Translate

Thursday, May 30, 2013

የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ


የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓም ተጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከተካሄደ በኋላ ህዝባዊ ትግሉን ወደፊት የሚያራምዱ ዉሳኔዎችን ካሳለፈ በኋለ ባለፈዉ ሰኞ ምሽት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ። ይህ የንቅናቄዉ አራተኛ መደበኛ ጉባኤ ንቅናቄዉ ባለፉት ሁለት አመታት የተጓዘባቸዉን መንገዶች፤ ያቀዳቸዉን ስራዎችና የዕቅዱን አፈጻጸም በጥልቀትና በስፋት በመዳሰስ መጪዉ የትግል ወቅት የሚጠይቀዉን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተመልክቶ ዘረኛዉን የወያኔ አገዘዝ በማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የዲሞክራሲ ጥማት ሊያረኩ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸዉን አበይት ዉሳኔዎች አሳልፏል።

የግንቦት 7 ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ህዝቡ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረበ

የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ከግንቦት 11 – 19/2005 አ/ም በበርካታ ወቅታዊ፣ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት እና የድርጅቱን አዲስ ም/ቤት በመምረጥ ወያኔን በማስወገድ ረገድ ሊከተል የሚገባውን ጠቋሚ አቅጣጫዎችንና ውሳኔዎችን ከተሳታፊው በመውሰድ ወሳኝ የሆነ ውይይት አድርጓል።
ንቅናቄው ከተለያዩ አለማት በአባላት የተወከሉ ጉባኤተኞች እና በተለያዩ የስራ ክፍል የሚገኙትን የድርጅቱን አባላት ያሳተፈ፤ ከዚህ በፊት ከተደረጉትም ጉባኤዎች እጅግ የላቀ አባላት የተገኙበት ነበር።
ጉባኤው የነበረውን የም/ቤት ሪፖርት፣ የስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የኦዲትና ማናጅመንት ኮሚሽን፣ የግልግልና ዳኝነት ኮሚቴን እና የፋይናንስ ሪፖርቶችን በማዳመጥ ጥልቅ የሆነ ወይይቶች አደርጓል።
የግንቦት 7 ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች፤ ደርጅቱ የጀመረውን ወያኔን የማስወገድ ትግል በየትኛውም አቅጣጫ አስፈላጊ ሆኖ የታመነበትን ማናቸውም መንገድ ሁሉ በመጠቀም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የዘረኝነትን ስርአት ድባቅ መምታት፤ አልፎም ዘላቂ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አስቸኳይና ማንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ግዴታው አድርጎ መውሰድ ያለበት አጣዳፊ ስራ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።

የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን በኅብረት ስራ ጀመሩ!

ዓርብ የፖለቲካና የሙስሊም እስረኛ ጠበቆችን ያነጋግራሉ

aba nsmneበኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተ የአሜሪካን የህግ ባለሙያዎች ማህበር (ABA – American Bar Association) ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ አርብ እንደሚጀምር ተገለጸ። አዲስ አበባ ካሉ የፖለቲካና የሙስሊም ወገን እስረኞች ጠበቆች ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ አርብ ግንቦት 23፤2005ዓም ያደርጋሉ። አቶ ኦባንግ ሜቶ የተረሱ እስረኞች ጉዳይም እንደሚካተት ጠቅሰው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለታሰሩ ዜጎች ጥብቅና የቆሙ ካሉ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ በቀጥታ እንዲገናኙ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢህአዴግ ደብሮታል!

575707_555196677856268_1202584028_nባለፈው ጊዜ ግንቦት 17 ሰማያዊ ፓርቲ በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ አቅርቦ መነግስት እንደተለመደው ዝም ብሎ ደብዳቤ አንቀበልም በማለት አላየንም አልሰማንም ብሎ የአራዳ ሰፈር ልጆች (ባላየ ባልሰማ ሙድ) እንደሚሉት አይነት ሊያልፈው ነበር፡፡

ሊደመጥ የሚገባው እና ጥልቅ የሆነ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አብርሃም ያየህ

A must listen interview with Abraham Yayeh on current events in Ethiopia
ከአቶ አብርሃም ያየህ
ዳዊት ከበደን አውራምባ ታይምስን ለዚህ ጥልቅ ቃለ መጠይቅ ከልብ እናመሰግናለን

Wednesday, May 29, 2013

‹‹አገሬን ያወቅኋት አሁን ነው፤ ዜጋ ነኝ ለማለት አይቻልም፤›› አቶ ነጋ፣የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በተጠርጣሪዎች 60 የክስ መዝገቦች መቋረጣቸውን አስታወቀ

 - የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት
- ሁለት ተጠርጣሪዎች በምርመራ ወቅት መደብደባቸውን ተናገሩ
‹‹ተያዘ የተባለው ሰነድ ሁሉ በሀብት ምዝገባ ያስመዘገብኩት ነው›› አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ምርመራ ቡድን፣ በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዲቋረጡ ከተደረጉት 60 የክስ መዝገቦች ውስጥ 28 ያህሉን መሰብሰቡን ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
a9ed2de4dd18d7819ad682d04e71a5e6_Lመርማሪ ቡድኑ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ እንዳስረዳው፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ባለፉት 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ላይ የሠራውን የምርመራ ሥራ እንዳብራራው፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሥራዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ሰብስቧል፡፡ ከተለያዩ ባንኮች በተወሰኑ ተጠርጣሪዎች ላይ ከአራጣ ብድር ጋር የተያያዙ ማስረጃዎችን፣ በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ (መኒ ላውንድሪንግ) መጠቀምን የሚያሳዩ ሰነዶችን መሰብሰቡን ገልጿል፡፡
መርማሪ ቡድኑ ጨምሮ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪዎቹ በአራጣ ብድር የተከሰሱ ሰዎችን ክስ ያቋረጡባቸውን የክርክር መዝገቦችን መሰብሰቡንና በኮንትሮባንዲስቶች ላይ በፍርድ ቤት ተጀምረው ከነበሩትና በሕገወጥ ጥቅም ከተቋረጡት 60 የክስ መዝገቦች ውስጥ 28 የሚሆኑት መሰብሰቡንም ገልጿል፡፡

Tuesday, May 28, 2013

አቶ ስብሐትና የተንኮል ፖሊቲካ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም (መነበብ ያለበት)

ጥቅምት 2005
አቶ ስብሐት ነጋ ሙሉ ነጻነቱን የሚወድ ሰው መሆኑን አደንቅለታለሁ፤ አስቦም ይሁን ሳያስብ አንደልቡ የመናገር ባሕርይ አለው፤ በበኩሌ ይህንን ባሕርዩንና በመብቱ መጠቀሙን አከብርለታለሁ፤ ሀሳቡ የተሳሳተ ይሁንም አይሁንም፣ እኔ የምስማማበት ሆነ አልሆነም፣ እኔ ልቀበለውም አልቀበለው ስብሐት ነጋ በሙሉ ነጻነቱ ተጠቅሞ ሀሳቡን ሁሉ መግለጹን አከብርለታለሁ፤ እሱም የእኔን ሀሳብ የመግለጽ ነጻነት አንደሚያከብርልኝና እንደሚያስከብርልኝ ተስፋ አለኝ፤ ከዚያም በላይ ነጻነት ሁልጊዜም፣ የትም ቦታ ከኃላፊነት ጋር የተቆራኘ መሆኑን እንድንገነዘብ ያሻል፤ ኃላፊነት የሌለበት ነጻነት የለም፣ ኃላፊነት የሌለበት ነጻነት ስሙ ሌላ ነው፡፡
በቅርቡ አቶ ስብሐት በአደረገው ቃለ መጠይቅ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የተሾመው ወያኔ ዱሮም አስቦበት ወንበሩን ከአማርኛ ተናጋሪዎችና ከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት በተዘጋጀበት እቅድ ነበር ብሎአል፤ ልብ ላለው አነጋገሩ በሁለት በኩል ስለት ያለው ቂል የያዘው ሰይፍ ነው፤ ከፊት ለፊት የተሰነዘረው አማርኛ ተናጋሪውንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አማኙን ለመምተር ነው፤ ቂል የሚያደርገው አማራ የሚባል ጎሣ ቢኖርም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በአማርኛ ተናጋሪዎች ታጥሮ ትግሬንና ኦሮሞን፣ ወላይታንና ጉራጌን፣ ሌሎችንም የማይነካ መስሎት ከባድ ስሕትት ላይ መውደቁ ነው፤ ከሁሉም በላይ እሱን የሚያህል ሰው የተክለ ሃይማኖትን ታሪክ አለማወቁ ያሳዝናል፡፡

