Translate

Thursday, January 30, 2014

“ታሪክ ለባለ ታሪኩ”

ገብረመድህን አርአያ፣ አውስትራሊያ

Ato Gebremedhin Araya is one of former Tigray People Liberation Front (TPLF) leaders
አቶ ገብረመድህን አርአያ የቀድሞ የሀወሀት ገንዘብ ያዥ
ኢትዮጵያ ሃገራችን ትልቁ እድሏ ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ የታሪክ ሊቃውንትና ጸሓፍት ያፈራች ሃገር መሆኗ ነው።

ህወሓት የፈሪዎችና የጨካኞች ስብሰብ መሆኑ አውቅ ነበረ::(አብርሃ ደስታ )

በሌሎች ላይ የምትፈፅሙት ተግባር ሁሉ በራሳቹ ላይ እንደምትፈፅሙ (እንደሚፈፀም) አስቡ። በስልጣን ላይ ያለ ሁሉ በስልጣን አይኖርም። የስልጣን ዕድምያቹ በጣም አጪር መሆኑ እናንተም ታውቁታላቹ። በሰዎች ላይ ግፍ ስትፈፅሙ ሰዎች ይጠሏችኋል። በሰዎች ስትጠሉ የስልጣን ዕድምያቹ ያጥራል። እናንተ ያላቹ የህዝብ ድጋፍ ሳይሆን ጠመንጃ ነው። ጠመንጃ ስልጣን ለመያዝ ይረዳ እንደሆነ እንጂ በስልጣን ለመቆየት አያስችልም። ስለዚህ በጠመንጃ አፈሙዝ የስልጣን ዕድምያቹ ለማራዘም የምታደርጉት ጥረት ከንቱ ልፋት ነው። እናንተ ከስልጣን ወርዳቹ ስልጣን የህዝብ ሲሆን፣ ፍትሕ ሲነግስ፣ እኩልነት ሲሰፍን ለፈፀማችሁት ወንጀልና ላደረሳችሁት በደል በሕግ እንደምትጠየቁ አያጠራጥርም። በስልጣን የኖረ የለም። እንኳን አምባገነኖች ዴሞክራሲያዊ ስርዓቶችም በስልጣን ኮረቻ ተቀምጠው ለዘላለም አይኖሩም።

ወያኔን ያሸበረው የግንቦት 7 መንገድ ምንድነው?


የትግራይን ሕዝብ ከብሄር ጭቆና ነጻ አወጣለሁ በሚል ጠባብ ዓላማ ተደራጅቶና ታጥቆ ለበትረ ሥልጣን የበቃው ህወሃት ወይም ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከተቆጣጠረ 23 አመት ሊሞላው እነሆ ጥቂት ወራቶች ብቻ ቀርተውታል።
ለጋራ ቤታችን ለሆነቺው አገራችን ኢትዮጵያና በአስተዳደር በደል ለከፋ ድህነት ለተዳረገው መላው ሕዝቦቿ የሚሆን አንዳችም ራዕይ ሳይኖረው ለመንግሥትነት ሥልጣን የበቃው ይህ ቡድን ላለፉት 23 ዓመታት ከግል ኑሮአቸው አሻግረው የአገርንና የወገንን ጥቅም ማየት የማይችሉ ወይም የማይፈልጉትን በዙሪያው አሰባስቦ እያካሄደ ካለው ዘርፈ ብዙ የሃብት ምዝበራ ወንጀል በተጨማሪ እየፈጸመ ያለው የመብት ጥሰትና አፈና ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።
ሰሞኑን እያፈተለኩ በመውጣት ላይ ከሚገኙ ምስጥራዊ የድምጽ መረጃዎች ለማረጋገጥ እንደተቻለው ደግሞ ለጥቂቶች የሃብትና የብልጽግና ምንጭ የሆነው ሥልጣን ከእጃቸው እንዳይወጣ በአንድ በኩል በምርጫ ስም እንዴት አድርገው ሕዝቡን ቀፍድደው የምርጫው ተሳታፊ ማድረግ እንደሚችሉ ሲዶልቱና በሌላ በኩል ደግሞ በቁጥጥራቸው ሥር የሌሉትንና ለሥልጣናቸው ያሰጉናል ያሉዋቸውን የደሃዉን ልጅ በማጋፈጥ እንዴት በጦርነት እንደሚጨፈልቁዋቸው ሲመክሩ ተሰምተዋል።

የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ

ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

coup map


በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት ሊከሰቱ የሚችሉ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋዎች ይፋ ሆኑ፡፡ በርካታዎቹ በአፍሪካ አገራት ሲሆኑ አደጋው ካንዣበበባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

“ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው የውጭ ገበሬዎች የሚያስፈልጓቸው? ምንድን ነው ይዘውልን የሚመጡት?” አቶ ግርማ

"አንድም ሰው ከቀዬው እንዲፈናቀል አልተደረገም" ሚኒስትር ዴኤታ

displaced anuaks


  • “ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንቶች እንደታሰቡት ውጤታማ አልሆኑም” መንግሥት
  • መንግሥት የውጭ ባለሀብቶች የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያን አይመለከትም አለ
የውጭ ባለሀብቶች በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወስደው እያለሙ እንጂ፣ መሬት ለመቀራመት ብለው ወደ ኢትዮጵያ አልገቡም ሲል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

Wednesday, January 29, 2014

መንግስታት ፈለጉት ኣልፈለጉት በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ለወደፊት ትውልዶች የሚቀጥል የመዋሃድ ዝምድና መኖር ኣለበት” ኢሳያስ ኣፈወርቂ


ኣቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ
ከኣሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ ያማርኛው ክፍል
ከጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ
ጋዜጠኛ ኣዲሱ ኣበበ፥ እየተገባደደ የነበረውን የኣውሮጳውያን የ1992 ዓ.ም. ምክንያት በማድረግ በተገባደደው ዓመት
ከተከስቱ ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹን ሲያስተናግድ፤ “1993 ዓ.ም. ላይ ደርሰናል፤ እንደ ኣውሮጳ ኣቆጣጠር። ኣቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ስለ
ኤርትራ ሬፈረንደም፥ ማለትም ህዝበ ውሳኔ፥ ይህን ብለው ነበር።” በሚል
መክፈቻ የስራ ባልደረባው የሆነቺው ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኣፈወርቂ ጋር ቀደም ሲል በድምፅ ያደረገችውን ቃለመጠይቅ ይለቃል። ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ፤ በግዴታም ይሁን በውዴታ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ተሳስስራ ቆይታለች። እና፥ እንግዲህ፥ የነፃነት ጥያቄ፥ የመገንጠል ጥያቄ ከማን? የሚለው [መልሱ] ከኢትዮጵያ ነው። እንግዲህ፥ [ኤርትራ] ከኢትዮጵያ ጋር ተሳስራ ስለቆየች። እና፥ ይህ የሬፈረንደሙ ነጥብ ራሱ ምንድንነው የሚለው፤ “ነፃነት ትፈልጋለህ? ኣዎን ወይም ኣይደለም” ዓይነት ነው። እና፥ ለምንድነው እንደዛ የጠበበው? ትንሽ ሰፋ ብሎ ወይም ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ኣንድነት ወይም ኮንፌደረሽን ወይም ፌደረሽን ወይም ሰፋ ያለ የራስ ገዝ ኣስተዳደር ወይንስ ነፃነት ነው የምትመርጠው? በሚል ሰፋ ባለ ይዘት ለምን ኣልቀረበም?

