Translate

Tuesday, May 31, 2016

ብሔራዊ ፈተናው ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 ይሰጣል ተባለ፤ የደመ ነፍስ ዕቅድ ወይስ ዳግም ‘’ምን ታመጣላችሁ?’’

shhh
shhhብሔራዊ ፈተናው ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 ይሰጣል ተባለ፤ የደመ ነፍስ ዕቅድ ወይስ ዳግም ‘’ምን ታመጣላችሁ?’’
ትላንት ለተ0001111ቋረጠው ፈተና፤ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ በነበረው ተቃውሞ ትምህርታቸው ተዘግቶ ለከረሙ ልጆች በቂ ጊዜ ባለመሰጠቱ በሽማግሌ ሳይቀር አስለምነን እምቢ ሲሉን ይሄንን እርምጃ ወስደናል ሲሉ ለፈተናው ሾልኮ መውጣት የኦሮሚያ ተቃውሞ አስተባባሪዎች ሃላፊነቱን መውሰዳቸውን ሰምተናል።
0001111መንግስትም ‘’ፕላን ቢ’’ አለኝ በጥቂት ቀናት ውስጥ ድጋሚ ፈትናለሁ… ብሎ ሲቀውጠው ተመልክተናል። ዛሬ ራዲዮ ፋና ሰበር ዜና ብሎ ባወጣው ዜና ታድያ ፈተናው ከአንድ ወር በኋላ ከሰኔ ሃያ ሰባት እስከ ሰኔ ሰላሳ እንደሚሰጥ ዘግቧል።
እንግዲህ አንድ እቅድ ሲነደፍ ካላንደር ተዘርግቶ በዕለቱ ምን ምን አለ… የሚለውን ከግንዛቤ ማስገባት የመጀመሪያው ስራ ነው። አሁን እንደምናየው ግን እነ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ይቺን እቅድ ሲነድፉ እግራቸውን ዘርግተው እንደሆነ እንጂ ካላንደር መዘርጋታቸውን ጥርጣሬ የገባው ጦማሪ አጥናፍ ፈተናው ይሰጣል፤ የተባለበት እለት የረመዳን ቀን ሊሆን እንደሚችል ጠቅሶ ስጋቱን በሶሻል ሚዲያ አጋርቶናል።

የጃዋር ስኬት እና የፖለቲካ ፈላሻዎች ( ሄኖክ የሺጥላ )

የብሄራዊ ፈተና ምስጢርን ለህዝቡ ቀድሞ በማሳወቅ ( « በማሰረቅ» የሚለው ስለማይጥም ነው ) ፥ ታቅዶ የነበረው የብሄራዊ ፈተና ክንውን ቢያንስ በታቀደለት እለት እንዳይከናወን ስለማድረጉ ብዙ እየተወራለት ነው ። ኦቦ ጃዋር
እርግጥ ጃዋር እጁ ረዝሞ ፥ ከሚኒሶታ አዲስ አበባ ተዘርግቶ ፥ ወያኔን ብስጭት እና ቁጭት ውስጥ የሚጥሉ ጉልህ ነገሮችን እያደረገ ሰለመሆኑ ተደረጉ የተባሉት ነገሮች ገላጭ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል ( መመርመር እንደሚኖርባቸው ባምንም)!! ። ባንፃሩ ግን ጃዋር እና ህቡዕ ድርጅቱ ፥ ፈጠሙ ከተባለው ጉዳይ ጀርባ ምናልባችም በበለጠ አንድ በረጋ እና በሰከነ ልቦና ልናጤን የሚገባው ጉዳይም አለ ። ይኽም ምንድን ነው ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ በትር ላለፉት 25 አመታት ሲሰቃይ የመኖሩን ያህል ወያኔን በዚህ ኣንድ እና ሁለት አመት ውስጥ ጃዋር እንዴት ሊፈትነው ቻለ? ፈተናውን ሰርቀው ለጃዋር የላኩት ግለሰቦችስ ፥ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ፥ ሃገርን ከወያኔ ክርን ለማውጣት በሚደረገው ትግል እና ትንቅንቅ ፥ ካሉት ተቃዋሚዎች መርጠው እና አወዳድረው ፥ ለጃዋር ሲገብሩ ለምን እና እንዴት ብሎ መጠየቁም አግባብነት አለው ባይ ነኝ ።

Monday, May 30, 2016

ዜና መረጃ… በረከት ስሞን አርበኞች ግንቦት 7 ያለዉ ዉስጣችን ነዉ ይላሉ!!

