Translate

Friday, November 7, 2014

የሰላም ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ታሰረ

የሰላምና የዕርቅ ሃሳብ መስበኩ "ወንጀል" ሆኖበታል

fantahun berhanu

ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማስተባበርና በማቀራረብ እርቅ ለማስፈን እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት የመግባባት፣ አንድነትና ሰላም (ሰላም) ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አቶ ፋንታሁን የታሰረው ‹‹የሰላም ጥሪ›› በሚል ነጭ ሰንደቅ አላማ በማውረብለብና የማህበሩን አላማ የሚገልጹ፣ እንዲሁም ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ ችግር የሚላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር የያዘ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በመበተን ማህበሩን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡

በራሪ ወረቀቱ የህሊና እስረኞች መፈታት እንዳለባቸው፣ መንግስት በሀይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎችን ማፈናቀሉ እንዲቆምና መንግስት በተቋማት ላይ ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ የሚመክሩ ሀሳቦች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ነጭ ሰንደቅ አላማ ሲያውረበልብ፣ የማህበሩን አላማና በህዝብ ላይ አሉ ያላቸውን ችግሮች ለህዝብ ሲያስተዋወቅ የተያዘው አቶ ፋንታሁን ህዝብን ለማነሳሳትና አመጽ ለመቀስቀስ ሙከራ በማድረግ በሚል እንደተከሰሰም ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አቶ ፋንታሁን እሁድ ጥቅምት 23 ሽሮ ሜዳ አካባቢ በራሪ ወረቀት ሲበትን ተይዞ ላዛሪስት በሚባለው ፖሊስ ጣቢያ ታስ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ (ምንጭ እና ፎቶ: ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia)

No comments:

Post a Comment