US House Appropriation Bill Requires Increased Accountability from Ethiopia as Prerequisite for Funding

SMNE's PRESS RELEASE

yinegalIs United States policy towards Ethiopia shifting? For years Ethiopians, social justice groups, human rights organizations and civic groups have been calling on donor countries to demand greater accountability from the Government of Ethiopia for funds received, citing the lack of political space, endemic injustice, the repression of basic freedoms and widespread human rights crimes; however, now, the people of Ethiopia

እስክንድር ነጋ የ2014 የነጻነት ወርቅ ብዕር ተሸላሚ ሆነ

Golden Pen of Freedom

የዓለም የጋዜጦችና ዜና አታሚዎች ማኅበር (WAN-IFRA) የ2014 የነጻነት ወርቅ ብዕር ሽልማቱን ለኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛና አሳታሚ እስክንድር ነጋ እንዲሰጥ መወሰኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቆዋል:: ህወሃት/ኢህአዴግ “የጸረ ሽብር ሕግ” በማለት ባወጣው አዋጅ ሰበብ እስክንድር ነጋ 18 ዓመት እንዲታሰር የተበየነበት መሆኑን መግለጫው ጨምሮ ገልጾዋል::

የታመቀው የኢትዮጵያውያን ምሬት፡ የሕይወት ማሽቆልቆልና በፍርሃት መሽማቀቅ አፋጣኝ መፍትሄ ይሻል

ኢትዮጵያ በሕወሃት ዘመነ አመራር የታወቀችባቸው ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ብዙ “እንዴ!”የሚይሰኙ ጥሩ አሳቦችም ፈልቀዋል – አፈጻጸማቸው እትይለሌ ቢሆንም። ከነዚህም መካከል መሠረተ ልማት፡ በጤናና በትምህርት መስኮች መሻሻሎች መታየታቸው ወዘተ መልካም ይነገርላቸዋል – የቢል ጌትስን የራስ ተጠቃሚነትና ኢምፓየር ግንባታ ወደጎን ትተን! በዕጦት ደረጃም በሀገራችን የስብዓዊ መብቶች አለመክበር፣ የፍትህ አለመኖርና ለአብዛኛው ሕዝባችን የምግብ ዕጦት ዋና ዋና ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው።

Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
ለምሳሌም ያህል፡ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 30 ስላማዊ ስልፍ የማድረግንና መንግስትን መቃወምን ግልጽ ቢያደርግም፡ እሁድ ዕለት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ለመሰጠት ለመቃወም: ለሚመለተው አሳውቀው ስላማዊ ስልፍ ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ ሲሉ የአዘጋጁ የስማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ጎንደር ውስጥ ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ መንገድ ትግራይ ውስጥም የአረና አመራሮች ሕዝቡን ቀሰቀሳችሁ በሚል ውንጀላ አዲግራት ውስጥ አመራሩና አባሎቹ ክፉኛ ተደብድበዋል – ጉዳት የደረሰባቸውም ሕክምና ለመሻት ተገደዋል። ይህንኑ አስመልክቶ፡ አንዱ ተደብዳቢ መምህር አብርሃ ደስታ የሚከተለውን ጽፏል፡

ኳሱ በማን እጅ ነው? (ይድነቃቸው ከበደ)


Ethiopian political commentator from Addis Ababa, Ethiopia. Ydnekachew Kebede
ይድነቃቸው ከበደ
ከአምስት ወር በፊት የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የአዲስ ዓመት የሥራ ዘመን መጀመር አስመልክቶ በጋራ ባአካሂዱት ጉባዔ አዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመም ፕሬዚዳንታዊ የመክፈቻ ንግግር ማድረገቸው የሚታወቅ ነው፡፡ የፕሬዚዳንቱ የንግግር  ይዘት መንግሥት በ2006 ዓ.ም. ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባሮች ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡፡ይሁን እንጂ የፕሬዚዳንቱ ንግግር በሕግ መንግስቱ በተሰጣቸው ሥልጣንና ተግብር መሠረት የተደረገ ንግግር ስለመሆኑ የሚያመላክት አንዳችም ነገር አላየሁበትም፤በመሆኑም የፕሬዚዳንቱ ንግግር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢነገር የተሸለ ይሆን ነበር ግን በሁለቱም ቢነገር ውጤቱ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ባቀረቡት የመክፈቻ ንግግር ላይ ሊካተቱ የሚገባቸው ነገር ግን ያልተካተቱ፣ እንዲሁም መካተት አልነበረባቸውም ያሏቸውን በመለየት አቶ ግርማ ሰይፉ ጥያቄና አስታየት አቀርበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም  ደሳለኝ በምክር ቤቱ በመገኘት በአቶ ግርማ ነጥቦች ዙሪያ ምልሽ መስጠታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ይሁን እንጂ ምላሻቸው ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ ስኬታማ አልነበረም ለዚህም ዋንኛው ምክንያት የመንግስት የአስተዳደር ብሉሹነት ነው ፡፡

ጌዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው? (ቁጥር ሁለት)

አለማየሁ መሰለ

ውድ አንባብያን፣ ይህ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር ተስፋዬ ገብረአብን አስመልክቶ አወጥተን ከነበረው ሪፖርት ጽሁፍ ተከታይ ነው። በዚህ መሰረት ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር አብረን ስንኖር እጄ ላይ ከወደቁትን መረጃዎች መሃከል የመጀመሪያው ጽሁፍ ተከታይ ይሆናል ብዬ የመረጥኳቸውን ቃል በገባሁት መሰረት ከነማብራሪያቸው አቀርባለሁ።
Tesfaye Gebreab Ethiopian author and writer
ተስፋዬ ገብረአብ
ለዛሬ የማቀርበው መረጃ ተስፋዬ ገብረአብ እንደ ሸፋን ከሚጠቀምበት የደራሲነት እና የጋዜጠኘነት ስራ ባሻገር ለማመን በሚያዳግት ይሰራ የነበረውን የወንጀል ድርጊት ፍንትው አድርጎ ያሳያል።
ከዚህ በታች አባሪ ተደርጎ የተያያዘው በእጅ የተጻፈ መረጃ፣በእጄ ላይ ካሉ መረጃዎች መሃከል ትኩረቴን የሳበው ነው።እንደምትመለከቱት በራሱ በተስፋዬ ገብረአብ እጅ የተጻፈ ነው።

Tuesday, January 28, 2014

በእውነት ወያኔ የተረከበው የፈራረሰ አየርሃይል ነበርን? አየር ሃይልስ እንዴት ተያዘ?

ፋንታ በላይ

MiG-23 Flogger Tactical Fighter
MiG-23 Flogger Tactical Fighter Jet
የስነ ስሁፍ ሰው አይደለሁም:: ይህንን ስሁፍ እንድጽፍ ያስገደደኝ ግን በኢትዮጳያ ቴሌቪዝን አየር ሃይልን በተመለከተ የተላለፈው ዜና ነው:: በዚሁ ዜና ላይ ያሁኑ አየር ሃይል ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ ኮሎኔል አስፋው ማመጫ በ 1983 ሰለነበረው አየር ሃይል ሲያስረዱ ” በ1983 የተረከብነው የደከመ የፈራረሰና የወደቀ አየር ሃይል ነበር” [i] በማለት እጅግ አስቂኝና ከውነት የራቀ መግለጫ ሰተዋል:: አዲሱ ትውልድ ስለቀደመው አየር ሃይል እውነት ጥቂትም ቢሆን ያውቅ ዘንድና አየር ሃይሉ ምን ይመስል እንደነበር እንዴትስ እጅ እንደሰጠ በጥቂቱ ልጽፍ ወደድኩ::

