
ኮንግረስማን ኮፍማን ዶ/ር ታደሰን ስለ ኤርትራ ቆይታቸው ምን እንደሚመስል ጠይቀዋቸው፡- ዶ/ር ታደሰም ሲመልሱ፡- በህወሃት መንግስት የሚደረገው ህዝብን የማጣላት፣ በኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝበ መካከል በጠላትነት እንዲተያዩ የሚያደርገው ዘመቻ የተሳሳተ መሆኑን ገልጸው አርበኞች ግንቦት 7 ዘላቂ ወዳጅነትን እየጠናከረ እንደሚገኝ እና የሁለቱ ህዝብ ጠላት TPLF እንጂ ሌላ መሰረታዊ ችግርች እንደሌሉ እና ለኤርትራ ህዝብ ያላቸውን አድንቆት በመግለጽ አብሮ መስራት እንደሚቻል ያላቸውን እምነት ገልጸውላቸዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ የምትከተለውን የውጪ ፖሊሲዋን እንደገና እንድትመረምረውም አሳስበዋል። አያይዘውም ኮንግረስማን ማይክ ኮፍማንና ሌሎች ሴነተሮች በቅርቡ በሜሪላንዱ ሴነተር ካርደን ቤንጃሚን ተረቆ የቀረበውን Resolution 432 በርካታ ሴነተሮች የፈረሙበትን የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብትና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ድጋፋቸውን ይሰጡ ዘንድ ኮንገርሰማኑን ጠይቀዋል።
በመጨረሻም ኮንግረስማን ማይክ ድርጅቱ በሁለቱ ሀገራት ህዝብ መካከል እየፈጠረ ያለውን የሰላም ድልድይ እና የማቀረረብ ሂደት አድንቀው፤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮችም እንደሚከታተሉ ገልጸውላቸዋል።
Abbay media
Abbay media
No comments:
Post a Comment