በአንባገነኖች የሀሰት ውንጀላ እስር እና እንግልት አንበረከክም! (ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር)


በአንባገነኖች የሀሰት ውንጀላ እስር እና እንግልት አንበረከክም! (ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር)

በአንባገነኖች የሀሰት ውንጀላ እስር እና እንግልት አንበረከክም! (ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር)
Statement from Baleraey Wetatoch

“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!”


በአቤ ቶክቻው

“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ጉንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አለ ታጋዩ…
“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ አሁን ደግሞ ለራሱ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ቆጣጥሮታልም፤ ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አልኩ እኔ…
“ኢህአዴግ ደርግን ደመሰሰ እና ሌላ ቀዳበት” አለ ልጅ ያሬድ! ”ኢህአዴግ ደርግን ደምስሶ በደርግ ዜማ ሌላ ቀዳበት” አልኩ እኔ
ዛሬ ግንቦት ሃያ ነው፡፡Abe Tokichaw (Abebe Tolla) the Popular Ethiopian Political Satirist
አነዛ ፀጉራቸውን አሳድገው አዲሳባ የገቡ ሰዎች ዲሞክራሲን እና መልካም አስተዳደር ያሳድጉልናል… ብሎ ተስፋ የጣለባቸው ሁሉ በቴስታ ብለው ከጣሉት እነሆ ሃያ ሁለት አመት እንደዋዛ ሆናቸው፡፡
መልካም አስተዳደሯንም ለራሳቸው እያደሯት፤ ዴሞክራሲዋንም ራሳቸው እየኮመኮሟት ህብረተሰቡን እንቁልጭልጭ አሉት፡፡
ዛሬ የግንቦት ሃያ በዓል ሲከበር የአባይ ወንዝን የማስቀየስ ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡ ወንዙ ተቀይሶ ምን ላይ ሊሆን ነው… እንዴት ነው ነገሩ በሳፋ ነው እንዴ ግድቡ የሚሰራው… ብዬ ልጠይቅ ወይስ አልጠይቅ…!

Monday, May 27, 2013

የኢህአዴግና የሻዕቢያ ድርድር ተበጠሰ


ኢሳያስ፣ ደሚት፣ ግብጽ፣ ኳታር፣ ኢህአዴግ

haile and esayas


ኳታር በተናጠል የጀመረችው ኢትዮጵያንና ኤርትራን የማሸማገል ሂደት መበጠሱ ተሰምቷል። ከሽምግልናው ዙሪያ የግብጽ ሚና ስለመኖሩ አመላካች ጉዳዮች አሉ እየተባለ ነው። በድርድሩ ኢህአዴግ በዋናነት እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠው የትግራይ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደሚት/ ጉዳይ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

መለስ ዜናዊ በአለማችን ላይ ሁለተኛው ሀብታም ጠቅላይ ሚኒስተር መሆኑን ምን ያህሎቻችን እናወቃለን?


ለማንኛውም therichest.org የተባለ ድህረ ገፅ ይፋ ያደረገው የሀብታም መሪዎች የሀብት ዝርዝር እነሆ
Richest Prime Ministers
Meles Zenawi net worth: Meles Zenawi Asres was the former Prime Minister of Ethiopia who presided over the country from 1995 to his death in 2012. He was also the President of Ethiopia from 1991 to 1995. He was one of the most recent literate and forward thinking leaders of Africa. Zenawi had an MBA from the United Kingdom, and a Masters of science in economics from Netherlands. His net worth currently stands at $3 Billion.

በነጭ ውሸት ላይ የተመሰረተ ትንተና የት ያደርሰን ይሆን?


በቴዎድሮስ በላይ

አቶ ጁዋር ሲራጅ መሃመድ በቅርቡ ከአቶ ደረጀ ደስታ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ በአጽንኦት ተከታትያለሁ። የሰውየው ግለ ታሪክና ያደረጋቸው ጉዞዎች መሳጭ ቢሆኑም አንዳንድ እርማት የሚያስፈልጋቸው የተሳሳቱና የተዛቡ ታሪኮችን እንደገና እንዲፈትሽ፤ ሆን ብሎ እያራገበው ከሆነም ቆም ብሎ እንዲያስብበት ለመጠቆም ወደድኩ። የተሳሳተ መረጃ መረጃ ራስንም ሌላውንም ክፉኛ ይጎዳል። ሊዘህ መነሻ የሆነኝ፤ ስለ ኦሮሞ ጭቆና መነሻውን ሲገገልጽ፤ አማራዎቹ የአውሮፓን መሳሪያ ቀድመው ስላገኙ የሚል፤ መሰረት የለሽ ውንጀላው ነው።
ጋዜጠኛ ደረጀ ስለ ኦነግ አመሰራረት ሲጠይቀው፤ ጁዋር እንዲሚከተለው መለሰ። “እንግዲህ በመቶ አመታት ወደዃላ ሂደን ስናይ አካባቢው በቡድን ግጭት የተሞላ ነበር-በተለይ ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ።

Saturday, May 25, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ :-የፖለቲካ መብረቅ!!

ተጻፈ በምንሊክ ሳልሳዊ
semayawiወያኔ ሆይ እኔ ምንም አልልም…ሃሃሃሃ…በፓርቲሽ ውስጥ ሰማይዊ ፓርቲን በተመለከተ የተፈጠረው ውዥንብር እስከዛሬ አለመታየቱ አሊያም በቅንጅት ሜዳ ላይ አለመፈጠሩ አንድም መለስ ዜናዊ አለመኖሩ ይሆናል አሊያም መውደቂያሽ መድረሱን እየጠቆመ ይሆናል እኔ ግን ምንም አልልም ..መረጃውንም ዘግየት ብየ ከሰልፉ በኋላ እለቀዋለሁ ::ግን አንድ አጠር ያለ ነገር ልል ነው ከተለመደው ሳልወጣ ማለት ወያኔ በፖለቲካ መብረቅ እንደተመታች ልናገረው :;
ወገን ብዙ እየተባል ነው ስለሚባለው ትጠን አንዳንድ ፖለቲካ ሳያኝኩ የሚውጡ ዲያስፖራዎች ግን ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ቀኑ መዘዋወሩን እንደ ፖለቲካ ክስረት ያዩት ለምን እንደሆን አይገባኝም ::ቢገባኝም እነሱ ምን አገባቸው ኪሳራ ብለው ፈርጠም አሉ ይህን የፈጠሩት ደሞ መሃል ሰፋሪ ሰኣቱን ጠብቀው ከባለድል ሊቀላቀሉ የሚፈልጉ ባለሟሎች የመኖሪያ ፍቃድ የማሳደሻ ሰነድ እንዳዘጋጁ በሰው ሃገር መቀበሪያ የገዙ ሲሆኑ እነሱም እነሱ እነሱም በፖለቲካ መብረቅ ተመተዋል::

