የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት በማንኛውም አይነት ሁኔታ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከሌላ አካል ጋር ሆነው ሲሰሩ የተገኙ በእስር ላይ ያሉት የአንድነት አመራር አካላት የኢትዮጵያ መንግስት ፍርድቤት የወሰነባቸውን የጥፋተኝነት ውሳኔ መጨረስ አለባቸው። እኛ የህሊና እስረኞች አንላቸውም ሲሉ ተናገሩ
ሰሞኑን የአንድነት ፓርቲ በመጪው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ መዘጋጀቱን በገለጹበት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፓርቲው ም/ሊመንበር አቶ ግርማ ሰይፉ ድርጅታቸው የፍርድቤት ውሳኔን ማክበርን ከመንግስት በላይ እንዲከበር እንሰራለን። በኢትዮጵያ ሰላምና ፀጥታ የሚያደፈርስ ጉዳዮችን ከገዥው አካል በበለጠ እንቃወማለን። ስለዚህ የታሰሩት የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አውቀውም ሆነ ሳያውቁት ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ሲሰሩ የተገኙ ፍርድቤት ጥፋተኛ ብሎ የወሰነባቸው የአንድነት የህሊና እስረኞች አይደሉም፤ የጥፋተኝነት ውሳኔውን በእስር ላይ ሆነው መጨረስ አለባቸው ሲሉ ለተሰብሳቢው አስታውቀዋል።
ተሰብሳቢው ግራ መጋባቱን ጨምሮ አቶ ግርማ ይህን ለምን ማለት እንዳስፈለጋቸው ባይታወቅም፤ መንግስት ከፍተኛ ጫና በማድረግ ወደ ምርጫው እንዲገቡ እና ይህን እንዲያወግዙ ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት ተቀብለናል። ከተሰብሳቢው ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት ም/ሊመንበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አሳዝነዋል። እነ አቶ አንዱአለም አራጌ የመሰሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ሽብርተኛ ሳይሆኑ የነጻነት ታጋዮች እንጂ ሰላም አዋኪዎች አይደሉም። እስክንድር ነጋ አለም አቀፍ ተሸላሚ እንጂ ወንጀለኛ አይደለም፤ ወጣት ናትናኤል መኮነን ለዲሞክራሲ መከበር የታገሉ እንጂ በውሸት የቀረበባቸውን ማስረጃ ተደብድበው አምነዋል የተባሉበትን ክስ የአንድነት ም/ሊመንበር አቶ ግርማ እስር ቤት ይቆዩ ማለታቸው አነጋጋሪ ነው።
አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ይህ በኢንጅነር ሃይሉ እና አቶ መለስ የተደረገውን የስምምነት ፊርማ ያስታውሳሉ። ወይም የስልጣን ሽኩቻ ሊኖር ስለሚችል አሊያም አቶ ግርማ የአቋም ለውጥ ሊያደርጉ በዝግጅት ላይ ሊሆኑ ይችላል ብለዋል። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተለመደ እየሆነ መምጣቱን አስታውሰዋል።
የኢትዮጵያን ትግል የሚጎዱት ራሳቸው የፖለቲካ ድርጅቶች አቋም ጥርት ያለማለት እና እምነት የማጣት ባህሪ ነው ያሉት ተንታኝ እንዴት የአንድነት ፓርቲ አመራር የኢትዮጵያ ካንጋሮ ፍርድቤት ሽብርተኛ ብሎ በጨለማ ቤት አስገብቶ በሃይል ድበደባ አድርሶ እና ጉዳት አድርሶ በራሱ ቴሌቪዥን ጠፋተኛ ብሎ የሚያናግራቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ ጀግኖች፣ የነጻነት ተምሳሌዎች የሆኑትን የህሊና እስረኛ አንድነት ሽብርተኛ ብሎ ማለቱ አንድነት መሪዎቹን ማሰበላትና አቅጣጫ ለመቀየር አስቦ ከሆነ ከወዲሁ ፍተሻ እንዲደረግ እና የኢትዮጵያ ህዝብ በፓርቲዎች አቋም መዘበራረቅ ሳይሆነ ለቆምክለት የነጻነት ትግል ተስፋ ሳይቆርጥ መቀጠል አለበት ብለዋል። አንድነት ፓርቲ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ሙሉ ቃለ ምልልሱን በኢሳት ሬዲዮ ያዳምጡ
No comments:
Post a Comment