Translate

Wednesday, June 15, 2016

የህወሀት ወንጀለኞች ያልተመዘገበ ቦንድ ባሜሪካ ሲሸጡ ማጅራቸዉን ተያዙ!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
T-TPLF Criminals Nabbed in America Selling Unregistered Bonds!
ባለፈው ሳምንት የዩኤስ አሜሪካ የቦንድ እና አክስዮን ልውውጥ  ኮሚሽን/U.S Securities and Exchange Commission (SEC) በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ለአራት ዓመታት ያልተመዘገበ ህገ ወጥ የቦንድ ሽያጭ በማካሄድ ያገኘውን 6.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲመልስ  (ዲስጎርጅመንት ወይም በትክክል ስተርጎም “ማስተፋት”)  ቅ ጣት  በይኖበታል ።

(ዲስጎርጅመንት ወይም  “ማስተፋት”  በአሜሪካን ሕግ ማለት  አንድን ዋጋ ያለውን ነገር በህገወጥ መልክ ወይም ደግሞ የሞራል ስብዕናን በጣሰ መልኩ የተገኘን ትርፍ ለባለመብቱ አካል መልሶ እንዲያስረክብ የሚያስገድድ ሕግ ማለት ነው።)  የዘ-ህወሓት ገዥ ቡድን ተገዶ 6.5 ሚሊዮን ዶላር  በሕገ ወጥ ዘዴ የበላዉን አጠፋለሁ ብሎ ለአሜሪካ የቦንድ እና አክስዮን ልውውጥ  ኮሚሽን በፊርማ አረጋገጧል ።
ይህ ትችት በእርግጥ ትንሽ ቴክኒካዊነት አጠቃቀምን የያዘ በመሆኑ ከሕግ አንጻር ሲታይ ለአንዳንድ ሕግን አጥብቀው ለማይከታተሉ አንባቢዎች ትንሽ ለመረዳት አስቸጋሪ ፅሁፍ ሊሆን ይችላል።
ሆኖም ግን የውይይቱ ዋና ዳህራ ግን ሙሉ በሙሉ ትክኒካዊ አይደለም፡፡ ዘ-ህወሀት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በኢትዮጵያውያን የዲያስፖራ ማህበረሰብ ላይ ያካሄደውን መጠነ ሰፊ ማጭበርበር በቀላሉ የሚተርክ ነው፡፡
ዘ-ህወወሀት የ”ሕዳሴው ግድብ” እያለ በሚጠራው ግድበ  ሰበብ የዲያስፖራ ደጋፊ ኢትዮጵያውያንን እና በዩናይትድ ሰቴትስ ያሉ ለእርሱ ቀረቤታ ያላቸውን ሌሎችን ሰዎች በገንዘብ መዋጮ እንዴት ማንቁርታቸዉን አንቆ እያለባቸው እንደሚገኝ የሚተርክ ነው፡፡
ዘ-ህወሀት የቦንድ ሽያጭ ፕሮግራም በሚል ድብቅ ማጭበርበርያ ዘዴ ለአራት ዓመታት ያህል በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን እንዴት አድርጎ ገንዘባቸውን ሲዘርፍ እንደቆየ የሚተርክ ነው፡፡
ማጭበርበር እና ሙስና ለዘ-ህወሀት ወንጀለኛ ድርጅት የህይወት ዘይቤው ነው፡፡
በእርግጥ ማጭበርበር እና ሙስና በዘ-ህወሀት የፖለቲካ ሰውነት የደም ዝውውር ውስጥ ሄሞግሎቢን እና ፕላዝማ ነው፡፡
ዘ-ህወሀት መዳፍና ጫማ  ቁጥጥር ስር ያለችው ኢትዮጵያ “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር” በሚል ርዕስ ዓለም ባንክ 448 ገጽ ያለው መጠነ ሰፊ የሙስና ዘገባ ያወጣባት ከዓለም ብቸኛዋ ሀገር ናት፡፡
ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ለማጭበርበር እና የጉዳት ሰለባ ለማድረግ ዘ-ህወሀት የፈጸመው ሸፍጥና ዘረፋ ገና ወደፊት በስፋት የሚነገር ነው፡፡
ለአራት ዓመታት ገደማ ያህል  በምጽፋቸው የ”ሰኞ ትችቶቼ” አማካይነት የሕዳሴው ግድብ እየተባለ የሚጠራው የቦንድ ሽያጭ ዘ-ህወሀት ዲያስፖራ የኢትዮጵያውያንን ኪስ እያለበ በእራሱ ኪስ የሚያጭቅበት እና በውጭ ሀገር በሚገኙ የሂሳብ አካውንቱ የሚያስቀምጥበት የማታለያ ስልቱ ነው በማለት ስናገር ቆይቻለሁ፡፡
ይሄው አሁን  እውነቱ  ወጣ!  ጉዱ ወጣ !
ከሶስት ዓመታት በፊት ጀምሬ ስሰጠው የነበረው ማስጠንቀቂያና  በየጊዜው ስተነብየው የነበረው የሀህዋሃት ወንጀለኛነት በእርግጠኝነት ባሜሪካ ሕግ ተረጋግጦ ላለም ህዝብ በገሃድ በምወጣቱ ከፍ ያለ ደስታ ሰጥቶኛል!
በውነቱ  ዘ-ህወሀት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ወንጀል ከመፈጸም እራሱን ነጻ ቢያደርግ ደስ ይለኝ ነበር ። ዘ-ህወሀት በዩናይትድ ስቴትሰ አሜሪካ ውስጥ ያልተመዘገቡ ቦንዶችን ወንጀለኛ በሆነ መንደድ ባይሸጥ አንዴት ደስ ባለኝ ነበር። ግን በማያታጠራጥር   መንገድ  ዘ-ህወሀት  አሜሪካን አገር ዉስጥ ከፍተኛ ወጀል ፈፅሟል። (ለዚህም  ወጀል አፈጣጠም  የ1933 የ”ደህንነት ድንጋጌን” (1933 ሴኩሪቲ  አክት ክፍል 20 (b) ይመልከቱ፡፡)
አውነቱን ለመናገር ዘ-ህወሀት ሞጭላፊ እጁን ከማሰሮው ውስጥ እንዳስገባ እጅ ከፍንጅ በመያዙ እና በሰራው ወንጀልም ተጠያቄ እንዲሆን በመደረጉ ከፍ ያለ ደስታ ይሰማኛል፡፡
ለበርካታ ዓመታት ብዙ ጊዜ ትንበያዎችን ስሰጥ ቆይቻለሁ፡፡ አብዛኛ ዎ እውን እንደሆኑ አምናለሁ፡፡
አሁን ደግሞ ዘ-ህወሀት እስከ አሁን ድረስ ለፈጸማቸው ከፍተኛ ወንጀሎች፣ በሰው ልጆች ላይ ለፈጸማቸው ወንጀሎች እና በኢትዮጵያ ላይ ስለፈጸማቸው ወንጀሎች ተጠያቂ አንደሚሆን አለምንም ጥርጥር አረጋግጣለሁ።
እኮ መቼ?
ዘ-ህወሀትን ጠይቁ፡፡ ዘ-ህወሀት  መቼ እንደሆነ በሚገባ ያውቁታል፡፡
ሆኖም ግን…
ይኸ እንደሚሆን አስቀድሜ ነግሪያቸዋለሁ!!!
ዘ-ህወሀትን ነግሪያቸዋለሁ!
ያንን ወንጀለኛ ድርጊት እንዳያደርጉ ለዘ-ህወሀት ደናቁርት አስቀድሜ ነግሪያቸው ነበር!
ለዘ-ህወሀት ወንጀለኞች ያልተመዘገበ ቦንድ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ውስጥ እንዳይሸጡ ነግሪያቸው ነበር፡፡ (ቦንድ ማለት ኢንቨስተሩ በሚታተም የወረቀት ቃልኪዳን ገንዘቡን ለመንግስታዊ አካል የሚያበድርበት መንግስትም የተበደረውን ገንዘብ በተለዋዋጭ ወይም ደግሞ በውሱን የወለድ መጣኔ ክፍያ አማካይነት የተወሰነን ተግባራት ለምሳሌ ያህልም የህዝብ ፕሮጀክትን ለመተግበር እንዲውል የሚያደርግበት የዕዳ ኢንቨስትመንት ነው፡፡)
ለዘ-ህወሀት ወንጀለኞች እንዴት አድርገው በትክክል ሕጋዊ በሆነ መንገድ ቦንድ ባሜሪካ መሸጥ አንደምችህሉ በዝርዝር አስረድቻቸው ነበር ።
በደንብ አድርጌ ደግሜ ደጋግሜ ለዘ-ህወሀት ወንጀለኞች  ተናግሪያለሁ! ተናግሪያለሁ! ተናግሪያለሁ!
ሆኖም ግን የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች እንደዚህ ያሉ ድርጊቶች ወንጀል መሆናቸውን እያወቁ  አሜሪካ ያልተመዘገቡ ቦንዶችን መሸጣቸውን በመቀጠል ገንዘብ ማሰባሰብ እና ማጭበርበራቸውን ቀጠሉ፡፡
ዘ-ህወሀቶች እያደረጉ ያሉት ድርጊት ያለጥርጥር ህገ ወጥ ነው እየተባለ በአደባባይ ከተነገራቸው በኋላ ጆሮ ዳበ ልበስ በማለት በአሜሪካ ውስጥ ያልተመዘገበ ቦንድ መሸጡን የቀጡለበት ምክንያት ምንድን ነው?
መልሱ እንዲህ የሚል አጭር እና ቀላል ነው፡
ዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከግድያ እና ከእልቂት ወንጀሎች ተጠያቂነት አምልጠዋል፡፡
ዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ምርጫን በአደባባይ እየዘረፉ ከ ተጠያቂነት አምልጠዋል፡፡  ባለፈው ዓመት ምርጫውን መቶ በመቶ አሸነፍን በማለት አውጀዋል፡፡ አዎ አውነት ነው መቶ በመቶ! (የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ አድርቅ ይባላል ።)
ዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በቢሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካን ዶላርን እየዘረፉ በውጭ በሚገኙ የባንክ ሂሳቦቻቸው እያጨቁ እና በውጭ ሀገር ኢንቨስት እያደረጉ ከዚህ ወንጀላቸው ለማምለጥ ጥረት አድረገዋል፡፡ (እንደ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ ዘገባ ከሆነ 365 የአሜሪካ ዶላር የነፍስ ወከፍ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ያላት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2000 እና በ2009 ህገ ወጥ በሆነ የፋይናንስ ዝውውር ምክንያት 11.7 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ህገ ወጥ በሆነ መንገድ አጥታለች፡፡)
የህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት “አንድ መቶ ዓይነት የቁጥጥር መንገዶች፡ በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ እና የመደራጀት መብት ጥሰት” በሚል ርዕስ ባወጣው ዘገባ ስልጣናቸውን ለማጠናከር ለእርዳታ የመጣን እህል እየዘረፉ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ለፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያነት ሲያውሉት ከቆዩበት የወንወጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ ጥረት አንደሚያደርጉ ማሰርጃ አቅረቧል፡፡
የህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም ዓይነት ሰብአዊ ወንጀሎች እና በይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት እና የይስሙላ ፓርላማው አማካይነት የሕግ የበላይነትን እየደፈጠጡ ከተጠያቂነት ወንጀል ለማምለጥ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
የህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ እና እልቂት እየፈጸሙ  ካሉበት አሰቃቂ ወንጀል ለማምለጥ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
የህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ወንጀልን በወንጀል ላይ እየደራረቡ የዩናይትድ ስቴት መንግስትን ጨምሮ ከጸሐይ በታች እነርሱን ለሕግ የሚያቀርብ እና ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያደርግ ምንም ዓይነት ምድራዊ ኃይል የለም የሚል እምነትን በመያዝ ከወንጀል ጥፋታቸው ለማምለጥ አየጣሩ ነው ፡፡
የህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ወደ አሜሪካ አገር በመምጣት በአሜሪካ ሕጎች ላይ መቀለድ እና ያልተመዘገቡ ቦንዶችን በመሸጥ ከዚህ ወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ አየጣሩ ነው ፡፡
የህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ወደ አሜሪካ ሀገር በመምጣት በአሜሪካ ሕጎች እና ሕገ መንግስት ላይ በመቀለድ እነርሱ ትርፋቸውን እያጋበሱ ከሚገኙበት የወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ አየጣሩ ነው ፡፡
ዘ-ህወሀት በአሜሪካ ውስጥ ያልተመዘገቡ ቦንዶችን ለበርካታ ዓመታት ሲሸጥ ቆይቷል፣ ምክንያቱም በዚህ ወንጀል ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደሚችሉ ስለአመኑ ነው፡፡
በመጨረሻም የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች እንዲህ የሚል አንድ ጠንካራ ትምህርት ተምረዋል፡ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ኢትዮጵያ አይደለችም፣ እንደዚሁም ሁሉ ዘ-ህወሀት ዎል ስትሪት አይደለም!
በአሜሪካ ውስጥ የተጭበረበረ የሸፍጥ ቦንድ መሸጥ ሊያስከፍል የሚችለው ከፍተኛ ዋጋ አለው፡፡
ይህንን ህገወጥ የሆነ ያልተመዘገበ ቦንድ ሽያጭ ህገወጥነት እ.ኤ.አ ግንቦት6/2013 ለዘ-ህወሀት አስጠንቅቄ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ ግንቦት 6/2013 “የማስመሰያ ምዕናባዊ የቦክስ ምት/Shadowboxing Smoke and Mirrors“ በሚል ርዕስ አዘጋጅቸው በነበረው ትችቴ ስሙ በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች ስም ዝርዝር የመረጃ ቋት ውስጥ ተመዝግቦ ለሚገኘው አሸባሪ ድርጅት ለዘ-ህወሀት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ውስጥ ያልተመዘገበ ቦንድ መሸጥ ህገውጥ ስለሆነ በአሜሪካ ውስጥ ወንጀል መስራቱን አቁሙ በማለት ተናግሬ ነበር፡፡
በአሜሪካ ውስጥ ያልተመዘገቡ ቦንዶችን በመሸጥ የተፈጸመ ወንጀል፣
በአሜሪካ ሀገር ውስጥ የመለስ ዜናዊ ግድብ (ወይም ለማስመሰል ዘህዋሃት የህዳሴ ግድብ ቦንድ ሽያጭ የሚለው የውሸት ገንዘድ ማሰባሰቢያ ዘዴ) ህጋዊነት በማስመልከት የሚነሱ በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡ በአሜሪካ ፌዴራሉ እና በአብዛኞቹ አካባቢያዊ መንግስታት ሕጎች ቦንድ ትርጉሙ ሰፋ ብሎ ስቶክ፣ ቦንድ፣ ዕዳ እና የኢኩቲ ቦንድ፣ የቃል ኪዳን ስምምነት፣ የኢንቨስትመንት ኮንትራክቶችን፣ ወዘተ ያጠቃልላል፡፡
በሕግ አስታልተፈቀደ (ኤግዘምስን) ድረስ ሁሉም ቦንዶች ከመሸጣቸው በፊት ወይም ደግሞ ለሕዝብ ሽያጭ ለማቅረብ ይፋ ከማድረግ በፊት በቦንድ እና በልውወጥ ኮሚሽኑ (SEC) እና/ወይም አግባብነት ባላቸው መንግስታዊ አካላት መመዝገብ አለባቸው፡፡
በSEC እና/ወይም አግባብነት ባላቸው መንግስታዊ አካላት የምዝገባ ፋይል ውስጥ ተመዝግቦ ያልተያዘ ማንኛውም የቦንድ ሽያጭ እንዳልተመዘገበ ይቆጠራል፡፡ በፌዴራል እና አካባቢ መንግስታት ሕግ መሰረት ያልተመዘቡ ቦንዶችን መግዛት ወይም መሸጥ ወንጀል ነው፡፡
SEC በ1993 ድንጋጌ (ዋናውን የሚያትሙትን የሚቆጣጠረው) ክፍል 20 (b) መሰረት ያልተመዘገቡ ቦንዶችን በሚሸጡ እና ከዚህ ጋር የሚያያዙ ሌሎችን ጉዳዮችን በሚመለከት የዳኝነት ስራ መስራት የሚችል ሲሆን የቦንድ ድንጋጌ ጥሰት ወይም ደግሞ የማይቀር የጥሰት ሁኔታ የሚታይ ከሆነ የፍርድ ቤት ማገጃ ትዕዛዝ ሊያወጣ ይችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ክፍል 8 A ለSEC ያልተመዘገቡ ቦንዶችን  የሚያትሙ ቦንድ አታሚዎች ከዚህ ህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ክፍል 20 (d) በተደነገገው መሰረት ቅጣታቸውን እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
እንደሌሎቹ ግዛቶች የአካባቢ መንግስታት ሁሉ የካሊፎርኒያ ኮድ ክፍል 25110-25118 በግዛቱ ውስጥ ለሚሸጡ ማናቸውም የቦንድ ሽያጮች ወሳኝ የሆነ መመሪያ አዘጋጅቶ በስራ ላይ አውሏል፡፡ ማንኛውም ሰው ወይም አካል በእራሱ ፈቃድ ያልተመዘገቡ ቦንዶችን የሚሸጥ ወይም በአካባቢ መንግስታት መካከል ለንግድ የሚያጓጉዝ ወይም እንደ እነዚህ ያሉትን ቦንዶች የሚገዛ በካሊፎርኒያ ኮድ ክፍል 25540 ንኡስ ክፍል (a) መሰረት እስከ ሶስት ዓመታት በሚደርስ እስራት እና እስከ አንድ ሚሊዮን ዶላር በሚደርስ መቀጫ እንዲቀጣ ያስደርጋል፡፡ የካሊፎርኒያ ዓቃብያነ ሕጎች እንደ ፌዴራል አቻዎቻቸው ሁሉ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሊያወጡ እና የወንጀል መቀጫውን ሊያስፈጽሙ ይችላሉ፡፡
ከምዝገባ አስፈላጊነት ህግ የሚዘለሉ (ለየት ብሎ ፍቃድ የሚሰጣቸው) ጥቂት የሆኑ ነገሮች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ለተወሰነ የውጭ ሀገር መንግስት የቦንድ ደላላዎች ወይም አስማሚዎች አንዱ ነው፡፡
እንደ 17 CFR 401.9 “የመንግስት ደላላ ወይም አስማሚ (የውጭ ባንክ ቅርንጫፍን ወይም ተወካይን ሳያካትት) የዩናይትድ ስቴትስ ኗሪ ያልሆነ ከክፍል 15 C (a), (b) እና (d) ድንጋጌ (15 U.C. 780-5 (a), (b) እና (d)  እንዲሁም 17 CFR 240.1 5a-6ን በማይጻረር መልኩ ተፈጻሚ ይሆናል… “ በሌላ አባባል የመለስን ግድብ ቦንድ ለመሸጥ ወደ አሜሪካ የተላኩት የቦንድ ደላላዎች እና አስማሚዎች የፌዴራል ቦንዱን ህግ እና ሌሎች አስፈላጊ የቁጥጥር ጉዳዮችን አካትቶ በሁለቱም ወገኖች በኩል ለሚነሱ አወዛጋቢ ነገሮች አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል ሙሉ በሙሉ ግልጽ የማድረግ፣ ምዝገባ የሚካሄድበት ማረጋገጫ መዝገብ እና ስለቦንድ ህትመቱ የጽሁፍ ስምምነቶች የሚሉትን ዘርፈ ብዙ መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የመለስን (የውሸት ቦንድ) ግድብ ቦንድ ለመሸጥ የመጡት ደላለሎች እና አስማሚዎች 17 CFR 240.15a–6 እና 15 U.S.C. 78o–5(a) ስር የተዘረዘሩትን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሟሉ አይደሉም፡፡
