Translate

Monday, November 30, 2015

ሳዑዲ ዓረቢያና ዩናይትድ ዓረብ ኤምሬትስ በየመን ላይ እያደረጉት ላለው ጦርነት የአሰብ ወደብ ለ30 ዓመታት ተከራዩት

የተባበሩት መንግሥታት የቁጥጥር ቡድን ያወጣቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ፣ ሳዑዲ ዓረቢያና ዩናይትድ ዓረብኤምሬትስ በየመን ላይ እያደረጉት ላለውጦርነት የአሰብ ወደብ 30 ዓመታት እንደተከራዩት፣ የኤርትራ ወታደሮች በየመኑ ውግያ ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውንና የጦር መሣሪያም ወደ ኤርትራ እየገባመሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

ነገር ግን የ ወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር  ሃይለማርያም ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሳዑዲ ዓረቢያና ከዩናይትድ ዓረብ ኤምሬትስ እየፈፀሟቸው ስላሉ ስምምነቶች ተጠይቀው ሲመልሱ ‹‹ሁለቱ አገሮች በተለይ ደግሞ ዩናይትድ ዓረብ ኤምሬትስ አሰብንተጠቅማ የመን ላይ ያላቸውን ስትራትጂያዊ ጉዳይ ለማስታገስ አውሮፕላናቸው የመን ላይ የኦፕሬሽን ሥራ እንደሚሠራይታወቃል፡….የተፈራረምነውም ግልጽ የሆነ 30 ዓመት፣ 40 ዓመት የለንም ነው ያሉት፡፡›› በሏል፡፡
ዘንድሮ የተከሰተው ድርቅ ‹‹በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከተከሰተው ድርቅ ሰፋ ያለና›› አብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል ያካለለ በመሆኑ የተረጂዎች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የተናገሩት ሃይለማርያም ‹‹ማንም የማይቆጣጠረው ሰፊ አካባቢ በድርቁተጠቅቷል፡፡››ብለዋል፡፡
በመቀጠልም ድርቁ ራሱ በፈጠረው የውኃ ችግር የኤሌክትሪክ እጥረት አጋጥሟል ያሉ ሲሆን ‹‹ብዙዎቹ ግድቦቻችን ለምሳሌ አዋሽ ወንዝ ላይ ያለው የቆቃ ግድብ በጣም ብዙ ችግር ውስጥ ገብቷል፡፡›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ ሌላው ቀርቶ የአዋሽ ወንዝ ፍሰቱ ጭምር ሊጠፋ የደረሰበት ደረጃ ላይ ነው ያለው፡፡በተመሳሳይ መልካ ዋከናቆሟል ማለት ይቻላል፡፡ ተከዜም 10 ሜጋ ዋት ብቻ ነው የሚያመነጨው፤ እየደረቀ ነው፡፡›› ከዚህ የተነሳም ‹‹ድርቁ ራሱበፈጠረው የውኃ ችግር የኤሌክትሪክ እጥረት አጋጥሟል፡፡›› በለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment