"ህወሃት የመቀበሪያ ጉድጓዱን በጥልቅ የቆፈረበት አዋጅ ነው"
ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም የሚገዛው ህወሃት ላለፉት 25ዓመታት መብት በገፍ ሲሰጥ የቆየ ይመስል ህገመንግሥታዊ መብቶችን የሚገፍ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። አዋጁ ለስድስት ወር ይቆያል ማለቱ የህወሃት ዕድሜ ከስድስት ወር እንደማይቆይ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
ከህወሃት በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ኃይለማርያም ደሳለኝ ትላንት እሁድ በሃገሪቱ “ያንዣበበውን አደጋ ለመቀልበስ” በሚል ሚኒስትሮች ምክር ቤት ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማወጁን አስታውቋል። እንደ ኃይለማርያም ንግግር ህገመንግሥታዊ መብቶች የማይጣሱ መሆናቸው ቢነገርም እዚያው የኃይለማርያም ካቢኔ አባል የሆነው የጠቅላይ አቃቤ ሹመኛው ጌታቸው አምባዬ ህወሃት በቀጣይ እንደፈለገ የሚያደርጋቸውንና የሚገድባቸውን መብቶች በዝርዝር ተናግሯል። እነዚህም:-
1) ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማንኛውንም ሰው ይታሰራል፤ (ለ25 ዓመታት ሲደረግ ነበር)
2) ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የማንኛውም ሰው ቤት፣ ንብረት፣ ይበረበራል፤ (ለ25 ዓመታት ሲደረግ ነበር)
3) ይፋይም ይሁን የህቡህ ቅስቀሳ ይከለከላል፤ (ለ25ዓመት ተከልክሎ ነበር፤ እስርቤት የታጎሩት ምስክር ናቸው)
4) ጽሁፍ ማዘጋጀት፣ ማተምና ማሰራጨት ይከለከላል፤ (ጋዜጠኞችን በማሰር፣ ከአገር በማባረር፣ … ህወሃት የሚገዛት ኢትዮጵያ ቀዳሚ ነች)
5) ትእይንት ማሳየት ይከለከላል፤ (ላለፉት 25ዓመታት ተከልክሏል)
6) በምልክት መግለጽ ይከለከላል፤ (የአማራ ተጋድሎና የኦሮሞ ተቃውሞን ምልክቶች ለመገደብ የታሰበ)
7) መልእክትን በማናቸውም መንገድ ለህዝብ ይፋ ማድረግ፤ (ማኅበራዊ ሚዲያ በተለይ ፌስቡክን ለመገደብ ትዊተርን ለማነቅ የታቀደ)

በዚህ ገለጻ ጌታቸው አምባዬ ከአለቃው ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በግልጽ የሚጋጭ መልስ ሰጥቷል፡፡
ያስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ካልወጣበት ቀን (ከቅዳሜ) ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል ተብሏል፡፡ ሟቹ መለስ በ1997ቱ ምርጫ ለአንድ ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲለፍፍ ወሩ ሲሞላ አዋጁ ስለመነሳቱ የተነገረ አለመኖሩ አገሪቱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነበረች የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ህወሃት አሁን በለፈፈው ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተፈጠረው ችግር “በጥልቅ መታደስ” ስላቃተው በጥልቅ ለመግደል ማሰቡ የራሱን መቀበሪያ ጉድጓድ በጥልቅ የቆፈረበት አዋጅ ነው ተብሏል፡፡
No comments:
Post a Comment