
የቀድሞ የጋምቤላ ፕሬዚደንት አቶ ኦኬሎ አኳይ የጋምቤላ ጭፍጨፋን በተመለከተ ለፍርድ ቤት ማብራሪያ ሰጡ። የጭፍጨፋውን ሂደት በማዛባት፣ የተሳሳተ መረጃ ለህዝብ እንዲያቀርቡ በመገደዳቸውና ጭፍጨፋው የህሊና ሰላም ሰለነሳቸው ፕሬዚደንትነታቸውን ጥለው ድንበር አቋርጠው መሸሻቸውን በጽሁፍ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።

ከሳምንት በፊት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልላዊ መስተዳደር በሚገኙ የኑኢር ማህበረሰብ ላይ ከጎረቤት ደ/ሱዳን አንደመጡ የሚነገረላቸው እጅግ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና የደ/ሱዳን የመከላከያ ሰራዊቱን የድምብ ልብስ ያጠለቁ መሆናቸው የተነገረላቸው የሞራሌ ጎሳ ተወላጆች በ 10 የኑዊር መንደሮች ላይ በከፈቱት የጅምላ የተኩስ እሩምታ ከ 200 በላይ ሰዎች ህይወትን በመቅጠፍ ከ100 በላይ ጨቅላ ህጻናትን ደግሞ አፍነው በመወሰድ ፣ከ 2ሺህ በላይ የቀንድ ከበቶቻቸውን በመዝረፋቸው ሳቢያ በበርካታ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊናኦች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ሃዘን እና ቁጭት መቀሰቀሱ አይዘነጋም።