ሽፈራው ሽጉጤን ከሃላፊነታቸው ለማንሳት ወያኔ በሚስጥር እየሰራ ነው፤


shiferaw-shigute
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋትና አለመተማመን ያሰጋው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ አቶ
ሽፈራው ሽጉጤን ከሃላፊነታቸው ለማንሳት የሲዳማን ህዝብ የማሳመን ስራ ጀምሯል።ታማኝ ምንጮች እንዳሉት አቶ ሽፈራውን
እንዲተኩ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ታጭተዋል።
ባለፈው ወር በክልሉ በተካሄደ ግምገማ ፕሬዚዳንቱ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በኪራይ ሰብሳቢነትና በሙስና ተፈርጀው ለህግ
ተላልፈው እንዲሰጡ ሲወሰን “እኔ ከተከሰስኩ ወ/ሮ አዜብ መስፍንም መከሰስ አለባቸው” በማለት መልስ ሰጥተው ስብሰባውን
ረግጠው መውጣታቸውን የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በስፍራው የሚገኙትን ምንጮች ጠቅሶ መዘገቡ የሚታወስ ነው።
በክልሉ አብላጫ የህዝብ ብዛት ካለው የሲዳማ ብሔረሰብ የተወለዱት አቶ ሽፈራው፣ከስልጣናቸው ተወግደው ለፍርድ
እንዲቀርቡ ቢወሰንም ውሳኔው ተግባራዊ ያልሆነው በሁለት ምክንያቶች እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው።የመጀመሪያው
ምክንያት ፕሬዚዳንቱ በተገመገሙበት የሙስና ወንጀል የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት መካተታቸው ሲሆን፣ሁለተኛው ደግሞ
የሲዳማ ህዝቦች ያምፃሉ በሚል ፍራቻ ነው።

በየፊናችን እየተማረርን መማራችን ለበጎ ነው (አዲስ አበባ)


ይነጋል በላቸው

እቲ ናይ ቀደም ሰላም ዘመን ክምለስ፤
ሰላም ኢልና ንዝመር ብሃደ መንፈስ፡፡…
(ከኤርትራው ተወላጅ ድምጻዊ ርዕሶም ገ/እግዚአብሔር የዘፈን ግጥም የተወሰደ)
Ethiopian Satellite Television (ESAT)ይሄ ኢሣት የሚባል ቴሌቪዥን በትዝታ ባህር እያስዋኘ ጊዜየንም ዕንባየንም እያስጨረሰኝ ነው፡፡ በግማሽ ሜትር ርቀት እሱው ጋ  - እቲቪው አጠገብ – ከተደቀንኩ የሚያስነሳኝ የለም፡፡ ቤቴ ሁሌ በአምባጓሮ እንደታመሰ ነው፡፡ ቤተሰብ የሚፈልገውና እኔ የምፈልገው ለየቅል በመሆኑ ትንሹ አምባገነን ሆኛለሁ፡፡ ለነገሩ አምባነንነት የሚጀምረው ከቤት ነውና ይቺ ተፅዕኖየ እየተሰማችኝ መጥታለች፡፡ ምን ላድርግ?
ትናንትና ጧት ላይ ሲሳይና ተወልደ ይበልጡን በግንቦት ወር ዙሪያ የሚያጠነጥንና እልህና ቁጭት ውስጥ የሚከት ዝግጅት እያቀረቡ ሳለ አንድ ሙዚቃ ጋበዙን፡፡

ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ


(ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. / May 24, 2013)

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ከተመሠረተ 2007 እ.አ.አ ጀምሮ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናትን የምዕራቡ ድንበራችን እርዝማኔው 1600 ኪ/ሜትር የጎን ስፋቱ ከ30 እስከ 60 ኪ/ሜትር የሚሆነውን ከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብትና ልዩ ልዩ ብርቅየ የዱር አራዊትና አውዋፍ የሚገኙበት አንጡራ ለም የድንበር መሬታችንን ፀረ-ኢትዮጵያው ወያኔ የገዥ ቡድን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት በምስጢር መደራደሩን ፤ ከዚያም በኋላ መስጠቱን ለሕዝብ በማጋለጥ በተከታታይ ሰፊ መግለጫዎች ማውጣቱ፤ ለልዩ ልዩ የዜና አውታሮች ቃለ-ምልልሶች መስጠቱ እና የተለያዩ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ማካሄዱ የሚታወስ ነው። ከዚህም በላይ፤ ይኽኑን አሳሳቢ የድንበር ጉዳይ በተመለከተ ስፋትና ጥልቀት ያለው ታሪካዊ ሠነድ እንደሚያዘጋጅ ቃል መግባቱ የሚታወቅ ነው።
በዚሁ ቃል-ኪዳን መሠረት፣ ከሁለት ዓመት በላይ ሰፊ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ሲያካሂድ ቆይቶ፤ ይህኑን ዓብይ ጉዳይ በተግባር ለማዋል እንዲችል፤ የድንበሩ ኮሚቴ ከፍተኛ አካል የሆነው ምክር ቤት ግንቦት 10 እና 11 ቀን 2005 ዓ.ም. ( May 18 and 19, 2013 ) ታላቅ ጉባዔ በሲሊቨር ስፕሪንግ ከተማ፣ ሜሪላንድ፣ አሜሪካ (Silver Spring, Maryland, USA) አካሂዷል።

Friday, May 24, 2013

ሰበር ዜና፣ የሰማያዊ ፓርቲ የግንቦት 17ቱን ሰልፍ ወደ ግንቦት 25 አስተላለፈ


ECADF – የሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ሲል ጠርቶት የነበረውን የሰላማዊ ሰልፍ በተመለከተ ለአዲስ አበባ አስተዳደር በደብዳቤ ለማሳወቅ በሞከረበት ወቅት የከተማው አስተዳደር ሀላፊዎች ሆን ብለው ደብዳቤውን አንቀበልም በማለታቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የአይን እማኞች በተገኙበት ደብዳቤውን በአንዱ የከተማው አስተዳደር ቢሮ ውስጥ እጠረጴዛ ላይ አኑረው እንደወጡና በህጉ መሰረት የሰላማዊ ሰልፉን ከጠራው አካል በኩል መደረግ ያለበት ሁሉ ስለተደረገ ፓርቲው በያዘው ፕሮግራም መሰረት ሰልፉን ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት እንደሚያካሂድ አሳውቆ ነበር።
የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰልፉን ፈቀደ
የሰማያዊ ፓርቲ ስለ ሰላማዊ ሰልፉ ለአዲስ አበባ አስተዳደር በደብዳቤ ለማሳወቅ በሞከረበት ወቅት ደብዳቤውን ለመቀበል አሻፈረኝ ብለው ሲያንገራብዱ የዋሉት የከተማው አስተዳደር ሀላፊዎች ዘግይተው የሰማያዊ ፓርቲ ባሳወቀው ቀንና ቦታ ሰልፉን ሊያካሂድ እንደሚችል ለፓርቲው በቀጥታ በተጻፈ ደብዳቤ አሳወቁ (እኛም የዚህን ደብዳቤ መልዕክት በሰበር ዜና ይዘን ወጥተን ነበር)። የሰማያዊ ፓርቲም ይህንኑ ደብዳቤ እንደተለመደው በፌስ-ቡክ ገጹ ላይ አትሞታል። (የደብዳቤውን ይዘት ለመመልከት እዚህ ይጫኑ።)

እጅግ ሰበር ዜና፤ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ በአዲሳባ ከንቲባ ጽ/ቤት እውቅና ተሰጠው! (ብራቮ ከንቲባ ብራቮ ሰማያዊ!!!)