በልቡ የሸፈተ ህዝብ የካድሬዎች ጋጋታና ሽብር አይገታውም

በዲያስፖራ የአረና ትግራይ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ሰሞኑሰሞኑን በትግራይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ከየመንደሩ የተውጣጡ ነብሰ ገዳይ፣ ስብሰባ በታኝና አፋኝ የዱሪየ ቡድኖችን በተለያየ መልኩ በማደራጀት በአረና ትግራይ አባላትና አመራር ላይ የከፈቱትን አዲስ የመንጥርና የድብደባ ዘመቻን አስመልክቶ

ህወሓት/ኢሕአዴግ በትረ ስልጣኑን ከተጎናፀፈና ካደላደለ ወዲህ ከሱ የተለየ አመለካከትና ሃሳብ ያላቸው ወገኖች ሁሉ የተለያዩ ቀለማ ቀለሞችን በመቅባት፣ የፈጠራ ስም በመለጠፍና ሰበብ አስባብ በመፈለግ በቀጥታም ሆነ በረቀቀ መንገድ የመመንጠር፣ የማፅዳት፣ የመሰወር፣ የማሰር፣ የመግደልና እርስ በርስ የማናቆር ስራ ዋነኛ የስርዓቱን ባህርይ መገለጫ ሆኖ መቆየቱ እሙን ነው። የእርምጃው ዋናው ምክንያትም እውነት ተቃዋሚዎቹ የሀገርና የህዝብ ጠላቶች ስለሆኑ አይደለም። ነገር ግን ጥያቄያቸው “ስለ ሀገራችንና ህዝባችን ጉዳይ እኛም ያገባናል!! አባቶቻችን ደም ከፍለው ያቆዩልንን ሀገር የመጠበቅ የኛም ግዴታ ነው!! ዘላቂ ልማትና ዕድገት የሚመጣው እውነተኛ ዲሞክራሲ፣ የሕግ ልዕልና፣ ፍትሕ፣ ነፃነት፣ ሰላምና አንድነት ሲረጋገጥ እንጂ በጡንቻ አይደለም!! ሕገ መንግስቱ የሰጠንን የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀት፣ የመንቀሳቀስ፣ የእምነት፣ የመምረጥና የመመረጥ ነፃነታችንን ይከበር!!” ብለው ሰላማዊና ሕጋዊ መንገድን ተከትለው በቆራጥነት ስለተንቀሳቀሱና ስለጠየቁ ብቻ መሆኑን ማንም ቅን ህሊና ያለው ኢትዮጵያዊ ሊገነዘበው የሚችል ጉዳይ ነው።

ከቀይ ወደ ሰማያዊ ጉዞ

ቹቸቤ

Ethiopia’s Blue party (Semayawi party) leaders in police controlከቀለማት ሁሉ ‘ቀይ’ አገራችንን አቅልሞ መዶሻው ቁልቁል ሲወቅረን ማጭዱ ከታች ሲያጭደን ኖረን ያለቀው አልቆ የተረፍነው ፈዘንና ደክመን ባለንበት ሰዐት ማጭዱንና መዶሻውን በብጫ ቀለም  ሸፍነው በትግራይ ስም አጨዳውን የቀጠሉበትና ቀን የሰጣቸው ጎጠኞች አገርም ሕዝብም ሊያጠፉ እንደገና በወገን ደም እያጨቀዩን ይገኛሉ። ቢሆንም ተስፋችን አላሟጠጠም። ብርቱዎች ቆርጠውና ቀልጥፈው ለነጻነት የሚደረገውን ትግል በሁሉም መስክ አፋፍመዋል። አዲስ የሆነው ነገር ከቀይና ነጭ ሽብር በሁዋላ ሰማያዊ ሰላማዊ ትግል የሚል መፈጠሩ ነው። ታሪክ ያልዘገባቸው ግን ከቀይ ሽብር ወደ ብጫ ስካር በሚል ጠጅ ቤት የቀሩ የአብዮት ትራፊ ወጣቶችን ህይወት ነው።

Monday, January 27, 2014

“ ሰው ጥሩ” ( አርአያ ተስፋማሪያም)

አሜሪካ መኖር ከጀመረ 16 አመት አለፈው። ለፍቅር ሲል ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈለ ታዋቂ አርቲስት ነው። እጅግ ለሚያፈቅራት ልጅ አቀንቅኖላታል። ይህ ድምፃዊ፥ አበበ ተካ ነው። “ሰው ጥሩ..” የሚለው የግጥም ድርሰት በህልሙ ነበር የታየው። ፍቅረኛው እታገኝ ሙላው ትባላለች።

አቤ በህልሙ “ፍቅረኛውን ጥቅጥቅ ባለ ጫካ ውስጥ እየሮጠ ሲከተላት..ሲሮጥ…ሳይደርስበት ይቀራል። ከዛም ደክሞት ለምለም ሳር በሆነ ሜዳ ቁጭ ብሎ…”ሰው ጥሩ..” እያለ ያዜማል፤”. ህልሙን ለገጣሚ ሙልጌታ ተስፋዬ (ነፍሰ ሄር) ይነግረዋል። ዘፈኑም ተሰራ። “ምንድነው ቀለበት፣.. እንዳንቺ አላየሁም በዝች ምድር ላይ፣.. አገሯ ወዲያ ማዶ፣..በይ ካልረሳሽኝ-ንገሪኝ..” ዜማዎች ለፍቅረኛው እታገኝ የተደረሱ ናቸው። አበበ ተካ በ1989ዓ.ም “ምርጥ የአመቱ ድምፃዊ” ተብሎ የገንዘብና ወርቅ ሽልማት አግኝቷል።

ደቡብ ሱዳን በጎሣ ፖለቲካ እሳት እየተበላች ነው!

የኃያላኑ የንዋይ ጥማትና የደቡብ ሱዳን የጎሣ ፍልሚያ

south sudan and the superpowers


ከተመሠረተች ምንም ያህል ያልሰነበተችው ደቡብ ሱዳን ሕዝቧ ሰላሙንና ነጻነቱን በደስታና በጸሎት አጣጥሞ ሳይጨርስ በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ከወደቀች አንድ ወር አልፏታል፡፡ ጎሣን መሠረት በማድረግ የተቀሰቀሰው ፍልሚያ ግን የተጀመረው ገና ደቡብ ሱዳን አገር ከመሆኗ በፊት እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ በደቡብ ሱዳን ሣር ላይ የኃያላኑ ዝሆኖች የእጅ አዙር ጠብና ፍጥጫም አብሮ የሚጠቀስ ነው፡፡

“ቀዶ ጥገና ካላገኙ በኦሮሚያ 200 ሺህ ያህል ሰዎች የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ” ቢቢሲ


eye treatment
በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኘው የኩዩ ቀበሌ ግማሽ ያህል ነዋሪዎቿ አይነ ስውር የመሆን አደጋ የተጋረጠባቸው ናቸው ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡ በዚሁ መንደር በሚገኘው የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪ የሆኑ ህጻናት በቤተሰባቸው ውስጥ የዓይን ችግር ያለበት ሰው እንዳለ ሲጠየቁ 20 ያህል ህጻናት እጃቸውን ያወጣሉ ይላል ዘገባው፡፡

“ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”

“ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”

teddy

ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣልፍቅር ያሸንፋል– የኔ ሳይሆን የትውልድ ድምጽ ነው
እዳ አለ የምንል ከሆነም፤ እዳ የሚከፈለውና የሚሸፈነው በፍቅር ብቻ ነው
የፍቅር ጉዞ ከሚለው ሃሳብ እንጀምር፡፡

ዳር ሆነው የሚመለከቱት የጎሳ ፖለቲካ ምሱ “ደም”!!