እ.ኤ.አ ሰኔ 8/2016 በቦንድ እና ልውውጥ ኮሚሽን (SEC) የተሰጠው መግለጫ እ.ኤ.አ ግንቦት 8/2013 የሰጠሁትን ማስጠንቀቂያ ትክክለኛነት ሙሉ በሙሉ ያረጋገጠ ነው፡፡
የSEC መግለጫ እንዲህ የሚል ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ድርጅት የዩኤስ አሜሪካን የቦንድ ምዝገባ ሕግ ሳያሟላ በአሜሪካ ሀገር ውስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የቦንድ ሽያጭ ገቢ በማሰባሰቡ ወደ 6.5 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ቂታት ለመክፈል ስምምነት አድርጓል፡፡
የSEC የትዕዛዝ መግለጫ እንዲህ ይላል፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል/Ethiopian Electric Power (EEP) በኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ለሚገነባው ግድብ ግንባታ የሚውል ያልተመዘገበ የቦንድ ሽያጭ አከናውኗል፡፡ 
EEP በዩኤስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድረ ገጽ እንዲሁም በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን በመጠቀም ሰፊ ቅስቀሳ በማድረግ በዩኤስ ታላላቅ ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባ በማድረግ በዩኤስ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የቦንድ ሽያጭ ግብይት አከናውኗል፡፡ 
EEP እ.ኤ.አ ከ2011 እስከ 2014 ድረስ ከSEC ምንም ዓይነት የቦንድ ምዝገባ ሳያደርግ በግምት ወደ 5.8 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን ዶላር ከ3100 ኗሪዎች ሰብስቧል፡፡
በ (SEC) ስምምነት የተደረሰበት ትዕዛዝ እንዲህ ይላል፡
EEP ለኢትዮጵያ የውኃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል ምዝገባ ያልተደረገባቸው ቦንዶችን የኢትዮጵያ ዝርያ ላላቸው ኢትዮጵያውያን አቅርቧል፡፡ ቦንዱ ለሽያጭ የቀረበው የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ማህበረሰብን ዒላማ በማድረግ በዩኤስ አሜሪካ በቴሌቪዥን እና በሬዲዮ ቅስቀሳ በማድረግ ነበር፡፡ ቦንዶቹ ለሽያጭ የቀረቡት በዋሺንግተን ዲ.ሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድረ ገጽ ሲሆን ኤምባሲው ከዚህም በተጨማሪ የቦንድ ሽያጭን ለማካሄድ ኃላፊነቱን ወስዶ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ EEP የቦንድ ሽያጩን በኮሚሽኑ አላስመዘገበም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የቦንድ ሽያጩን ከምዝገባ ነጻ የሚያደርግ ሕግ አልነበረም፡፡ በአሜሪካ የEEP ያልተመዘገበ ስጦታ እና የቦንድ ሽያጭ የቦንድ ድንጋጌውን ክፍል 5 (a) እና 5 (c)ን ጥሷል፡፡
የቦንድ ድንጋጌ ክፍል 5 (a) በአካባቢ መንግስታት መካከል ማንኛውም ሰው ቢሆን እየተዘዋወረ በማንኛውም መንገድ ምንም ዓይነት ምዝገባ ሳያካሂድ መሸጥ ወይም ደግሞ ቦንዶችን ለመሸጥ ቅድመ ምዝገባ ሳይካሄድ ማጓጓዝ ህገ ወጥ ነው ይላል፡፡
የቦንድ ድንጋጌ ክፍል 5 (c) ደግሞ የምዝገባ መግለጫ እስካልያዘ ድረስ ማንኛውም ሰው ቢሆን ቦንድ መሸጥ ወይም መግዛት አይችልም የሚል ድንጋጌ አስቀምጧል፡፡ እንዲሁም የምዝገባ መግለጫው ሽያጩ እንዲቆም ወይም ደግሞ ሌላ የህግ ችግር ካለ መሸጥም ሆነ መግዛት አይችልም በማለት በግልጽ አስቀምጧል፡፡ (15 U.S. ኮድ ክፍል. 77eን በተጨማሪ ይመልከቱ፡፡)
የSEC ትዕዛዝ ዋናው ዓላማ ኢንቨስተሮች ያበደሩትን ዋናውን ገንዘብ ከነወለዱ መመለስ መቻሉን ለማረጋገጥ ነው፡፡
ያልተመዘገቡ ቦንዶችን ለመሸጥ የዘ-ህወሀት የወንጀል ዘመቻ፣
“በ1993 ድንጋጌ 8 A መሰረት የቦንድ ሽያጭን የማቆም ሂደት“ የሚለው የSEC ትዕዛዝ SEC ያልተመዘገቡ ቦንዶችን መሸጥ እያለ ለሚጠራው ሕግ ዋናው ትኩረት የማጭበርበር የማታለል ወንጀልን ለማቆም ነው።
እንደ SEC አገላለጽ EEP እ.ኤ.አ ከ2011 ጀምሮ ለውኃ የኤሌክትሪክ ግድብ ማመንጫ በሚል ያልተመዘገቡ የቦንድ ሽያጮችን እስከ 2014 አከናውኗል፡፡ የቦንድ ሽያጩ የመመለሻ ጊዜ ከ5 ዓመታት እስከ 10 ዓመታት ድረስ ሲሆን (በሎንዶን ባንክ የመመለሻ መጣኔ/London Interbank Rate (LIBOR) መሰረት ለ5 ዓመት መመለሻ ጊዜ የወለድ መጣኔ 1.25 ፐርሰንት ባመት፣ እንዲሁም ለ10 ዓመት የመመለሻ ጊዜ የወለድ መጣኔው 2 ፐርሰንት ነው ብሏል፡፡)
እ.ኤ.አ ከ2011 እስከ 2014 ድረስ EEP የኢትዮጵያን የዲያስፖራ ማህበረሰብ ዒላማ ባደረገ መልኩ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድረ ገጽ፣ ኤምባሲው በሚያዘጋጅባቸው ቦታዎች፣ በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን ቅስቀሳዎች በመላ በዩኤስ አሜሪካ ውስጥ ተከታታይነት ባለው ሁኔታ የሚከተሉትን ቦታዎች ጨምሮ ያልተመዘገቡ የቦንድ ሽያጮችን ዘመቻ አከናውኗል፡