968802_418767841554502_16363769_n

ወያኔ እና እኛ ሙስና ስንል


በቅርቡ በሀገር ውስጥ ገቢና በጉሙሩክ አገልግሎት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ጥቂት ባለስልጣኖችና ተባባሪ የተባሉ ግለሰብ ነጋዴዎች፣ በሙስና ተወንጅለው ወህኒ መውረዳቸውን ተከትሎ ወያኔ ፀረ-ሙስና ድርጅት ለመምሰል ከተግባሩ የበለጠ የከበሮ ድምጽ እያሰማን ይገኛል። አንዳንድ የዋህም ይህን ከበሮ በመስማት ሙስናን ለማጥፋት ዘመቻ የተጀመረ መስሏቸው ተስፋ ሲያደርጉ ይታያል።
በመሰረቱ ሙስና በወያኔ ስርአት ውስጥ የስርአቱ መቆሚያ ምሰሶ ከሆነ ውሎ አድሯል። በሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት እየተመናመኑ በሄዱበት ፍጥነት ነው ሙስና እየደራ የሄደው። ከላይ እስከታች በተዘረጋው የወያኔ ስርአት ውስጥ ከቁንጮ ባለስልጣናት እስከታችኛው አገልጋይ ድረስ በሙስና ያልተዘፈቀ የስርአቱ አገልጋይ መፈለግ ከዝንጀሮ ቆንጆ የመምረጥ ያህል ከባድ ሆኗል።
የወያኔ ትላልቅ ሙሰኞች ለምልክት ትንንሽ ሙሰኞችን አልፎ አልፎ በማሰር ፀረ ሙሰኛ መስለው ሊያሞኙን ቢሞክሩ ዛሬ የመጀመሪያቸው አይደለም። ወያኔ ሙስናን ክስ የሚጠቀምበት አንድም በውስጡ ካፈነገጡ ሃይሎች ጋር የፖለቲካ ልዩነትን ለማወራረጃ ወይም ለውጭ ለጋሾች ሙስናን የሚጠላ መስሎ ለመታየት ሲፈልግ ብቻ መሆኑን ከልምድ እና ከተግባሩ ህዝቡ ያውቀዋል።
የወያኔ መንግስት ሀገሪቱን ወደ ድህነት ማቅ ቁልቁል እያስገባና ሀገሪቱ በእዳ እያስያዘ፣ በአንጻሩ ግን የስርአቱ ቁንጮ ባለስልጣናት በሙስና ተዘፍቀው፣ በልፅገውና ከብረው፤ ራሳቸውን ከሙስና ነጻ ሆኖ ለመታየት ሲያሻቸው ግልገሎቹን በማሰር እና በራሳቸው ሚዲያ አስረሽ ምችው ይጨፍራሉ።

“…መብቴን ነፃነቱን ጠየቅሁ እንጂ እኔ… ለግንብ ለፎቅ እማ ምን አለኝ ጣሊያኔ”

Abe Tokchaw
Yegna sferየቦሌ መንገድ ተሻሽሎ ተገንብቶ ዛሬ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን ሰማሁ፡፡ ጥሩ ነው፡፡ “መንገድ ምናባቱ አይባልም ደርሶ የወሰደውን ሰው ያመጣል መልሶ” ነውና የቦሌም መንገድ የሊማሊሞም መንገድ ቢታደሱ በበኩሌ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ነው፡፡ የቦሌውም እኛን እንደወሰደ ይመልሰን ይሆናል የሊማሊሞም “በሊማሊሞ አቋርጡ” የተባሉትን በሙሉ ሊመልስ ይችላልና ሁሉም መንግዶች፤ ሰፋ ሰፋ ብለው መጠበቃቸው ፌሽታችን ነው፡፡
በዛ ሰሞን ከፌስ ቡክ ሰፈር ልጆች የሰማኋት አንዲት ግጥም አለች፡፡ ሙሉ በሙሉ ግጥሟን ማስታወሴን እንጃ መልዕክቷ ግን እንዲህ ይላል///

ዜና በጨዋታ አይነት ነገር፤ ሰማያዊዎች አምርረዋል፤ አምረዋልም! Abetokichaw


253297_418646384899981_1037053069_n
የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ግንቦት 14 ለአዲሳባ ስብስባ እና ሰላማዊ ሰልፍ “አዋቂ” ጽ/ቤት (ሙሉ ስሙን ረስቼዋለሁ… በህገ መንግስቱ መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ አይጠየቅም እወቁልን ነው የሚባለው… ስለዚህ ስሙን ከተሳሳትኩ እንኳ እንዲህ ነው መሆን ያለበት የሚል መከራከሪያ ላነሳ ፈልጌ ነው ማለት ነው…) ብቻ ለማሳወቅ ደብዳቤ ይዘው ቢሄዱ የጽ/ቤቱ ሃላፊዎች ደብዳቤውን አንቀበልም ብለው… “ገግመው” ነበር፡፡ “ገገመ” ቃሏ ከአራዳ ስትሆን እምቢ ማለት ሳይገባው እምቢ አለ… ለማለት ታገለግላለች፡፡

የደህንነት ሹሙ ስዊድን ይመጣሉ


አዲስ አደረጃጀትና አዲስ ሬዲዮ በስካንዲኔቪያ

eprdf1
በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security Service) የብሔራዊ ደህንነትና የደኅንነት አገልግሎት ሁለተኛ ሰው የሆኑት አቶ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ ስዊድን እንደሚመጡ ተሰማ። በስካንዲኔቪያ አገራትና በድፍን አውሮፓ በሚኖረው ዲያስፖራ ላይ የሚያተኩር “የግል” መሰል የሬዲዮ ስርጭት ለመጀመር መታሰቡም ተሰምቷል።

Thursday, May 23, 2013

Ethiopia Amnesty International Annual Report 2013


Ethiopia Amnesty International Annual Report 2013

amn
The state stifled freedom of expression, severely restricting the activities of the independent media, political opposition parties and human rights organizations. Dissent was not tolerated in any sphere. The authorities imprisoned actual and perceived opponents of the government. Peaceful protests were suppressed. Arbitrary arrests and detention were common, and torture and other ill-treatment in detention centres were rife. Forced evictions were reported on a vast scale around the country.

Background

In August, the authorities announced the death of Prime Minister Zenawi, who had ruled Ethiopia for 21 years.

አንዲት ፀሎት፤ ጥቁር ለባሾችን ከነጭ ለባሾች ይጠብቅልን!


ህብረትን 50ኛ አመት በዓል ትንሽ ሰብሰብ ብለው ሊያከብሩ እና ትንሽ ሰብሰብ ብለው ሊያሸልቡ ተቀጣጥረዋል፡፡
ብዙ ጊዜ የውጪ ሀገር እንግዶች ወደ ኢትዮጵያ ለስብሰባ መጥተው ሲወጡም ሆነ ሲገቡ መንገዱ ታጥሮ የሰው ዘር ዝር ብሎ አይተው ስለማያውቁ ሀገራቸው ሲሄዱ አዲሳባ የፌደራል ፖሊሶች እና የቤተመንግስቱ ጠባቂዎች መኖሪያ ብቻ ሳትመስላቸው አትቀርም፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ልጆች  እንዳሰቡት ከተሳካላቸው፤ ለአፍሪካ መሪዎች እና ለሌሎቹም እንግዶች በሀገሪቷ ውስጥ ከፌደራል ፖሊስ እና ከቤተመንግስቱ ጠባቂዎች ሌላም ሰው መኖሩን እናሳያለን ብለዋል፡፡ ሰው ብቻም ሳይሆን በመንግስቱ ላይ ያዘነ ማቅ የለበሰ ሰው አለ የሚለውን ለማሳየት ጥቁር እንለብሳለን ሲሉም ጨምረዋል፡፡