(ርዕሰ አንቀጽ)

image1

ሂውማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ይበልጥ ጠቧል



መንግስት፤ ተቋሙ የተቃዋሚዎች የፕሮፖጋንዳ ማስፈፀሚያ ነው
“በኢትዮጵያ የነፃ ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ ነው”
“በኤርትራ የመብት ጥያቄ ማንሳት ነውር ሆኗል” ብሏል
የኢትዮጵያ መንግስት የዜጐችን  ሰብአዊ መብት በስፋት ይጥሳል በማለት ተደጋጋሚ ወቀሳና ስሞታ የሚያቀርበው ሂውማን ራይትስ ዎች የተሰኘው አለማቀፍ የመብት ተቋም፤  ሰሞኑን ይፋ ባደረገው አመታዊ ሪፖርቱ፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ነፃነት ይበልጥ መጥበቡንና የነጻ ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ገለፀ፡፡

23 ዓመት + አስደንጋጭ + አሳዛኝ = ወዴት እየሄድን ነው?

“የአዲስ አበባ ተማሪዎች ለከፍተኛ የስነ ምግባር ጉድለት ተጋልጠዋል”

prostitute-in-Addis-Ababa


  • ተማሪዎች ያለዕድሜያቸው ጫት፣ ሲጋራና ልቅ ወሲብ ይጀምራሉ
  • ሴት የቢሮ ሠራተኛ ሴቶች በወሲብ ንግድ ኑሮአቸውን ይደጉማሉ
  • ኢትዮጵያ ልጆችዋን እየከሰረች ነው
  • ትግራይ ጫት መቃም ክልክል ነው
  • “በስነምግባር የታነፁ ዜጐችን በማፍራት ረገድ አገሪቱ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ናት”

የብሔር ፖለቲካ አሳፋሪ ነው፡፡

የብሔር ፖለቲካ አሳፋሪ ነው፡፡

አንድነታችንን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ብናተኩር ሁላችንንም ይጠቅመናል፡፡ 

ኢትዮጵያ ምሳሌ ልትሆንበት የምትችልበት ነገር ሃይማኖት ብቻ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ ብሔር ብሔረሰቦችን በውስጧ አቅፋ የያዘች አገር ናት፡፡ አይደለም ሰማንያ ቀርቶ ሁለት ብሔረሰቦች ያሉባቸው አገሮች ግጭት ውስጥ ሲገቡ እናያለን፡፡ 

ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃቅን ግጭቶች የሉም ማለት ባንችልም፣ በአጠቃላይ ግን ለመኖር የሚያዳግት ግጭት ግን አስተናግዳ አታውቅም፡፡ ይህ ታሪካችን የሚያኮራን ቢሆንም፣ አሁን አሁን ግን የሚስተዋሉት ነገሮች ሃይ ሊባሉ የሚገባቸው ናቸው፡፡ ስለአብሮ መኖር ታሪካችን የማንጠነቀቅለት ከሆነ ይህ አኩሪ ታሪክ ሊበላሽና ሊጠፋ ይችላል፡፡

በተለያዩ ወቅቶች በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚነሱ የብሔር ግጭቶች የጉዳዩን አሳሳቢነት ሊያሳዩን ይችላሉ፡፡ በተለይም አገሪቱ ተስፋ የምታደርግባቸው እነዚህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠባብ በሆነ የብሔር ፖለቲካ ውስጥ ገብተው ሲጋጩና ሲበጣበጡ ማየት አሳፋሪ ነው፡፡

ስኬታማ ውድቀት (Successful Failure!)

ይሄይስ አእምሮ (አዲስ አበባ)

Ethiopian books reviewለውድቀት ስኬት “የምሥራች!” ወይም “እንኳን ደስ ያለን!” የማይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ከነዚህ የደስታ ማብሠሪያ አባባሎች በአንደኛው ጽሑፌን መጀመር ቃጥቶኝ ነበር፡፡ ለማንኛውም ሀገራችን በማንኛውም ዘርፍ በገባችበት ውድቀትና ኪሣራ ምክንያት ልባችሁ ያዘነና ቅስማችሁ የተሰበረ ወገኖቼን “እግዚአብሔር ያጽናችሁ፤ የሀገራችሁን ትንሣኤም ፈጣሪ በአፋጣኝ እውን እንዲያደርግላችሁ የእግዚአብሔርን ልብ ያራራላችሁ” በሚለው የልመና ቃል ፈጣሪን እየተማጸንኩ ወሬየን ልቀጥል፡፡ ትንሽ በንዴት እንድትንጨረጨሩ ፈቃዳችሁ ይሁንልኝ፤ መልካም መንጨርጨር!

Sunday, January 26, 2014

ጃዋርና የቀቢጸ ተስፋ እርምጃዎቹ (ክፍል 5)

ዓለማየሁ መሀመድ (ክፍል 5)

እንደምን ከረማችሁ?
መረጃ 1
Jawar Mohamed Muslim fundamentalistኦሮሞ ፈርስት በሚል ጃዋርና ሸሪኮቹ የከፈቱት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ሰንበቴ ቤትን በተመለከተ ከዚያው መንደር የደረሰኝ መረጃ ነው። ይህ ማህበር ከመቋቋሙ በፊት ጃዋር ያላንኳኳው በር; ያልረገጠው ደጃፍ የለም። ጃዋር የቢዝነስ ጭንቅላት ያለው ይመስላል። ነጋዴ ነገር ነው። ገንዘብ እንዴት እንደሚገኝ ያውቅበታል። በአቋራጭ እንዴት መበልጸግ እንደሚችል ቀን ከሌሊት ያውጠነጥናል። በእርግጥ ኦሮሞ ፈርስት ጥሩ ብልሃት ናት።

የወያኔ የውሸት ዘገባዎች ሲጋለጡ

የወያኔ የውሸት ዘገባዎች ሲጋለጡ

“ኦክስፋም” በመልካም ሥራቸው ከታወቁ ትላልቅ ዓለም ዓቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አንዱ ነው። በቅርቡ አንድ መቶ ሀያ አምስት አገሮችን ያካተተ ከምግብ አቅርቦትና አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ አራት ዝርዝርና አንድ አጠቃላይ አመላካቾች አሉት።
1. አመላካች አንድ: የምግብ እጥረት
ይህ አመላካች “በየአገሮቹ ምን ያህል ለበላተኛው የሚበቃ ምግብ አለ?” የሚለውን ይለካል። በጥናቱ ውጤት መሠረት በምግብ እጥረት እጅግ የተጎዱ የመጨረሻዎቹ አስር አገሮች የሚከተሉት ናቸው: – ቡሩንዲ፣ የመን፣ ቻድ፣ ኢትዮጵያ፣ ማዳጋስካር፣ ናይጄሪያ፣ ላኦስ፣ ባንግላዴሽ፣ መካከለኛዉ አፍሪካ ሪፑብሊክ እና ህንድ። ኢትዮጵያ አገራችን ከመጨረሻ አራተኛ ናት።
2. አመላካች ሁለት: ለምግብ የመክፈል አቅም (Affordability)
ይህ አመላካች “የአገሩ ሕዝብ በአገሩ ዋጋ ምግብ ገዝቶ ለመብላት ምን ያህል አቅሙ ይፈቅድለታል?” የሚለውን የሚመልስ ነው። አሁንም ከመጨረሻ እንጀምር። አንጎላ፣ ዚምባቡዌ፣ ቻድ፣ ጉያና፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ጋምቢያ እና ኢራን የየአገሩ ሕዝብ ምግብ መሸመት የሚቸገሩባቸው
 አገሮች ናቸው። አገራችን ኢትዮጵያ ከመጨረሻ አምስተኛ ናት።

Saturday, January 25, 2014

ሱማሊያዊት ኢትዮጲያ(አሌክስ አብርሃም )

