(Satenaw) — የአል ጀዚራ ባልደረባ የሆነዉ ሃሰን ሁሴን (Hassen Hussein) እንደዘገበዉ ጃንዋሪ 8 ላይ ግብጽ የአባይ ግድብ ግንባታ እንዲቋረት ጠይቃለች ይህዉም በሁለቱ ሐገራት መካከል ዉስጥ ለዉስጥ እየተካረረ የመጣ ዲፕሎማሲያዊ ጸብ ወደ ተለያየ አቅጣጫ እንደሚሄድ ሲነገር ቆይቶ ሰንብቶ ነበር።
በ2017 ይጠናቀቃል የተባለዉ የአባይ ግድብ የተለያየ ችጎች ሲገጥሙት ቆይተዉ በስተመጨሻ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከግብጽ ጋር ሚያደርጉት አለመግባባት ከተካረረ ግብጽ በኤርትራ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በማስታጠቅ ትጎዳናለች ወደሚል ስጋት ስለጣላቸዉ ብቻ የካዮዉን መንግስት (Cairo’s collaboration) ለድርድር በመጥራት እሹሩሩ ጀመረች በስተመጨረሻም ግድቡን ዉሃ ላለመሙላት በመስማማት አጭብጭባና ተጨብጭባ ወደ ወደምትዋሸዉ ህዝብ ተመለሰች። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሳሊኒ የተባለዉ ግድቡን ሊሰራ የተዋዋለዉ ድርጅት በተባለዉ ወቅት አጠናቆ ለመዉጣት እንደማይችል በመረዳቱ ጓዙን ጠቅልሎ ተሰናብጧል አልጀዚራ እንዲህ አስቀምጦታል ( Salini Construttori, circumventing its own contract procedures and international standards on procurement. The construction is reportedly lagging behind schedule and faces several unresolved technical problems )
ዛሬ የአባይን ግድብ በተመለከተ አዲስ መረጃ አግጥጦ እየወጣ ይገኛል ይህዉም በቦንድ እና በልግስና ከሐገር ዉስጥ እንዲሁም ከሐገር ዉጭ የተሰበሰበዉ ገንዘብ በሙስና እንደተመዘበረ የዉስጥ መረጃዎች እየመሰከሩ ነዉ፡፤ በሰሞኑ በዚሁ ዙሪያ ላይ በተደረገ ግምገማ በቢሊዮን የሚቆጥር ገንዘብ በብር መመዝበሩን ተጋልጧል! በዚሁ መሰረት በተለይም ከደቡብ አፍሪካ ለመሰብሰብ ከታቀደዉ ገንዘብ መካከል እንደተገመተዉ ባዮንም ከከንባታና ሐዲያ ማህበር እና በዚያ ከሚኖሩ የወያኔ ደጋፊዎች የተሰበሰበዉ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከደቡብ አፍሪካ ወደ ቻና ተሸጋግሮ ከቻይና ወደ ኢትይጵያ ተልኮ ያለምንም ቀረጥ ለመስፍን ኢንጂነሪንግ እቃ ተገዝቶ መላኩን እና መስፍን ኢንጂነሪንግ ገንዘቡን አለማወራረዱን እማኞች ሲመሰክሩ በደቡብ አፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ ስደተኛዉን በማስተባበር ገንዘብ ለመሰብሰብ የተባበረ አንድ በወንጀል የተጨማለቀ ግብረ ወያኔ! ስሙን ለጊዜዉ መግለጽ ያልተፈለገ ግለሰብ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ተሰጥቶት የገንዘብ ዝዉዉሩን እዳከናወነዉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአባይ ግድብ ስም ከምስኪኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የተመዘበረዉ ገንዘብ ባጠቃላይ የወያኔ ካምፓኒዎች ማለትም የኤፈርትን አቅም በሚያጎለብት መልኩ ብቻ ተግባራዊ እንዲሆን በታቀደዉ መሰረት የመሶበ ሲሚንቶ ፋብሪካ አሁን በስራ ላይ ላልሆነዉ የግድቡ ኮንስትራክሽን ቅድመ ክፍያ ከ2.7 ቢልዮን ብር በላይ መሰጠቱን እና ባጠቃላይ የኤፈርት ካምፓኒዎችና ተዛማችነት ያላቸዉ ቤተሰባዊ ወያኔ ለሆኑ ድጅቶች ወደ ጥቅም ያልተወራረደ ከአንድ መቶ ሃምሳ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ሲጋለጥ ለዚሁ ሁሉ መሰረታዊ ምዝበራ ግንባር ቀም ሚና የሚጫወቱትም ተጠቅሰዋል።
በመሆኑም ከባለስልጣናቱ መካከል በተለይም ስብሃት ነጋ የተባለዉ ግለሰብ የሴት ልጁ ባለቤት በግድቡ ዙሪያ ላይ በሚወጡ የስራ ፕሮፎርማዎች ላይ ማንኛዉንም መመሪያና ትእዛዝ እየተቀበለ እንዲሁም ስራዉ ለማን መሰጠትና ማን ተጠቃሚ እንደሚሆን ተራ በተራ የህዝብን ንብረት በመመዝበር ላይ መሰማራታቸዉን የደርሰን መረጃ ያመለክታል።
No comments:
Post a Comment