከአንድ ግምብ አጠገብ አደረሰው፡፡ ግንቡ እጅግ ቁመታም እና ረዥም ነበር፡፡ ተንጠላጥሎ ለማለፍም ምንም ዓይነት መወጣጫ አልነበረውም፡፡ ምናልባት የሚያስገባ ቀዳዳ ባገኝ ብሎ የግንቡን ጥግ ተከትሎ ሮጠ፡፡ ነገር ግን እርሱ ደከመው እንጂ መገቢያ ሊያገኝ አለቻለም፡፡
አንድ ሰው ከሚያሳድዱት ሰዎች እየሸሸ ይሮጣል፡፡ ሊያመልጥ በሚችልባቸው መንገዶች ሁሉ እየተሹሎከሎከ ተጓዘ፡፡ ሰዎቹ እንዳያዩት ሊደበቅባቸው በሚችሉ አማራጮች ሁሉ ተፈተለከ፡፡ በስተ መጨረሻ እግሩ ከአንድ ግምብ አጠገብ አደረሰው፡፡ ግንቡ እጅግ ቁመታም እና ረዥም ነበር፡፡ ተንጠላጥሎ ለማለፍም ምንም ዓይነት መወጣጫ አልነበረውም፡፡ ምናልባት የሚያስገባ ቀዳዳ ባገኝ ብሎ የግንቡን ጥግ ተከትሎ ሮጠ፡፡ ነገር ግን እርሱ ደከመው እንጂ መገቢያ ሊያገኝ አለቻለም፡፡
Tuesday, July 18, 2017
አዲስ አበባ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ትፈነዳለች! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
እንደብሂላችን ጥሩ መመኘት ጥሩ ነበር፡፡ ግን ጥሩ ስለተመኙ ብቻ ሁሌ ጥሩ ይገኛል ማለት አይደለም፡፡ ታዲያንም አስገዳጅ ሁኔታ ሲፈጠር እውነቱን ተናግሮ እመሸበት ማደርን ይመርጧል እንጂ በባዶ ተስፋ የራስንም ሆነ የሌላን ሆድ አይቆዝሩም፡፡ እናም ቁርጣችሁን ዕወቁ – አዲስ አበባ – ከፈለጋችሁም ፊንፊኔ – ካሻችሁም አዶገነትና ሸገር በሏት- ልትፈነዳላችሁ እጅጉን ተቃርባለች፡፡ ጠብቁ! በኔ ግምት ከአንድ እስከ ሁለትና ምናልባትም ሦስት ዓመታት ውስጥ ለይቶላት ትፈነዳለች፡፡ ትንቢት አይደለም – በግልጽ የሚታይ ገሃድ እውነት ነው፡፡ በውጭ ያላችሁ ወይ ባገር ውስጥ ሆናችሁ ሁሉም ነገር የተመቻቸላችሁ ቅንጡዎች እርግጥ ነው ለእናንተ ሁሉም ነገር ቀኝ በቀኝ ሊሆንና በዓለም ዘጠኝ ልትምነሸነሹ ትችሉ ይሆናል- “ያልተነካ ግልግል ያውቃል” እንደሚባለው፡፡ እዚህ ግን በሁሉም ዜጋ አፍ የሚነገረው የሀገራችን ብቸኛው ምፅዓት እየመጣ እንደሆነ ነው፡፡
የሕሊና ዳኝነት እና ቀጣዩ ፈተና | ከኤርሚያስ ለገሠ
” ችግሩ ካልተፈታ የአማራ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልን እናደርጋለን!” ይሄን የተናገረው የብአዴን ካባ የለበሰውና አማራ ክልል ተብሎ የተፈጠረውን አስተዳደር ለረጅም ጊዜ የመራው አቶ አዲሱ ለገሰ አይደለም። ” ኦቦ!” ምን ጐድሎበት ይሄን ይላል። ” ላለፋት አስር አመታት አንድም አዲስ ማከፋፈያ አልተገነባ።” ይሄንንም ያለው የኢህአዴጉ ጐብልስ በረከት ስምኦን አይደለም። እሱስ ቢሆን ምን ጐድሎበት ። ” ያሉት 25 ሐይል ማከፋፈያ (substations) አብዛኛው በደርግ ጊዜ የተሰሩ ናቸው። አርጅተዋል። ቮልታቸው አነስተኛ ነው።
Monday, July 17, 2017
የዘፋኞች “እንጀራ” ከነእስክንድር ነጋ “እንጀራ” በላይ ነው
በጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ (ከፌስቡክ ገጽ የተወሰደ)
- ቦይኮቱ አስቴርና ጎሳዬን ሲነካ ደርሶ ድንገት የዘፋኝ መብት ተቆርቋሪ ለሆናችሁ
- ዘፋኞች የገዢው ስርዓት ድግሶችን ቢያደምቁ በንዴት “እቀባ አታድርጉባቸው:: እንጀራቸው ሆኖ እንጂ ሕዝቡን ይወዱታል:: የት ሄደው ይዝፈኑ?” ለምትሉ
አጋዚ በአምቦ ሁለት ወጣቶችን ተኩሶ ገደለ | በአድአ ከተማ ቀብር ከሚሄዱ ሰዎች መካከል ሰላሳዎቹ በአጋዚ ታፈኑ | ጊንጪ ዛሬ ሰኞ ንግድ ቤቶች ሁሉ ዝግ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል
(ዘ-ሐበሻ) በገንዘብ እጦት እየታመመ እንደሆነ በምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚተቸው ሕወሓት መራሹ መንግስት በሕዝቡ ላይ በጫነው አግባብ ያልሆነ ግብር ተቃውሞ እየተነሳበት እንደሆነ ዘ-ሐበሻ በተለያዩ ዜናዎች እየዘገበች ትገኛለች::
በአምቦ ከ4 ቀናት በፊት በጀመረው ሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ የተረበሸው የሕወሓት አጋዚ ሰራዊት ትናንት እሁድ ጁላይ 16, 2017 አምቦ ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ ሁለት ወጣቶችን ተኩሶ መግደሉን የዓይን እማኞች ገልጸዋል::
Sunday, July 16, 2017
የፀረ-ሽብር ሕጉ ዓላማ ሕዝቡን መሪ-አልባ ማድረግ ነው!
ስዩም ተሾመ
ባለፈው ጓደኛዬ ከአንድ ታዋቂ ምሁር ጋር አስተዋወቀኝና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየን። እኚህ ምሁር ቀድሞ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ መምህር የነበሩ ሲሆን አሁን ጡረታ ወጥተዋል። ቦሌ አከባቢ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ለሁለት ሰዓታት ያህል ተወያየን። ውይይታችን በዋናነት ያተኮረው ከኢህአዴግ መንግስት በፊትና በኋላ የሀገሪቱ የፖለቲካ ልሂቃን ሚና ምን ይመስላል በሚለው ዙሪያ ያተኮረ ነበር። እኚህ ምሁር ብዙውን ግዜ “The Amhara Hegemony” የምትለዋን አገላለፅ እንደሚያዘወትሩ ስለማውቅ የእኔም ጥያቄ ከዚያ ላይ ነው የጀመረው። “ዶክተር… ይህቺ ‘The Amhara Hegemony’ የሚሏት ነገር ፅንሰ-ሃሳቧ ምንድነው? በቀድሞ ስርዓት ‘የአማራ የበላይነት/አገዛዝ’ አለ ለማለት የቻሉበትን ምክንያት ቢያስረዱኝ?” አልኳቸው።
Thursday, July 13, 2017
አዲሱ የህወሓት ጋሻጃግሬ – ለማ መገርሳ (በያ ደሳለኝ)
በያ ደሳለኝ
