የአማራውን ሕዝብ “ልፋጫም” ብሎ የተሳደበዉና ሕወሃት ጉልበት ብቻ አመራር ላይ የተቀመጠው አለምነህ መኮንን ባረፈበት ሆቴል ድብደባ እንደተፈጸመበት መረጃዎች ይጠቁማሉ። አለመነህ በሕወሃት ታጣቂዎች ታጅቦ ሾልኮ ከአካባቢው ያመለጠ ሲሆን፣ ብዙዎች ሰዉዬው አይኑን በጨው አጥቦ በዚህ ወቅት ሕዝብ ፊት ለመቅረብ መድፈሩ አስገርሟቸዋል።
በጎጃም እነብሴ ሳር ምድር፣ቋሪት እና ሌሎች ደጋማ ቦታወች ያሉ አርሶ አደሮች መንግስት ፈርሷል የሚል ወሬ በመስማታቸው የቀበሌ ሊቀመንበር እና ፀሃፊወችን ቤታቸውን በድንጋይ እና በጥይት እንደደበደቡ እየተነገረ ነው። እስካሁን አራት የገጠር ሚሊሻወች የተገደሉ ሲሆን አቶ ቢያድጌ አለሙ የሚባል ሊቀመንበር መገደሉ ታውቋል።
በመላው ጎጃም ይህን የመንግስት መፉረስ ወሬ በመነዛቱ የየቀበሌ ሹማምንቶች ንብረታቸውን ሌላ ዘመድ ቤት እየደበቁ መሆኑ ታውቋል።
ጎንደር እንደሰሞኑ ሁሉ አሁንም ውጥረት ይታያል!! (ብአዴን በውስጥም እየተለበለበ ነው፡፡ ህዝቡን ለማረጋጋት የሚጥሩት የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከራሳቸው አባሎች ጀምሮ ክፉኛ ተተችተው እቅዳቸውን ሳያሳኩ በውርደት ተከናንቦ መመለሱ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
በጎንደር ዙሪያ የክልሉ ከፍተኛ አመራር አቶ ደሳለኝ አስራደ ብ/አ/ክ/መ/የድር/ጉ/ሕ/ግንኙነት ሃላፊ በስፍራው ተገኝተው በጎንደር የአመራር ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን ከተሰብሳቢው መሀል የጎንደር ሚሊሻ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ግዛቸው የተባሉት የሰጡት አስገራሚና ድፍረት የተሞላው ንግግር በስብሰባው ተሳታፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ደስታና ሙገሳ እንደተሰጣቸው ተሰምቶዋል፡፡
አቶ ግዛቸው እንደተናገሩት የአማራ ሕዝብ መብቱ የት ድረስ ነው? ሕዝብን አሳንሶ በኢህአዴግ ስም ተሸፍኖ ለአናሳ ቡድን መገዛት አሁን አይቻልም፡፡ ሕዝባችን በሰላማዊ መንገድ ለጠየቀው ፍትሃዊ የማንነት ጥያቄ መንግስት ማስተዳደር ካልቻለ ለምን ብዬ አገልጋይ እሆናለሁ?? እኔም ጀግና የተፈጠረበት መንደር አርማጭሆ ገብቼ ለነጻነቴ እዋደቃለሁ በማለት ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ የፈጠረው ቁጭት በአዲስ መልክ የትግል መነሳሳት ከሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል እስከ ምስራቅ ኦሮሚያ ዙሪያውን ተቀናጅቶ እየመጣ ባለው ሕዝባዊ ቁጣ የህወሓት መንግስት በቅርቡ ታሪክ ሆኖ እንደሚቀር ብዙዎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው፡፡
በተለይ የአማራ ህዝብ የነጻነት ተጋድሎ ተኩሰው ሲገሉኝ እገላለሁ በሚል በትጥቅ ጭምር ቆርጦ መነሳቱ (ብአዴን) እየተናደ መሆኑ ይነገራል፡፡ ምናልባት ሰሞኑን በብዙ የአማራ ክልል ሕዝባዊ ንቅናቄ መደረጉ የማይቀር መሆኑ ሞቅታው እየጨመረ ስርዓቱ በቅርብ ጊዜ በሕዝባዊ ሃይል ስር እንደሚወድቅ ግምታቸውን የሚሰጡ ወገኖች በርካቶች ናቸው፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ የውሸት ግንባር በውስጥ አርበኞች ሊፈርስ እንደሚችል ከቅርብ አመራሮች ሳይቀር በአደባባይ እየተሰማ ይገኛል፡፡ (ጉድ በል አሁን ነው እሮጦ መፈርጠጥ ..
ድል ለጭቁን ህዝብ!!
ድል ለጭቁን ህዝብ!!
No comments:
Post a Comment