Translate

Wednesday, September 10, 2014

የዌብሳይትን ትራፊክ በአዲስ አመት ለማጨናነቅ እና ኪስን ለመሙላት ትግሉን መጉዳት ተገቢ አይመስለኝም

eliyas
ኢትዮ ሪቪው በጉጉት ስንጠባበቅ የነበረውን “የፖሊስ ምርመራ ይፋ አደረገልን” ። በይሆን ይሆናል ማስረጃ የተደገፈው ይሄው “ሪፖርት” ታላቅ ሆኖ ሰሞኑን ይነበብ ዘንድ እና ወያኔን እንድንታገለውም ይላል። ሁሌም ታጋዮች በጠላት እጅ ሲወድቁ አደርባዮች ትግሉ እየሞተ ይመስላቸውና ከወዲሁ ካባ መቀየር በኢትዮጵያኖች ዘንድ የተለመደ ቢሆንም ይሄኛው ደግሞ የወረደ ነው።

ኤልያስ ክፍሌን ጋዜጠኛ ካልነው ‘ጋዜጠኛ’ ያልሆነ ትግል ሜዳ ላይ ገብቶ እቃቃው ፈረሰ የሚል ጀማሪ ግራ የገባው ጀግና ኢትዮጵያዊ ነው። ማንን መታገል እንዴት መታገል ወደየት ጥይት መተኮስ ያልገባው ታጋያችን የጀግኖች ሜዳ ላይ ገብቶ አቦራ መቃም ያለበትም አይመስለኝም።
ኤልያስ ከዚህ በፊት የአመቱ ታላቅ ሰው እያለ የሚሸልምልን ኢሳያስ አፈወርቂ እና የጀግኖች ሁሉ ጀግኖች እያለ ሲተርትልን የነበሩትን የአርበኞች ግንባርን እያስታወሰ፤ ነገር ግን በአንድ አጋጣሚ እኔ የመፃኢቱ ኢትዮጵያ ሊ/መንበር መሆን የምችል የራሴ ጀግና ነኝ እና ልምራችሁ በሚል ግጭት ከተባረረ በኋላ ዛሬ በዛ አካባቢ የሚመጡትን ማናቸውም የተቃዋሚ ሃይሎች እየተከታተለ ትግሉን ለማዳከምና እንደማይሰራ ለማሳየት የሚያደርገው በራሱ ዌብሳይት ዘመቻ አይ ኢትዮጵያ ታጋይ አይውጣብሽ፣ ምቀኞችን ያፍራብሽ ተብላ የተረገመች ሀገር ያስመስላታል።
የኢትዮጵያ እንባ ከባድ ሀዘኑም መራራ ቢሆንባትም ይህን የተረዳ እውነተኛ ጀግኖችም ባንጻሩ አሉ። ግንቦት 7 ይህን ተረድቶ ላንዳፍታም ቢሆን ቢዘናጋ ይገርመኛል። ጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች ከአበው የተማሩት አደርባይነትን ምቀኝነትን ሳይሆን መቻቻልን፣ እምቢተኝነትን በመሆኑ ይህ የፈጠራ ሪፖርት አንዳችም ችግር አይፈጥርም። በርግጥም ወያኔ ህወሃት ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ይህን ሊጠቀምበት ይችላል። ትግሉንም በጥርጣሬ አይን ሊያራዝመው ይችላል እንጂ ጸሃይ በኢትዮጵያ ተራራዎች መፍንጠቋ ግን ከቶ አይቀሬ ነው። ያውም የእማማ ኢትዮጵያን አርንጎዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ባንዲራ ፊታቸው ደም ተላብሶ ብቅ እንደሚሉ ከቶም ጥርጣሬ የለኝም።
ትግል መራራ ነው ባንድ ሰው ምኞት ከቶውኑም አይቆምም። ዛሬ አንዳርጋቸው ሚሊዮኖች ሆኗል። ግንቦት 7 ዛሬ ግንቦቶችን ወልዶል። የነጻነት ጥሪ ማህተብ በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ተመቷል። የማይፋቅ ያንዳርጋቸው ፍሬ ያረፈበት። ኢሳያስ በለው ፍጹም እየተባለ ለአንዳች የምያዘናጋበት የትግል ጉዞ… የማይቆም ሀዲድ…
ስለዚህ ልጅ ኤልያስ ባላውቅህም ቅሉ የግል ችግርህን የግል ጥላቻህን የድህረ ገጽህ ጎብኝዎች እንዲበዙ ብለህ ታሪካዊ ስህተት አትስራ! ሰለ አንተ የምሰማው ታታሪነትህ ዛሬ ወረደብኝ፤ ያንተን የቆየ ቁስል ከጀግናው አንዳርጋቸው ጋር በማያያዝ የትግሉን መንፈስ ለመቀየር ያሰብከው ትንሽ የብእር ቀለም ጠብታ የማይለቅ ጠባሳ ልቤ ላይ አደረግክበት።
ይገባኛል ትግሉ በረዘመ ቁጥር ማንም ሰው የሚሰማውን ስሜት እረዳለሁ፤ ችግሩ ምን ይሆንም የሚል ጥያቄዎችን ያስነሳል። የአንተ ግን ከዚህ ዘለለ እናም እባክህ የግለሰብ ጥላቻህን ወደ ፖለቲካ አትቀይረው። አንዳርጋቸው መሰዋእት የሆነው ላንተም ነው።
የኤርትራ መንግስት ይህን ሊያደርግ ካሰበ ማስገድልም ይችላል ወይም አትምጣም ሊለውም ይችላል። ከዛ ውጪ ከድሮ ጀምሮ ላንዳርጋቸው ያለህ ጥላቻ አንዴ እግሩ ተሰበረ፣ ተደበደበ፣ ታሰረ እያልህ በተደጋጋሚ ስታወጣ አስታውሳለሁ። አሁን ምናልባት ያንን ምኞትህ ቀይረህ አቶ ኢሳያስ አስደረገው ያልከው  ከአንድ ፖለቲከኛ ወይም በተቃዋሚ ተፈርጅህ የምትሰራ ጋዜጠኛ ተብዪ መስማቴ ላንተ ያለኝን የስራህ ጥናካሬ አውርዶ ዝቅ አደረገብኝ እና እባክህን ይህን የብእርህን አቅጣጫ ወደ እውነተኛ ሙያህ ትመልሳት ዘንድ ባክብሮት እጠይቃለሁ።
ባዲስ አመት የነጻነት ታጋዮቻችን ይፈቱ ዘንድ እንታገላለን እንጅ ትግሉ ላይ ውሃ ለመቸለስ የብእር ትግል መግባት የለብንም። ልዩነቶቻችንን ብዙ ናቸው። ባንዴም አይፈቱ ነገር ግን ጠላታችን አንድና አንድ ነው ወያኔ! ስለዚህ ይህ ያስተሳስረናል እንጂ አያፋታንም። ነገር ግን ለትግሉ መጎተት፣ ለወያኔ ማበር ወይም መተባበር ግን ይቅር የማያሰኝ ስህተት ነው። ኢሳያስ ሌላ ግንቦት 7 ሌላ። ኢሳት ሌላ ኢትዮ ሪቪው ሌላ።
ልጨርስ;- አንባቢዎቼ መቼም ይህን የመሰለ ይትግል ጉዞ አስጠሊታ ቢሆንም እንክርድዱን እያጣሩ መሄዱ ግን የእርሰዎ ነው። ግንቦት 7 ጥሩም ሆነ መጥፎ ጎን ሊኖረው ይችላል ነገርግን ወያኔን የሚረዳ ትግሉን እንድንጠራጠር እና ጀግኖች እንዳይታገሉ ማድረግ ተገቢ አይደልም። እስቲ ከኤርትራ ውጪ የትግል ሜዳ ልስራ የሚል ካለ ኤልያስን ጨምሮ ይንገረኝ እና ትግልን እንደ አቶ አንዳርጋቸው ጀምሮ ያሳየን። ብእር ሌላ ትግል ሌላ።
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ምን መምሰል እንዳለባቸውም መረዳት ወይም በፖለቲካው ሳይንስ ትምህርቱ ያለፈው subject ካልሆነበት በቀር ኢትዮጵያዊው ኤልያስ ያንን አይጽፍም። የአኬልዳማ ታላቅ የፖሊስን ምረመራ አስታወሰኝ! ለሁሉም እኔ በጉጉት የምጠብቀው የእንደዛ አይነቱን ምርመራ ያልሆነ መራራ ወረቀት ሳይሆን ህዝባዊ ሃይሎች ተዋሃዱ፣ ክፍፍል በቃ የሚል ነው። መልካም አዲስ አመት
አምሳሉ ጸጋዪ

No comments:

Post a Comment