ወሎን ሰፈር ተሻግሮ ሩዋንዳ ሙልሙል ዳቦ አካባቢ ወደ ቦሌ በሚወስደዉ መንገድ በስተቀኝ ወደ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ይገኛል ከዩኒቨርሲቲዉ በተጓዳኙ በስተግራ ካለዉ ነጭ ህንጻ ላይ በደረጃ ቀስ እያልን ወደ 5ተና ፎቅ አመራን ከቢሮዉ በተያያዘ ቱሪዝም ኤጀንሲ ባጎራባች ሲኖር ከስሩ ደግሞ ሱፐር ማርኬት አለ በዋናነት ወደዛ የሄድንበት ምክንያት የበረከት ስሟን ቢሮ እዚያ እንደሚገኝ በደረሰን መረጃ መሰረት ነዉ።
ቢሮዉ እነደደረስን ጸሐፊዉን ለማግኘት ትንሽ ብንጠብቅም አግኝተን አናገርናት የበረከት ስሞን ቢሮ መሆኑን ካረጋገጥን በኍላ ትንሽ ጠብቁ ተብለን ተቀመጥን ከጥቂት ቆይታ ወዲህ በረከት በሁለት ሰዎች መካከል ሆኖ ከተፍ ሲል ተመለከትነዉ የመሰብሰቢያ ቢሮ በመሰለዉ ቢሮ ዉስጥ በአይኑ ሁላችንንም ገርበብ አድርጎን በአንገቱ ሰላምታ ሰጥቶን ወደ ዉስጥ ዘለቀ!
እኛም እዚያዉ መጠበቅ ጀመርን ከጥቂት ቆይታዎች በኍላ እቃ እንደረሳንና በሌላ ቀን እንደምንመለስ ለጸሐፊዋ ነግረን ተመልሰን ወጣን።
መኪናችን ዉስጥ ገብተን ወደተቀመጥንበት ሆቴል ገሰገስን ክፍላችን ዉስጥ እንደገባን መቀረጸ ድምጻችንን በቢሮዉ ዉስት ንደምን ለጥፈነዉ እንደወጣን እየተወያየን ተዝናናን!
ክትትላችንንም በመጠኑ በተለያዩ አካሎቻችን በማከናወን መግቢያ መዉጫቸዉን አጠናን ከ3 ቀናት በኍላ የተቀረጸዉን ድምጽ በእጃችን አስገባን መቅረጻችንም በጥቂቱ ይህን ይዟል።

“የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄን በመጀመሪያ ለክልል ማቅረብ እንደ ግዴታ ሊቀመጥ ነው”

21241-paarlaa1
ሪፖርተር ላይ የወጣው ጽሁፍ “የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ከመቅረቡ በፊት፣ የክልል መፍትሔን አሟጦ የመጨረስ ሕጋዊ ግዴታ ሊቀመጥ ነው” ይላል፡፡
ረቂቅ ድንጋጌው አክሎም ይህ የሚሆነው ‹‹የራስን ዕድል በራስ የመወሰን የመብት ጥያቄ ወደ ምክር ቤቱ የሚቀርበው በክልሉ በሚገኙት የተለያዩ የመስተዳደር እርከኖች ቀርቦ አጥጋቢ መፍትሔ ያልተሰጠው መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፤›› ይላል፡፡ በክልሎች ፖለቲካዊ ሁናቴዎች መብቴ አልተሟላም የሚል የራስን እድል በራስ የመወሰን ጥያቄ አቅራቢ “ክልላዊ አስተዳደሩን ጠብቆ ለፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሊቀርብ” ይችላል፡፡ ከዚህ በፊት በጥያቄ አቅራቢው ፍላጎት ወይ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አልያም ወደክልል ይቀርቡ እንደነበርም ሪፖርተር አትቷል፡፡ አዲስ ረቂቅ ድንጋጌ የተወጠነበትም ምክንያት “የተጭበረበረ ወይም እውነተኛ ያልሆነ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄ በአሁኑ ወቅት እየተበራከተ” በመምጣቱ ነው ይላል፡፡

Friday, May 27, 2016

የሰራተኛው ኑሮ በደርግና በወያኔ ዘመን (በገለታው ዘለቀ)

