በኢትዮጵያ ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ለዲሞክራሲ ፣ ለፍትህ እና ለነጻነት ለሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርጫፍ ጽ/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት የ 119ኛው የአድዋ ድል በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከበረ ፡፡
በዕለቱ የአድዋን በዓል ታሪካዊነት በዝርዝር የሚያስረዳ እና የአብዛኛውን ታዳሚ ቀልብ የሳበ ታሪካዊ ትንታኔ የቀረበ ሲሆን የአድዋን ድል የሚገልጹ ጽሑፎች ግጥም እና “የሚኒሊክ ወቀሳ” በሚል ርዕስ ድራማ ቀርቦ ታላቅ አድናቆትን አትርፏል፡ አሁን ሀገራችን ኢትዮጵያ ና ህዝቦቿ ለ23 አመታት በወያኔ ስርአት እየደረሰባቸው የሚገኘውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፣እስር ፣ ግድያና ዝርፊያ የሚገልጽ በራሪ ወረቀት ለኖርዌጂያን ማህበረሰብ ታድሏል ፡
በመቀጠልም ከተጋባዥ እንግዶች ጋር በአድዋ ድል ዙሪያ ውይይት ተካሂዱዋል በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት ቀኝ ገዢው ጣሊያን ካደረሰብን በደል በላይ ባንዳው የወያኔ መንግስት እያደረሰብን የሚገኘው ውርደት ፣ ስደት፣ ሞትና ስቃይ ምን መደረግ አለበት በሚል ሰፊ ውይይት ተካሂዶ አባቶቻችን ከዛሬ 119 አመት በፊት ያቀናጁንን ድል ዛሬም ታሪክ ሰሚና ተራኪ ብቻ ሳንሆን ታሪክ ሰሪ ሆነን በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ ይህንን አስከፊ ስርዓት ለመቀየር የሚታገሉ ሃይሎችን ገንዘብ ያለው በገንዘቡ ጉልበት ያለው በጉልበቱ እውቀት ያለው በእውቀቱ በመደገፍ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወያኔን ማስወገድ እንደሚገባ ፣ በታሪክ በስልጣኔ ለአፍሪካ የነጻነት ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን ወደ ቀድሞ ክብሯ እንድትመለስ የዚህ ትውልድ አደራ መሆኑን ተገልጾ የዝግጅቱ ፍጻሜ ሆኗል ፡፡
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት
የበርገን ቅርጫፍ ጽ/ቤት
No comments:
Post a Comment