(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉት በሰበታ፣ ዓለም ገና፣ በፉሪና አየር ጤና ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ በመውጣት በመንግስት ላይ ተቃውሞውን በማሰማት ላይ መሆኑ ተሰማ:: ለዘ-ሐበሻ የመጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በነዚህ ከተሞች የንግድ እንቅስቃሴዎች ቆመዋል::: ሕዝቡን ለመበተን የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች እየተኮሱ መሆኑ ተሰምቷል::

በቅድሚያ በፉሪ የጀመረው ተቃውሞ ወደ አየር ጤና የተዛመተ ሲሆን ዓለም ገና እና ሰበታም በሕዝብ ተቃውሞ እየተደበላለቁ ይገኛሉ::
ከፉሪ እስከ ጆሞ ድረስ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልላዊ ፖሊስን ዩኒፎርም የለበሱ የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች እንደወረሩት ሲሰማ ሕዝቡን ለመበተንም ተኩስ ከፍተዋል::
በቅድሚያ በፉሪ የጀመረው ተቃውሞ ወደ አየር ጤና የተዛመተ ሲሆን ዓለም ገና እና ሰበታም በሕዝብ ተቃውሞ እየተደበላለቁ ይገኛሉ::
ከፉሪ እስከ ጆሞ ድረስ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልላዊ ፖሊስን ዩኒፎርም የለበሱ የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች እንደወረሩት ሲሰማ ሕዝቡን ለመበተንም ተኩስ ከፍተዋል::
በፉሪ ሱቆች እና ካፌዎች በአጠቃላይ ንግድ እንቅስቃሴ መቆሙም ተዘግቧል:: ጆሞ አካባቢ ልጆቻቸውን የሚያስረምሩ ወላጆች ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ልጆቻቸውን እያወጡ ሲሆን በነዚህ አካባቢዎች ትራንስፖርት መቆሙም ታውቋል::
በአዲስ አበባ አለምገና በሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ንብረቶች ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን የአካባቢው ወጣቶች መንገዶችን በመዘጋጋት ትግሉን በማቀጣጠል ላይ ነው::
አሁን በደረሰን መረጃ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወደ ሕዝብ በመተኮስ በርካታ ወጣቶችን አቁስሏል::
No comments:
Post a Comment