downloadከ25 ዓመታት በፊት አንድ የኮሌጅ ዲፕሎማ የነበረው ኣስተማሪ ሲቀጠር የመነሻ ደመወዙ 347 ብር ነበር። ይህን ገቢ በወቅቱ ከነበረው የዶላር ምንዛሬ ኣንጻር ስናየው 173.5 ዶላር ይመዝን ነበር። ይህ ኣስተማሪ ገና ሲቀጠር የቀን ገቢው 5.8 ዶላር ነበር ማለት ነው። ከፍ ያለ ነበር። ከ25 ኣመት “እድገት” በሁዋላ በህወሃት ኢህዓዴግ ዘመን ኣንድ የኮሌጅ ኣስተማሪ ዲፕሎማውን ይዞ ሲቀጠር 1663 ብር ቢከፈለው ኣሁን ባለው ምንዛሬ ሲታይ 77.3 ዶላር ያገኛል። ይህ ማለት የቀን ገቢው በዶላር 2.57 ሳንቲም ነው ማለት ነው። ይህ ማለት የደርግ ጊዜው ኣስተማሪ ደመወዝ ከህወሃት ኢህዓዴግ ጊዜ ኣስተማሪው ደመወዝ ከሁለት እጥፍ በላይ ይበልጣል ማለት ነው። በዓለም ኣቀፍ ደረጃ የድህነት ወለል የሚባለው ሁለት ዶላር ኣካባቢ ሲሆን ይህ በህወሃት ኢሃዴግ ዘመን የኮሌጅ ዲፕሎማ የያዘው ኣስተማሪ በዚያው በድህነት ወለል ኣካባቢ ነው ማለት ነው። ነገር ግን በደርጉ ጊዜ ከሃያ ዓምስት ዓመት በፊት የነበረው ዲፕሎማ ኣስተማሪ በቀን የሚያገኘው ገቢ ወደ 6 ዶላር የሚጠጋ ሲሆን እጅግ በተሻለ ህይወት ውስጥ የነበረ በዓለም ኣቀፍ የገቢ መለኪያም የተሻለ ገቢ የነበረው ነበረ። በኣሁኑ ሰዓት ኣንድ የሁለተኛ ደረጃ ኣስተማሪ ሲቀጠር 2197 ብር የሚያገኝ ሲሆን ይህ ማለት 102 ዶላር ማለት ነው። ይህ መምህር በቀን 3.40 ሳንቲም የሚያገኝ ሲሆን በደርግ ጊዜ ዲፕሎማው ወደ 6 ዶላር የሚጠጋ በቀን ያገኝ ስለነበር በደርጉ ጊዜ የነበረ ያ ጀማሪ የዲፕሎማ መምህር የዛሬውን የዲግሪውን መምህር ክፍያ በጅጉ ይበልጠዋል። በዚህ ቀላል መንገድም ሆነ በፈለገው የኢኮኖሚክ ሞዴል ብናሰላው በህወሃት ኢህኣዴግ ጊዜ ያለው ሲቪል ሰራተኛ ገቢ ከደርጉ ጊዜ መምህር በጅጉ ወርዶ እናያለን። በደርግ ጊዜ ኣንድ የሁለተኛ ደረጃ ኣስተማሪ ሲቀጠር የቀን ገቢው ወደ ዘጠኝ ዶላር የሚጠጋ ሲሆን በኣሁኑ ጊዜ የሚቀጠረው መምህር 3.40 ሳንቲም ብቻ በመሆኑ ልዮነቱን ማየት ይቻላል። 

እንደኔ ቆሻሻ ፊት ከማነስ ይሰውራችኹ! (ከአቤል ዋበላ)

ከአቤል ዋበላ
“እያዩ ፈንገስ” ወይም “ፌስታሌን” የተሰኘውን ትያትር ብዙዎቻችኹ አይታችኹታል ብዬ ገምታለው አልያም ስለ ማኀበራዊ እና ፖለቲካ ቀመስ ትችቶቹ በወሬ በወሬ ሰምታችኃል፡፡ እኔ ዝናውን የሰማኹት እስር ቤት ሳለኹኝ ነበር፡፡ ወያኔ እግዜር የስራዋን ይስጣትና እኔ ከወህኒ እስክወጣ ድረስ መድረክ ላይ አቆየችው፡፡ በትያትር ቤት ታድሜ እንደተዋራለት ሆኖ አገኘኹት፡፡ ይህን ጥበብ ለመድረክ እንዲበቃ ያደረጉትን እና በመድረክ እንዳይታይ ለማስተጓጎል ያልሞከሩትን አመስግኛለው፡፡Ethiopian blogger Abel Wabela
የትያትሩ አንድ ገቢር ግን እስካኹን ድረስ ውስጤ ቀርቷል፡፡ የተነሳኹበትን ሐሳብ ለማስረዳት ይረዳኛልና ይህንን ክፍል እንድተርከው ይፈቀድልኝ፡፡ እያዩ ፈንገስ ውድ ንብረቶቼ የሚላቸው ዕቃዎቹን የያዘ አንድ ፌስታል እንደጠፋበት ይናገር እና ለፍለጋ ይሰማራል፡፡ በሚኖርበት ሰፈር አቅራቢያ በሚገኙ ገንዳዎች፣ ቆሻሻ መጣያ ስፍራዎች ፈልጎ ያጣዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ቆሻሻ መጣያ ስፍራ ሄዶ ቢፈልግም እንዳላገኘው ለተመልካቹ በሞኖሎግ ያስረዳል፡፡ በመጨረሻም የአዲስ አባባ ቆሻሻ በሙሉ “ቆሼ” እንደሚጣል እንደሰማ ተናግሮ ለፍለጋ ወደ መድረክ በስተጀርባ (ወደ ቆሼ) ይሄዳል፡፡ ከዚያ ሲመለስ የተናገረው ነገር ነው የኔን ቀልብ የማረከው፡፡ እያዩ አንዲት ፌስታሉን ፍለጋ ቆሼ ቢሄድ እራሱን ተራራ ከሚያክለው ቆሻሻ ጋር አወዳድሮ ወደተመልካቹ ተንበርክኮ “ዛሬ በቆሻሻ ፊት አነስኩላችኹ፤ እንደ እኔ በቆሻሻ ፊት ከማነስ ይሰወራችኹ” ሲል ሲቃ በተመላበት ድምጽ ተናገረ፡፡

