Translate

Tuesday, August 18, 2015

አብርሃም ጌጡ በማዕከላዊ

Legese Weldehana's photo.
የመላው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አብርሃም ጌጡ ሰኔ 12 /2007 ልደታ ፓሊስ መምሪያ ታሰረ ብዙም ሳይቆይ ወደ 5ኛ ፓሊስ ጣቢያ ተዛወረ ልደታ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 13/2007 ዓም የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ወጣቶችን አደራጅተህ ሚያዝያ 14/2007 ዓም መንግስት የጠራውን ሠልፍ እንዲረበሽ አድርገሃል የሚል ክስ ቀረበበት ጊዜ ቀጠሮ ላይ እያለ ሳይቋጭ ሰኔ 25/2007 ዓም ወደ አዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን (3ኛ) ተወስዶ ታሰረ አ.አ ፓሊስ ኮሚሽን (3ኛ) ድብደባ እንደተፈፀመበት ነግሮናል አራዳ ፍርድ ቤት እያቀረቡ ጊዜ ቀጠሮ እየጠየቀበት ነበር ሀምሌ 17/2007 ዓም አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ተወስኖ እያለ የቀጠሮው ቀን ከመድረሱ በፊት ክሱን አቋርጠው ሀምሌ 15/2007 ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተወስዶ እየተሠቃየ ይገኛል
አብርሃም በማዕከላዊ የደረሠበት ግፍ
ከሀምሌ 15 ጀምሮ ከባድ ድብደባ ተፈጽሞበታል በነሱ አጠራር 84/3 (ሣይቤሪያ) ተብሎ በሚጠራው ቀዝቃዛ ክፍል ውስጥ ይገኛል ከሀምሌ15 – 19 /2007 ዓም ጀምሮ በተፈፀመበት ከባድ ድብደባ ለ 3 ቀን እራሱን ስቶ እንደነበረ በእስረኞች ድጋፍ እና እንክብካቤ ማገገም ችሏል እንደገና ቆሞ መራመድ ሲጀምር ተጠርቶ እየተወሰደ በድብደባ ብዛት እራሱን በሸክም አምጥተው ጥለውት እንደሚሄዱ ታውቇል
ለ3 ቀን ያክል እህል ውሃ እንዳልቀመሠ እና
በድብደባ ብዛት የሱ ያልሆነ ቃል እራሳቸው ያዘጋጁት
ላይ እንዳስፈረሙትም ተውቇል
በድብደባ ወቅት አፀያፊ ስድብ ይሰድቡት እንደነበረ ተረጋግጧል
በምርመራ ወቅ ት የሚከተሉትን ጥያቄ እየተጠየቀ ተደብድቧል
፠ ትግሬን ትጠላለህ
፠ በትግሬ መገዛት የለብንም ብለህ ትቀሰቅሳለህ
፠ ወጣቶችን ታደራጃለህ የመሣሰሉትን እየተጠየቀ ተደብድቧል
በድብደባ ብዛት በርካታ የሠውነት ክፍሎቹ ተጎድተዋል
ለምሳሌ
፠የግራ ጆሮው አይሰማም
፠ የእጁ 3 ጣቶች አይሰሩም
ተሸካሚውን ሲያገኝ ግፍ ይበረታል ።

No comments:

Post a Comment