ሰበር ዜና፣ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን በታቀደው ቦታና ስዓት እንደሚያካሂድ አስታወቀ


ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማብራሪያ

ሕገ ወጥነት ከዓላማችን አይገታንም!!!
ሕግ ምን ይላል?
አዋጅ ቁጥር ፫/፲፱፻፹፫ ዓ.ም
ስለ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት የወጣ አዋጅ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው አካል ስላለበት ግዴታ በአንቀጽ ፬ ላይ እንዲህ ይላል  አንቀጽ ፬፤ የማሳወቅ ግዴታ፤
፩/ ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ህዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የሚያዘጋጀው ማንኛውም ግለሰብ፣ ቡድን ወይም ድርጅት የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ከሚካሄድበት ጊዜ ቢያንስ ከ፵፰ ሰዓታት በፊት በጽሑፍ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

ኢሳት ጋዜጠኞች ጆሮ ላይ ስልክ ለምትዘጉ ባለስልጣኖች ማሰጠንቀቂያ


እስከ ነጻነት

Ethiopian Satellite Television (ESAT)መረጃ የማግኘት መብት የስብዓዊ መብት ዋናው መሰረት ነው፡ መረጃ የማግኘት መብት ዋናው የሰብዓዊ መብት ምሰሶ መሆኑን የሃገራት ደርግ (League of Nations) የደነገገው በ1946 ዓ.ም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነበር፡ ያደጉ ሃገራት ይህንን መብት በሚገባ ይጠቀሙበታል፡ ገልብጦ መጻፍ እንጂ ማንበብ የማይችልው የወያኔ ዘረኛ ስርዓትም ይህንኑ መብት በህገመንግስቱ ላይ አሰቀምጦታል። ለነገሩ ያላሰቀመጠው ነገር የለም ግን ማን አንብቦት ተግባራዊ ያደርገዋል እንጂ። ተግባራዊ እየሆነ ያለው ዘርን ለማጥፋት የተወጠነው የጫካው ህጋቸው ብቻ ነው።

ኦባንግ ለኬሪ የጥሪ ደብዳቤ ላኩ!


አኢጋን ለታቀደው ሰልፍ ድጋፍ ሰጠ

smne state

ጆን ኬሪ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በፋክስ የሚደርስ ቀጥታ ደብዳቤ ላኩ፡፡ በደብዳቤው ላይ አቶ ኦባንግ ሰሞኑን በአፍሪካ ህብረት አካባቢ ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድርጅታቸው ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
በቅርቡ በሚከበረው 50ኛው ዓመት የአፍሪካ ኅብረት ክብረበዓል ላይ በተጋባዥነት ለሚገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 

በጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋ በሰላሳ ሳንቲም መቀነሱ አነጋጋሪ እየሆነ ነው


በጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋ በሰላሳ ሳንቲም መቀነሱ አነጋጋሪ እየሆነ ነው

dollar1


በአዲስ አበባ የሚገኙ የጥቁር ገበያ ባለድርሻዎች በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ነጋዴዎች ከሙስና ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በመታሰራቸው በተፈጠረ መደናገጥ መነሻ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ እያጋጠማቸው መሆኑን ገልፀው፣ የዶላር ምንዛሪ በታሪኩ የሰላሳ ሳንቲም ቅናሽ አሳይቷል።

Tuesday, May 21, 2013

በአዲስ አበባ በባልና ሚስት የተደረገ ታይቶና ተሰምቶ የማያቅ ዘግናኛ ድርጊት


‹‹ጉዳዩ የተፈፀመው በአዲስ አበባ ጎተራ ኮንዶሚኒየም ቤት ውስጥ ነው፡፡ ባል እና ሚስቱ የህክምና ዶክተሮች ለብዙ ዓመታት
አብረው በሞቀ ትዳር ውስጥ ቆይተው ነበር፤ ከትዳራቸውም አንዲት የ9 ዓመት እና አንዲት የ6 ዓመት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሀይማኖታቸው የተለየ ፍቅር በማሳደር ከፍተውት የነበረውን ክሊኒካቸውን ዘግተው ራሳቸውን አስገዝተው ሲኖሩ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለላቸው፡፡
ይሄውም እንደ ጌታ እየሱስ 40 ቀን እና 40 ሌሊት ለመፆምና ለመፀለይ ቆርጠው ተነሱ! ለልጆቻቸውም ፓስታ ምናምን ገዝተው ፆሙን ጀመሩ፤ ልጆቻቸውም ከቤት እንዳይወጡ ቆለፉባቸው፡፡ የልጆቹን ምግብ የሚያበስለው አባትየው ነበር (ትንሽ ትንሽ ቀምስ ነበር አሉ)፤ የሆነ ሆኖ የልጆቹ ምግብ በ25ኛው ቀን አለቀ ልጆቹም በርሃብ ደከሙ፤ እነ ዶክተር ግን ፆማቸውን ቀጥለዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ከታገቱበት ሲና ተለቀቁ!!


በዶላር ወደ ሲና፤ በዶላር ወደ ሸገራብ

tigist gebre


የሱዳን፣ የኤርትራና የግብጽ ዜግነት ባላቸው ራሻይዳዎች ታፍነው ወደ ሲና በረሃ የተወሰዱት ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ካይሮ መግባታቸው ታወቀ። ወ/ሮ ትዕግስት ቅዳሜ ረፋዱ ላይ ካይሮ የገቡት አጋቾቹ እንዲሰጣቸው ከጠየቁት 25 ሺህ ዶላር በድርድር 15 ሺህ ዶላር ተከፍሏቸው ነው።

የሰማይ ላይ ግንብ (Tower in the sky)


የሰማይ ላይ ግንብ (Tower in the sky)

Book Review: Tower in the Sky
የሰማይ ላይ ግንብ (Tower in the sky)
የመፅሀፉ ርዕስ፡ Tower in the sky (የሰማይ ላይ ግንብ)
ደራሲ፡ ህይወት ተፈራ
አሳታሚ፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ
የገፅ ብዛት፡ 437
የታተመበት ዘመን፡ እ.አ.አ 2012
የመሸጫ ዋጋ፡ 74 ብር
“የሰማይ ላይ ግንብ” ሲጀመር ደራሲዋ የተማሪ ቤትና የልጅነት ህይወቷን እንደዋዛ በመተረክ ቀስበቀስ ከሀረር ወደ አ.አ. አመጣጥዋን፣ በጊዜው የነበረውን የወጣትነት ህይወት የወቅቱን የወጣቶች የልብ ትርታ ይዘረዝራል። ይቀጥላል…

ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የ ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ ሊቀመንበር ከላይፍ መጽሄት ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ


ላይፍ መጽሄት

ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የ ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው፡፡ ፓርቲው ከተመሰረተ ጥቂት እድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚነሳ ለመሆን በቅቷል፡፡ የላይፍ መጽሄት አዘጋጅ የሆነው ዳዊት ሰለሞን ግንፍሌ አካባቢ በሚገኘው የፓርቲው ጽ/ ቤት በመገኘት ኢንጅነሩን በዋናነት ስለ አማሮች መፈናቀል አነጋግሯቸዋል፡፡Interview Eng. Yilkal Getnet
ላይፍ ፡- ለፖለቲካ ስራ ሙሉ ጊዜን መስጠት በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አስቸጋሪ አይሆንም?
ኢንጅነር ይልቃል ፡- መኖር ስላለብኝ ጥቂት ስራ እሰራለሁ፣ የሚበዛውን ጊዜዬን ግን የማሳልፈው ለፓርቲው ስራ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ለምርጫ አስቸጋሪ ሲሆኑ የምትወስደው ውሳኔ አንዱን በማጠፍ ለአንደኛው ብቻ ራስህን መስጠት ይሆናል፡፡
ላይፍ ፡- የሚመሩት ፓርቲ ሰማያዊ የፖለቲካ ፍልስፍናው በምን ላይ የተመሰረተ ነው?