Wednesday, May 25, 2016

በጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ላይ የቀረበው የሽብር ክስ ዝርዝር

Getachew Shiferawየፌደራል አቃቤ ህግ ግንቦት 10/2008 ዓ.ም በተጻፈ የክስ ማመልከቻ የሽብር ክስ የመሰረተበት የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ላይ የቀረበው ክስ የጸረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 7(1) ላይ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት መተላለፍ የሚል ነው፡፡
ተከሳሹ ከ24/05/2006 ዓ.ም እስከ 13/04/2008 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ግንቦት ሰባት ከተባለ የሽብር ድርጅት አመራሮች ጋር በማህበራዊ ድረ ገጽ በተለይም ፌስቡክ እና ስልክ ግንኙነት በመፍጠር ለሽብር ቡድኑ ተልዕኮ የተለያዩ መረጃዎች በማስተላለፍና በሽብር ድርጅት ውስጥ መሳተፍ ወንጀል ፈጽሟል ሲል አቃቤ ህግ በክሱ ላይ ጠቅሷል፡፡
በአቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመለከተው ተከሳሽ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው በህግ ተመዝግቦ በሀገር ውስጥ ህጋዊና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርገው ሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጋር ያደረገው የመልዕክት ልውውጥ ክስ ሆኖ ቀርቦበታል፡፡

Tuesday, May 24, 2016

ሰበር ዜና.. የብሔራዊ መረጃዉ ሐላፊ ጌታቸዉ አሰፋ ስብሰባ አቋርጦ መውጣቱ ተነገረ.

በትናንትናዉ እለት የወያኔ ተላላኪ ከሆኑት እና ከብሔራዊ መረጃ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ካላቸዉ ግለሰቦች መካከል አምባሳደር ቀጸላ ከብሀራዊ መረጃዉ ሐላፊ ከጌታቸዉ አሰፋ ጋር አርበኞች ግንቦት 7 በአርባ ምንጭ ላይ የወሰደዉን እርምጃ ተንተርሶ ዉይይት በሚያደርጉበት ወቅት በተመሳሳዩ በደቡብ ኢትዮጵያ ኮንሶ አካባቢ በትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ተፈስሞ ከ 55 በላይ የሚጠጉ የፖለቲካ እስረኞች ማምለጣቸዉ 19 የወያኔ ታጣቂዎች መገደላቸዉና ቁስለኛ መሆናቸዉን የሚያበስር ዜና በስብሰባዉ ላይ የደረሰዉ ጌታቸዉ አሰፋ በአፋጣኝ ስብሰባዉን አቋርጦ መዉጣቱን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
አርበኞች ግንቦት 7 በፓርላማ ዉስጥ ሳይቀር መነጋገሪያ እርእስ መሆኑን የገለጹት ምንጮቻችን አክለዉ የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የፈጠረዉ ፖለቲካዊና ህዝባዊ ጫና እንዳለ ሆኖ በጎንደር አርማጭሆ ሁመራ እና በትግራይ ጎንደር አዋሳኝ በኡማህጅር አካባቢ ድንገተኛና አደገኛ ጥቃቶች መሰንዘራቸዉን እንዲሁም በ24 እና በ25ኛ ክፍለጦር ተዉጣጪ የጸረ ሽብር ሐይል ላይ በተደረገ ሽምቅ ዉጊያ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን መረጃዎች ጠቁመዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
(ጉድሽ ወያኔ)

የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ታደሰ ብሩ ከአሜሪካን ሴነተሮችና ባለስልጣናት ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ።

ዶ/ር ታደሰ ብሩ ለአጭር ጊዜ ጉብኝት አሜሪካን ሀገር የሚገኙ ሲሆን፤ በቆይታቸው ወቅት በኢትዮጵያ የሰባዊ መብት፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ዙሪያዎች ከአሜሪካን ኮንግረስማን ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል። በተለይም ከከሎራዶው ኮንግረስማን ማይክ ኮፍማን ጋር በወቅታዊ እና ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ አመርቂ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጾል።
ኮንግረስማን ኮፍማን ዶ/ር ታደሰን ስለ ኤርትራ ቆይታቸው ምን እንደሚመስል ጠይቀዋቸው፡- ዶ/ር ታደሰም ሲመልሱ፡- በህወሃት መንግስት የሚደረገው ህዝብን የማጣላት፣ በኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝበ መካከል በጠላትነት እንዲተያዩ የሚያደርገው ዘመቻ የተሳሳተ መሆኑን ገልጸው አርበኞች ግንቦት 7 ዘላቂ ወዳጅነትን እየጠናከረ እንደሚገኝ እና የሁለቱ ህዝብ ጠላት TPLF እንጂ ሌላ መሰረታዊ ችግርች እንደሌሉ እና ለኤርትራ ህዝብ ያላቸውን አድንቆት በመግለጽ አብሮ መስራት እንደሚቻል ያላቸውን እምነት ገልጸውላቸዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ የምትከተለውን የውጪ ፖሊሲዋን እንደገና እንድትመረምረውም አሳስበዋል። አያይዘውም ኮንግረስማን ማይክ ኮፍማንና ሌሎች ሴነተሮች በቅርቡ በሜሪላንዱ ሴነተር ካርደን ቤንጃሚን ተረቆ የቀረበውን Resolution 432 በርካታ ሴነተሮች የፈረሙበትን የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብትና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ድጋፋቸውን ይሰጡ ዘንድ ኮንገርሰማኑን ጠይቀዋል።
በመጨረሻም ኮንግረስማን ማይክ ድርጅቱ በሁለቱ ሀገራት ህዝብ መካከል እየፈጠረ ያለውን የሰላም ድልድይ እና የማቀረረብ ሂደት አድንቀው፤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮችም እንደሚከታተሉ ገልጸውላቸዋል።
Abbay media
 

Monday, May 23, 2016

መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብሎ ሞተ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

መስፍን ወልደ ማርያም
Mesfin Woldemariamመንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፣ ይቅናችሁ ማለት ነው፤ ለልማት ለሚሰማሩ ሰዎች ምርቃት ይሆናል፤ ለጥፋት ለሚሰማሩ ሰዎች እርግማን ነው፤ እርግማን ብቻም አይደለም፤ የጥፋት ምኞትም ነው፤ ሰዎች ለጦርነት ሲዘጋጁ፣ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን ለመግደል ሲሰናዱ፣ ሰዎች እርስበርሳቸው ለመገዳደል ጦራቸውን ሲስሉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ማለት ከጀግና አንደበት የሚወጣ አይደለም፤ ብዙ ሰዎች ለእንጀራ ብለው ሕይወታቸውን ወደአጥርነት ለውጠው ሕይወቱን የሚጠብቁለት ሰው ጦር ቢወረወር አይደርስብኝም ብሎ ሌሎችን ለሞት ቢዳርግ አይደንቅም ይሆናል፤ አጥሩን ጥሶ ወደሱ የሚገሰግስ ሞት ሲያይ ቢፈረጥጥም አያስደንቅም፤ ሆኖም የሞት መንገድ ከጎን ብቻ ሳይሆን ከላይም ሊሆን እንደሚችል አለማወቁ ቀላል አለማወቅ አይባልም፡፡
ባህላችን ገዳይን የምናከብር፣ ለገዳይ የምንዘፍን ሕዝብ ቢያደርገንም፣ በድንቁርና ዘመን የነበረውን ይዘን ዛሬ ትንፋሽ የማትችለዋ ቢምቢ ሰውን መግደል እንደምትችል እያወቅን ለገዳይ ብንዘፍን ለሰውነታችን ውርደት ይሆናል፤ ይህንን ብለን ጉዳዩን እንዳንዘጋው በመግደል ልቡ የደነደነ፣ በድን ያልሆነለትን ሁሉ መግደል ልማዱ የሆነ፣ ከመግደል በቀር እምነቱን የሚገልጽበት መንገድ የሌለው፣ ከመግደል ሌላ እንጀራ የሚበላበት ሙያ የሌለው … እንዲህ ያሉ ሰዎች ሁሉ ተሰባስበው መገዳደልን የኑሮአቸው ዓላማና ዘዴ ሲያደርጉ በዝምታ መቀበል፣ ማለት አባቱ ሲገደል ልጁ ዝም ሲል፣ ባልዋ ሲገደል ሚስት ዝም ስትል፣ … ማንም ሰው አለፍርድ ሲጠቃ እያዩ ዝም ማለት ገዳዮችን ያራባል እንጂ ግድያን አያቆምም፤ እንዲህ ያለው በመንፈስ የሞቱ የበድኖች ዓለም ነው፤ በአውሬዎች ዓለም ጉልበት ያለው ደካማውን እየበላ ይኖራል፤ የተፈጥሮ ሕግ ነው፤ የሰው ልጅ በዚህ በአውሬዎች የተፈጥሮ ሕግ አይመራም፡፡

Wednesday, May 18, 2016

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለከተማ ህገወጥ ቤት ሰርታችኋል በሚል የመንግስት ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ 7 ሰዎች ተገደሉ

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለከተማ ህገወጥ ቤት ሰርታችኋል በሚል የመንግስት ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ በትንሹ 7 ሰዎች ተገደሉ ብዙ የቆሰሉ አሉ ። ፎቶዎች በውስጥ መስመር እየደረሱን ነው ይመልከቱ
ethiopiandj23
Ethiopia: Police killed residents in Addis Ababa and commit suicide Breaking NewsEthiopia: Police killed residents in Addis Ababa and commit suicide