ድፍን ኢትዮጵያ በአመፅ ስትናጥ ቆይታ ፣ መንግስት የአዲስ አበባን የማስተር ፕላን ትግበራ እንዳቆመው ከገለፀ ከጥቂት ጊዜያቶች በኋላ የጥምቀት በአልን በአዲስ አበባ ከድሮው መለስ ባለ ድባብ አከበርን፡፡ ታዲያ በጥምቀት ማግስት ፤ የሚካኤል ንግስ እለት አስራ አንድ ያክል ሰዎች ፣ በአንድ አባዱላ ሚኒባስ መኪና ሆነን ፣ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ወደሚበዙበት ለገጣፎ ጉዟችንን ጀመርን፡፡ የካራ አደባባይን ጥቂት አለፍ እንዳልን ፤ ታቦት አጅበው ባቅራቢያው ወደሚገኘው የሚካኤል ቤተክርስቲያን የሚመልሱ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች፤ በባህል ልብስ ነጭ ሆነው ከርቀት ታዩን፡፡ ቀረብ ስንል ግን ከነሱ ቁጥር የማይተናነስ ብዛት ያለው፣ የፖሊስ ግሪሳ ምእመናኑን ከቦ በተጠንቀቅ አብሮ እየተጓዘ እንዲሁ አየን፡፡
Wednesday, July 12, 2017
የተዳፈነ ገሞራ
የተዳፈነ ገሞራ
እነሆ በሐምሌ 5 ቀን , 2008 በመላ ኢትዮጲያ በተለይም በጎንደርና በኦሮሚያ ተቀጣጥሎ የነበረው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ከተከሰተ ድፍን አንድ አመት ሆነው። የኢትዮጲያ ሕዝብ በተደጋጋሚና በተለያየ መንገድ ለስርአቱ ያለውን ተቃውሞ ሲገልጽ ሩብ ምዕተ አመት ቢያስቆጥርም ያለፈው አመቱ ቁጣ ግን በቅርጹም በይዘቱም የተለየ ነበር። በዚህ የዘመናዊ አርበኝነት ትግል ውስጥ ከሁሉም ጎልተው የታዩትና የተሰሙት ሁለት አውራ መልዕክቶች ነበሩ። አንደኛው ሕዝብን ያላሳተፈ፣ ሕዝብ ተጠቃሚ ያልሆነበት ልማት ባፍንጫችን ይውጣ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እኛ ኢትዮጲያዊያን መቼ መቼም ቢሆን አንከፋፈልም የሚሉ ነበሩ።
እነሆ በሐምሌ 5 ቀን , 2008 በመላ ኢትዮጲያ በተለይም በጎንደርና በኦሮሚያ ተቀጣጥሎ የነበረው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ከተከሰተ ድፍን አንድ አመት ሆነው። የኢትዮጲያ ሕዝብ በተደጋጋሚና በተለያየ መንገድ ለስርአቱ ያለውን ተቃውሞ ሲገልጽ ሩብ ምዕተ አመት ቢያስቆጥርም ያለፈው አመቱ ቁጣ ግን በቅርጹም በይዘቱም የተለየ ነበር። በዚህ የዘመናዊ አርበኝነት ትግል ውስጥ ከሁሉም ጎልተው የታዩትና የተሰሙት ሁለት አውራ መልዕክቶች ነበሩ። አንደኛው ሕዝብን ያላሳተፈ፣ ሕዝብ ተጠቃሚ ያልሆነበት ልማት ባፍንጫችን ይውጣ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እኛ ኢትዮጲያዊያን መቼ መቼም ቢሆን አንከፋፈልም የሚሉ ነበሩ።
Monday, July 10, 2017
ቁርጥ ግብር – የህውሓት ገጀራ (ካሳ አንበሳው)
የሰሞኑ የማህበራዊ ሚዲያ አጀንዳ አዲስ አበባ ውስጥ በአነስተኛ የንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎች ላይ የተጣለው ከፍተኛ “ግብር” ነው፤ ይህ ግብር “ቁርጥ ግብር” ወይንም “Presumptive tax” በመባል ይታወቃል፤ “ቁርጥ ግብር” ታማኝ ያልሆኑ ዜጋ የሚቀላበት (የሚወገድበት) ሎሌ የሚተከልበት የህውሓት አንዱ ስውር ገጀራ ነው:: ይህ ገጀራ ከወያኔ የዕዝ ሰንሰለት ውጭ በንግድ ተሰማርተው የተገኙትን ዜጎች ይቀስፋል፤ የወያኔ ዕዝ <<የህብረት ስራ ማህበራት፣ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝስ ወ.ዘ.ተ>> በሚባሉ ስያሜዎች የሚታወቁት ናቸው፤ የወያኔ ገጀራው ከሰገባው የሚመዘዘው በአመት አንዴ ነው፤ ብዙ ዜጎችን ሙት እና ቁስለኛ ሳያደርግ ወደ ሰገባው አይመለስም፤ የዚህ ገጀራ ሰለባ ከሆኑት መካከል ጋሽ መሐመድ ሐሰን አንዱ ናቸው::
Sunday, July 9, 2017
ባንዳነት ጌጥ የሆነላቸው (መስቀሉ አየለ)
መስቀሉ አየለ
ቡልጋሪያ የምትባል የምስራቅ አውሮፓ ክፍል አለች። ለአራት መቶ አመት ያህል በቱርክ የእሳት ሰንሰለት ተጠፍንጋ የኖረች አገር ናት። የኦቶማን ቱርክን ጦር ቀጥቅጦ ወደ መቃብር የገፋላት የሩሲያ ጦር ነበር። ቡልጋዎች ይህን የነጻነት ቀን በያመቱ ሲያከብሩ የክብር እንግዳው የሚመጣው ከሩሲያ ነበር። ባለፈው አመት ግን ይኽ አልሆነም። በሶፊያ፣ ቡልጋሪያ የሚገኘው የ አሜሪካን አምባሳደር ተቆጣ አሉ፤ ተቆጥቶም አልቀረም ይልቁንም የክብር እንግዳው ከቱርክ መሆን አለበት ብሎ ቀጭን ትእዛዛ ያስተላለፈው ለአገሪቱ ፕሬዝዳንት ነበር።በጌታና የሎሌ ግንኙነት ወቅት ፕሮቶኮል ትርጉም የለውም።
የናዚ ጀርመን ጦር አውሮፓን እንዳይወር በወቅቱ የነበሩት መራሄ መንግስትታ ለሂትለር እጅ መንሻ የመስዋእት ጠቦት አድርገው የሰጡት ፖላንድን ነበር። ክፋቱ ሂትለር እርሷን በልቶ አለማቆሙ ነው እንጂ። ፖላንድን ከናዚ ጦር ነጻ ለማውጣት ስድስት መቶ አምሳ ሺህ የሩሲያ ጦር ነበር ያለቀው። በታሪኩ አሰቃቂ በተባለለት አስቸጋሪ የበረዶ ላይ ከበባ ዋጋ ለከፈሉትና ድፍን አውሮፓን ከናዚዝምና ከፋሽዝም ለታደጉት የሩሲያ ወታደሮች መታሰቢያ በፖላንድ ዋርሳው የቆሙትን ሃውልቶች ዛሬ ከአሜሪካ በላይ አሜሪካዊነት በሚሰማቸው የፖላንድ መሪዎች መፈራረስ በመጀመራቸው የሩሲያ መንግስት የወታደሮቹን አጽም በክብር ወደ አገሩ መልሶ ለማሳረፍ ቃል ገብቷል።ዛሬ ፖላንድ ማለት በምስራቅ አውሮፓ ውስጥ ያለች አንዱዋ የአሜሪካን ላፕዶግ መሆኗን በብዙ አጋጣሚ እያስመሰከረች ያለችበት ሁኔታ ነው ያለው።
Friday, July 7, 2017
እፉኝቶቹን ተሸክመን የመጓዝ ግዴታ የለብንም (መስቀሉ አየለ)
አጼ ኃይለስላሴ በአንድ ወቅት ኒውዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር። ወቅቱ የፓን አፍሪካኒዝም ስሜት ጣራ የነካበት፤ ባሪያ ፈንጋዮቹ አፍሪካን ጥለው መፈርጠጥ የጀመሩበት፣ አፍሪካውያን በንስሮቹ ባለራእይ ወጣት መሪዎች ኩዋሚ ንክሩሁማን፣ ጁሊየስ ነሬሬ፣ ጆሞ ኬንያታ ወዘተ መመራት የጀመሩበት፣ ለሶስት ሺህ ዘመን የአፍሪካ ሳይሆን የመካከለኛው ምስራቅ አካል ሆና ታሪኳን፣ ወግ፣ ባህል፣ ቋንቋና ሃይማኖቷን ጭምር ከቤተ እስራኤል ስትዋረስ የኖረችው አገራችን ለመጀመሪያ ግዜ ፊቷን ወደ ጎረቤት አፍሪካውያን የመለሰችበት እና ይልቁንም በባርነት ለኖሩት አፍሪካውያን የነጻነት ቀንዲል በመሆን የአፍሪካ ህብረትን በመናገሻዋ ያኖረችበት በዚህም እስከ ካረቢያን ያሉ አንድ በሁኔታው የተደመመ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ንጉሱን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፤ “ለመሆኑ ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? ” እርሳቸውም ቆፍጠን ባለ አነጋገር “ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ትህትና ነው” አሉት።
Wednesday, July 5, 2017
የሚንስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ ላይ የEDF አቋም መግለጫ
የኢትዮጵያ የውይይትና መፍትሔ መድረክ
የኢትዮጵያውያን የውይይትና ምክክር መድረክ (ኢውምመ) (EDF) በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የተመሰረተ መድረክ ሲሆን በኢትዮጵያ መሰረታዊ የኢኮኖሚ የማህበራዊና የፖለቲካዊ ችግሮች ዙሪያ ምርምሮችን እያካሄደ ለተፈላጊ ለውጦች የሚታገል ድርጅት ነው። የዚህ ድርጅት አመራር አባላት በቅርቡ በሚንስትሮች ምክር ቤት የወጣውን የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም የሚተነትነውን ረቂቅ አዋጅ በጥልቀት ተወያይቶበታል።
ተወያይቶ የሚከተለው መደምደሚያ ላይ ደርሷል በEDF እምነት በመጀመሪያ ደረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መሰረታዊ ችግር ከብሄር ፖለቲካ የመነጩ አንዳንድ የህገ መንግስቱ አንቀጾች ናቸው። ለዚህ ለአሁኑ የሚንስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅ መነሻውም ይሄው ህገ-መንግስቱ ላይ የተቀመጠው አንቀጽ 45 ንኡስ አንቀጽ 5 ነው። ህገ-መንግስቱ ከብሄር ፖለቲካ አስተሳሰብ በመነጨ የተቀረጸ በመሆኑ መግቢያው ላይ ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች አገር መሆኑዋን ሲገልጽ ለዜግነት ቦታ አልሰጠም። በአንጻሩ የብዙ ዴሞክራት ሃገሮች ለምሳሌ የተባበረችውን አሜሪካንን፣ አውስትሬሊያን፣ ህንድን ብንመለከት “እኛ” በሚል ይጀምራል። የአንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የተባበረ ማህበረሰብ እንደመሰረቱ በቃል ኪዳናቸው ላይ አስፍረዋል። ይህ መሰረታዊ እምነትና ቃል ኪዳን ለአንድ ሃገር ህልውና በጣም ወሳኝ ነገር ነው። ፖሊሲዎችና ህጎች ሁሉ ከዚህ ከህገ መንግስቱ የህግ ምንጮች የሚቀዱ በመሆናቸው ህገ መንግስቱ የአንድን ሃገር ህዝብ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ወጥነት ማረጋገጡ ቁልፍ ነገር ነው።
Subscribe to:
Posts (Atom)