የ (ዳይስፖራ ገንዘብ ዘረፋ)
ዘመቻ ቀን                                             የዘመቻው ቦታ                የተሰበሰበ/ቃል የተገባ ገንዘብ
ነሐሴ 2011                                ዴንቨር፣ ኮሎራዶ                          $130,000
ሰኔ 2012                                   ዋሺንግተን ዲ.ሲ                          $1,500,000
ሚያዝያ 2013                             ችጋጎ ኢሊኖስ                               $110,000
ሚያዝያ 2013                             ሲያንዲያጎ ካልፎርንያ                     $43,000
ሚያዝያ 2013                             ሀውስተን ቲቅሳስ                          $50,000
ግንቦት 2013                              ኒዮርክ                                       $100,000
(***SEC የዘ-ህወሀትን ያልተመዘገበ የቦንድ ሽያጭ “ዘመቻ” በሚል አስገራሚ ቃል ገሎጾታል ምክንያቱም ያልተመዘገቡ ቦንዶችን በመሸጥ ዘመቻ የሚለው ቃል ሲጠቀሙ ብዙ ጊዜ የገበያ ማጭበርበርን ለመግለጽ የምተቀሙት ቃል ነው፡፡***)
እንደ SEC ዘገባ ከ3100 በላይ የዩኤስ አሜሪካ ኗሪዎች በተናጠል ከ5 እስከ 10 ሺ ዶላር ቦንድ የገዙ ሲሆን በአጠቃላይ በኢንቨስተር ደረጃ ሲታይ ደግሞ ከ50 እስከ 1 ሚለዮን ዶላር ይዘልቃል፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ የዩኤስ አሜሪካ ቦንድ ገዥዎች በግምት ወደ 5.8 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል፡፡ አብዛኞቹ ኢንቨስተሮች-64 በመቶ የሚሆኑት የዩኤስ አሜሪካ ኗሪዎች መሆናቸው ዘግበዋል፡፡
 SEC ትዕዛዝ መሰረት ዘ-ህወሀት ምን ማድረግ እንዳለበት የዘ-ህወሀት ተግባር፣
ዘ-ህወሀት በSEC የተጣሉትን የሚከተሉትን ስምምነቶች እና ማዕቀቦች ለመፈጸም ቃል በሕግ ተገዶ ገብቷል፡፡
EEP የቦንድ ድንጋጌ ክፍል 5ን መጣሱን እንዲያቆም እና ወደፊትም ከእንደዚህ ዓይነት ሕገ ወጥ አሰራር እንዲታቀብ፡፡
EEP በሕገ ወጥ መልክ ያገኘውን 5,847,804 ዶላር እና 601,050.87 ወለድ በድምሩ 6,448,854.87 ዶላር መክፈል አንደሚከፍል፡፡
EEP እ.ኤ.አ ከሀምሌ 8/2016 በፊት 601,050.87 ዶላር በጊዚያዊነት በዩኤስ አሜሪካ የፋይናንስ ተቋም ሂሳብ ገቢ በማድረግ ገቢ ለማድረጉ ማስረጃ የሚሆነውን ደረሰኝ ለSEC ኮሚሽን ሰራተኛ እንዲያቀርብ፡፡
የቦንድ ክፍያውን ለባለቦንዱ ለመክፈል የሚያስችል አስፈላጊ የሆነውን ስራ መከታተል የሚችል ነጻ ገለለትኛ አስተዳዳሪ  የሆነ ሶስተኛ ወገን መቋቋም ይኖርበታል፡፡ ክፍያውን ከመፈጸም ጋር በተያያዘ መልኩ ሊከሰቱ የሚችሉ ወጭዎችን ዘህዋሃት መሸፈን ይኖርበታል፡፡
እ.ኤ.አ ከነሐሴ 8/2016 በፊት አስተዳዳሪው የገንዘብ ክፍያ አመዳደብ ዕቅዱን በመስራት ለማጸደቅ ለኮሚሽኑ ሰራተኞች ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሚዘጋጀው የገንዘብ ክፍያ አመዳደብ ፋይል ሊገኝ በሚችልበት እና አስተማማኝ በሆነ መልኩ፣
ሀ) የእያንዳንዱን ቦንድ ባለቤት ሙሉ ስም እና ግለሰቡ ሊገኝበት የሚችለውን የተሟላ አድራሻ፣
ለ) ለእያንዳንዱ ባለቦንድ ሊከፈል የሚገባውን ትክክለኛ የገንዘብ መጠን፣ እና
ሐ) ለእያንዳንዱ ባለቦንድ ሊከፈል የሚገባው ክፍያ እንዴት እንደተሰላ የሚያሳይ መግለጫ መያዝ ይኖርበታል፡፡
ለቦንድ ባለቤቶች ሊከፈል የሚገባው ክፍያ እ.ኤ.አ ከሰኔ 8/2017 በፊት መፈጸም ይኖርበታል፡፡
አስተዳዳሪው ከሚሰራጨው የክፍያ ገንዘብ ውስጥ የቦንድ ባለቤቱን ወይም የተወካዩን አድራሻ ባለማግኘቱ ምክንያት ገንዘቡን ማሰራጨት ካልቻለ አስተዳዳሪው ይህንን ክፍያ ያልተፈጸመበትን ገንዘብ በቀጥታ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ግምጃ ቤት እንዲያስገባ፡፡
በSEC ትዕዛዝ መስጫ ላይ ያልተመለሱ ታላላቅ ጥያቄዎች፣
የዕዝል ቁጥር 1 ጥያቄዎች፡
እንደ SEC ዘገባ ከሆነ EEP 5,847,804 በህገ ወጥ መልክ የተገኘውን ዶላር እና አስቀድሞ ውሳኔ የተሰጠበትን 601,050.87 ዶላር ወለድ በጠቅላላው 6,448,854.87 ዶላር መክፈል ይኖርበታል፡፡ ይህ ቁጥር ዘ-ህወሀት በይፋ እሰበስበዋለሁ ካለው ገንዘብ አንጻር ሲታይ በጣም ትንሽ ገንዘብ ነው፡፡
እ.ኤ.አ መጋቢት 16/2016 በዘ-ህወሀት ባለስልጣኖች እንደተሰጠው መግለጫ፡
በጠቅላላ ለፕሮጀክቱ ከሚሰበሰበው ጠቅላላ ብር 6.9 ቢሊዮን ወይም 377.53 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ውስጥ ከሀገር ውስጥ የሚሰበሰብ ሲሆን ብር 0.6 ቢሊዮን እና 0.092 ሚሊዮን ብር እንደየቅደምተከተላቸው ከዲያስፖራ ማህበረሰቡ እና ከእርዳታ የሚገኝ ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብን ክፍያ ከየሀገራቱ ያለውን ስርጭት ብንመለከተው እንኳ የሕዳሴውን ግድብ ታላቁን የቦንድ ድርሻ የሚይዘው በዩኤስ አሜሪካ የሚኖረው ማህበረሰብ ነው፡፡ 0.6 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወደ ዶላር የምንዛሬ ምጣኔ ሲመነዘር ወደ 28 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ይሆናል፡፡ በዩኤስ አሜሪካ የሚኖረው ማህበረሰብ የቦንድ ግዥ ድርሻ በመቶኛ ምን ያህል ይሆናል? ከዘ-ህወሀት መግለጫ ለመገመት እንደሚቻለው ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ የሚገኘው የቦንድ ግዥ ድርሻ በጣም ብዙ እንደሆነ እና ምናልባትም አሁን SEC ዘ-ህወሀትን እንዲከፍል ከወሰነበት ገንዘብ ሁለት ወይም ሶስት እጥፍ ሊበልጥ እንደሚችል ማንም መገመት ይችላል፡፡ ዘ-ህወሀት ወደ 6.5 ሚሊዮን ገደማ የሚሆውን ዶላር ለመክፈል ስምምነት ካደረገ በኋላ እንደ ዘራፊ ተይዞ እንደዘራፊ በመተው ምንም ዓይነት ተጠያቂነት ሳይኖርበት ዝም ብሎ ይታለፋልን?
ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ስለተሰበሰበው ገንዘብ ለዘ-ህወሀት ኪስ እና ህዳሴ እየተባለ ስለሚጠራው ግድብ ስለመዋሉ ምን ማስረጃ ሊኖር ይችላል?
የዕዝል ቁጥር 2 ጥያቄዎች፡
ዘ-ህወሀት ያልተመዘገበ ቦንድ መሸጥ ህገወጥ ስለሆነ ወንጀል ነው በማለት ግልጽ በሆነ እና በማያሻማ መልኩ እየተነገረው ቢያንስ ላለፉት አራት ዓመታት ያህል ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ግዥውን አጣጡፎ የቆየው ለምንድን ነው? ዘ-ህወሀት ያልተመዘገቡ ቦንዶችን በዩኤስ አሜሪካ ከመሸጡ በፊት ስለጉዳዩ ሁኔታ ለትንሽም ጊዜ ቢሆን አስቦ ነበርን? ዘ-ህወሀት በዩኤስ አሜሪካ ውስጥ ያልተመዘገቡ ቦንዶችን ለመሸጥ ዕቅድ ሲወጥን የሕግ አማካሪ ወይም ምክር ሰጭን አማክሮ ነበርን?
SEC ይህንን እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ዘ-ህወሀት ያልተመዘገቡ ቦንዶችን ለመሸጥ በሕግ አማካሪ ተወክሎ ነበርን? ዘ-ህወሀት በዩኤስ አሜሪካ ውስጥ የህግ አማካሪ የማይፈልግ ከሆነ አማካሪ ለመፈለግ የተሳነው ለምንድን ነው?
ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ ሰብአዊ መብትን የሚያስከብረውን ሕግ ለማሸነፍ D L A Piper ለተባለ የህግ ድርጅት በወር 50 ሺ ዶላር ይከፍል ነበር፡፡ በዩኤስ አሜሪካ ውስጥ ቦንድ ለመሸጥ ሲያስብ አማካሪ ለመቅጠር የተሳነው ለምንድን ነው? (***D L A Piper ኢትዮጵያን በመወከል ለኮንግረስ ምክር ቤቱ በላከው የውስጥ ማስታዋሻ “የፖለቲካ እስረኞች እና የህሊና እስረኞች የሚሉትን በትክክል ለማወቅ ስለማይቻል እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ስለሚያባብሱት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የተቃዋሚ ወትዋቾችን ያስራል እየተባለ ስለሚወገዝ ከሕጉ መወገድ ይኖርባቸዋል“ በማለት ሞገተ፡፡****)
የህዳሴ ግድብ ቦንድ አጭር መግለጫ ዘ-ህወሀት ያልተመዘገቡ ቦንዶችን ለመሸጥ ከበቂ በላይ እውቀት እንዳለው በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ዘ-ህወሀት በማወቅ እና ሆን ብሎ አምኖበት ሕገወጥ በሆነ መልኩ ያልተመዘገቡ ቦንዶችን በመሸጥ የሙስና ድርጊቱን ፈጽሟልን? ዘ-ህወሀቶች ርካሽ ውራጅ ልብስ እንደሚሸጥበት ገበያ በተመሳሳይ መልኩ ቦንድንም ሲሸጡ የለየላቸው ጨካኞች እና ምንም ነገር የማያውቁ የደናቁርት ስብስብ ናቸውን? ዘ-ህወሀት አስገዳጅ የሆነውን የቦንድ ሽያጭ ምዝገባ ሆን ብሎ ወደ ጎን ገሸሽ በማድረግ ወይም ደግሞ በህጉ እንዲታለፍ ይፈልጋል ምክንያቱም፣
1ኛ) የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮችን ለማታለል ዓለማ አድርጓል፣
2ኛ) የቦንድ ሽያጩ ህገወጥ እና ሙስና ነው የሚለውን መረጃ እንዲደበቅ አድርጓል፣
3ኛ) የእርሱን የሙስና ደረጃ ለህዝብ ክትትል ይፋ ማድረግ ስላልፈለገ ነው፡፡
የዕዝል ቁጥር 3 ጥያቄዎች፡
እ.ኤ.አ ታህሳስ 2014 ዘ-ህወሀት የኤሌክትሪክ፣ የባቡር እና የሸንኮራ አገዳ ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ 1 ቢሊዮን ዩሮ የ10 ዓመት ቦንድ ሽያጭ ፈጸመ፡፡ የ10 ዓመት ቦንድ ሽያጩ ከዝቅተኛው 6.625 እስከ 6.75 በመቶ የወለድ መጣኔ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
የህዳሴው ግድብ የ5 -10 ዓመት ቦንድ ሽያጭ በሎንዶን ባንክ የመመለሻ መጣኔ/London Interbank Rate (LIBOR) መሰረት ለ5 ዓመት መመለሻ ጊዜ የወለድ መጣኔ 1.25፣ እንዲሁም ከ8 እስከ 10 ዓመት የመመለሻ ጊዜ የወለድ መጣኔው 2 ነው ብሏል፡፡
ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው አጭሩ የወለድ መጣኔ የሚሰጣቸው?