ወያኔ ለሕዝብ የሚያከፋፍላቸው አደንዛዥ ዕፆች

ፍርዱ ዘገዬ
እያንዳንዱ መንግሥት በተለይ ደግሞ ዴሞክራሲን የሚጠየፍ አምባገነን መንግሥት የሚገዛውን ሕዝብ የሚያደነዝዝበት የተለያዩ ሥልቶችን ይነድፋል፤ እነዚህንም ሥልቶች እያፈራረቀና እንዳስፈላጊነቱም በጅምላ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በብልግናና በኢሞራላዊ ምግባራት የተሞሉ የሙዚቃና የፊልም ኢንዱስተሪዎችን ማስፋፋትና በአደንዛዥ ዕፅ በተለይ ወጣቱን ትውልድ መበከል ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ እግር ኳስንና የውሸቱን የነፃ ትግል ትርዒት (wrestling) የመሳሰሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችንም በዚሁ የሕዝብን የትኩረት አቅጣጫ ማስለወጫ መንግሥታዊ “ጥበቦች” ውስጥ ማካተት ይቻላል፡፡ የዛሬውን አያድርገውና በቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት የነቮድካን ዋጋ እጅግ በማርከስና ማንኛውንም የውጭ ሚዲያ ዝግ በማድረግ ሕዝቡን አደንዝዘው ይገዙ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ ወያኔ ግን የመጠጦችንም ዋጋ ከሰማይ አዝልቆ እየሰቀለ መደበሪያና መቆዘሚያም እያሳጣን ነው – የ330ሚ.ሊ ቢራ በዚያን ክፉ ዘመን ሊያውም ተወደደ ተብሎ በ40ሣ. እንዳልተጎነጨናት ዛሬ በዝቅተኛ ሆቴሎች ባማካይ ከ16 ብር በታች አልገኝ ብላለች፤ እሷም ባቅሟ ተንጠባረረችብን፡፡ ያገር ተወላጇ ካታማይሲን(ቁንድፍት) ራሷ ከንፈርን ለማታረጥብ ቀልበ-ቢስ መለኪያ 3 ብር እንከፍላለን – በቅርቡ ከዚያ ከዓመታት ሁሉ ተለይቶ ባይፈጠር የሚሻለው 97ዓ.ም የምርጫ ወቅት በፊት በስሙኒ ነበር የምንቸልሳት፡፡ ባይገርማችሁ የቼልሲ ደጋፊ ነኝ – የማታ ቸልሲ እንጂ ለቅሪላ ደንታም የለኝ ታዲያ፡፡
በቀጥታ ወደ ሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ እንግባና የሀሽሽ ዓይነቶችን እንመልከት፡፡ ወያኔዎች በተንኮል ሥራ እጅግ የተጠበቡና የተራቀቁ አማካሪዎች እንዳሏቸው (ከሚሠሩት ወንጀልና ጥፋት አንጻር) ከዕድሜያቸው መንዘላዘል ብቻ ሣይሆን ዘወትር ከሚያከናውኗቸው ነገር ግን ከነርሱ በፍጹም ሊጠበቁ ከማይችሉ ዕኩይ ተግባሮቻቸው በሚገባ መረዳት ይቻላል፡፡ ጎሣን ከጎሣና ሃይማኖትን ከሃይማኖት ማጋጨቱን የተበላ ዕቁብ ይዘን ቤተሰብን እስከማፋጀት የሚደርሰውን የሸር ሥራቸውን ስናጤን  በማይምነትና ምናልባትም በየዋህነት የምናውቃቸው  እነዚህ ወንድሞቻችን ይህ ሁሉ ከተዓምር ያላነሰ ድርጊታቸው ካላንዳች ረዳት እንደማይሆን እንገነዘባለን፡፡ ለኛ ከማይተኛ ትልቅ ኃይል ጋር እንደሚሠሩ ለማወቅ ነቢይነትን አይጠይቅም፡፡ የዋህ ታዛቢ ግን ወያኔዎች ብቻቸውን የሚገዙን እየመሰለው በኛ በብዙዎች “ፍርሀትና ትግስት” መደነቁ አይቀርም፡፡

መምህር ግርማ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 2 ሚሊዮን ብር ለገሱ!

🏻ባለፈው ወራት በቅድስት አገራችን በአንድ አንድ ክፍለ ሃገሮች በድርቅ እንደተጎዱና በርከት ያሉ ሰዎች ና እንስሳትን ለሞት መዳረጋቸውን የሚታወስ ነገር ነው።

Wednesday, May 11, 2016

ኢትዮጵያ በፓናማ ዶሴዎች!

panama papersዋዜማ ራዲዮ- “የፓናማ ዶሴዎች”  (The Panama papers) በመባል የሚታወቁትን ምስጢራዊ ሰነዶች ለህዝብ ይፋ ያደረገው አለማቀፉ የምርመራ ጋዜጠኞች  ቡድን (International Consurtium of Investgative Journalists ) በዚህ ሳምንት ያሰባሰባቸውን ተጨማሪ መረጃዎች ይፋ አድርጓል። መረጃው ሞሳክ ፎንሲካ (Mossack Fonseca) በተባለ ተቋም አማካይነት ድርጅቶቻቸው ከአገራቸው ውጭ በተለይም በፓናማና በሌሎችም ልል የታክስ ሕግ ባለባቸው አገሮችን ያስመዘገቡ ግለሰቦችን ማንነት ይፋ ለማድረግ የሞከረ ነው።
ድርጅትን በተለያዩ አገሮች ማስመዝገብ (ኦፍሾር ምዝገባ) በራሱ ወንጀል ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ ኩባንያዎችና ባለቤቶቻቸው ግን ይህን የሚያደርጉት ግብር ለማጭበርበር፥ በሙስናና በሌሎችም ወንጀሎች የተገኘ ሀብትን ለመሰወር ወይ በድብቅ ወደ ሕጋዊነት ለማሸጋገር ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ይናገራሉ። “የፓናማ ዶሴዎች”ን ይፋ መሆን ተከትሎ አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች ሕጎቻቸውን ወደማጥበቅና በዶሴዎቹ የተጠቀሱትን ግለሰቦች ወደመመርመር ሲሄዱ፥ ስማቸው በዶሴዎቹ በመገኘቱ ስልጣን እስከመልቀቅ በሚያደርስ ውዝግብ ውስጥ የተዘፈቁ ግለሰቦች፥ ለውስጣዊ ውዝግብ የተጋለጡ ድርጅቶች ብዙ ናቸው።

ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደና የተበላሸ ሂሳብ ያለው ንግድ ባንክ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ማውጣቱ ታወቀ

Image result for commercial bank of ethiopia
ለኢሳት የደረሰው የባንኩ የውስጥ ኦዲት ሪፖርት እንደሚያሳየው በበጀት አመት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2013 እና 2014 ባንኩ ያላወራረደው 11 በሊዮን ብር እንዲሁም የተበላሸ ገንዘቡ 1 ቢሊዮን ብር ቢደርስም፣ የባንኩ ባለስልጣናት ከተመደበላቸው መደበኛ በጀት ውጭ 729 ሚሊዮን ብር አውጥተዋል። “ሙስናን በመዋጋት አገራችንን ከዘላለማዊ ከእዳ እንታደግ “ በሚል የባንኩ ሰራተኞች የውስጥ እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን፣ ከመንግስት ባለስልጣናትና ከህወሃት ታዋቂ ባለሀብቶች ጋር ከፍተኛ የጥቅም ቁርኝት የፈጠሩት የንግድ ባንኩ ስራ አስኪያጅ፣ ባንኩንና አገሪቱን ለከፍተኛ እዳ እየዳረጉዋት ነው ይላሉ።

በአርባምንጭ የነጭ ሳር ፓርክ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ከ20 ያላነሱ የመንግስት ታጣቂዎች ተገደሉ


የአካባቢው ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት ታጣቂዎቹ ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት 20 የመንግስት ወታደሮች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። ከተገደሉት መካከል የአካባቢው ወታደራዊ አዛዥም ይገኝበታል። የተኩስ ልውውጡ ለረጅም ሰአታት የቀዬ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ህክምና ተወስደዋል።
የመንግስት የጸረ ሽብር ግብረሃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ከኤርትራ የተንቀሳቀሱ ሃይሎች በሞያሌ በኩል ወደ አርባምንጭ ጫካ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ገልጿል። መንግስት በቁጥጥር ስር የዋሉና የተገደሉ ታጣቂዎች መኖራቸውን ቢገልጽም ፣ በአሃዝ ከመግለጽ ተቆጥቧል። ይሁን እንጅ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ድንገተኛ ጥቃቱን የፈጸሙት የታጠቁ ሃይሎች፣ ጥቃቱን ካደረሱ በሁዋላ ከአካባቢው ተሰውራል። ይህን ተከትሎም ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የከተማው ሰዎች እየታፈሱ ተወስደዋል።
አርበኞች ግንቦት 7 ጥቃቱን እንደፈጸመ በከተማው እየተወራ ቢሆንም፣ ንቅናቄው እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።

ሰበር ዜና..አል ሸባብ የኢትዮጵያን ወታደሮች ጠለፈ


ወደ ባይ_ዶዋ አካባቢ የተወረወሩ የአል_ሸባብ ታጣቂዎች ሶስት የኢትዮጵያን ወታደሮች አግተዉ የአል_ሸባብ ወታደራዊ ጣቢያ ( base ) ወደ ሆነው ኢል_ ቡር ( El_bur ) መዉሰዳቸዉን የሚጥቁሙ መረጃዎች ለወያኔዉ የምስራቅ እዝ ወታደራዊ ደህንነት ደርሰዉታል!
በቅኝት ላይ ተሰማርተዉ ከነበሩ ጥቂት የዝዝዉር ወታደሮች መካከል ሶስቱ መሰወራቸዉን ተንተርሶ ፍለጋ ቢደረግም ምንም አይነት ፍንጭ ጠፍቶ የነበረ ሲሆን ወታደሮቹ በአል_ሸባብ መጠለፋቸዉን የሚጠቁሙ መረጃዎች ከወደ ኢል_ቡር መንደር እንደደረሰዉ የስምሪት አዛዡን ተንተርሶ አንድ የምክትል መቶ አለቅና ሌሎች ተራ ወታደሮች መጠለፋቸዉን በሶማሌያ የኢትዮጵያዉ ጦር አዛዥ ኮነሬል የማነገብረ ማርያም ለምስራቅ እዙ አሳዉቋል።
በታህሳስ ወር 2006 እ.ኤ.አ የተመሰረተዉ አል_ሸባብን ማጥፋት ማለት መላዉ የሶማሌያን ሕዝብ ማጥፋት ማለት ነዉ! ያሉት ምንጫችን አክለዉ አል_ሸባብ ማለት እጅግ ጨካኝና አረመኔ የጥፋት ቡድን ነዉ። ከአልሸባብ ጋር የሚደረጉ ትንቅንቆች በሙሉ ከሶማሌያ ህዝብ ጋር የሚደረግ ትንቅንቆች ናቸዉ። ምንም እንኳን በዚህ በሶማሌያ ያሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች መጠን ቢቀነስም የአል_ሸባብ ድንገተኛ ጥቃት ግን ፈጽሞ አልቀነሰም አሁን የተጠለፉት ወታደሮቻን የሚጠብቃቸዉ የከፋ ሞት ብቻ ነዉ ብለዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

Tuesday, May 10, 2016

ይህ ምሁር የት ነው ያለው??

