Translate

Friday, November 13, 2015

የሞቱ ካሉ የሞቱት በረሃብ አይደለም ይላሉ ም/ጠ ሚኒስተሩ – የሚሊዮኖች ድምጽ

8c1e31b24cd68f93e746d072f1231338_XL
የኢትዮጵያ መንግስት 600 ሺህ ሜትሪ እህል አዟል ይሉት አቶ ደመቀ መኮንን 200 የሚሆነው ጅጅቡቲ ወደብ እንደደረሰ ለፋና ራዲዮ ተናግረዋል።ሄ መልካም ዜና ነው። ረፍዷል፤ ቢሆንም ረፍዶም እርምጃዎች መወሰዳቸው ጥሩ ነው።
“የተለያዩ የውጭ መገናኛ በዙሃን በድርቁ የተነሳ የሰው ህይወት አልፏል እያሉ እያሰራጩ ካለው ዘገባ አንጻር በተጨባጭ ያለው እውነታ ምን ይመስላል” በሚል ከፋና ለቀረበላቸው ጥያቄ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱ፥ “የውጭ መገናኛ ብዙሃን ከተለያዩ አካላት ጋር እንደሚሰሩ ይታወቃል። ከዚያ በላይ ግን፣ አፍ ለማዘጋት አልያም ለማስተባበልና ምላሽ ለመስጠት ሳይሆን፣ ረሃብ የሚባለው ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ የለም” ይየሚል ማልሽ ነው የሰጡት።

“ዕርዳታ ባለመድረሱ ሰዉ ተሰዶ የሄደበት፣ ዕርዳታ ባለመድረሱ ርሃብ የተከሰተበት ሁኔታ የለም፤ በየትኛውም ጊዜ በማንኛውም መንገድ በህይወት ያለ ሰው ሕይወቱ ሊያልፍ ይችላል” ያሉት አቶ ደመቀ፥ “ ዋናው ጥያቄ እልፈቱ የተከሰተው በረሃብ የመጣ ነው ወይ የሚለውን ህዝቡ ውስጥ ገብቶ ማየት ሚዛን ይደፋል የሚለው አሳማኝ ይሆናል” የሚል አስተይአየት ነው ለፋና ራዲይፕ የሰጡት።
እዉነታዉን ለሕዝብ እየገለጹ ያሉ እንደ ቢቢሲና አልጃዚራ ፣ እንዲሁም አገር ቤት የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ያሉትን፣ የ”የተለያዩ” ካሏቸው ( ምናልባት እነሻእቢያና ግንቦት ሰባት አርበኞች ያሉት አስበው ሊሆን ይችላል) ጋር የሚሰሩ ናቸው ሲሉ ለመክሰስ ሞክረዋል። ቢቢስ፣ አልጃዚራና ሪፖርተር የዘገቡት፣ እንደ ፋና ራዲዮ ያሉ የአገዛዙ ሜዲያዎች ማድረግ የነበረባቸው ግን ያላደረጉትን፣ የተጎዱ ወገኖቻችን ያሉበት ድረስ በመሄድ በአይናቸው ያዩትትን ነው። የአቶ ደመቀን አባባል እንዋስና “ ሕዝቡ ዉስጥ ገብተውው” አይተው ነው።
አቶ ደመቀ ምናልባት ዊስክኪ ከሚረጩበትና ጮማ ከሚቆርጡበት፣ የአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ውጥተው ፣ ወደ ራያና ቆቦ፣ ወድ አጽቢ፣ ወደ አፋር …በመሄድ ወለዮዋን ብርቱካን አሊን፣ አፋሩን ኡመር መሃመድን እንዲሁም የአጽቢዉን አርሶ አደር ትግሬውኡን ሐጎስ ሄደው ቢያነጋገሩ ጥሩ ነበር።
የራዲይዮ ፋናና ዘገባ ከዚህ ቀጥሎ ያንብቡ።

No comments:

Post a Comment