 ይሄውላችሁ ዛሬ ቤት ለቀኩ !! ምርጧን ቅዳሜ እቃ ከዛ ከዚህ በማንዘፋዘፍና ‹‹ቆምጨ›› ጋር በመነታረክ እንዳሳለፍኳት ስነግራችሁ በታላቅ ደስታ ነው ! ምክንያቱም ቅዳሜ ቀን ምንም ይፈጠር ምን ቅዳሜ መሆኑ በራሱ አንዳች የሰላም ስሜት አለውና …. ብለን ቅዳሜያችንን የነጀሱትን ነገራ ነገሮች ሁሉ አፉ ካልን በኋላ ስለነበረው ነገር ጨዋታችንን እንቀጥላለን ! (አሌክስ አብርሃም ነኝ ከአዲሱ ቤቴ ልበል እንዴ? )

ጓድ መንግስቱ ሃይለማሪያም ‹‹አንድነት ሃይል ነው ›› የሚል መፎክር እንደነበራቸው ‹ሰምቻለሁ› ብላችሁ ‹‹እድሜየ አልደረሰም በደርግ ጊዜ አልተወለድኩም ልትል ነው …ምናምን ›› ስለምትሉኝ የጓድ መንግስቱን መፎክር ባልሰማ አልፈን የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹መደራጀት ሃይል ነው ›› ያሉትን ንግግር ለዚህ ፅሁፍ እጠቀማለሁ ! እውነት ነው መደራጀት ሃይል ነው ! ዛሬ ነው የገባኝ እነዚህ ተደራጅተው በተለይ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ እቃ የሚያወጡና የሚያወርዱ ‹ቆምጨወች› እንዴት ሃያል ሁነዋል ጃል ? 

እኔኮ መንግስት ሌባና ሱሰኛ ጎረምሶችን እያደራጀ ህዝብ እንዲዘርፉ መላኩን አልሰማሁም ነበር ! እንግዲህ ያው ባለፈው አከራዮቸ ኪራይ ጨመሩብኝ ብየ ስነጫነጭባችሁ እነደነበር ታስታውሳላችሁ ብዙወቻችሁ ‹‹ አሌክ አይዞህ ሽ አመት አይኖር መዝረጥ አድርገህ ክፈላ ›› የሚል ምክራችሁን ስለላካችሁልኝ የአከራይ ተከራይ አምላክ የእናተን መጨረሻ ያሳየኝ ብየ እንባየን ወደሰማይ ረጭቸባችኋለሁ ! ቀልዱን እንተወውና አከራይ የፈለገውን ማስከፈል እንደሚችል ‹‹ነፃገባየው ›› ደንግጎለታል ! ሚስትህ በወለደች በሁለተኛው ቀን እንደአራስ ጠያቂ እቤትህ መጥቶ ‹‹ኪራይ ጨምር ካልሆነም ውልቅ ›› የሚልህን አከራይ ኧረ በህግ ልትለው አትችልም ‹መብቱ› ነዋ !

አብረሃ ደስታ በአዲግራት ድብደባ ተፈጸመበት


Ethiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekele
አብረሃ ደስታ
(ECADF) አብረሃ ደስታ ፌስቡክን በመጠቀም ከመቀሌ (ትግራይ) በሚያሰራጫቸው ወቅታዊ መረጃዎች፣ የፖለቲካ ትንታኔዎች እና ዜናዎች በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ዘንድ አብዝቶ ይታወቃል። የአረና-ትግራይ ፖለቲካ ፓርቲ አባል እንደመሆኑ ደግሞ የፓርቲውን ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች ይዘግባል።

Friday, January 24, 2014

የሁለት አመት ህዝባዊ ንቅናቄ ዛሬም ተደገመ! (ድምፃችን ይሰማ)

የትግላችን ማረፊያ ድል ብቻ መሆኑን ዛሬም አውጀናል!

አርብ ጥር 16/2006
Ethiopian Muslims protest Jan 23, 2014
የዛሬዋ እለት ለህዝበ ሙስሊሙ ካለፉት ስድስት ወራት ለየት ያለ ክስተትን አስተናግዳ ያለፈች ጁሙዓ ነች፡፡

ሌንጮ ከኦነግ እስከ ኦዴግ


በዘሪሁን ሙሉጌታ
የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች አንዱ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለሱ መሆኑ በሰፊው ሲዘገብ ቆይቷል። አቶ ሌንጮ ከኦሮሞ ሊሂቃን አንዱ ከመሆናቸው ባለፈ “ትግሉን ወደ ሀገር ቤት ማስገባት” በሚል መርህ ከኦነግ ወጥተው የራሳቸውን ድርጅት አቋቁመዋል።
አቶ ሌንጮ ያቋቋሙት ድርጅት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) የሚባል ነው። ድርጅቱ በውጪ ሀገር ቢመሰረትም በኢትዮጵያ ውስጥ ሕጋዊ እውቅና ሊኖረው የሚችለው በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሲመዘገብ ብቻ ነው። አቶ ሌንጮ ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል፣ አልመጡም የሚለው ጉዳይ ለጊዜው ግልፅ አይደለም። ግልፅ የሆነው ጉዳይ አቶ ሌንጮና የመሠረቱት ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ የመምጣት ሀሳብ ያለው መሆኑ ብቻ ነው። ይሄም የተረጋገጠው የድርጅቱ መሪ አቶ ሌንጮ ለታም ሆኑ፤ የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሌንጮ ባቲ በግልፅ “ትግሉን ወደ ሕዝቡ እናስገባለን” ማለታቸው ነው። 
አቶ ሌንጮም ሆኑ ጓደኞቻቸው “ትግሉን ወደ ኢትዮጵያ እናስገባለን” ከማለት ባለፈ እንዴት? የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ አልመለሱም። ይሄው መሠረታዊ ጥያቄ ባለመመለሱም በብዙዎች ዘንድ መላምታዊ አስተያየት እንዲሰጥ አስገድደዋል። የኦዴግ ቃል አቀባይ “ስንገባ ሁሉንም እንናገራለን” ከማለት ባለፈ የአገባባቸውን እንዴትነት “ሾላ በድፍን” አድርገውታል። 
የኦዴግ አገባብ ለጊዜው ምስጢራዊ ቢመስልም፤ አንድ ነገር መገመት ይቻላል። እሱም ኦዴግ [የአቶ ሌንጮ ድርጅት] ኢህአዴግ ሁልጊዜ በቅድመሁኔታነት የሚያስቀምጠውን “ሕገ-መንግስቱን መቀበል” የሚለውን ቅድመ ሁኔታ መቀበል፤ በሌላ በኩል ደገሞ እነ ሌንጮ ለታ በኢትዮጵያ ፓርላማ “ሽብርተኛ” ከተባለው ኦነግ በይፋ ጋብቻቸውን በመቅደዳቸው ሕገ-መንግስቱን “በቅድሚያ ተቀበሉ” የሚለውን የኢህአዴግን ቅድመ ሁኔታ ላይቀርብላቸው እንደሚችል መገመት ይቻላል። ይሁን እንጂ ጉዳዩ በቅድመ ሁኔታ ቀረበም፣ አልቀረበም አቶ ሌንጮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎአቸው እስከቀጠለ ድረስ ሕገ-መንግስቱን አክብረው፣ በሰላማዊ መንገድ መቀጠል የውዴታ ግዴታቸው ይሆናል ማለት ነው። 

Thursday, January 23, 2014

ሀገርን ቆርሶ በመስጥት በስልጣን መቆየት አይቻልም

ብሌን ንጉሴ (ከጀርመን)

Ethiopian government to hand over land to Sudanአንባገነኑ የኢትዮጵያ  መንግስት የሀገሪቱ እና የህዝቦችን ጥቅም ያላአንዳች ይሉኝታ ለባእዳን አሳልፎ ሲሰጥ እነሆ 22 አመታት ተቆጥረዋል፡፡ መቼም እያንዳንዱን የወያኔ ጉድ መዘርዘር አንባቢን ማሰልቸት ቢሆንም ከሰሞኑ ደግሞ የአቶ መለስን ራዕይ ከማስፈጸም ውጭ የራሱ የሆነ አመክንዮ የሌለው ጠ/ር ሀይለማሪያም ደሳለኝ በአያት ቅድመ አያቶቻችን አጥንት ተከብሮ የቆየውን የሀገራችን ለም መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ሙሉ ፈቃደኝነቱን አሳይቶ ተፈራርሞ ተመልሷል፡፡

ከቃሊቲና ቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ የሚያንጸባርቁ ከዋክብት (ዳዊት ከበደ ወየሳ፣ አትላንታ)


Reeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Journalism Award winner.
ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ)
(ይህ ጽሁፍ የርዕዮት አለሙ የልደት በአል በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት; ከውጭ አገር ንግግር እንዳደርግ በተጋበዝኩበት ወቅት… የስራ ባልደረቦቼን እስክንድር, ውብሸት እና ርዕዮትን በማሰብ የተዘጋጀ ነው)
ይህ ሳምንት የታላቁ ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በመላ አሜሪካ የሚከበርበት ነው:: በአሜሪካ ከክርስቶስ ልደት ቀጥሎ ስራ እና ትምህርት ቤት ተዘግቶ ልደቱ የሚከበርለት አንድ ሰው ቢኖር ማርቲን ሉተር ኪንግ ብቻ መሆኑን ልብ ይበሉ::

አልበሺር እና የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ጥረት

የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር ሀሰን አልበሺር በኤርትራ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ኣጎራባች ኣገሮች ግንኙነት ከማጎልበት ጎንለጎን በአካባቢያዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገለጸ። ኣልበሺር ከኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ባደረጉት የሶስት ቀናት ቆይታ የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ
በተለይም የኢትዮ ኤርትራን የሰላም ንግግር ስመልክቶ መነጋገራቸውን ምንጮች ኣመልክቷል።
የኣሁኑ ውይይት በሁለቱ ተደራዳሪ ኣገሮች በኩል ሊቀርቡ በሚችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነበርም ተብሏል።
የሱዳኑ መሪ ኦመር ሓሰን ኣልበሺር፣ ባለፈው ሳምንት በኤርትራ ያደረጉት የሶስት ቀናት ጉብኝት፤ የሱዳኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ኬርቲ ለዜና ወኪሎች እንዳስረዱት፤ የሁለቱን ኣጎራባች ኣገሮች ግንኙነት በማጎልበት ላይ ያተኮረ ነበር። የኣልበሺር ጉብኝት ባለፈው ህዳር ወር የኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተደረገ መሆኑን የጠቀሱት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኬርቲ በዚህ ግንኙነት ሁለቱ መሪዎች ከዚህ ቀደም የተፈረሙ የውል ስምምነቶች ሊተገበሩ ስለሚችሉባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም ኣስረድቷል።
ባለፈው ማክሰኞ ኤርትራ ሲገቡ ደማቅ ኣቀባበል የተደረገላቸው ኣልበሺር ከኣስመራ ውጪ ያሉ ኣንዳንድ ከተሞችንም የጎበኙ ሲሆን በኤርትራ 21ኛ ዓመት የነጻነት በዓል ላይም ተገኝተው ነበር። ሁለቱ መሪዎች፣ ኣልበሺር እና ኢሳያስ፣ የዔርትራው ገዢ ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች የበላይ፣ የማነ ገ/ዓብ፣ ለዜና ምንጮች እንደገለጹት፣ የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ በበርካታ አካባቢያዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ ኣንዱና ዋናው የመሪዎቹ አጀንዳ የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ንግግር ነው ተብሏል።
በኖርዌይ ኣገር፣ ስታቫንገር ዩኑቨርሲቲ፣ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑት ዶ/ር ግሩም ዘለቀ እንደሚሉትም የኣልበሺር የኣስመራ ጉብኝት የሰላም ንግግሩ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን በሁለቱ ወገኖች በኩል ሊቀርቡ በሚችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
እርቀ ሰላም መውረዱ ለሁለቱም ኣገሮች በተለይ ም ደግሞ ዶ/ር ግሩም እንደሚሉት ለኤርትራ ከፍተኛ ጠቀሜታ ነው ያለው።
ከኤርትራ በኩል በጉዳዩ ላይ እስከ ኣሁን ይፋ የሆነ መግለጫ ባይኖርም በኢትዮጵያ በኩል ግን፤ የጠ/ሚኒስትሩ ቃ/አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ እንደሚሉት፣ ቀደም ሲል የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ለመደራደር ግን መንግስት ዝግጁ ነው።
በዚህ የሰላም ንግግር፤ ከተሳካ ማለት ነው፤ ተጠቃሚዎቹ በዋናነት ሁለቱ ኣገሮች ቢሆኑም ዶ/ር ግሩም ዘለቀ እንደሚሉት ደግሞ ኣልበሺርም ቢሆኑ በግልም ጭምር ተጠቃሚ መሆናቸው መዘንጋት የለበትም።
ከተገንጣዩዋ የደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር ካለባቸው የግዛት ይገባኛል ውዝግብ በተጨማሪም የዳርፉር ቀውስን ጨምሮ በሰሜን ኩርዱፋን እና በብሉ ናይል ግዛቶችም በውስጥ ችግሮች ተጠምደው የሚገኙት ኣልበሺር ምንም እንኳን ከኣፍሪካ ህብረት በኩል አንጻራዊ ተቀባይነት ቢኖራቸውም በምዕራባውያኑ ዘንድ እንደ ወንጀለኛ መፈረጃቸው ይታወቃል። በዚሁ የተነሳም ዓለም ዓቀፉ ፍ/ቤት ICC የእስር ማዘዣ እንደቆረጠባቸው ይገኛሉ።
ጃፈር ዓሊ
ኂሩት መለሰ

እነ አንዷለም አራጌ ነገ ሰበር ሰሚ ችሎት ይቀርባሉ፤ ሕዝብ ችሎቱን እንዲከታተል ጥሪ ቀረበ፤

አንባቢዎች ዘንድ የ2005 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ ሰው የሚለውን ስያሜ ያገኘው የሕሊና እስረኛው አንዷዓለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንንና ክንፈ ሚካኤል ደበበ ነገ ጥር 16 ቀን 2006 (ጃንዋሪ 24 ቀን 2014) በሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚቀርቡ ከቤተሰቦቻቸው አካባቢ የተገኘው መረጃ አመለከተ። እነዚህን የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚፈልጉ ወገኖች 6 ኪሎ የሚገኘው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።
በአንካሳው የኢትዮጵያ የሽብር ሕግ ከግንቦት 7 ጋር በማያያዝ ሽብር ለመፈጸም በማቀድ በሚል እድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷአለም አራጌ በእስር ቤት በመሆንም በጽናት በመታገል የሰላማዊ ትግል አርማ ሆኗል በሚል በብዙዎች ዘንድ ይወደሳል። ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷዓለም አራጌ የተላለፈበትን ዕድሜ ልክ እስራት ፍርድ፤ እንዲሁም ናትናኤል መኮንን እና ክንፈሚካኤል ደበበ የተላለፈባቸውን ቅጣት ለታሪክ ለመተው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲታይ የወሰዱት ሲሆን ነገ ሰበር ሰሚ ችሎቱ የሚሰጠው ውሳኔም በቤተሰቦቻቸው ዘንድ በትልቅ ተስፋ እንደሚጠበቅ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ነገ በስድስት ኪሎ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ሲሰየም እነ አንዷለም አራጌም አብረው የሚቀርቡ ሲሆን የሚታገሉለትና መስዋዕትነት እየከፈሉለት የሚገኘው ሕዝብ በችሎቱ በመገኘት ይህን «ፍትህ የምትዋረድበትን
ወይም ፍትህ የምትታይበትን» ታሪካዊ ቀን እንዲመለከት ከቤተሰቦቻቸው እና ከወዳጆቻቸው ጥሪ ቀርቧል። ይህን ተከትሎም በፌስቡክና በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች «እነ አንዷለም ፍትህ ያግኙ፤ ይፈቱ» የሚለው ቅስቀሳ ቀጥሏል።

Deacon Daniel and Megabe-Hadis Eshetu at Topia Jazz poetry

Wednesday, January 22, 2014

በሰብአዊ መብት አያያዝ አደጋ ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ ገፅታ አሁን ደግሞ ተባብሷል ይለናል Human Right Watch በ2014

በሰብአዊ መብት አያያዝ አደጋ ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ ገፅታ አሁን ደግሞ ተባብሷል ይለናል Human Right Watch በ2014 የዓለም የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርቱ፡-ኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል፤ በ2013 ዓ.ም ተጨባጭ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ አልታየም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት እና በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ላይ የጣሉትን ጥብቅ ገደብ ማስፈጸማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን የሲቪል ማህበራትን እና ነጻ መገናኛ ብዙሃንን እንቅስቃሴ ለማዳከም አፋኝ ሕጎችን ይጠቀማሉ፤ግለሰቦችንም ፖለቲካዊ መነሾ ያላቸውን ክሶች በመመስረት የጥቃት ዒላማ ያደርጋሉ።

በርካታ ሙስሊሞች “ሕዝብን ለሽብር ቀስቅሻለሁ” ብላችሁ እመኑ በሚል በእስር ቤት እየተገረፉ መሆኑ ተዘገበ

ህወሐት መራሹ የኢትዮጽያ መንግስት ሕዝበ ሙስሊሙ ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው ሲል ቢቢኤን ራድዮ ዘገበ። እንደ ራድዮው ዘገባ ከኢዱ ጅምላ ጭፍጨፋ ቡኋላ መንግስት ልዩ ግብረ ኃይል በማቋቋም በአ/አበባ በወልቂጤ እንዲሁም በአዳማ ከተማዎች ላይ የሚገኙ መስጂድ የሚያዘወትሩ ወጣቶችን ከየቦታው አፍኖ በመውሰድ በአገራችን ጏንታናሞ ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ “ሕዝብን ለሽብር ቀስቅሻለሁ” ብላችሁ እመኑ እየተባሉ ቀን ከሌት የስቃይ አይነት ሲያስቆጥራችው ከርሞ ጥር 7 2006 ቁጥራቸው 16 የሚደርሱ ወጣቶችን የወያኔ ፋሽን የሆነውን የሽብርተኝነት ክስ መስርቶ ወደ ቂሊንጦ (ሒጅራ ኮምፓውንድ ) አዛውሯቸዋል::

ከሱዳን ጋር የሚደረገው የድንበር ውዝግብ የሞራልና የሶሻል ጥያቄ እንጅ የህግ ድጋፍ የለውም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ

ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኑ ይህን የተናገሩት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የደህንነት ሰራተኞች በተገኙበት በተደረገው ግምገማና ውይይት ላይ ነው።

በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር የማካለል እንቅስቃሴ ከ1965 ዓም ጀምሮ በጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌና በሱዳኑ አቻቸው ጃፋር ኤሊ ሜሪ መካከል የተጀመረ እና እስካሁኑም የዘለቀ መሆኑን ባለስልጣኑ አውስተዋል።
ሱዳኖች “ኢትዮጵያውያን የጉዊን መስመር እየተባለ የሚጠራውን ቦታ አልፈዋል” በሚል  ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ተመሰርቶ ኮሚቴ መቋቋሙን ያወሱት ባለስልጣኑ፣ “ይሁን እንጅ ኮሚቴው ምንም አይነት የድንበር ማካለል ሳያደርግ እስከዛሬ ቆይቷል ።”
“አሁን በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል የሚደረገውን ውይይት የምትገዛው ደብዳቤ ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተለዋወጡት ደብዳቤ መሆኑን  ባለስልጣኑ ጠቅሰው ፣ ኮሚቴው በጊዜው ችግሩን በሰላም ለመፍታት የመፍትሄ ሃሳቦችን አቅርቦ እንደነበርም አክለዋል።

በኢትዮያ እና ሱዳን ድንበር ዙሪያ ወቅታዊና ትምህርታዊ የውይይት መድረክ (ሰማያዊ ፓርቲ )

Blue Party Ethiopia



ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮ ሱዳን ጉዳይ ላለፉት ወራት ነገሩን በቅርበት ሲከታተል የቆየ ሲሆን በጉዳዩም ላይ አቋሙን በመግለጫ መልክ ማውጣቱ ይታወሳል አክሎም ፊታችን ጥር 25 ቀን ለቦታው ቅርበት ካላቸው ከተሞች አንዷ በሆነችው ጎንደር ከተማም ተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል፡፡

በሰማያዊ ፓርቲ ስም አመሰግናለሁ! (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ባለፉት በርካታ ሳምንታት በተናጠል እና በቡድን እየሆናችሁ በአሜሪካ እና በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች የስብሰባ አዳራሾች በመገኘት ለሰማያዊ ፓርቲ ድጋፋችሁን ላደረጋችሁ ወገኖቼ ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ!Semayawi party chairman Engineer Yilkal Getnet's Washington D.C. meeting.
ባለፈው ሳምንት ኢትዮሜዲያ/Ethiomedia.com የተባለው ድረገጽ ባወጣው ዘገባ መሰረት ሰማያዊ ፓርቲ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ ትግል ሂደት “አዲስ የተቃውሞ ኃይል” ሆኖ በመቅረብ ሰላማዊ የስርዓት ለውጥ ሽግግር ለማምጣት “አዲስ ተስፋን ፈንጣቂ” ሆኗል በማለት ገልጾታል፡፡ ወጣቱ እና መንፈሰ ጠንካራው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በተለያዩ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር በተስፋ፣ በሰላም እና በአንድነት መሰረት ላይ ፍቅር የነገሰባት አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ሰማያዊ ፓርቲ ያለውን ራዕይ ለኢትዮጵያውያን/ት ግልጽ አድርጓል፡፡

Tuesday, January 21, 2014

“የአፄ ምኒልክ ወታደሮች በአያቴ ላይ ብዙ በደል አድርሰዋል” – ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (ቃለምልልስ)

“በኢህአዴግ በኩል የአፄ ምኒልክ ሐውልት ይፍረስ የሚል እንቅስቃሴ አልነበረም” ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (ቃለምልልስ)
 
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለ3 አመት የመሩትን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ለኢ/ር ግዛቸው አስረክበዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በፓርቲ ፖለቲካ እንደማይታቀፉ ከተናገሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር በፓርቲ ቆይታቸው፤ በቀጣይ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው፣ በአፄ ምኒልክ፣ በደቡብ ሱዳን በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ዙሪያ ከ“ሎሚ” መፅሔት ም/አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
 
ሎሚ፡- ያለፉት 3 ዓመታት የአንድነት ፓርቲ ቆይታዎ ምን ይመስላል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ከጤንነትም ከቴክኒክ ሁኔታ (ለምሳሌ መኪና የለኝም)፤ ከዚህ ከዚህ አኳያ የመንቀሳቀስ ብቃቴ የተገደበ ነበር፡፡ ይሔ መገደቡ ደግሞ ለፓርቲው አይጠቅምም፡፡ ብዙ መሠራት ያለበትን ነገር ያለመስራት ሁኔታ አለ፡፡

ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጅ አሸባሪ ናት ብየ አላምንም!

(ነቢዩ ሲራክ)

reeyot

የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ስራዎች በቅርብ ተከታትያለሁ! ውንጀላ እስራቷን ፣ ህክምና እንድታገኝ መደረጓን እና የቤተሰብ እና የወዳጆችዋ ጉብኝት እንዳታገኝ መከልከሏን ሰምቻለሁ ! ይህ ሁሉ በዚህች የመናገር የመጻፍ ነጻነቷን ተጠቅማ ህገ መንግስታዊ መብቷን በተጠቀመች ወጣት ጋዜጠኛ ላይ የሚከፈል መስዋዕትነት ቢሆንም ስቃይ መከራዋ ፣ በደል መገፋቷ ያንገበግበኛል!እናም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ተተገፈፈቸው መብቷ ይመለስ ዘንድ በሚደረገው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ደጋፊ ነኝ ! ርዕዮት አሸባሪ አይደለችም ብየ አምናለሁና ፊርማየን ለድጋፍ ሳስቀምጥ ኩራት ይሰማኛል !
ፍትህ ለጋዜጠኛ ርዕዮትና ለመሰሎቿ ስመኝ ለኢትዮጵያስ እንኳንም ተወለድሽ የምላት አሁንም በኩራት ነው! ግጥሙን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ::

የወያኔ ነፍስ በበረከት ስምዖን በኩል ስትቃዥ

ነፃነት ዘለቀ (አዲስ አበባ)

አንደኛው መስከረም ጠብቶ ሌላኛው መስከረም እስኪጠባ ድረስ ባሉት የ365.25 ቀናት ውስጥ ስንት ጉድ መስማት እንዳለብን የሚጠቁም አሃዛዊ መረጃ ሊኖር እንደማይችል መቼም ግልጥ ነው፤ ነገር ግን የዘመናችን ኢትዮጵያ የታሪክ ጎርፍ ያመጣብን ከወያኔና መሰሎቹ በስተቀር ሌሎቻችን ያልጠበቅነው ዱብዕዳ ክስተት ምሥጋና ይንሳውና በዬቀኑ የማንሰማውና የማናየው ዕንቆቅልሽ እንዳይኖረን ሆነናል፡፡ በዚህ መልክ በተለይ ባለፉት 22.8 ዓመታት ውስጥ የታዘብነው የታሪክ ምፀትና ወኔያዊ የውሸት ስንክሳር በረጂሙ ታሪካችን ታይቶም ሆነ ተሰምቶ እንደማያውቅ ማንም ጤናማ ኅሊና ያለው ዜጋ የሚመሰክረው ይመስለኛል፡፡ ለዛሬ አንዱን የወያኔ ነጭ ውሸት እንመለከታለን፡፡Bereket Simon, Woyanne propaganda chief
በነገራችን ላይ ወያኔና እውነት ዐይንና ናጫ መሆናቸውን የማይረዳ ወገን እንደማይኖር እገምታለሁ፡፡ የወያኔን ተፈጥሮ ወያኔ ራሱን ጨምሮ ሁሉም ያውቃል፤ የወያኔ እውነት፣ የእውነት ግልባጭ የሆነችው ሀሰት ናት፡፡ ለወያኔ ውሸት ማለት እውነት ናት፡፡ ለወያኔ እንደእውነት የሚመርና የሚያቅር ነገር የለም፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ለወያኔ እንደሀሰት የሚጣፍጥ ምንም ነገር የለም፡፡

የ 2014 የዓለም የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት፡- ኢትዮጵያ

Aerial view of “Maekelawi” compound, the main federal police investigation center, in Central Addis Ababa, on February 18, 2013.
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል፤ በ2013 ዓ.ም ተጨባጭ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ አልታየም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት እና በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ላይ የጣሉትን ጥብቅ ገደብ ማስፈጸማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን የሲቪል ማህበራትን እና ነጻ መገናኛ ብዙሃንን እንቅስቃሴ ለማዳከም አፋኝ ሕጎችን ይጠቀማሉ፤ግለሰቦችንም ፖለቲካዊ መነሾ ያላቸውን ክሶች በመመስረት የጥቃት ዒላማ ያደርጋሉ።

Monday, January 20, 2014

“ወደው አይስቁ” (ክንፉ አሰፋ)

የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ  የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።
የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ።  “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። …  የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”
በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። “የባሰ አታምጣ!” ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል።  የሚናገሩትን አያውቁትም።  የማየውቁትን ነገር ሁሉ ይናገራሉ።  እነሱ የሚናገሩትን ደግሞ በምኒሊክ ቤተ-መንግስት ያሉ ሰዎቻቸው በተግባር ይፈጽሙላቸዋል።

በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!

ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ

Ethiopian government to hand over land to Sudanሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች ፣መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪባህልና ወግያለን፣የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉአላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት። በተለያየ ወቅት የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመትና ሉአላዊነቷን ለመዳፈር የሞከሩ ሃገራት ሁሉ፣በውድ ልጆቿ የተባበረ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ኢትዮጵያን ዳግም እንዳይመኟት የተባረሩበትና የኢትዮጵያን አይበገሬነት በአፍሪካም ሆነ በአለም መድረክ ያስመሰከረች፣ አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ በማቆየት በአለም ታሪካዊ ስፍራ ያላት፣ በቀደምት ውድ ልጆቿ የደም መስዋዕትነት ሀገራችን ሉአላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ አመታት ቆይታለች።

“ነፃነታችንን መልሱልን!?” ከተመስገን ደሳለኝ

ቃር ከሚገፋ ፈተና የሚታደጋቸውን ብቸኛ የመውጫ መንገድ ለማስታወስ እሞክራለሁ፡፡
‹‹እስልምናን መቆጣጠር››
ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ገዥው ፓርቲ እስልምናን ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠር እቅዱን ዳር ለማድረስ ያልፈነቀለው ድንጋይ፣ የአልማሰው ሥር እንዳልነበር ጥቂት የማይባሉ ምልክቶችን አይተናል፡፡ ለምሳሌነትም የቅርቡ በተለምዶ ‹‹የአወሊያ ንቅናቄ›› ተብሎ የሚጠቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ በቂ ይመስለኛል፡፡

Sunday, January 19, 2014

ሾልኮ የወጣ የጥምቀት የጭፍጨፋ ድግስ ሚስጥር

ቹቸቤ

በመጀመርያ ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ። እንዲያው ይሁን ብዬ እንጂ ጥምቀተ ባህር እንኳን ሙስሊም ጓደኞቻችንም አብረውን ይውሉ እንደነበር አስታውሳለሁ።የጥምቀተ ባህር ፀበል ብቻ ሳይሆን የፍቅር ፀበልም የሚረጭበት  የፍቅር በታ ነው።: በተለይ  ተረ … ተረረረ…. ረረረ የምትል ማንም ከደፈረ የሚጫወታት ሃርሞኒካ ተይዛ ከሚጨፈርበት እነ አብዱና እነ ሙስጠፋስ መች ይጠፉ ነበር። ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ብለው ሜዳውን የሚሞሉት ኮረዶች መካከልስ ተቃቅፈው ወይ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከሚሄዱት ሃሊማና ሩቅያስ መች ይታጡ ነበር። “ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስትያኑ…ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ”  ያለው ቴዲ ይህን በዐይኑ አይቶ እንጂ ተረት ሰምቶ አይደለም። ደግሞም ነገም ወደፊትም አብረን እንኖራለን የማያኖሩን አይኑሩ! አሜን አላችሁ?

ግራና ቀኝ ