ክፋት በዛ
[ረሃብ እንደ ቀይ ሽብር፤ ህወሃት እንደ ደርግ]
ክፉ ቀን ብዙ ክፉ ምግባሮች ይዞ ይመጣል።
በቀይሽብር ወቅ በመቀሌ ከተማ ያጋጠመ አንድ የክፉ ምግባር ምሳሌ ነበር።
ዘስላሰ የተባለ ወጣት በፀረ ደርግነት ተጠርጥሮ የቀይ ሽብር ሰለባ በመሆን በባዛር እየተባለ የሚታወቀውና አሁን በስሙ ዘላሰ የተሰየመው የአፄ ዮሐንስ ቤተ መንግሥት ፊትለፊት የሚገኝ አደባባይ ይረሸናል። ወላጅ እናቱ በደርግ ወታደሮች ተገድደው እልልል እያሉ፣ እያጨበጨቡ ደስታቸው እንዲገልፁ ተደርገዋል።
ያ ቀይ ሽብር ክፉ ቀን የወለደው ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል። አሁንም ይሄ ጥቁር ታሪክ ዳግማዊ ትንሳኤውን አግኝቷል።
የጥቁር ታሪክ ባለቤት የሆነችው የሰሜን ወሎ ዞን፣ ቆቦ ወረዳ 027 ቀበሌ ነዋሪ እናት ወይዘሮ ብርቱኳን ዓሊ ነች። የ5 ዓመት ልጇን በረሃብ አጥታ እያነባች ለቢቢሲ የሰጠችው ቃለ ምልልስ ኢህአዴግን አስቆጥቶ ልክ እንደ የዘስላሰ እናት አስገድደው እንድታስተባብል አድርጓታል።
የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ልክ እንደ የደርግ ወታደሮች ሁሉ ወይዘሮ ብርቱኳን የልጇን ሞት ሃዘን እንዳትችል እያዋከቡና እያስፈራሩ እንድታስተባብል አስገደዷት። ይባስ ብሎ የአሜሪካ ድምፅ VOA ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩም የወንጀሉ አካል መሆኑ እጅግ ያሳዝናል።
ግርማይ ገብሩ የህወሓትን ሴራ እያወቀው ልጇ በድንገተኛ ሞት እንዳጣች፣ በሬ፣ ላም፣ እህል ወዘተ እንዳገኘባት መዘገቡ ያስገምተዋል። እዚህ ላይ የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ያስተላለፉት በቀጣይ ልጆችዋ በረሃብ እንዳታጣ መስጋትዋ ገልፃለች። ግርማይ ግን ከነሱ ብሶ መዘገቡ ያሳዝናል።
ህወሃት “የትግራይ ገበሬ 100% ሞዴል፣ የአንድ ዓመት ምርት 113 ሚሊዮን ኩንታል አመረተ”፤ ብሎ የሚዋሽ ድርጅት መሆኑ እያወቀና ጋዜጠኞች እንደሚሄዱ አውቀው የጠቀሳቸው ከብቶችና እህል አስቀድመው በቤትዋ ማስቀመጥ እንዴት ያቅታቸዋል ብሎ ያስባል?
ቅለል ያለው … ሆነ እንጂ የቢቢሲ መግለጫዋ ያስኮነነው ህወሃት UN በየቀኑ ሁለት ሰዎች ድርቅ ባስከተለው ረሃብ እየሞቱ እንዳሉ ገልፀዋል።
የቀይ ሽብር ተግባር በድርቅ ሲደገም እጅጉን ያማል። (Amdom Gebreslasie)
No comments:
Post a Comment