Translate

Monday, January 16, 2017

ሂውማን ራይትስ ውች 2017 ሪፖርት፡ ኢትዮጵያ

Armed security officials watch as protesters stage a protest against government
የታጠቁ የመንግስት ወታደሮች በመስከረም ወር 2009 ዓ. ም በቢሾፍቱ ኢትዮጵያ በተከበረው የኢሬቻ በአል ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰዎችን ሲመለከቱ።
እ.ኤ.አ. ከህዳር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ በስፋት ትልቁ በሆነው በመላው ኦሮሚያ ክልል እና ከሃምሌ 2016ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በአማራ ክልል ያልተጠበቀ እና እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ተቃዉሞዎች ተደርገው ነበር። የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ባብዛኛው ሰላማዊ የነበሩትን ሰልፈኞች ለመበተን በወሰዱት የሀይል እርምጃ ከ500 በላይ ሰዎችን ተገድለዋል።


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ብሾፍቱ ከተማ ዓመታዊዉን የኢሬቻ በዓል ለማክበር በተሰበሰቡት የበዓሉ ታደሚዎች ላይ ፖሊስ የከፈተዉን ተኩስ እና አስለቃሽ ጭስ ለመሸሽ ሲሞክሩ በተፈጠረው የህዝብ መረጋገጥ የብዙ ሰዎች ህይዎት አልፏል። ወጣቶች የመንግስት ህንጻዎች እና የግል ንብረቶችን ማውደማቸውንም ተከትሎ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 9 ቀን መንግስት ለ6 ወር የሚቆይ አፋኝ እና መጠነ ሰፊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመላው የሀገሪቱ ክፍል አውጇል። አዋጁ የዜጎችን የመሰባሰብ፣ የመደራጀት እና ሀሰብን በነጻነት የመግለጽ የመሳሰሉ መብቶችን በእጅጉ ይገድባል። የአዋጁ መመሪያዎች ያለፍርድ ቤት ትዛዝ ዜጎችን በዘፈቀደ ማሰርን ጨምሮ ብዙ የጸጥታ ሀይሎች የወሰዱትን የጥቃት መንገዶች ህጋዊ ሽፋን አላብሶታል፡፡
የተቃውሞ ሰልፎቹ የተካሄዱት ምንም የፖለቲካ ተሳትፎ ክፍተት በሌለበት ሁኔታ ዉስጥ ነበር። የሀገሪቱ ፓርላማ ወንበሮች መቶ በመቶ በገዥው ፓርቲ ግንባር ተይዘው ነው ያሉት። በሲቪክ ማህበረሰብ እና ነፃ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ ገደቦች አሉ። መንግስትን በንቃት የማይደግፉ ግለሰቦች ጥቃት ይደርስባቸዋል፣ ያለፍርድ ቤት ትዛዝም ይታሰራሉ።
ኢትዮጵያ ወታደሮቿን የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ (አሚሶም) አካል አድርጋ ልካለች። እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም. ልዩ ፖሊስ የሚባሉትን ተወርዋሪ ወታደሮቿንም ጨምራ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጎን ለጎን ወደ ሶማሊያ አንዳሰማረችም ተዘግቧል።  ከአሚሶም ትዛዝ ዉጭ የሚንቀሳቀሱት የኢትዮጵያ ሀይሎች እ.ኤ.አ. ሃምሌ 2016 ዓ.ም. በሶማሊያ ቤይ ክልል ዉስጥ አልሸባብ ላይ እርምጃ በሚወስዱበት ወቅት 14 ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል። (የሶማሊያን ምዕራፍ ያንብቡ)

በነጻነት የመሰባሰብ መብት

እ.ኤ.አ. በ 2016 ዓ.ም.  መንግስት የአዲስ አበባን ማዘጋጃ ቤት ድምበር ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማስፋፋት ያቀረበው እቅድ ህዝቡን በማስቆጣት በመላው የኦሮሚያ ክልል መጠነ ሰፊ ተቃዉሞን ያስነሳ ሲሆን የመንግስት የጸጥታ ሀይሎችም ሰልፈኞቹ ላይ ከባድ የሀይል ምላሽ ሰጥተዋል። የአዲስ አበባ የተቀናጀ ልማት መርሃ ግብር ተብሎ የቀረበው እቅድ ላለፉት አስር አመታት ክስተቱ እየጨመረ የመጣውን እና የኦሮሞ ገበሬዎችን ከመሬታቸው ያፈናቅላል በሚል ስጋት ፈጥሯል።  እ.ኤ.አ. ጥር 2016 ዓ.ም. መንግስት ተቃዉሞ ያስነሳዉን የአዲስ አበባን መርሃ ግብር መሰረዙን ቢገልጽም ከዚህ በፊት በርካታ ቃል የገባቸውን ጉዳዮች ባለመፈጸሙ ምክንያት ይኄኛውም ብዙ ታማኝነት አላገኘም።  ሰልፈኞቹ ላለፉት አስርት ዓመታት የነበሯቸዉን ታሪካዊ ቅሬታዎች እና የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሚወስዶዋቸዉን እስከመግደል የሚያደርሱ የሀይል እርምጃዎች ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል። ሰልፈኞቹ በተወሰነ ቦታ አመጽ አንዳስነሱ ተዘግቦ ነበር ሆኖም በአብዛኘው ቦታዎች ግን ሰልፎቹ ሰለማዊ ነበሩ።  እ.ኤ.አ. በ2014 ዓ.ም.  ሚያዝያ እና ግንቦት ወር ዉስጥም ተመሳሰይ የተቃዉሞ ሰልፎች እና ተመሳሰይ የመንግስት አጸፋዎች ተወስደው እንደነበር ይታወሳል።
በሰልፎቹ ወቅት የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን፣ የጤና ባለሙያዎችን እና ከጸጥታ ሀይሎቹ የሚሸሹትን ሰልፈኞች ያስጠለሉትን ወይንም ያገዙትን ሰዎች ጭምር በገፍ አስረዋል።  ከታሰሩት ብዙዎቹ ቢለቀቁም ቁጥራቸው በዉል የማይታወቅ ዜጎች አሁንም ያለምንም የህግ ባለሞያ ድጋፍ እና ያለ ቤተሰብ ጥያቃ እንዲሁም  ክስ ሳይመሰረትባቸው ታስረው ይገኛሉ። በህጋዊነት ተመዝግበው የሚንቀሳቃሰው የተቃዋሚ ፓርቲየኦሮሞ ፌዴራልስት ኮንግረስ አመራሮች ሰላማዊ ትግልን በጽኑ በመስበክ የሚታወቀው የፓርቲው ምክትል ሊቀ-መንበር በቀለ ገርባን ጨምሮ   በጸረ-ሽብር ሕጉ ተከሰው ታስረዋል።
እ.ኤ.አ. በሃምሌ ወር ለረዥም ግዜ ያልተፈታ የድንበር ማካለል ችግሮችን ለመፍታት የሚንቀሳቀሰውን የወልቃይት ማንነት ኮሚቴ አባላትን መታሰር ተከትሎ የህዝብ ተቃዉሞው ወደ አማራ ክልልም ተስፋፍቷል። በ አማራ ክልል የተነሱት ተቃዉሞዎች በዋናነት ያልተመጣጠና እና ኢ-ፍትሃዊ የስልጣን እና የሃብት ክፍፍል ላይ ያተኮረ ቅሬታ ላይ ያተኮረ ነው። እ.ኤ.አ. ነሃሴ 6 እና 7  በመንግስት ጸጥታ ሀይሎች በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በባህርዳር ብቻ የተገደሉትን 30 ሰዎች ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎችን ተገድለዋል። ባህርዳር ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ለተቃዉሞ ታይቷል። በመላው የአማራ ክልል መጠነ ሰፊ አፈሳ ሲካሄድ እንደነበር ተዘግቧል።
እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር በደቡብ ብሄር ብሐረሰቦችና ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን ዉስጥ የአስተዳደራዊ ድንበርን አስመልክቶ በተነሳ የህዝብ ተቃዉሞ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በወሰዱት እርምጃ በደርዘን የሚቆጠሩ የኮንሶ ብሄር ተወለጆች ተገድለዋል።
በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በኮንሶ የተነሱትን የህዝብ ቅሬታዎች ለመፍታት መንግስት ምንም ፈቃደኝነት አላሳየም። ለተከሰቱት አለመረጋገቶች የመልካም አስተዳደር እጦት እና የወጣቶች ስራ እጦትን እንዲሁም የውጭ ሀይሎች የቀሰቀሱት ነው በሚል አስተባብሏል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በኮንሶ የተፈጸሙትን ግድያዎች በተገቢው መልኩ ለመመርመር አልቻለም። የመንግስት አካል የሆነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እ.ኤ.አ. በሰኔ ወር ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት የጸጥታ ሀይሎች የወሰዱት እርምጃ የተቃውሞ ሰልፍ አድራጊዎቹ ሊያደርሱት ከነበረው አደጋ አንጻር ተመጣጣን ነው በሚል መረጃዎች ከሚያሳዩት በተቃራኒ ደምድሟል።
እ.ኤ.አ. በጥቅምት ወር የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያ መንግስት   ምንም አይነት የተቃውሞ ሰልፍ ያለፈቃድ እንዳካሄድ አና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የጊዜ ገደብ እስኪጠናቀቅ ድረስ በኮማንድ ፖስቱ በተወስኑት ቦታዎች ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ እስር እንዲፈፀም ይፈቅዳል፡፡
የሶማሌ ክልል ልዮ ፖሊስ በመባል የሚታወቀውወታደራዊ ፖሊስ ከኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ጋር በሚዋጉበት ወቅት ከፍተኘ የሰብዓዊ መብት ጥሰታቸውን ቀጥለዉበታል። የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግምባርን ይደግፋሉ ተብሎ የሚገመቱ ዜጎች ያለ ፍርድ እንደሚገደሉ ፣ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ታስረው እንደሚቆዩ እና ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እንደሚሰነዘር የተለያዩ ዘገባዎች አሉ። እ.ኤ.አ. ሰኔ 12 ቀን  በአዉስትራሊያ ሜልቦርን የሶመሌ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አብዲ ኢሌይን የአውስትራሊያ ጉብኝት በመቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ የወጡት ሰዎች መካከል በደርዘን የሚቆጠሩ በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦች  ቤተሰቦች ታስረዋል።

ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ እና የመደራጀት መብት

መገናኛ ብዙሃን አሁንም በመንግስት ቁጥጥር ስር እንደወደቀ ነው። እ.ኤ.አ. 2016 ዓ.ም. መጨረሻ የታወጃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የባሰዉኑ አዳፍኖታል። በርካታ ጋዜጠኞች ምርጫ ራስን በራስ ሳንሱር ከማድረግ፣ ለትቃት ከመጋለጥ፣ ከመታሰር እና ሀገር ጥሎ ከመሰደድ አጣብቂኝ አማራጮች ውስጥ ወድቀዋል።  እ.ኤ.አ. ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ቢያንስ 75 ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው ተሰደዋል። ጋዜጠኞችን ከማስፈራራት በተጨማሪ መንግስት ገለልተኛ መገናኛ ብዙሃንን የሚገድብበት ዘዴዎች አሳታሚዎችን፣ የማተሚያ ተቋሞችን እና አከፋፈዮችን ማትቃት ያካትታል፡፡
እስክንድር ነጋ እና ዉብሸት ታዬን ጨምሮ በርካታ ጋዜጠኞች፣ ተቃዉሞ ሰልፈኞች እና የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች በጸረ ሽብር ህግ ስር ተከሰው ታስረዋል። ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በህዳር ወር ዉስጥ የመንግስት ስም አጥፍተሃል በሚል ክስ ጥፋተኛ ተብሎ የአንድ ዓመት ዕስር ተፈርዶበታል። ጦማሪ ዘላለም ወርቃገኘሁ 700 ቀናት በእስር ከቆየ በኃላ እ.ኤ.አ. ግንቦት 10 ቀን በጸረ ሽብር ህጉ ጥፋተኛ ተብሎ 5 ዓመት ከ 2 ወር እንዲታሰር ተፈርዶበታል። ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው እ.ኤ.አ. ነሃሴ 2015 ዓ.ም.  በጸረ ሽብር ህጉ ጥፈተኛ ነህ ተብሎ 4 ዓመት ከታሰረ በኃለ እ.ኤ.አ. መስከረም 10 በይቅርታ ከዕስር ተለቇል።
መንግስት የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን መጠቀሚያ መንገዶችን በወሳኝ ጉዳዮች ላይ የመንግስትን ትረካ የሚያከሽፉ ድረ-ገጾችን በመደበኛነት ይገድባል። በኢሬቻ በዓል የተከሰተውን የህዝብ መረጋግጥ ጨምሮ አሳሳቢ ሁናቴዎች በሚከሰቱበት ወቅት መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ አቋርጧል።
የኢትዮጵያ መንግስት እ.ኤ.አ. በነሃሴ እና መስከረም ወሮች ዉስጥ የጀርመን ድምጽ ራዲዮን እና የአሜሪካ ድምጽ ራዲዪየመሳሰሉትን አለም ዓቀፍ ጣቢያዎችን ስርጭት ሞገድ ያግዳል። ማህበራዊ መገናና ብዙሃን እና  የዲያስፖራ ቴሌቭዥን ጣብያዎች መረጃዎችን በማሰራጨት እና ህዝብን በማነሳሳት ሁነኛ ሚና ተጫውተዋል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ዜጎች የዲያስፖራ ቴሌቭዥን ጣብያዎችን እንዳይከታተሉተከልክሏል፣ መረጃዎችን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አንዳያጋሩ ተከልክሏል፣ የንግድ ተቋሞቻቸዉን ለአድማ ብሎ እንዳይዘጉ ተከልክሏል እንድሁም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከመገናኛ ብዙሃን ጋር እንዳይነጋገሩ በር ዘግቶዉባቸዋል።
እ.ኤ.አ. የ2009ዓ.ም. የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ ገለልተኛ የሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንደገደበ ነው። አዋጁ ድርጅቶቹ ከዓመታዊ ገቢያቸው 10 በመቶ በላይ ከዉጪ ሀገር የሚያገኙ ከሆነ ሰብዓዊ መብቶች፣ መልካም አስተዳደር፣ ግጭት አፈታት፣ የህጻናት፣ የሴቶች እና የአካል ጉዳተኖች ጉዳይ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ አንዳይሰሩ ይከለክላል።
የመንግስትን የልማት ፖሊስዎች መተቸት እጅግ አደገኛ ጉዳይ ሲሆን  ተሟጋቾች ይህን ካደረጉ ክስ ይመሰረትባቸዋል። በምሳሌነት ለአለም ባንክ የቁጥጥር ቡድን የባንክ ኢንቨስትመንት በደሎችን ለመመርመር በአከባቢው ሲንቀሳቀስ በአስተርጓሚነትና መንገድ መሪነት ሲያገለግል የነበረው የፓስተር ኦሞት አግዋ እ.ኤ.አ. እስከ 2016 ዓ.ም. ቀጥሏል።   ከኦሞት ጋር የተከሰሱት ሁለት ሰዎች በህደር ወር ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል። ተከሳሾቹ  እ.ኤ.አ. መጋቢት 2015 ዓ.ም. ወደ ኬንያ ናይሮቢ ምግብ ዋስትና ላይ የተዘጋጀ ውይይት ላይ ለመሳተፍ ከቦሌ አየር መንገድ ሊነሱ ሲሉ ነው ተይዘው በቁጥጥር ስር ከቆዩ በኃላ እ.ኤ.አ. መስከረም 7 ቀን 2015 ክስ የተመሰረተባቸው።

የእስር ቤት ስቃይና በዘፈቀደ መታሰር

የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ሲቪል ለበስ የጸጥታ እና የደህንነት ሃይሎችን ጨምሮ ፌዴራል ፖሊስ፣ ልዩ ፖሊስ፣ እና ወታደሮች  በህጋዊ እና ድብቅ ማቆያ ቤቶች ዉስጥ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ቃል እዲሰጡ እና መረጃ ለማወጣታት ይገርፏቸዋል አልያም ያልተገባ አያያዝ ይፈጽሙባቸዋል። በቅርቡ በተካሄደው ሰለማዊ ሰልፍ ላይ ተያይዞ ከታሰሩት አብዛኞቹ በአስር ቤቶች እና በወታደር ካምፖች ጨምሮ  ስቃይ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። በርካታ ሴቶች በዕስር ቤት ዉስጥ መደፈራቸዉን አሊያም የወሲብ ትንኮሳ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። እንደዚህ  አይነት የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ የጸጥታ ሀይሎች ምርመራ ስለመካሄዱ አሊያም ስለመቀጣታቸው ምንም ፍንጭ የለም።
ከአዲስ አበባ መስፋፋት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የንግድ እና ኢንዱስትሪ እድገት ጋር እንዲሁም በታችኛው የኦሞ ወንዝ ሸለቆ የሚካሄደው የመንግስት ስኳር ልማት ተክል መስፋፋት ምክንያት አስገድዶ የማፈናቀል ውንጀላ ይጠቀሳል፤ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ቦታ ሲሆን  በኦሞ ሸለቆ የሚኖሩ ህዝቦች የሣር ግጦሽ ቦታዎችን እና  የኦሞን ወንዝ እንዳይጠቀሙ ተደርገዋል። ከኦሞ ወንዝ ጀርባ ያለው የግልገል ጊቤ 3 ግድብ እ.ኤ.አ. ከጥር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ግድብ የመሙላት ሂደት ተጀምሯል። ከዝህ የተነሳ እ.ኤ.አ. በ2015 ዓ.ም. ምንም ሰው ሰራሽ ጎርፍ ኣልነበርም ። እ.ኤ፣አ. በ2016 ዓ.ም. ጎርፍ ይኖራል ብሎ መንግስት ቃል ቢገባም በጣም አነስተኛ ጎርፍ ብቻ ነበር የተለቀቃው። ጎርፉ ለቱርካና ሀይቅ ሚዛን መጠበቅ እና በኦሞ ወንዝ ዳሪቻ ለሚገኙት የዕርሻ ማሳዎች አስፈላጊ ነው።

ዋና ዋና  ዓለም ዓቀፍ ባለድርሻ አካላት

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን የምታስተናግድ ሀገር በመሆኖዋ ምክንያት የአካባቢው ሃገራት ቡድን ዋና ተዋናይ በመሆኗ፣ የዓለምዓቀፉ መንግስታት ሰላም ማስከበር ተልዕኮ አካል በመሆኗ፣ በከባቢው የጸረ ሽብር አጋር በመሆኗ፣የስደተኞችና የእርዳታ ጉዳይ ላይ ከምዕራብ መንግስታት ጋር ላለት አጋነት፣ እንዲሁም በልማት በኩል ወደፊት እየተራመደች ነው በሚለው እሳቤ ከዉጪ ለጋሾች እና ከጎረቤት ሀገሮች ከፍተኛ ድጋፍ እያገኘች ነው። ኢትዮጵያ ለብዙ ስደተኞች መነሻ፣ መሸጋገሪያ እና ተቀባይም ጭምር ነች።
የኢትዮጵያ መንግስት ሰልፈኞች ላይ የወሰደው ጭካኔ የተሞላበት አፈና እና ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የኢትዮጵያ አጋሮች ሳይቀር ከሌላው ጊዜ የተለየ መግለጫዎችን እንዲያወጡ አስገድዷል። የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ሰብዓዊና ህዝባዊ መብት ኮሚሽን ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው መግለጫ  አውጥተዋል። የአዉሮፓ ህብረት ፓርላማ ጠንካራ ነዉ የሚባል የማሻሻያ ሀሳብ ሲያወጣ፣ የአሜሪካ ህግ መወሰኛ እና የህዝብ ተወካች ምክር ቤት ዉስጥም ኣንድ ረቂቅ ተዋውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኢትዮጵያ የሃምሌ ወር የተፈጸሙ ግድያዎችን በተመለከተ  በአለማቀፍ የምርመራ ቡድን እንድጣራ ይፋ ጥሪ አስተላልፏል። እንደ አለም ባንክ ያሉ ሌሎች ለጋሾች ምንም እንዳልተፈጠረ አንድም ግልጽ የሆነ መግለጫ ሳይወጡ የተለመደ ስራቸዉን ቀጥለዋል።
እ.ኤ.አ. በሰኔ ወር ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ተመርጣለች። ምንም እንኳን ከተባበሩት መንግስታት ልዩ አጣሪ ቡድን ጋር ያለመተባበር ታሪክ ቢኖራትም የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆናለች። ኢትዮጵያ ይሄን ሁሉ ድርሻ እያላት እንኳን የኤርትራ ልዩ አጣሪ ቡድን እ.ኤ.አ. በ2006 ዓ.ም. ከገባ በኃላ የተባበሩት መንግስታት ልዩ የሰብዓዊ መብት ቡድን ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዳይገባ አግዳለች።

No comments:

Post a Comment