በስዩም ወርቅነህ
የቀድሞ ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከምርጫ 97 ሦስት ዓመት በፊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን በሰበሰበበት ወቅት ታሪካዊ ንግግር ያደረገው በፎቶ የምትመለከቱት ምሁር ቪድዮ ብዙ ሰው በማህበራዊ ድረ-ገፆች ሲወያይበት፣ ሲያካፍል፣ ሲያዳምጠው ቆይቷል ሆኖም ይህ ምሁር የት እንዳለ ሲጠይቅ አላየሁም። እሱም እንደተነበየው ኢትዮጵያ አዘቅት ውስጥ ስትወድቅ ምንም አይነት አስተያየት ሲሰጥ አልተመለከትኩም። እውን ይህ ምሁር በህይወት አለን? ወይስ መሰሪው አፓርታይዱ ፋሽስት የወያኔ/ኢህአዴግ ስርዓት እንደ ሌሎች ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አስሮታል? ገሎታል?Confronting Meles Zenawi
ለሁሉም መራጃ ያላችሁ ብታሳውቁን። አልያም ሚዲያዎች ይህን ምሁር ምን ላይ እንዳለ ሙያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም እጠይቃችኋለሁ። ይህ ምሁር ሃገራዊ ግዴታውን ለመወጣት በድፍረት በመናገሩ የደረሰበት ነገር ካለ የኢትዮጵያ ህዝብ ማወቅ መቻል አለበት።
በህይወት ካለና በሚዲያ መቅረብ የማይችል ከሆነ ፎቶውን በማስደገፍ መረጃ ስጡን!
ታሪክ የሰሩትን በደል ሲደርስባቸው ከጎናቸው መሆን ካልቻልን ሌላ ታሪክ ሰሪ መፍጠር አንችልም!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Wednesday, May 4, 2016

በኢትዮጵያ በሕግ ሽፋን የዜጎችን መብት መጣስ ተባብሶ መቀጠሉን ሂውማን ራይት ሊግ አስታወቀ

ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ ሽብር ሕግን ከለላ በማድረግ መብታቸውን የሚጠይቁ ዜጎችን ማሰር፣ መግደልና ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን መፈጸም ተጠናክሮ መቀጠሉን የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሊግ ገልጿል። ድርጅቱ በኦሮሚያ ክልል የበርካታ ንጹሃንን ሕይወት የቀጠፈው ዘግናኝ እልቂት በህወሃት ኢህአዴግ መራሹ ገዥ ቡድን የተቀነባበረ መሆኑን አስታውቋል።
ይህን ኢሰብዓዊ እልቂት ተቃውመው ለመብታቸው የታገሉት ከ 22 በላይ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች የሃሰት ክስ እንደተመሰረተባቸው አመልክቶ ፣ በህወሃት የተቀነባበረ ሴራ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ካለ ፍትሕ በእስር ቤት እየማቀቁ ነው ብሎአል።
በኢትዮጵያ ያለው የፀረ ሽብር ሕግ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በሚጻረር መልኩ የወጣ ሲሆን ይህም የዜጎችን የመጻፍ፣ የመናገርና የመቃወም ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በሚጥስ መልኩ ሆን ተብሎ ተረቆ በሥራ ላይ መዋሉን አስታውቋል።
በኦሮሚያ የተነሳውን ሰላማዊ የዜጎችን ጥያቄ በመደገፍ ከሕዝባቸው ጋር በመሆን ሲቃወሙ ከነበሩት ውስጥ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ የፓርቲው ፀሃፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ አቡላና ሌሎችም በፈጠራ የሽብር ክስ መከሰሳቸውንና የመብት ጥሰቱ ተባብሶ መቀጠሉን ሪፖርቱ አመላክቷል።
መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ በሽብር ሕግ ስም አላግባብ ታስረው የሚገኙ ንጹሃን ኢትዮዮጵያዊያንን ህወሃት መራሹ መንግስት ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታዎች ክሳቸውን በማንሳት ሊፈታቸው ይገባል ብሎአል።

10421433_648203905313009_8566024657772797199_n

ሰበር መረጃ ወያኔ በሀገ ወጥ ሰዉ ዝዉዉር ሰንሰለት ዉስጥ !

Gudish Weyane's photo.
የኢኳዶር ፖሊስ ( Ecuadorean police ) የኮሎምቢያ የጸረ አጋች ቡድን ወይም ኽዉላ ( Colombia’s elite anti-kidnapping squad, known as GAULA ) የአሜሪካዉ ሆም ላንድ ሴኪዉሪቲ ( us Home land security ) የብራዚል የህገ ወጥ ሰዉ ዝውውር ቁጥጥር ፖሊስ ( Brazilian migration police ) እና የሩቅ ምስራቅ ሀገራት ፖሊስ መረጃዎች እንዲሁም አለማቀፍ ፖሊስ ( Interpol ) በመተባበር የህገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉርን ለማኮላሸት በጋራ መስራት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል!