Translate
Monday, March 30, 2015
Friday, March 27, 2015
ለዓመታት የስለላ ሠራተኛና የአዲስ አበባ ቀጠና ኦፊሰር የነበረች የህወሃት አባል መክዳቷ ታወቀ።
በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ።
የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው።
Thursday, March 26, 2015
አርበኞች ግንቦት7 – ጉዞአችን ወደ ነፃነት ነው!! መዳረሻችንም የነፃነት አደባባይ ብቻ ነው!!
አለማችን አንባገነን ስታስተናግድ ወያኔ የመጀመሪያው አይደለም። ዘረኛንም እንዲሁ …….. እኛም ስለነፃነት ብለን ለትግል ስንነሳ የመጀመሪያዎቹ አይደለንም …… አለማችን እንደየዘመኑና እንደ የወቅቱ አንባገነኖች ያለ የሌለ የመሳሪያና ወታደራዊ ሀይላቸውን በመጠቀም ህዝብን በፍርሀት አሸማቀውና ረግጠው ለመግዛት ሲውተረተሩ በተደጋጋሚ ታይተዋል። በዚያው ልክ ህዝባዊ ሀይልን መመከት ተስኗቸው ሲንኮታኮቱ በተደጋጋሚ የታየ ወደፊትም አናባገነኖች እስከተከሰቱ ድረስ በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገው መቀመቅ ሲወርዱ መታየቱ አይቀሬ ነው ። ህዝብ የወደደውን አስተዳዳሪ እንጂ ረግጦ ሊገዛው የሚፈልገውን አንባገነን ተቀብሎ አያውቅም ፤ዛሬም አልተቀበለም ፤ ነገም አይቀበልም ። ይህን በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚና በጉልህ የሚታይ ግዙፍ እውነት መቼም ተቀብለውና ከታሪክ ተምረው ስለማያውቁ አሳፋሪው ውድቀታቸው በተደጋጋሚ ሲታይ አለ።
ሀገራችን የአለማችን አካል እንደመሆኗ አንባገነኖች ተፈራርቀውባታል። አንባገነኖችም በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገውባታል። ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ትልቅ ወታደራዊ ሀይል የነበረው የትናንቱ ደርግ እንደ እንቧይ ካብ ሲናድ ተመልክተናል። አንባገነኖች መናገር እንጂ መስማት የማችሉ፤ ማየት እንጂ ማስተዋል የተሳናቸው በመሆናቸው እነሆ ዛሬም የወያኔ ዘረኛው ቡድን ህዝባ ላነሳው የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል በጠራራ ጸሀይ በማሰለፍ መቼውንም ያልተቻለውን ህዝብን በሀይል አሸማቆ ለመግዛት መከራውን ሲያይ ይስተዋላል። ለዚህም ነው ….. ከሌላው የሀገራችን ክልሎች ከፍ ባለ ሁኔታ የህዝባዊ እንቢተኝነት እየታየ ባለበት ጎንደርና አካባቢው በሰራዊት ማጥለቅለቅ የተያያዘው።

የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለ8ኛ ጊዜ ተመለሰ
• ኢብኮና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት መልሰዋል
• ‹‹አማራጫችን እንዳናቀርብ እየተከለከልን ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አናስተላልፍም›› ብለው መመለሳቸውን ድርጅቶቹ ለፓርቲው በላኳቸው ደብዳቤዎች ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የብሔራዊ ራዲዮ በአማርኛ ስርጭት የሚተላለፍ ‹‹መንግስታዊ አወቃቀር›› የሚል የቅስቀሳ መልዕክት ልኮ የነበር ሲሆን ባለፉት 24 አመታት ተግባራዊ የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም ለግጭት መንስኤ መሆኑን በመረጃ ዘርዝሮ ማቅረቡን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ይሁንና ኢብኮ ይህን የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹በተለያዩ ጊዜያት በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ተከሰቱ ያሉትን ግጭቶች በመዘርዘር በህዝቦች መካከል ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስና እንዲባባስ የሚያደርጉና ግጭት የሚያራግቡ፣ አንዱን ብሔር ከሌላ ብሔር የሚያገጩ ናቸው፡፡›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡ ከዚህም ባሻገር በመልዕክቶቹ ውስጥ ‹የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት›፣ እንዲሁም ‹የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት› የሚለው አገላለጽ የፓርቲውን ህጋዊ መጠሪያ የማይወክል በመሆኑ›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡
በሌላ በኩል እነዚህ ግጭቶች በአሁኑ ወቅትም የቀጠሉና የጎሳ ፌደራሊዝሙ እስካለ ድረስ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ መሆናቸውን የገለጸው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ መልዕክቶቹ ከፓርቲው ማንፌስቶ የወጡ፣ ኢብኮ እንዳለው ለግጭት ሳይሆን ከግጭቶቹ መማር እንዲቻልና አሁን ያለው የጎሳ ፌደራሊዝም ከተስተካከለ ችግሮቹ እልባት እንደሚያገኙ በሚያሳይ መልኩ የተላለፈ መልዕክት ነው ብሎአል፡፡ ‹‹እኛ ያቀረብነው አማራጫችን ነው፡፡ አማራጫችን ስናቀርብ ደግሞ የጎሳ ፌደራሊዝም የፈጠረውም ቀውስም በማሳያነት ማቅረብ አለብን፡፡ ይህን እውነታ የአገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ዘግበውታል፡፡ አብዛኛዎቹ መንግስትም ያመነባቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ስርዓቱ የሰራቸው ጥፋቶች ይፋ አውጥተን እንዳናቀርብ ስለተፈለገ መልዕክቱን መልሰውታል፡፡ በግልጽ አማራጫችን እንዳናቀርብ ተከልክለናል›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹ከሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ጋር የሚጻረር፣ ብሔር ብሄረሰቦችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዲያመሩ የሚገፋፋ፣ የሌላ ፖለቲካ ፓርቲን ስም የሚያጎድፍ ይዘት የተካተተባቸው›› ናቸው በሚል መልሷል፡፡ ይህ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ሲመለስ ለ8ኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡
Wednesday, March 25, 2015
ድምፃችን ይሰማ 2ኛውን የሰላማዊ ተቃውሞ ይፋ አደረገ * “ሳንቲም በመሰብሰብ በራስ ላይ እቀባን በማድረግ ለመንግስት ተቃውሞን መግለጽ”
2ኛው አነስተኛ የትብብር መንፈግ ተቃውሞ መርሃ ግብር
ሳንቲም በመሰብሰብና በማጠራቀም ራስ ላይ የመቆጠብ እቀባ በማድረግ ለመንግስት የተቃውሞ መልእክት ማስተላለፍ
ረቡዕ መጋቢት 16/2007
ሳንቲም በመሰብሰብና በማጠራቀም ራስ ላይ የመቆጠብ እቀባ በማድረግ ለመንግስት የተቃውሞ መልእክት ማስተላለፍ
ረቡዕ መጋቢት 16/2007
በሰላማዊ ህዝባዊ ትግል ውስጥ ትብብር የመንፈግ እና የቦይኮት ተቃውሞ ከመንግስት ኃይሎች ጋር ሳይፋጠጡ እና አካላዊ ግጭት ውስጥ ሳይገቡ ትብብርን በመንፈግና የቦይኮት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ በደል እያደረሰ ለሚገኘው አካል የተቃውሞ መልእክት የማተላለፍ ስልት ነው፡፡ የትብብር መንፈግ ተቃውሞዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓይነቶች ያሏቸው ሲሆን በአገሪቱ ውስጥ የሚገባንን የዜግነት መብት እስክናገኝ ድረስ ለመታገል ቆርጠን በገባንበት ታላቅ ህዝባዊ ትግል ውስጥ ካሁን ቀደም እምብዛም ሳይሞከር ቆይቷል፡፡
ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተቃውሟችን ወደቦይኮት እና ትብብር የመንፈግ ስልቶች እንደሚሸጋገር፣ ይህም አደባባይ ተኮር በሆኑ ተቃውሞዎች የገዛ ህዝቡ ላይ ጥይት ለመተኮስ የማያመነታው መንግስት ጡጫ እንዳያሳርፍብን ለመከላከል እንደሚያስችል መገለጹ ይታወሳል፡፡
ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተቃውሟችን ወደቦይኮት እና ትብብር የመንፈግ ስልቶች እንደሚሸጋገር፣ ይህም አደባባይ ተኮር በሆኑ ተቃውሞዎች የገዛ ህዝቡ ላይ ጥይት ለመተኮስ የማያመነታው መንግስት ጡጫ እንዳያሳርፍብን ለመከላከል እንደሚያስችል መገለጹ ይታወሳል፡፡
Tuesday, March 24, 2015
ጎንደር ዝምታውን ሰብሯል – የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዋል
መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል።
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ ሰራዊትም ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች አቅንቷል።ወታደራዊ ልምምዶችና አዳዳስ ምልመላዎችም እየተካሄዱ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።
ማንነታቸው በውል ያልታወቀ የተቃዋሚ ሃይሎች ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚሊሺያ አዛዥ የሆነውን ኮማንደር ተፈራን ገድለው ካመለጡ በሁዋላ፣ እነሱን ለመያዝ መጋቢት 12 አርማጭ ልዩ ቦታው እንኮይ ተራራ ላይ በተደረገ ጦርነት ፣ ከተቃዋሚዎች በኩል ሻምበል ይርዳውና
አዲሱ የተባሉ ሲገደሉ፣ ከመንግስት ታጣቂዎች በኩል ደግሞ የልዩ ሃይል አባል የሆነው እባበይ እንዲሁም አንድ ስሙ በውል ያልታወቀና ሁለት የሚሊሺያ አባላት ተገድለዋል። ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ እስከ ምሽት በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ፣ አንድ ተማሪ በመንግስት
ሃይሎች ተገድሏል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ምሽት ላይ አካባቢውን ጥለው መውጣታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን አስተያየት ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።
የጄት ድብደባ ወይንስ የአውሮፕላን መከስከስ?
አበበ ገላው (ከፌስቡክ የተወሰደ)
ወያኔ ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ አንድ የካናዳ የወርቅ ማእድን በአውሮፕላን መደብደቡን አፍቃሪ ወያኔ የሆኑ ድረ ገጾች “ወታደራዊ ምንጮችን” በመጥቀስ ዘግበዋል።
ይሁንና እንኳን ድብደባው የጥቃቱን ውጤት ያሳያል ተብሎ የተለቀቀውም ፎቶ የውሸት መሆኑ ተረጋግጧል። አውራንባ ታይምስ አስተማማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ድብደባውን ማረጋገጡን የዘገበ ሲሆን ዘገባውም በፎቶ ማስረጃ የታጀበ ነው። ይሁንና ፎቶው የሚያሳው ኤርትራ ውስጥ የተኪያሄደውን የአየር ጥቃት ውጤት ሳይሆን ቢቢሲ በኦገስት 9 2013 አንድ የወያኔ አየር ሃይል የእቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን ሞቃዲሹ ውስጥ ተከስክሶ ሲጋይ የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃን ነው። ይህም ፎቶ የተነሳው በሮይተርስ ሲሆን በቢቢሲ ድረ ገጽ ላይ ከዜናው ጋር በክብር ታትሞ ይገኛል።
አውራምባ ታይምስ ግን ዜናውን እውነት ለማስመሰል ከርክሞ እውነተኛውን ምንጭ ሳይጠቅስ ለታዳሚዎቹ አቅርቧል። በዚህም ጥፋት የሚያሳይ ፎቶ የተደነቁ በርካታ ወያኔዎች “አየር ሃይሉን” በማወደስ አስተያየት ሰንዝረዋል። የካናዳው የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ካምፓኒ ግን አንዳንድ ሰራተኞቹ የተወሰኑ ማሽኖች ሆን ብለው ማበላሸታቸውን እና ጥገና አድርጎ ስራ መቀጠሉን በይፋ ገልጿል።

አርበኞች ግንቦት7 – ህዳሴም ሆነ ዉዳሴ ክህዝብ የሚደበቅ ምንም ነገር የለም!
