Translate

Saturday, September 13, 2014

የ2007 ዓ/ምን አዲስ አመት በማስመልከት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ


url
አምባገነኖች የጭቆና ቀንበር ለመላቀቅ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ ለነፃነቱና ለመብቱ ሲታገል ለኖረውና የትግሉ ባለቤት ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፣
- በአርበኝነት ትግል በዱር ገደሉ ህይወታችሁን፣ ጉልበታችሁን፣ ጊዜያችሁንና ዕውቀታችሁን ሳትሰስቱ ለተቀደሰው ዓላማ በማበርከት ላይ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት፣

- ከአስከፊው የስደት ውጣ ውረድ ኑሮ ላይ በመቀነስ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በሞራል እና በሀሳብ የአርበኝነት ትግሉን በመደገፍ ላይ ለምትገኙ በውጭ የምትኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም
- ለወደፊቷ ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያ በጎ ምኞትን በማሰብ ትግሉን ያለመታከት በመደገፍ ላይ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ
እንኳን ለ2007 ዓ/ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ አደረሰን!   
ታሪክ ራሱን ደግሞ፣ የሀገር ህልውና ዳግም አደጋ ላይ ወድቆ ኢትዮጵያችን ልጆቼ በማለት የአድኑኝ ጥሪዋን ማሰማት ከጀመረች እነሆ ዓመታትን አስቆጠረች።በየዕለቱ በወያኔ የሚገደለው፣ የሚታሰረው፣ የሚሰደደውና የሚደበደበው ሕዝብ ቁጥር በአሐዝ ለማስፈር አዳጋች እየሆነ መቷል። የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ግፍ፣ በደልና የሉዓላዊነት መደፈር ጉዳዮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቤቱን ያላንኳኳበት ሰው አለ ማለት ዘበት ነው።
ወቅቱ ለጠየቀው የሀገር አድን ጥሪ ምላሽ በመስጠት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የአርበኝነት ትግል ችቦውን በመለኮስ እንደ ሻማ በመቅለጥ ብርሃን እየሰጠ እንደሆነ ይታወቃል። የተለኮሰውም ችቦ ሳይጠፋ የታለመለት ግብ ድረስ እንዲዘልቅ የደምና የአጥንት መስዋዕትነት በቋሚነት እየተገበረ ይገኛል። በዚህም ብዙ ሀገርና ወገን አፍቃሪ ጓዶች ከጎናችን ወድቀዋል፤ እኛም የመስዋዕትነት ረድፍ ላይ ሆነን የአርበኝነት ተጋድሎውን በጽኑ ሀገራዊና ወገናዊ ፍቅር ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግረነዋል። አዎ! አዲስ የትግል ምዕራፍ! ለዓመታት ሲካሄድ የቆየውን የተበታተነ ትግል በመሰብሰብ የወያኔን አገዛዝ እድሜ ለማሳጠር የተደረገው እልህ አስጨራሽ ጉዞ ፍሬ አፍርቶ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7 የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ የውህደቱን መንገድ ጀምረነዋል። የፍሬውም ተቋዳሽ የምንሆነበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።
አዲስ መንፈስ፣ አዲስ ዕቅድና አዲስ ራዕይ የአዲስ አመት አንዱ መገለጫዎች ናቸው። እነዚህንም መገለጫዎች ወደ መሬት ለማውረድ የአዲስ ዓመት ውጥን ማዘጋጀት የተለመደ ሂደት ነው።በመሆኑም የመላ ኢትዮጵያዊ የ2007 ዓ/ም አዲስ ዓመት ተቀዳሚ ውጥን መሆን ያለበት የወያኔን አገዛዝ ለማስወገድ የበኩሉን አስተዋፆ ለማበረከት ቆርጦ መነሳት ነው። የዚህንም ተፈፃሚነት ለማረጋገጥ አንድም ወደ ትግሉ በመቀላቀል ሲሆን ሌላው ደግሞ በየጊዜው ለሚኖሩ ሕዝባዊ ጥሪዎች ባለ አቅም ሁሉ ምላሽ በመስጠት ትግሉን መደገፍ ነው። በመሆኑም በአዲሱ አመት ውጥናችን ውስጥ መካተት ያለባቸውን ነገሮች መካተታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
አዲሱ ዓመትም የድል ዘመን እንዲሆንልን በተባበረ ክንድ የወያኔን አምባገነናዊ አገዛዝ ለማስወገድ የተጀመረውን ሁለገብ የአርበኝነት የትጥቅ ትግል በመደገፍ ሁሉም ዜጋ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ጎን እንዲቆምየትግል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
አንድነት ኃይል ነው!!!
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
መስከረም 2007 ዓ/ም

No comments:

Post a Comment