Monday, May 20, 2013

የ“ቀዩ መስመር” ሰላባዎች?


የ"ማበስበሱ" ቁማርና የደኅንነቱ ሚና!!

red-tape2
መለስ ህይወታቸው እንዳለፈ ከተሰጡት አስተያየቶችና ትንቢቶች መካከል ቀዳሚው የመለስ ሞት ለህወሃት ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ መሆኑ ነበር። በዚሁ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግ ዲፕሎማት “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ይህ እንደሚከሰት ቁልጭ አድርገው ተናግረው ነበር።

“መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”


“መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”

the hole


ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ባለሥልጣናትና የታዋቂ ነጋዴዎች የፍርድ ቤት ውሎ



lideta


“ያለመከሰስ መብቴ አልተነሳም መንግሥት የሚያውቀው ሕመም አለብኝ” አቶ መላኩ ፈንታ፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር
“እኔ በተጠረጠርኩበት ወንጀል ልጠየቅ ቤተሰቦቼን ግን ለምን? ምን ዓይነት አገር እየሆንን ነው?” አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር

የበረከትና አላሙዲ ልሳን (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


ከኢየሩሳሌም አርአያ

በአላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት፣ በረከት ስምኦን ከጀርባ የሚመሩት እና በአንድ ኤርትራዊ የሚዘጋጀው ጋዜጣ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር ሲሞክር መታየቱን ተከትሎ ምስጢሩን የሚያውቁ የቅርብ ምንጮች ጉዳዩን አጋለጡ። « ሰንደቅ» የተባለውና በነፃ ፕሬስ ስም የሚያደናግረው ጋዜጣ ፍሬው አበበ በተባለ ዋና አዘጋጅነት እንዲሁም በኤርትራዊው ፋኑኤል ክንፉ ምክትል ዋና አዘጋጅነት የሚሰናዳ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሲሆን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በውድ ዋጋ ቢሮ ተከራይቶ እንደሚሰራ ያስታወቁት ምንጮቹ አያይዘውም ፍሬው አበበ ከዚህ ቀደም የብአዴን ልሳን በሆነው « ማህቶት» ጋዜጣ ላይ ይሰራ እንደነበረና ከብአዴን አመራር አባላትም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው አረጋግጠዋል።

ግንቦት 7 የፖለቲካ ድርጅት እንዳልሆነ ያውቁ ኖሯል?


አሰፋ ከዳላስ

ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 3፣ 2005 (May 11, 2013) በዳላስ ከተማ በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌ ቪዥን (ኢሳት) የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነበር:: እጅግ በጣም የተሳካ እና የደመቀ ፕሮግራም ነበር:: ታዲያ በዝግጅቱ ላይ ትኩረቴን የሳቡት ብዙ ነገሮች ቢኖሩም በዚች አጭር ፅሁፌ የማተኩረው የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ያነቧት ዘንድ ተሰራጭታ በነበረችው እና እኔም እጅ በገባችው አንዲት በራሪ ወረቀት ላይ ነው::Ginbot 7 press release in Amharic
ይቺ አንድ ገፅ በራሪ ፅሁፍ ስለ ግንቦት 7 ድርጅት የምታወራ ሲሆን ርዕሷም ግንቦት 7ን ያውቁት ኖሯል? የሚል ነው:: በበራሪ ወረቀቷ ላይ እንደተጠቀሰው “ግንቦት 7 ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች የሚለይበትን ዋና ነጥብ ተረድተዋል?” ይልና እንደ ምክንያትም “ግንቦት 7 የትምህርት: የኢ ኮኖሚ: የውጪ ጉዳይ… ወዘተ ፖሊሲ የለውም” በማለት ያትታል:: ርግጥ ነው አንድን ድርጅት የፖለቲካ ድርጅት ከሚያሰኙት ነገሮች ውስጥ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች እንደሚገኙበት አያጠራጥርም::

ስድስት:- ቃል ኪዳን፤ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ


ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

እንግዲህ ኢሳት በነገረኛነትም ሆነ በጠመንጃ-ያዥነት በኩል ከሎሌነት ጠባይ ጋር የተያያዘውን ኢትዮጵያውያን ያለንን አጉል ባህል ሁሉ እየነቀስን እየጣልን በዘመናዊና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ መሠረት ለመጣል ዋና መሣሪያ ሊሆነን ይችላል ብሎ ማመን መነሻ ይሆናል፤ ይህ እምነት ከሌለ የእምቧይ ካብ ነው፤ ይህ እምነት ራስን ማጽዳትንም ይጠይቃል።
Prof. Mesfin Woldemariamማክሸፍ እንደምንችልበት ከማመን እንጀምር፤ ስለዚህም ኢሳት ሊከሽፍ የሚችልበትን እያንዳንዱን መንገድ ማጥናትና በቅድሚያ ፈውሱን ማዘጋጀት የሚጠቅም ይመስለኛል፤ ይህንን ጉዳይ በትጋት ለመከታተል የኢሳትን አማራጭ የማይገኝለት የአገር ጥቅም በእውነትና በትክክል መገንዘብ ያሻል፤ ዘመን-አመጣሽ ነገር ብቻ አድርጎ መመልከቱ ለወረት ይዳርገዋል፤ ወረትን ማክሸፍ ቀላል ነው፤ ከከሸፈ በኋላ እንዲያንሰራራ ለማድረግ በጣም ከባድ ሥራን ይጠይቃል፤ ስለዚህ ከወዲሁ ኢሳት ጠንካራ መሠረት ላይ እንዲተከል የተቻለውን ሁሉ ማድረግ ዘለቄታ እንዲኖረው ማረጋገጫ ይሆናል።

አሸባሪው ማን ነው?


አሸባሪው ማን ነው?


Author and writer Tesfaye Zenebe from Norway
ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)
ከሳምንታት በፊት በልእለሀያሏ አሜሪካ በቦስተን ከተማ የደረሰውን በአሸባሪዎች ጥቃት ህይወታቸውን ላጡና  ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የሃገሪቱ ዜጎች በህዝብ ይሁንታ ስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ለደረሰው አደጋ ሀዘናቸውን ለመግለፅና የወንጀሉን ፈፃሚዎች በቁጥጥር  ስር ለማዋል መመሪያ ሲሰጡ ሰዓታት  እንዳልወሰደባቸው ስንመለከት ወራት አልተቆጠረም፡፡በመሰረቱ ይህንን ዘግናኝ ጥቃት የፈፀሙት ፅንፈኛ አክራሪዎች ብዙም ሳይቆዩ በሃገሪቱ የፀጥታ ሃይሎች ታድነው በአጭር ጊዜ ውስጥ መያዛቸው ለሕዝቡ ታማኝ  የሆነ መንግስት ዜጎቹን ከጥቃት ለመታደግ ምን ያህል እረፍት እንደሌለው የሚያመላክት ነው፡፡
ከላይ እንደመነሻ ያነሳሁት ሃሳብ ለዛሬው ፅሁፌ እንደ መንደርደሪያ እንዲረዳኝ እንጂ እውነተኛው የዲሞክራሲያዊ ስርዓት አራማጆች ለዜጎቻችቸው የሚሰጡት ክብር የሚሳት ሆኖ አይደለው፡፡

Saturday, May 18, 2013

ወገኖቼ እባካችሁ ለጥያቄዬ መልስ ስጡኝ (ተሾመ ደባልቄ)


ተሾመ ደባልቄ

ዲሞክራሲና ትግል
ዲሞክራሲ አገሮች የሚኖሩ የወያኔ ጉጅሌዎች የሚወዱትን መሪ መርጠው ለኢትዮጵያ ህዘብ ግን ወያኔ ይበቃዋል ማለታቸው ማሞ ቂሎ መሆናቸውን ያቁታል?
ለህዝብ ነፃነት እታገላለሁ የሚል የግለሰብም ሆነ የቡድን ልዩነት የሚመጣው ከህዘብ ይልቅ እራሴን ላስቀድም የሚል ስግብግብነት ነው ቢባል ዕውን አይሆንም?
ነጻነትና ዲሞክራሲ ሲባል ሆዱን የሚቆርጠውና የሚያስለፈልፈው ዜጋ የሌባ እንጀራ የበላ ብቻ ይሆን?
ወያኔስ በድንቢጥ ምስክሮቹ 99.6 በመቶ ህዝብ መረጠኝ ብሎ መንግስት ነኝ ሲል ደጋፊዎቹን ቆረቆሮ ራስ ደንቆሮዎች እያለ የሚፌዝባቸው ምን ያህል ቢንቃቸው ነው?
ይህ አቢዩታዊ ዲሞክራሲ የሚሉት የወያኔ ሥርዓት ፓርላማ መግባት እንጂ መውጣት አያቅም ማለት ነው? አብዮት ነፍስ ለመብላት ዲሞክራሲ ደግሞ ለማጭበርበር ቢባልስ ያስወነጅላል?

አጀንዳን እያስቀደሙ ማዘናጋት ከተጠያቂነት አያድንም!


አልፎ አልፎ የጉዞን ጎዳና መመርመር ከብዙ ስህተት ያድናል። ግምገማ -እንደሚሉት የ”ለምን አልታዘዝክም” -“ለምን የብዝበዛው አካል/አፋኝ አልሆነክም” ውጠራ ሳይሆን የሕዝቡን የእርምጃ መስመር በተቻለ ለመጠበቅ- ከላስፈላጊ—–ፍጆታም ለመላቀቅ የሚበጅ መሆኑን በማጤን ነው።

በቀደመ መጣጥፍ ስርአቱ አሁን ሞቷል የሚንቀሳቀሰው በበበድኑ ነው የሚል ታማኒ የሆነ ሓሳቦች ተጨብጦ ነበር። ስርአቱ በቁሙ ሙት ነው ግን ዘለቀ ስንል ሊያዘልቁት ያበቁትን ጥቂት ነጥቦች በጥቅሉ ተቀምጠውም ነበር።
አንድ ሀቅ ይፋ መውጣት አለበት ከተባለ መነገር ያለበት አብይ ጉዳይ-የሆነውስ ሆነ- ትላትናና ዛሬ የህዝቡን ትግል የሚመራው ማነ ነበር-ዛሬስ ማነው ብለን መጠየቅ የግድ ነው። እንደ አነጋገርም ስልት “እርሱ አጀንዳ አለው” “የአንተ አጀንዳ ምንድር ነው” “እርሱ የሚያራምደው የራሱን አጀንዳ ነው” ይባላል። በእርግጥም የዚህ ጥቆማ አጀንዳ “አጀንዳ” እንደመሆኑ ሁሉም የራሱ አጀንዳ አለው። የሚያራምደውም አጀንዳውን ነው። የራስን አጀንዳ የሁሉ ማድረግ ደግሞ በክፉም በደጉም አንድ እርምጃ አስቀድሞ ማስተዋልን ያመለክታ።

የሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ዝግጅት እያደረገ ነው


የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ባስተላለፈው መሰረት አመራሮቹ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆኑ ገለጹ።

Ethiopian blue party, semayawi party
ፓርቲው “በመንግስት ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ ለመፈለግ…” በሚል ባስተላለፈው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት ድምፃችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ያነሳናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበራትና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእነዚህ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ” ሲል አሳስቧል።

ታሪክን የኋሊት፤ የአቶ መለስ ድንጋጤ! (አቤ ቶኪቻው)


እንግዲህ ይህ ከሆነ አመቱ ሆነ አይደለ… ቅዳሜም ቅዳሜ፣ እሁድም እሁድ ነው እና ምናልባት ካልተገናኘን… እንዳንረሳው፤ ከወዲሁ ቀኑን እንደሚከተለው እንዘክረው… (በቅንፍም ኤድያ እነ እንትናዬ ደግሞ ሊበሳጩብኝ ነው… (በሌላ ቅንፍ እንግዲህ ይቻሉት እኛ ስንቱን ችለነው የለ…))

Melese Zenawi
በመጀመሪያም፤
ብስጭቴ
እኔ እኮ የምለው ሰው አይኑ እያየ የሰራውን ስራ እያወቀ ወደ አሜሪካ ለዛውም ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይሄዳል እንዴ!? እውነቱን ለመናገር እኔ አቶ መለስ ዜናዊን ብሆን ኖሮ ዲቪ እንኳ ቢደርሰኝ ሀገር ይቀየርልኝ እላለሁ እንጂ አሜሪካ አልሄድም። እነ ቻይና ባሉበት አለም እነ ሰሜን ኮሪያ በሚኖሩበት ምድር ሰው እንዴት ወደ አሜሪካ ይሄዳል? (ይቅርታ ሰው በሚል የተጠቀሱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ነው)

Friday, May 17, 2013

ግንቦት 7 – ታሪካዊ ቀን በክፍሉ ታደሰ -(ግንቦት 7 /ኢትዮጵያ፤ እኮ ለምን? እንዴት?/ ከሚለው መጽሐፍ የተቀነጨበ



ginbot-7--በግንቦት 7/1997 ምርጫ 524 የምክርቤት ወንበሮች ለምክር ቤት ቀረቡ፡፡ 23 የሚሆኑት በነሐሴ ወር በሱማሌ ክልል ለሚደረገው ምርጫ ወደጎን ተተዉ፡፡
ግንቦት 7 በተካሄደው ምርጫ ተሳትፌያለሁ፡፡ ማን ይናገር የነበረ፤ ማን ያርዳ የቀበረ እንደሚባለው ያየሁትን፣ የሰማሁትን፣ የተሳተፍኩበትን ነው የማቀርበው፡፡ እኔ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ በሦስተኛ ሰው አድርጌ ታሪኩን ላቀርበው ሞክሬ፤ ራቀብኝ፣ ባዕድ ሆነብኝ፣ የኔ መስሎ አልሰማህ አለኝ፡፡ እናም ታሪኩን በቀጥታ ለመተረክ ወሰንኩ፡፡

Thursday, May 16, 2013

ግንቦት ሰባት የትግል ቃልኪዳን የሚታደስበት ቀን ነዉ!!



Official Site for Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy

ግንቦት ሰባት የትግል ቃልኪዳን የሚታደስበት ቀን ነዉ!!

ጋዜጣዊ መግለጫ
 የኢትዮጵያ ህዝብ በታሪክና በባህል ትስስሩ፤ በረጂም ግዜ አብሮ መኖር ልምዱና እንዲሁም በነፃነትና ዲሞክራሲ ትግል ምዕራፉ ዉስጥ በጋራ ያፈራቸዉና በባለቤትነት የሚጋራቸዉ የተለያዩ እሴቶች አሉት። ቆየት ያሉትንና በኩራት የሚያስፈነድቀንን የአድዋን ድል ወይም በኃዘን ስሜታችንን ሁሌም የሚቆጠቁጡዉን የሰማዕታት ቀን ትተን የአጭር ግዜ ትዉስታችንን ስንፈትሽ ፊታችን ላይ እንደ መስታወት ድቅን እያሉ እራሳችንን ከሚያሳያዩን ቀኖች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ግንቦት 7 1997 ዓም የዋለዉ ታሪካዊ ቀን ነዉ። ይህ ቀን በኢትዮጵያ ህዝብ የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል ሂደት ዉስጥ የፀሐይንና የጨረቃን ያክል ገዝፎና ደምቆ የሚታይ ልዩ ቀን ነዉ። ግንቦት ሰባት 1997 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ ብሩህና የወደፊቱን አመላካች የሆነ ፍሬያማ ጉዞ ጀምሮ ፍሬዉን ከማየቱ በፊት የጀመረዉን ጉዞ እንዲያቋርጥ የተገደደበትና ለዘመናት አንገቱ ላይ አንደ ቀንበር ተጭኖበት የቆየዉን የአምባገነኖች ክፉ ጫና አዉልቆ ለመጣል ሲዘገጅ ዝግጅቱ በአጭር የተቀጨበት ጨለማና ተስፋ፤ ቁጭትና ጽናት አንድ ላይ የታዩበት ትንግርታዊ ቀን ነዉ።
ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. በዛሬዉና ለወደፊት በተከታታይ በሚመጣዉ ኢትዮጰያዊ ትዉልድ ልብ ውስጥ ተስፋን፤ ልበሙሉነትን፤ ጅግንነትንና መስዋዕትነትን እየጠቆመ ለዘለአለም የሚዘከር ቀን ነዉ። ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያ ህዝብ በጠመንጃ ኃይል እላዩ ላይ የተጫነበትን ዘረኛ አምባገነን ስርዐት በምርጫ ካርድ ጥሎ ለእድገት፤ ለሰላምና ለአንድነቴ ይበጁኛል ያላቸዉን መሪዎቹን መርጦ ስልጣን ወንበር ላይ ለማስቀመጥ ታሪካዊ እርምጃ የወሰደበትና አርቆ አሰተዋይነቱን ለአለም ህዝብ ያሳየበት ቀን ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ ግንቦት ሰባት አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ለህዝብ ምርጫና ፍላጎት የማይገዛና የስልጣን ዘመኔን ያሳጥርብኛል ብሎ ያሰበዉን ሁሉ ያለ ርህራሄ የሚገድል ጸረ ህዝብ ኃይል መሆኑን ያረጋገጠበት ቀን ነዉ።

ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል


ህወሃት በእሱና በራሱ ጉጅሌ አባላቶቹና ሚዲያዎቹ “በአገራችን ታሪክ ያልታየ ክስሰት በዋናነት ዜጎች በአንድነት፣ ከድህነት በማውጣት በደስታ የተሞላ ህይወትን ለማምጣት የኢኮኖሚ እድገታችን እያደገ ነው ይለናል” ይህ በሬዲዮ አዲስ አበባ፣ በሬዲዮ ኢትዮጵያ እና በሬዲዮ ፋና ብቻ ነው። ይህ ውሸት እንደተጠበቀ ሆኖ አዲሱ የለውጥ ምእራፍ ደግሞ የወያኔ ቡችሎች በየጊዜው ከህወሃት መጋረጃ በስተጀርባ ያለውን የተደበቀውን እውነት ወይም ግንቦት 7 ሲል የነበረውን የሚያረጋግጡ መረጃዎችን መስማት መጀመራችን ነው።
ህወሃታዊ መነቃቃትን ለማምጣት ደካሞችንና ለሆዳቸው ያደሩ ባለስልጣናቱን ሰብስቦ ስለ እድገት ጎዳናና ኃይል የሚያመረቁ ትሩፋቶችን በሚዲያዎቹ ያስነግራል። የዜጎችን የስነ ልቦና ውድቀት በከፍተኛ ደረጃ የሚፈልገው ህወሃት ባሪያዎቹንና አገልጋዮቹን በጥቅማጥቅም በማሸነፍ እውነትን ይደብቁለት ዘንድ ሁሌም ሙከራ ያደርጋል። አንዱም ተሳክቶለት አያውቅም እንጅ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት የሆነው ህወሃትና የእነሱ ተላላኪ ወያኔዎች ጦር ሰብቀው፣ መሣሪያ ወድረውና በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲያቸው ተጠቅመው ሀገሪቷን እና ህዝቡን ከፋፍለው በዘር ካርድ ተጫውተው የስልጣን እድሜያቸውን ማራዘም ተቀዳሚ አጀንዳቸው እንጂ መቼም ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና እድገት አስበውም አልመውትም አይውቁም፡፡ የሶማሊያው ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ሙሃመድ የተናገረውም ይህንኑ ነው ተደጋገመ እንጂ።

ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የትግል አንድነት ጥሪ


ሲራጅ ደታንጎ

አዲስ አበባ ዉስጥ በግንቦት 17 ቀን 2005 በሚደረገው ሠላማዊ ሠልፍ የሁሉንም ብሶተኛ ኢትዮጵያዊ ክፍል ጥያቄዎች አንግበን በሙሉ ልብ እንሳተፍ፣ የሕዝቡን አንድነትም ለሚጠራጠሩት ሁሉ በተግባር እናረጋግጥ። በዚህ ወቅት አዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ኅብረት 50ኛ ዓመት፣ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት ከበርካታ የአፍሪካ ሀገሮችና ከአንዳንድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም እንግዶች ስለሚኖሩ፣ የህዝቡን የፍትኅና የመብት ጥያቄዎች ለዓለም ኅብረተሰብ ጭምር ልናሰማ የምንችበት ጥሩ አጋጣሚም ነው እንላለን። አፋኙንና ግፈኛውን መንግሥትም በዓለም ህዝብ ፊት ይበልጥ ለማጋለጥ ያስችለናል።A call for demonstration in Addis Ababa, Ethiopia
ትልቁ አስፈላጊ ተግባር፣ ምላሽ የሚጠይቁት አንገብጋቢ የፍትኅ፣ የመብት (የዕምነት መከበር ጭምር)፣ የህግ የበላይነት፣ … ጥያቄዎች በግልጽና በአንድነት፣ የችግሮቹ ሰለባ በሆነው ህዝብ በራሱ በአደባባይ በሠላማዊ መንገድና በይፋም መገለጻቸው ላይ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በገዥው አምባገነናዊ ቡድን ሙሉ መብቱንና ሠላሙን ጭምር አጥቷል።

የመንግሥት ሌቦች አደራ-ቢስነትና ሕዝብ ኃላፊነት (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም)


ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

 Prof. Mesfin Woldemariam ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ስለመንግሥት ሌቦች እየተናገረ ነው፤ ሌቦቹን ግን እሱም አያውቃቸው፤ እነሱም እየሰሙት አይደለም፤ የመንግስት ሌቦች የተባሉት የሚግጡባቸው ዋናዎቹ መስኮች ታክስ፣ መሬትና የንግድ ውድድር መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጾአል፤ ከዚህም በላይ የተባሉትን የሌብነት መስኮች ከለምነት ወደበረሃነት ለመለወጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ኃላፊነት አለበት ያለ መሰለኝ፤ ሥልጣን ሳይኖር ኃላፊነት ከየት ይመጣል? እንግዲህ የፌዴራል ፖሊሱንና ሌላውን አልፎ፣ የደኅንነቱን ሰራዊት አልፎ፣ የጸረ-ሙስና ኮሚሽንን አልፎ፣ ዓቃቤ ሕግን አልፎ ሕዝብ እነዚያን ለምለም መስኮች ማድረቅ እንዴት ይችላል? ሌቦቹ ያሉት በመንግስት ጎራ ብቻ ሳይሆን በህዝብም ጎራ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቆም አድርጎአል፤ እንዲህ ከሆነ ‹‹አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ›› የሚባለው ሁኔታ ሰፍኖአል ማለት ይመስላል፤ ይህ እውነት ከሆነ ሌብነት ሥርዓት ሆኖአል ማለት ነው።