ከሰሞኑ አገራችን ኢትዮጵያን በተለይም ብሄራዊ ጥቅሟንና ደህንነቷን በተመለከተ ሁለት አቢይ ዜናዎች የአገራቸን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጉዳዮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸዉን አገሮች የአየር ሞገደች ተቆጣጥረዉት ነበር። ከእነዚህ ዜናዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ኢትዮጵያ፤ ሱዳንና ግብፅ የህዳሴዉን ግድብ አስመልክቶ ስምምነት ላይ ደረሱ የሚል ዜና ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች የህዳሴዉ ግድብ የሚሰራበት ቦታ ድረስ ሄደዉ ባካሄዱት ጥናት መሠረት የህዳሴዉ ግድብ ፕሮጀክት ባጋጠመዉ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት የተነሳ እንዲዘገይ መወሰኑን የሚያወሳ ዜና ነዉ። አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚሰሩ ምንም አይነት ስራዎችና በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከየትኛዉም አገር መንግስትና መንግስታዊ ካልሆነ ተቋም ጋር ለሚደረጉ ስምምነቶችና ዉሎች ሁሉ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነዉ ብሎ ያምናል፤ ስለሆነም አርበኞች ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ከሚመለከቱና በሚስጢር መጠበቅ አለባቸዉ ተብሎ ከሚታመኑ አንዳንድ ጉዳዮች ዉጭ ሌላ ምንም ስራ ወይም አለም አቀፍ ስምምነትና ዉል የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያዉቀዉና ሳይሰማዉ በድብቅ መደረግ የለበትም የሚል የጸና እምነት አለዉ። ሆኖም ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ አገዛዝ ኢትዮጵያን ከቅኝ ገዢዎች በከፋ መልኩ የሚገዛ የጥቁር ፋሺስቶች አገዛዝ በመሆኑ የሚሰራቸዉ ስራዎችና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚፈርማቸዉ ዉሎችና ስምምነቶች የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅም የሚጻረሩና የሚጋፉ ድብቅ ስምምነቶች ናቸዉ።
Monday, March 23, 2015
ኑሮ በአዲስ አበባ (ነፃነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ)
ትናንት ሲያቀብጠኝ ከአንድ ጓደኛየ ሞባይል እነዚያ አይሲስ የሚባሉ ጉግማንጉጎች እነዚያን 21 ክርስቲያን የግብፅ ዜጎች በሊቢያ አንድ የባሕር ዳርቻ ላይ አንገታቸውን ሲቀሉ የሚያሣይ ቪዲዮ አየሁ – እስከመጨረሻው መዝለቅ አልቻልኩምና ግን ዋናው ባራኪ በግራ እጁ የያዘውን ጩቤ ወደ እኛ ወደተመልካቾቹ ዘርግቶ እያስፈራራ ሲዝት አጠፋሁት፡፡
የሰው ልጅ በሰው ልጅ ላይ እስከዚህ መጨከኑ የሚያመላክተን ዋና ቁም ነገር የዚች ምድር ሰዎች የደረስንበት አጠቃላይ መንፈሣዊና ኅሊናዊ ኪሣራ ሊቀለበስ ወደማይችል ከፍተኛ የመጨረሻ ደረጃ መድረሱን ነው፡፡ ለምግብነት የተፈቀዱልንን እንስሳት እንኳን ስናርድ የሚዘገንነንና በዚህም ምክንያት የማናርድ ብዙ እንስፍስፍ ሰዎች አለን፡፡ ሰውን የሚያህል ክቡር ፍጡር ሊያውም በሚከተለው ሃይማኖት ምክንያት ብቻ በስለት አንገቱን ቀንጥሰው ጀርባው ላይ ሲያስቀምጡ ሊሰቀጥጣቸው ይቅርና በደስታ የሚፈነጥዙ “ሰዎች”ን በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ስናይ በሰዎች ተፈጥሮ መለያየት እጅግ እንገረማለን፡፡
Sunday, March 22, 2015
ሰማያዊ ፓርቲ ስለ ወጣት ታጋዮቹ መታሰር ምንም አለማለቱ እያነጋገረ ነው
እየሩሳሌም ተስፋው፣ በርሃኑ ተክለያሬድ እና ፍቅረማርያም አስማማው የተባሉት ታዋቂና ወጣት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወያኔ የፖለቲካ እስረኞችን በሚያጉርበትና ስቃይ በሚፈጽምበት ማዕከላዊ እስር ቤት እንደሚገኙ ታውቋል።
ወጣቶቹ በማዕከላዊ እስር ቤት መሆናቸው በይፋ ከመታወቁ በፊት ጓደኞቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ ሳያውቁ ሰንብተዋል።
ወጣቶቹ የት እንዳሉ ባልታወቀበት ሰዓት አንዳንድ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ከወጣቶቹ መሰወር ጋር በተየያያዘ በፌስቡክ ላይ የሚያውቋቸውን እነርሱ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ወይንም ደጋፊዎች ያሏቸውን ግለሰቦች ሲወቅሱ ከርመዋል።
እንደ ሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወቀሳ ከሆነ ኢሳት በማዕከላዊ ታስረው ስለሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች “ወጣቶቹ አርበኞች ግንቦት 7ን ለመቀላቀል ሲንቀሳቀሱ ታሰሩ” ብሎ መዘገብ ነበረበት ይላሉ።
ኢሳት በዚህ ጉዳይ ላይ ይፋዊ መልስ ባይሰጥም የኢሳት ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ የሚከተለውን ብሏል፣

Thursday, March 19, 2015
በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ግሰለቦች የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ
በኤልያስ ገብሩ
‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ኢህአዴግ አሸባሪ ነው፡፡ ለሽብር ሀሳቡም ፍላጎቱም የለኝም›› ዳንኤል ሺበሺ
‹‹የተባለውን ለነገር አለማድረጌን ከእኔ በላይ የከሰሰኝ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል›› ሀብታሙ አያሌው
‹‹ለእኔ ብቸኛው አሸባሪ ህወሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡ እኔ የህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ ነኝ›› አብርሃ ደስታ
‹‹ይሄ 19ኛ ችሎት የጦር ፍርድ ቤት ችሎት እየመሰለ ነው›› የሺዋስ አሰፋ
‹‹ሃይማኖቱንና ማኅበረሰቡን ከሚፈራ ህዝብ ወጥቼ እንዲህ አይነት ተግባር አልፈጽምም›› ባህሩ ታዬ
————————
ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓ.ም፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት እና በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ ያሉ 10 ሰዎች ቀርበው ነበር፡፡ መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመቀበል እና ከ1-5ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተከሳሾች በእስር ቤቱ ደረሰብን ብለው ባቀረቡት አቤቱታ ላይ አስተያየት ካላቸው ለመቀበል መሆኑን የችሎቱ የግራ ዳኛ ገልጸዋል፡፡
የተከሰሾቹን የጽሑፍ አስተያየት በጠበቃ ተማም አባቡልጉ በኩል ቀርቦ ከመዝገብ ጋር ከተያያዘ በኋላ ተከሳሾቹ በየተራ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ የግራ ዳኛው በመናገር 1ኛ ተከሳሽን ‹‹በክሱ ላይ እንደቀረበው ወንጀሉን ፈጽመሃል ወይስ አልፈጸምክም?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡

በአርበኞች ግንቦት 7 – ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ!
ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል።
በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው ሕዝብ ጎን በመቆም አምባገነኖችን አስወግዶ የሽግግር መንግሥት ያቆማል። በቅርብ ጊዜያት በሕዝባዊ እምቢተኝነት መንግሥት በተቀየረባቸው አገሮች ያየነው እንደዚህ ዓይነቱን ሀቅ ነዉ።
አገራችን ውስጥ ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል። ህወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ የገነባው የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አመራር በዘር የተደራጀ በመሆኑ የሕዝቡን አጠቃላይ ብሶት ደግፎ ሊቆም ይችላል ብሎ መጠበቅ አይቻልም። ሠራዊቱ እንደ ተቋም ከተበደለው ሕዝብ ጎን እንዲቆም በመጀመሪያ በራሱ በሠራዊቱ ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ መካሄድ አለበት።በዚህ አቅጣጫ የሚሠሩ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ሠራዊቱ ዘረኛ ገዢዎቹን አስወግዶ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም፣ አይገባምም። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት በሕዝባዊ አመጽ መታገዝ አለበት የሚለው ሁለገብ የትግል የትግል ስትራቴጂ ተመራጭ እንዲሆን ያደረገው ዋነኛ ምክንያት የሠራዊቱ ዘረኛ አወቃቀር ነው።

Tuesday, March 17, 2015
የህወሃት ታሪክ የመሻማት ሩጫ
ዘሪሁን ተስፋዬ
ላለፈው ሁለት ወር በህወሃት መሪነትና ባጋፋሪዎቹ ርብርብ የህወሃትን 40ኛ አመት ምስረታ ለማክበር በሚል የብዙ ሚሊዮን ብሮችን ወጪ የጠየቀ ታሪካዊ ጉብኝት፣ ስብሰባዎችና ተጓዳኝ ፈንጠዝያ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገሮች ሲካሄድ ሰንብቷል።
ለተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ገነት፣ ለብዙሃን የህብረተሰቡ ክፍል ደግሞ ሲኦል እየሆነች ባለችው ሀገራችን ለአንድ ብሄር ድርጅት ምስረታ በአል በሚል በብዙ ሚሊዮን ብሮች ወጪ የተካሄደው ፈንጠዚያ በራሱ እጅግ አሳፋሪ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም።
ይህ ሰማእታትን ለመዘከር፣ የትግል ታሪክንና ተመክሮዎችን ለአዲሱ ትውልድ ለማስተላለፍ. . . ወዘተ የሚሉ ማደናገሪያዎችን በመጠቀም፣ ህወሃት ውዥንብር ሊፈጥርበት ቢሞክርም፣ በቅጡ ላጤነው ግን የድርጅቱንና የመሪዎቹን ገድል እንደ ቀድሞ የሀገራችን የተወደዱ ጀግኖች፡ [ዳር ድንበር ሲያስከብሩ፡ለነጻነትና ለሰው ልጆች እኩልነት ሲታገሉ እንደወደቁት ሁሉ] እንዲወደሱ፣እንዲተረክላቸው፣ እንዲዘፈንላቸው፣ እንዲተረትላቸውም ለማባበልና ለማስገደድ የሚደረግ ሙከራ ነው። ባጭሩ የታሪክ ሽሚያ ነው።
ውይይታችን ኢሳያስ መልዓክ ነው ያድነናል አልያም ጭራቅ ነው ያጠፋናል አይነት ባይሆን?
አዜብ ጌታቸው
በቅርቡ የኢሳት ጋዜጠኞች ወደ አስመራ ተጉዘው፤ የወያኔን አገዛዝ በትጥቅ ትግል ለመፋለም የተሰለፈው ወገን የሚገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ ተመልክተውና እንደ ጋዜጠኛ ዘገባቸውን አጠናቅረው ተመልሰዋል። ይህም ተግባራቸው ኢሳት እንደ ህዝብ ሚዲያነቱም ሆነ የወያኔን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ለመጣል የሚደረገውን ሁለንተናዊ ትግል በተግባር በማገዝ ረገድ አንድ እርምጃ ወደፊት መሄዱን ያረጋገጠ ነው ብዬ በድፍረት እናገራለሁ። ይህ ስሜት የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ስሜት መሆኑንም በተለያዩ መንገዶች አረጋግጫለሁ።
የኢሳት ጋዜጠኞች ወደ አስመራ ተጉዘው ካጠናቀሩት ዘገባዎች ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ኢትዮጵያዊውን ወገን እያወያየ ያለው ከኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ነው፡፡
ለዚህም በቂ ምክንያት አለው። ኢሳያስ አፈወርቂ ወይንም ሻቢያ ሃገራችን አሁን ለምትገኝበት አጣብቂኝ ግዙፍ የሆነ ሚና የተጫወቱ መሆናቸው ነው፡፡
የኢሳት ጋዜጠኖች ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስን አስመልክቶ አቶ ክንፉ አሰፋ የጻፈውን አስተያየት አንብቢያለሁ።ልናስተውላችው የሚገቡ ነጥቦችን አንስቷል። ቀጥሎም የአዲስ ድምጽ ጋዜጠኛ አበበ በለው ክንፉ አሰፋንና ሌሎች ሁለት እንግዶችን በመጋበዝ በዚሁ በፕ/ት ኢሳያስ ቃለ መጠይቅ ዙሪያ ከሁለት ሰአት በላይ የዘለቀ ሰፊ ወይይት መድረክ አዘጋጅቶ አስደምጦናል።
Thursday, March 12, 2015
የዲሞክራሲዊለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ድጋፍ አሰባሳቢ ጊዜያዊ ግብረ ኃይል የተሰጠ የአቋም መግለጫ !!
የባዕዳን ወራሪዎች ለሃገራቸው ቀናኢ በሆኑ ጀግኖች አባቶቻችን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ነጻነታችንን የተቀዳጀንበት እንዲሁም ለጥቁር ህዝብ አርአያ የሆንበት 119 የአድዋ በዓል በሚከበርበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ ማንነቱ ተዋርዶና ተንቆ በጥቂት ዘረኛ ፋሽስቶች እየደረሰበት ያለው ግፍና መከራ ውሎ እያደረ እየመረረና እየከረፋ መምጣቱ ከማንም ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አደለም፡፡
አንባገነኑ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ከመቼውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ በሃገርና በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ሰቆቃ ለመታገል ኢትዮጵያንና ህዝቧን አስተማማኝ መሰረት ያለው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ባለቤት ለማድረግና ከዚህ በዘር ከተደራጀ የሃገርና የህዝብ ጠላት ነጻ ለማውጣት በውጪም ሆነ በውስጥም ውድ ህይወታቸውን ለመስዋእትነት ያቀረቡና ለማቅረብ የተዘጋጁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ይሁንና ይህው ዘረኛዉ የወያኔ ሥርዓት ከወትሮው በረቀቀ መልኩ በሃገር ውስጥ የሚደረገውን የነጻነት ትግል ለማዳፈን ከማሰርና ከማሰቃየት በዘለለ ባስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ደፋ ቀና የሚሉ አውራና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን የህዝብ ፓርቲዎች ሌት ተቀን የሚዘምርለት የይስሙላ ምርጫ ከመድረሱ በፊት የሥርዓቱ ክንፍ በሆነው የወያኔ ምርጫ ቦርድ ተብዬው አማካኝነት በነጻነት የመደራጀት መብታቸውን በመግፈፍ እንደበታተናቸውና ምርጫው ከመካሄዱ ከወራት በፊት ለተጨማሪ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ራሱን ለመጫን ብቻውን እሮጦ ብቻውን የሚያሸንፍበትን ጥርጊያ መንገድ እያመቻቸ መሆኑ በገሃድ እየታየ ነው፡፡
Wednesday, March 11, 2015
አስር የድረ-ገጽ አዘጋጆች ቴድሮስ አድሃኖም ውሸታቸውን እንዲያርሙ አሳሰቡ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ፒኖሾ” የሚል ስያሜ አግኝተዋል
ጋዜጣዊ መግለጫ
ዋሽንግተን ዲሲ፤ አስር የድረ-ገጽ አዘጋጆች በአንድነት በመሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እና በፌስቡክ ገጻቸው የተናገሩትን አጸያፊ እና ሃላፊነት የጎደለው ውሸት እንዲያርሙ ጠይቀዋል። ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በመገናኛ ብዙሃን (ስለ) ታዳጊ ወጣት በሪቱ ጃለታ የተናገሩትን የ20 ሚልዮን ዶላር የፈጠራ ታሪክ እስካሁን ባለማረማቸውና ህዝብን ይቅርታ ባለመጠየቃቸው፣ የድረገጽ አዘጋጆቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን በአንድ ድምጽ “ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ፒኖሾ” የፈጠራ ገጸ-ባህርይ የሚል ስያሜ ሰጥተዋቸዋል።
የአቡጊዳ፣ የአዲስ ቮይስ፣ የኢካድ ፎረም፣ የኢትዮፎረም፣ የኢትዮ ፍሪደም፣ የኢትዮ ሜድያ፣ የኢትዮጵያን ሪቪው፣ የቋጠሮ፣ የሳተናው እና የ ዘሃበሻ ድረ-ገጽ አዘጋጆች በጋራ በመሆን ይህንን አቋም የወሰዱት፣ ሚኒስትሩ በህዝብ ፊት በመቅረብ ነዋሪነትዋ በሜልቦርን ስለሆነው የ14 አመት ተማሪ ብሪቱ ጃለታ በተናገሩት ፍጹም ሃላፊነት የጎደለው ቅጥፈት የተነሳ ነው።

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)
ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።
Tuesday, March 10, 2015
የአውሮፓ ህብረት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ተወያየ!!!
የአውሮፓ ህብረት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ተወያየ!!!
10 March 2015
‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
...
10 March 2015
‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
...
የአውሮፓ ህብረት ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ባደረገው ስብሰባ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በተጋባዥ እንግዳነት ተገኝተው ከህብረቱ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ ያላቸው 20 ያህል የህብረቱ አባል አገራት በተገኙበት ስብሰባ ላይ አብዛኛዎቹ በአምባሳደሮቻቸው እንዲሁም ቀሪዎቹ በምክትል አምባሳደሮቻቸው ተወክለው የተገኙ ሲሆን ተወካዮቹ ወቅታዊ የምርጫ ሂደት እንቅስቃሴና የሰማያዊን የምርጫ እንቅስቃሴ፣ በምርጫው ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች፣ የፓርቲው አማራጭ ፖሊሲዎች፣ የድርጅቱን ጥንካሬ፣ የአንድነት አባላትወደሰማያዊ መምጣታቸው ለትግሉ የሚኖረው ትርጉምና ሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ ዕጩዎች በህገ ወጥ መንገድ እንደተሰረዙበት፣ የፓርቲው የቅስቀሳ መልዕክቶቹ ከ6 ጊዜ በላይ በሚዲያ እንዳይተላለፍ መከልከሉን፣ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ድብደባ፣ እስራትና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቅሰው በምርጫ ሂደት ኢህአዴግ አፋኝነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸዋል፡፡

Monday, March 9, 2015
ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ኢህአዴግ›› በሚል ስም የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ጠየቀ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ኢህአዴግ›› የሚል ውህድ ፓርቲ እንዳለ ተደርጎ በህግ ጥሰት በስሙ የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድን ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ የካቲት 30/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምግዝባ አዋጅ ‹‹’ግንባር’ ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ የሆነ ስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ኖሯቸው ለመንቀሳቀስ ሲወስኑ የሚደራጅ አካል ነው፡፡›› እንደሚል ገልፆ፣ ግንባር የሆነው ኢህአዴግ እንደ ውህድ ፓርቲ ተቆጥሮ በስሙ ዕጩዎች መመዝገባቸው ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲው በላከው ደብዳቤ ‹‹በአዋጁ እንደተደነገገውም ኢህአዴግ አራት ህልውና ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ግንባር እንጂ ፓርቲ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አባል የለውም፡፡ በእርሱ ስም ግለሰብ ዕጩዎች ሊወዳደሩም ሆነ ሊመረጡም አይችሉም፡፡›› ሲል በኢህአዴግ ስም ዕጩዎች መመዝገባቸውን ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
ምርጫውን ለህዝባዊ እንቢተኛነት እንዴት?
ዳዊት ዳባ
ህዘባዊ እንቢታ ማለት ዜጎች የስርአት ለውጥን ሆነ መብታቸውን ለማስከበር በብዙ ቁጥር ሆነው በጋራ አንድን ነገር ማደረግ ወይ አለማድረግ ነው። አለቀ። ብብዙ ቁጥር ተቃውሞ አደባባይ መውጣት በጋራ ልናደርጋቸው ከምንችላቸው በትንሹ ከሺ ነገሮች ውስጥ አንዱ የህዝባዊ ተቃውሞ አካል ነው። ተቃውሟችንን ለመግለፅ በጋራ ልናደርጋቸው የሚቻሉን ነገሮች ሁሌ የግድ ከባድም አጋላጭም መሆንም የለባቸውም። በይበልጥም ስንጀምረው።
ማወቅ ያለብን አምላክ የሰውን ልጅ ሲፈጥር እስከነፃነቱ እንዲሆን አልሞ ነው። ሲፈጥረው ባስፈለገው ጊዜ አፈጣጠሩን በሙሉ ነፃነቱን ማስጠበቂያ አድርጎ እንዲጠቀምበት ነው። ሀሰት የሚል ካለ ይህንን አፈጣጠሩን ነፃነቱንና መብቱን ማስከበርያ አድርጎ ሊጠቀምበት አይችልም ይበል። እኛም ኢትዬጵያዊያን ሰዎች ነን። የሰው ልጅ እንደመሆናችን ስሜታችንን ፤ አካላዊ እንቅስቅሴያችንን፤ ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ አካላችንን ፤ድርጊታችንን፤ አኗኗራችንን፤ የማሰብ ችሎታችንን፤ ፍላጎችንን፤ድምፃችንን ብቻ ሁለንተናዊ አፈጣጠራችንን መጠቀሙን እናውቅበታለን አናውቅበትም ነው እንጂ ጉልበታሞችን ልክ ማስገቢያ ካምላክ የተሰጠ ሀይላችን ነው።
Sunday, March 8, 2015
የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለአራተኛ ጊዜ በሚዲያ እንዳይተላለፍ ተከለከለ
• ኢቢሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አላስተላልፍም›› ብሎ መልሷል
• ‹‹ኢቢሲ ከገዥው ፓርቲ ጋር ወግኗል›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አላስተላልፍም›› ብሎ መመለሱን ዛሬ የካቲት 29/2007 ዓ.ም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ ኢቢሲ በደብዳቤው ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በምስሉ ግርጌ የተቀመጠው እንዲሁም በቅስቀሳ መልዕክታችሁ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚታየው ሰንደቅ አላማ ምስል የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ የማይወክልና ህገ መንግስቱን…. የሚፃረር ሆኖ አግኝተነዋል›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡
ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
ክንፉ አሰፋ
አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ። መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት።
“ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው። ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!”
አይቴ ቴድሮስ በፌስ ቡክ ገጻቸው የለቀቁት መልእክት ይህ አልነበረም። ይህ አሸባሪዎች በርዘው የለቀቁት እንጂ፣ የዶ/ር ቴድሮስ ትክክለኛው መልእክት እንዲህ ይነበባል።
“ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጅቷን ባንጐዳ፡፡ ያሰበችው ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው፡፡ አሁን ዋናው ጉዳይ በሪቱ ጃለታ አሕመድ ህልሟን እንድታሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው፡፡ Galatoomaa በሪቱ፡፡ አላህ ይባርክሽ፡፡ Rabbi si haaeebbisu በርቺ፡፡ Jabaadhuu”

ሚኒስቴሩ መልስ ሰጡ! የቴድሮስ አድሃኖም የ20 ሚሊዮን ዶላር ፕሮፓጋንዳ
ኤርትራ ተወልዶ ያደገውና በአሁኑ ወቅት በችሎታው ሳይሆን በዘሩ እና በወያኔነቱ ተመርጦ “የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር” ለመሆን የበቃው ቴድሮስ አድሃኖም ሰሞኑን የተለመደ ወያኔዊ ፕሮፓጋንዳ ሰርቶ ሲያራግብ ከርሟል። ይሁንና የዚህኛው ፕሮፓጋንዳ ታሪክ የሚጀምረው ወያኔዎች ከማይቆጣጠሩት ሩቅ ሃገር (አውስትራሊያ) በመሆኑ የፕሮፓጋንዳው ታሪክ ሃሰት እንደሆነ ለማወቅ ጊዜ አልፈጀም።
የታሪኩ ምንጭ የሆነችው ታዳጊ በሪቱ ጃለታ አሕመድ በሃገረ አውስትራሊያ በምትማርበት ትምህርት ቤት በተካሄደ ውድድር በማሸነፏ የተሸለመችውን 20 ሚሊዮን ዶላር ይዛ ኢትዮጵያ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን ልትገነባ (ኢንቬስት) ልታደርግ ገስግሳ መጥታለች በማለት ነበር አይተ ቴድሮስ አድሃኖም በፌስቡካቸውና በቴሌቪዥናቸው የፕሮፓጋንዳ ዜናቸውን ያሰራጩት።
ጋዜጠኛ አበበ ገላው፣ ኢሳት እና ነዋሪነታቸው በአውስትራሊያ የሆነ ኢትዮጵያውያን ጉዳዩን ለማጣራት ባደረጉት ሙከራ እንደተረዱት ከሆነ ያን ያህል ገንዘብ ለአንዲት ታዳጊ ወጣት በሽልማት መልክ የሰጠ የአውስትራሊያ ተቋም አልተገኘም።

Saturday, March 7, 2015
ምርጫ እና ምርጫ በ2007!
ዕጣ! ጣጣ! . . . የምር ይውጣ
ምርጫ 2007ን ከሌሎች ምርጫዎች ሁሉ ልዩ የሚደርገው ምርጫ ቦርድ ከምርጫው በፊት ፓርቲዎችን (ተፎካካሪ) በማፍረስ ጀምሮ የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎችን (ከ200 በላይ) አልመዘግብም ማለቱ እና በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል ደግሞ ወደ ምርጫው ለመግባት ተወዳዳሪው በዕጣ መለየት አለበት ማለቱ ነው፡፡ ዕጣው ደግሞ ለሁሉም ፓርቲዎች ሳይሆን ሰማያዊን ጨምሮ ጥቂቶች ላይ የተደረገ ነው፡፡ ይኸውም በማፍረስ እና በመከልከል ተጀምሮ ”ምርጫ በሎተሪ” መሆኑ ነው፡፡
Friday, March 6, 2015
ተዋቂው ጋዜጠኛ አለምንህ ዋሴ የህዝቡን ትግል ተቀላቀለ !
ጋዜጠኛው በኢትዮጵያዊነቱ አያሌ በደሎች እንደ ተፈጸሙበት ያወጋል ! በተለይ ይላል ጋዚጠኛ አለምነህ ዋሴ ፍትህ እኩልነት በሌለባት ሃገሬ ጋዜጠኛ ርዩት ዓለሙ ላይ የተፈፀመው ኢሰባዊ ድርጊት ከሁሉም በላይ ከህሊናው ሊጠፋ የማይችል ዘግናኝና አረምኔያዊ ድርጊት መሆኑን ይገልጻል ። ጋዜጠኛው ልጆቹን ከማሳደግ ባሻገር ሃገሩ ላይ ሲኖር ደስተኛ እንዳ ልነበረ በመጥቀስ ክእንግዲ አለ ጋዜጠኛ አለምንህ ዋሴ « ፍትህ እኩልነትና ነጻነት እስኪሰፍን » ሃገር አለኝ ብዬ ፊቴን ወደ ኢትዮጵያ አልዞርም ብሏል ። ጋዜጠኛው ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጀት ገለልተኛ ሆኖ ወገኑን ማገልገል እንዳልቻለና የገዢው ስረአት ወሬ… አቀባይ ሳይሆኑ ገለልተኛ ሆኖ በነጻነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሰርቶ መኖር ለህልውና አደገኛ መሆኑን የራሱን ተሞክሮ በመጥቀስ ያብራራል። በስራው ላይ ይደረግበት በነበረ ጫና የማስታወቂያ ስራዎቹ ለአየር እንዳይበቁ በደል እስከመፈጸምና በሙያው በቀን 10 በር ብቻ ተከፍሎት እንዲሰራ የተገደደበት አጋጣሚ እንደነበረ ለኢሳት በሰጠው መረጃ አጋልጦል።
የአድዋ ድልን እያከበርን ለዛሬ ነፃነታች ቃል እንግባ!
መቶ አስራ ዘጠነኛውን የአድዋ ድል በዓል እየዘከርን እንገኛለን። እንደዛሬው ሁሉ ያኔም ቀደምቶቻችን በርካታ የውስጥና የውጭ ችግሮች ነበሩባቸው። እንደዛሬው ሁሉ ያኔም በመካከላቸው የሀሳብና የጥቅም ልዩነቶች ነበሩ። ያም ሆኖ ግን ቀደምቶቻችን በአገር ነፃነት ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ መግባባት ላይ መድረስ በመቻላቸው በዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችና ድርጅት የተጠናከረውን የአውሮፓ ጦር በጥቁር የጦር አዛዦችና ተዋጊዎች መመከት ቻሉ። ከአድዋ በፊት አፍሪቃ በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ አውሮፓዊያን የተሸነፉባቸው ተናጠል አውደ ውጊያዎች ነበሩ፤ ጦርነትን ሲሸነፉ ግን አድዋ የመጀሪያው ነው። በዚህም ምክንያት ነው የአድዋ ድል የአፍሪቃውያን ከዚያም አልፎ የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ድል ተደርጎ የሚወሰደው።
ዛሬ ግን እኛ ያኔ የነበሩት አያትና ቅድመ አያቶቻችን እደረሱበት የመግባባት ደረጃ ላይ መድረስ ባለመቻላችን አገር በቀሉን ቅኝ ገዢ – ህወሓትን – ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ ላይ ማውረድ አቅቶን አገራችንና ሕዝቧን ከባዕድ በባሰ ሁኔታ እያዋረደ በመግዛት ላይ ይገኛል።ያኔ ለሀገሩ፣ ለነፃነቱና ለክብሩ ቀናዒ የሆነው ኢትዮጵያዊ ራሱን ወታደር አድርጎ በየጎበዝ አለቃው አዝማችነት በጠላት ላይ ዘምቶ ድልን ተቀዳጅቷል። ዛሬ ግን ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ የመከላከያ ሠራዊት አባል ለህወሓት አዛዦች ሎሌነት አድሮ የራሱን ወገን ይፈጃል። ያኔ በአገዛዙ ላይ ብሶት የነበረው እንኳን ሳይቀር ብሶቱን ችሎ ለሀገር ሉዓላውነትና ክብር ሲል ተዋድቋል። ዛሬ ግን ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ወገኖቻችን የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ከብሶቶቻቸው በላይ አሻግረው መመልከት ተስኗቸዋል።
Wednesday, March 4, 2015
ለኢትዮጵያ መብትን፣ ክብርን እና ነጻነትን የሚያጎናጽፍ ሰነድ? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የእንግሊዝ ህዝብ መሰረታዊ ህገ መንግስት 800ኛ ዓመት በዓል በማክበር ላይ እገኛለሁ
እንዴት!?
አንዴ በጅ በሉኝ! ጥያቄአችሁን ተገንዝቤዋለሁ!
በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ሀገር የሚኖር አንድ በአፍሪካ ያውም በኢትዮጵያ የተወለደ ሰው በመካከለኛው ዘመን ከ800 ዓመታት በፊት በእንግሊዝ ሀገር ያመፁ ባለጉልት ባላባቶችና በነጉሳቸው መካከል በተደረገው የስልጣንና የግል ጥቅም ትግልና ስምምነት ለምንድነው የሚያከብረው? ስለነሱ መብትና ነፃነት ምን ግድ አገባው?
ብላቸሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ።
ብላቸሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ።
የፊውዳል ወይም ደግሞ የንጉሳውያንን ስርዓት በፍጹም አልወድም፡፡ ተወልጀ ያደግሁት በፊውዳሏ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ የፊውዳሉን ስርዓት አስከፊነት፣ ስብዕና የለሽነት እና የበሰበሰ መሆኑን በሚገባ አይቸዋለሁ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት የመንግስት ዓይነት ንጉሳዊ የመንግስት ስርዓት ነበር፡፡
Tuesday, March 3, 2015
ወሬ ሲነግሩህ ሃሳብ ጨምርበት
(በእውቀቱ ስዩም)
ምኒልክ ጥቁረቱን ክዶ ነበር የሚል ቀደዳ በፌስቡክ ሲዞር ኣየሁ ልበል?
ትልልቅ ቅጥፈቶች ጀርባ ኣንድ ትንሽ መነሻ ይኖራል፡፡
መነሻውን እንመርምር እስቲ፡፡
ያድዋ ድል ማግስት የምኒልክ ዝና የጠራቸው የውጭ ኣገር ሰዎች ኢትዮጵያን መጎብኘት ጀምረው ነበር፡፡ ከኒህ እንግዶች ኣንዱ የሄቲው ታጋይ ጋዜጠኛ ቤኒቶ ሲልቪያን ነው፡፡
ሲልቪያንና ምኒልክ ያደረጉትን ጭውውት ስኪነር የተባለ ኣሜሪካዊ ዘግቦታል፡፡
በጭውውታቸው መሀል ምኒልክ ለሄቲው ሰውየ I am not a Negro I am a Caucasian ማለቱን ስኪነር ዘግቧል፡፡
ምኒልክ ኔግሮ ኣይደለሁም ብለው ከሆነ ደግ ኣደረጉ ከማለት ውጭ የምለው የለኝም፡፡ ምኒልክ ጥቁር እንጂ ኔግሮ ኣይደለም።ኔግሮ የውርደት ስም ሲሆን ጥቁር የክብር ስም ነው፡፡
ኮኬሽያን የሚለው ቃል ግን ያስተርጓሚ ስተት መሆን ኣለበት፡፡በምኒልክ ዘመን ሰዎች ዘርን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው ቃላት ከብሉይና ሃዲስ የተቀዱ ናቸው፡፡ የሴም ዘር የካም ዘር የያፌት ዘር ወዘተ ይሰኛሉ፡፡ ኮኬሽያን የሚለው ቃል በወዘተ ውስጥ ኣይካተትም፡፡ ኮኬሽያን በጊዜው በሊቃውንቱም ሆነ በመኳንንቱ ኣንደበት የሚዘወተር ቃል ኣልነበረም፡፡
ምርጫ በኢትዮጵያ ምን ይመስላል?
ገለታው ዘለቀ
በሃገራችን ታሪክ ውስጥ ብሄራዊ ምርጫ የተጀመረው እንደ ኣውሮፓውያን ኣቆጣጠር በ1957 በዓጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ሲሆን በ1955 የወጣውን ህገ -መንግስት መሰረት ያደረገ ንጉሱንና የላይኛውን ቤት ወይም ሴነቱን የማይመለከት ነገር ግን የተወካዮች ምክር ቤት ኣባላትን መምረጥ ተጀምሮ ነበር። እማኞች ሲነግሩን ምርጫውና ቆጠራው ግን ሃቀኛ ነበር ኣሉ። ታዲያ ንጉሱ በነበሩበት ዘመን የነበሩት ምርጫዎች ጅማሪያቸው መልካም ቢሆንም ዓለም በማህበራዊ ለውጥ ላይ በነበረችበት በመጨረሻው ሰዓት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ ህገ-መንግስታዊ ሞናርኪ ቀይሮ የፖለቲካውን ስልጣንና የህዝቡን ተሳትፎ ማስፋት ስላልተቻለ ወታደራዊ ደርግ ኣብዮቱን ኣንግቦ ብቅ ኣለ።
ደርግ ወታደራዊ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ የሶሻሊዝም ርእዮት ተከታይ ነኝ በማለቱ በየማህበራቱ የሚደረጉት ምርጫዎች ሁሉ ከዚያው ከኣንድ ምንጭ የሚቀዱትን የሶሻሊዝም ጓዶች መምረጥ ሆነ ምርጫ ማለት። ደርግ ኣብዩቱ ማለት ሞቱ ነበር።

Monday, March 2, 2015
የ119ኛው የአድዋ ድል በዓል በኖርዌይ በርገን ከተማ ቅዳሜ መጋቢት 19.2007 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተከበረ
በኢትዮጵያ ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ለዲሞክራሲ ፣ ለፍትህ እና ለነጻነት ለሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርጫፍ ጽ/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት የ 119ኛው የአድዋ ድል በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከበረ ፡፡
በዕለቱ የአድዋን በዓል ታሪካዊነት በዝርዝር የሚያስረዳ እና የአብዛኛውን ታዳሚ ቀልብ የሳበ ታሪካዊ ትንታኔ የቀረበ ሲሆን የአድዋን ድል የሚገልጹ ጽሑፎች ግጥም እና “የሚኒሊክ ወቀሳ” በሚል ርዕስ ድራማ ቀርቦ ታላቅ አድናቆትን አትርፏል፡ አሁን ሀገራችን ኢትዮጵያ ና ህዝቦቿ ለ23 አመታት በወያኔ ስርአት እየደረሰባቸው የሚገኘውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፣እስር ፣ ግድያና ዝርፊያ የሚገልጽ በራሪ ወረቀት ለኖርዌጂያን ማህበረሰብ ታድሏል ፡

ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ
የአውስትራሊያ መንግስት እና የሮተሪ ፋውንዴሽን በሪቱ ጃለታን አናውቃትም ገንዘብም አልሰጠንም አሉ
በአበበ ገላው [PDF]
(አዲስ ቮይስ) ሰሞኑን የህወሃት መራሹ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአንድ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ውድድር አሸናፊ በመሆን እና አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በማሸነፍ ያገኘችውን ገንዘብ ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ትገኛለች የተባለችን የ14 አመት ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገጾች ከማስተዋወቅ አልፈው በቢሯቸው ከልጅቷ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
ሚኒስትሩ በሪቱ ጃለታ አህመድ ገና በለጋ እድሜዋ ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለልማት በማዋሏ ለኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዲያስፖራው አርአያ መሆኗን በይፋ አውጀው ነበር። ወጣቷ የሽልማት ገንዘቡን በሙሉ አባቷ አቶ ጃለታ አህመድ በተወለዱበት በምስራቅ ሀረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ትምህርት ቤት ልታሰራበት ማቀዷን ለጋዜጠኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝታ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገች ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ከፊሉ ከአውስትራሊያ መንግስት፣ ከፊሉ ደግሞ ከአውስትራሊያ የሮተሪ ክለብ መሆኑን ይፋ አድርጋ ነበር።
Subscribe to:
Posts (Atom)