የዕዝል ቁጥር 4 ጥያቄዎች፡
በ1993 የቦንድ ድንጋጌ በክፍል 20 (b) ስር SEC የቦንዱን ድንጋጌ ወይም ማንኛውንም ሕግ ወይም ደንብ መጣስ ማስረጃ በማቅረብ በጠቅላይ አቃቤ ሕጉ በማስቀረብ በእራሱ ስልጣን በዚህ ርዕስ ስር የፍርድ ሂደቱን መከታተል ይችላል፡፡
SEC ስለዘ-ህወሀት ውጤታማ የሆነ የተከፈተ እና የተዘጋ ጉዳይ ነበረው፡፡ የSEC ትዕዛዝ ዘ-ህወሀት በኤሌክትሪክ ኃይሉ እና በኤምባሲው አማካይነት በለየለት የቴሌኮሙኒኬሽን ግንኙነት ማጭበርበር፣ በፖስታ ግንኙነት ማታለል እና በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሸፍጥ ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል፡፡
SEC ይህንን ጉዳይ በወንጀል ተጠያቂነት ለፍትህ መምሪያው የማያቀርበው ለምንድን ነው?
ከSEC ትዕዛዝ ግልጽ እንደተደረገው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያልተመዘገቡ ቦንዶችን ሽያጭ ሲያቀላጥፍ እና በድረ ገጹ፣ በስብሰባ ቦታዎች እና በሌሎች ተግባራት አማካይነት ግዥ ሲያካሄድ እንደነበር ግልጽ አይደለምን? ዘ-ህወሀት የዴፕሎማቲክ አይነኬ ክልከላን (diplomatic  immunity ) እንደ መሳሪያ በመጠቀም የእራሱን ኤምባሲ የቦንድ ሽያጭ ማጭበርበር ወንጀል እንዲፈጽም ተጠቅሞበታልን?
SEC በኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ያሉ ባለስልጣኖችን በስም በመጥቀስ ከሌሎች ክሶች ጋር ያልተመዘገቡ ቦንዶችን በመሸጥ የሸፍጥ ወንጀል በመፈጸም፣ የሀሰት የህግ ሰነዶችን በመሸጥ፣ የሀሰት የህግ ሰነዶችን በማጓጓዝ፣ ለመሸጥ በመሞከር እና በአካባቢ ግዛቶች በማጓጓዝ ለመሸጥ በመሞከር በማለት ለሕግ መምሪያው ክስ መመስረት ያልቻለው ለምንድን ነው?
SEC ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ መልኩ ለአራት ዓመታት የቦንድ ህጉን በመጣስ በዘ-ህወሀት፣ በኤምባሲው እና በሌሎች በእርሱ ቁጥጥር፣ ክትትል እና አመራር ስር ባሉት አካላት ዓይን ባወጣ መልኩ የተፈጸመውን የጥፋት ወንጀል በመያዝ ጉዳዩ ለፍትህ አካል እንዲቀርብ ያላደረገው ለምንድን ነው?
በSEC ትዕዛዝ ዘ-ህወሀት ለወንጀል ቅጣት እንዳይቀርብ በመከላከል ላይ ያለው ለምንድን ነው? በሌላ አገላለጽ ዘ-ህወሀት ሌላውን የወንጀል ቅጣት ለማስቀረት የእርሱን ኤምባሲ ባለስልጣኖች፣የEEP ሰራተኞች በወንጀል ከመጠየቅ ለማስቀረት ሲባል 6.5 ሚሊዮን ዶላር በእርግጥ ለመክፈል ስምምነት አድርጓልን?
በSEC ትዕዛዝ ከበቂ በላይ ሊያረጋግጥ የሚያስችል በቂ ማስረጃ እያለ እና ዘ-ህወሀት በዩኤስ አሜሪካ ውስጥ ያለውን የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለአራት ዓመታት ያህል ሲያጭበረብር እና ሲያታልል ሲቆይ እያየ ለምንድን ነው? ገላጭ ምርመራ ማድረግ እየቻለ የሚመሩ የምርመራ ዘዴዎችን ለመከተል የቻለው? 
የዕዝል ቁጥር 5 ጥያቄዎች፡
የSEC ትዕዛዝ SEC የዩናይትድ ሰቴትስ የዉጭ መምሪያ (State Department ) ክፍልን ያመሰግናል፡፡ በእርግጠኝነት የዩናይትድ ሰቴትስ የዉጭ መምሪያ ክፍልን ለSEC ምን ዓይነት እርዳታዎችን ነው ያደረገለት? የዩናይትድ ሰቴትስ የዉጭ መምሪያ ክፍል በ”ኢትዮጵያ መንግስት” እና በSEC መካከል በተደረጉ ስምምነቶቸ ላይ ተሳትፎ አድርጓልን? የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ መምሪያ ክፍል በ”ኢትዮጵያ መንግስት” እና በSEC መካከል የነበረውን ስምምነት ሲያፋጥን ነበርን? የዩናይትድ ሰቴትስ የዉጭ መምሪያ ክፍል የዘ-ህወሀት ወኪሎች በወንጀል አንዳይከሰሱ  የፖለቲካ ተጽእኖ ያደርግ ነበርን?
የዕዝል ቁጥር 6 ጥያቄዎች፡
በቦንድ ድንጋጌው ስር SEC በእያንዳንዱ ኢንቨስተር ጎን በመሆን እርምጃ አይወስድም፣ ሆኖም ግን የቦንድ ድንጋጌው እያንዳንዱን ኢንቨስተር በበርካታ ጉዳዮች ላይ የሲቪል እርምጃ እንዲወሰድ ይፈቅዳል፡፡
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮች እና የቦንድ ባለቤቶች በድንጋጌው ክፍል 11 በዘ-ህወሀት ያልተመዘገበ የቦንድ ሽያጭ ሸፍጥ ሰለባ ሲሆን መብታቸው እስከምን ድረስ ነው?
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮች እና የቦንድ ባለቤቶች በድንጋጌው ክፍል 5 እና (a) (1) መሰረት በገዥዎች ምዝገባ ያልተካሄደበትን ቦንድ ለመሸጥ በዘ-ህወሀት ሲቀርብ ያላቸው መብት ምንድን ነው?
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮች እና የቦንድ ባለቤቶች በድንጋጌው ክፍል 15 መሰረት ሰዎችን በመቆጣጠር ወይም ደግሞ ተከላካዮችን በሚቆጣጠሩ ሰዎች ላይ በክፍል 11 እና 12 የስቶክ ባለቤት ከመሆን፣ ወይም በድርጅቱ ዋና ኃላፊ፣ በጋራ እና በወል ተጠያቂ እንደሚሆኑ ከማወቅ አንጻር ያላቸው መብት እስከምን ድረስ ነው?
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮች እና የቦንድ ባለቤቶች በድንጋጌው ክፍል 17 (a) የተጭበረበሩ ቦንዶች ሽያጭ ወይም ደግሞ በክፍል 10b በቦንድ ልውውጥ ድንጋጌ እና በደንብ ቁጥር 10b-5 ተጠያቂነትን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ለማወቅ ያላቸው መብት እስከምን ድረስ ነው (ስለማጭበረብር የተደነገገው)?
የዕዝል ቁጥር 7 ጥያቄዎች፡
ያልተፈቀዱ ቦንዶችን መሸጥ ዘ-ህወሀት በዩኤስ አሜሪካ ለሚፈጽመው ወንጀል ዋነኛው ነውን?  ዘ-ህወሀት በአሜሪካ ዜጎች እና ህጎች ላይ ሲፈጽማቸው የቆዩት እና በቀጣይነትም ሊያስከትላቸቀው የሚችላቸው ወንጀሎች ምን ምን ናቸው?
እ.ኤ.አ በ2014 ሚስተር ኪዳኔ የሚባል የአሜሪካ ዜጋ (የእርሱን ማንነት ለመደበቅ የተጠቀመበት የብእር ስም) የ”ኢትዮጵያ መንግስት” በድብቅ ሶፍት ዌር በቫይረስ እንደበከለበት፣ የእራሱን የስካይፔ ጥሪም እንደሚጠልፍበት እና ለወራት ያህል የቤተሰቡን የኮምፒውተር አጠቃቀም ሲሰልለው በመቆየቱ ክስ ለመመስረት ይፈልጋል፡፡
ዘ-ህወሀት በድብቅ አሁንም ህገወጥ በሆነ መልኩ የአሜሪካንን ህጎች እና የዩኤስ አሜሪካንን ህገ መንግስት በሚጻረር መልኩ በህገወጥ መልክ ስልክ መጥለፉን ይቀጥላልን? 
የዕዝል ቁጥር 8 ጥያቄዎች፡ 
ዘ-ህወሀት ያልተመዘገበ ቦንድ በሚሸጥበት ሀገር ያሉ የአካባቢ መንግስታት ዘ-ህወሀትን ተጠያቂ ለማድረግ ምን ዓይነት የሕግ ማዕቀፎች አሉ?
ለምሳሌ ያህል በካሊፎርኒያ ኮርፖሬሽን ኮድ ክፍል 25110-25118፣ 25540 በዚያ ግዛት ውስጥ ለሚሸጡ ማናቸውም ዓይነት ቦንዶች ዝርዝር መመሪያ አውጥቷል፡፡
ማንኛውም ሰው ወይም ደግሞ አካል ያልተመዘገቡ ቦንዶችን በግዛቶች መካከል የሚሸጥ ወይም የሚያጓጓዝ ወይም የሚገዛ በካሊፎርኒያ ኮርፖሬሽን ኮድ ክፍል 25540 ንኡስ ክፍል (a) እስከ ሶስት ዓመት በሚያደርስ መቀጮ እና እስከ 1 ሚሊዮን በሚደረስ የገንዘብ ቅጣት ይጣልበታል፡፡
ዘ-ህወሀት በካሊፎርኒያ ግዛት ህግ መሰረት ከESC ጋር ስምምነት ሳያደርግ ነጻ በሆነ መልኩ በኮርፖሬሽኑ ኮድ ከላይ በቀረቡት የሕግ ክፍሎች አማካይነት ለሕግ ተጠያቂ ሊሆን ይችላልን? 
የዕዝል ቁጥር 9 ጥያቄዎች፡
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮች እና የግድብ ቦንድ ባለቤቶች ስለዘ- ህወሀት የማጭበርበር ሸፍጥ መረጀ ለማግኘት ለማን ይደውሉ?
በርካታ መረጃ የሚፈልጉ ኢንቨስተሮች የስርጭት አስተዳዳሪ ለሆነው ጊላርዲ እና ኩባንያው Gilardi & Co. LLC, በ844-851-4591 በመደወል ማግኘት ይችላል፡፡
የዕዝል ቁጥር 10 ጥያቄዎች፡ 
በዩኤስ አሜሪካ ዘ-ህወሀት የሚያካሂደው የቦንድ ማጭበርበር ሸፍጥ ስፋት እና ጥልቀት እስካለ ድረስ የኮንግረስ ምርመራ ዋስትና ሊሆን ይችላልን?
SEC ስለዘ-ህወሀት የማጭበርበር ሸፍጥ በይፋ ሲገልጽ የማይታይ ምን ዓይነት ማስረጃ አለ?
በጉዳዩ ላይ የSEC ትዕዛዝ የመጨሻው ምዕራፍ ነውን?
የSEC ትዕዛዝ በዩኤስ አሜሪካ ውስጥ የዘ-ህወሀት የማጭበርበር እና የወንጀል ምርመራ አባዜ መጨረሻ አይደለም፡፡
ይህ ገና የመጀመሪያ ነው! 
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  
ሰኔ 6 ቀን 2008 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment