ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በ2016 የክረምት ወቅት መጀመሩ ነውን?
አንድ ህዝብ ታምቆ ፣ ታምቆ ማለት ተጨቁኖ በዘመንታ አይቆይም ። ዩኒቨርሳል universal ማለት ነው ። አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ መጠን በዓለም ታሪክ አንዳስቀመጡት አንደፈለጉት የሚቀመጥ አይደለም። ሲመረው ይፈነዳል። ይሄ
ዓለም አቀፋዊ እውነታ /universal truth ነው። ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም። በታሪክም /historically። አሁንም። ለወደፊትም ። (
አዛውንቱ የእንጨት ሽበት ባለቤቱ አቦይ ስብሀት ነጋ፣ የዘ-ህወሀት ጭንቅላት፣ ንጉስ፣ የክርስትና አባት፣ ተጽእኖ ፈጣሪ እና የአለቆች ሁሉ አለቃ (ካቦ) እ.ኤ.አ በ2015 ከተናገረው የተወሰደ።) (ለማዳመጥ
እዚህ ይጫኑ ።)
በዘ-ህወሀት ላይ የፍርዱ ቀን ደረሰ ማለት ነውን?
እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 “የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በበጋው ወቅት መጀመሩ ነውን? በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ በመምጣት ላይ ስላለው የጸደይ አብዮት ትችት አቅርቤ ነበር፡፡“