የሙሉነህ ዮሐንስ ዘገባ
*ከጎንደር ከተማና ከትግራይ አቅጣጫ የሚመጡ ከ200 በላይ መኪናዎች ታግተው ውለዋል።
*ያስተዳደር የፍትህና መሰል የመንግስት ህንፃዎች በድብደባ ተሰባብረዋል።
*ከፍተኛ የሆነ የተኩስ እሩምታ ቀኑን ሙሉ ውሏል።
*አመፁ ባካባቢው ከሰፈረው ታጣቂ አቅም በላይ ስለሆነ የፌደራል ሃይል እየገባ ነው።
*ብዙ ሰውና ንብረት ላይ መጠኑ ያልታወቀ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
*ትራንስፎርመር ጭና የነበረችው መኪና በእሳት ጋይታለች።
*ትራንስፎርመር ነቃዮቹ 25 ኪ.ሜ. እርቀው በደባርቅ ፖሊስ ጥበቃ ስር እንደሚገኙ ታውቋል።
*ያስተዳደር የፍትህና መሰል የመንግስት ህንፃዎች በድብደባ ተሰባብረዋል።
*ከፍተኛ የሆነ የተኩስ እሩምታ ቀኑን ሙሉ ውሏል።
*አመፁ ባካባቢው ከሰፈረው ታጣቂ አቅም በላይ ስለሆነ የፌደራል ሃይል እየገባ ነው።
*ብዙ ሰውና ንብረት ላይ መጠኑ ያልታወቀ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
*ትራንስፎርመር ጭና የነበረችው መኪና በእሳት ጋይታለች።
*ትራንስፎርመር ነቃዮቹ 25 ኪ.ሜ. እርቀው በደባርቅ ፖሊስ ጥበቃ ስር እንደሚገኙ ታውቋል።
*የስርአቱ የጎንደር ዞን አስተዳዳሪን ጨምሮ ብዙ ባለስልጣናት በከፍተኛ ጥበቃ ታጅበው ህዝቡን ለማረጋጋት እየተለማመጡ ይገኛሉ። ህዝቡ ግን ዳባትን የት ታውቋታላቹህ ድሮም ወያኔን ለብዙ አመታት ስለተዋጋነው እንደ ጠላት ነው የምታዩን። ምንም አይነት መሰረተ ልማት ለ25 አመት ሙሉ እልተቋቋመም። እጣ የወጣልን ሆስፒታል ነጥቃችሁ ደባርቅ ነው የምትሰሩት። የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤትና ላይብረሪ አልሰራም ስላላችሁ ውጭ አገር ባሉ የዳባት ተወላጆችና በህዝብ ነው የሰራነው። ከዳባት አጅሬ ጠገዴ የመንገድ ጥርጊያ በህዝብ ርብርብ ቢስተካከልም መንገዱን መንግስት ተረክቦ አልሰራ በማለቱ እስካሁን ህዝባችን በበሽታ በወንዝ ሙላትና በረዥም የእግር ጉዞ እየተሰቃየ ነው። ወልቃይት ጠገዴ ለዘመናት ሁሌም በዳባት ወረዳ ሲስተዳደሩ የነበሩት በሃይል ወደትግራይ መወሰዱ ያንገበግበናል አሁንም ይመለሱ በማለት አቋሙን እየገለፀ ነው። ይህች ጥንታዊ ውብና ታሪካዊ ከተማ ፍርስርሷ እንዲወጣ ተደርጓል በማለት ህዝቡ የወያኔ አስተዳደር በቃ ብሏል።
ዳባት ከተማ በቅርብ ጊዚያትም የህዝባዊ አመፅ በተደጋጋሚ አስተናግዳለች። ያሁኑ አመፅ መነሻ ግን ደርግ የተከለውን ትልቅ ትራንስፎርመር ነቅለው ወደትግራይ ሲወስዱ በዳባት ከተማ ቆፍጣና ወጣቶች እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው ነው።
ዳባት ከጎንደር ከተማ ወደ ሰሜን በኩል 75 ኪ. ሜ. እርቀት ላይ እጅግ ባማረ መልካ ምድርና ወይና ደጋ አየሯ ትታወቃለች። የገናናው የራስ አያሌው ብሩ መናገሻ ከተማም ናት።
No comments:
Post a Comment