ወይንሸት ሞላ የሰማያዊ ፓርቲ አባል እና የወጣቶች ጉዳይ ውስጥ አመራር ላይ ካሉት ሃላፊዎች አንዷ ነች። ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ሲገልጻት ”ቀጭን እና ጠንካራ” ይላታል። ይቺ ልጅ አርብ እለት (ጁምዓ) በአንዋር መስጊድ ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶቻችን ሰላማዊ ጸሎት ለአላህ፤ እና ሰላማዊ ተቃውሞ ለመንግስት በሚያሰሙ ጊዜ የመንግስት ታጣቂዎች ያገኙትን መደብደብ እና ማፈስ ሲጀመሩ ወይ ጉዳዩን ለመታዘብ ስትበር በቦታው ተገኝታ፤ አልያም በአጋጣሚ በአንዋር መስጊድ አካባቢ ስታልፍ ብቻ ለጊዜው ለዚህ ዜና ጸሀፊ ግልጽ ባልሆነ አጋጣሚ አንዋር መስጊድ አካባቢ ከዚህ በፊት ይከታተላት የነበረ ደህነነት አያት፤ ከዛም ለቀም አድርጎ እየደበደበ ከፖሊሶች ጋር ተባብሮ ወሰዳት። ከዛም ማንም የርሷ ወገን ባልተገኘበት ፍርድ ቤት አቀረቧት፤ ይቺ ቀጭን ወጣት እና ጠንካራ ፖለቲከኛ ዳግም ለሐሙስ ሐምሌ 16 ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኝ ፍርድ ቤት ትቀርባለች።
ሌላ ሀምሌ አስራ አንድ የመንግስት ታጣቂዎች በሰላማዊው ጸሎተኛ እና ሰላማዊ ተቃዋሚ ህዝብ ላይ ያደረሱት ድበደባ አፈሳ እና ማሰቃየት ”ጥቁር ሽብር” የሚል ስያሜ እንደተሰጠው የድምጻችን ይሰማ ልጆች ነግረውኛል።
ሌላ ቅድም ያልኳችሁ የመሬ ነገር የምር መሆኑን ከመሬ አረጋግጠውልኛል። መሬ እምቢኝ ብሏል! (የከፋ ጉዳት ተወዳጇ መሬ ላይ እንዳይደርስ መጸለይ አትርሱ!) ኢህአዴግ ሰው ብትሆን ይሄ አይነቱ ነገር ሲገጥማት ጦሯን ወደ መሬ ከማዝመቷ በፊት ለሚ ላይ ቁጭ አድርጌ ብመክራት ደስ ይለኝ ነበር። ህዝብ ካመረረ ጥይት ሳይሆን ጸሎት ነው መፍትሄው እላት ነበር። ችገሩ ኢህአዴግ ሰው አይደለችም ግንባር ነች እንጂ… ለዛውም ቴስታ ካልተማታ የሚታመም ግንባር!
No comments:
Post a Comment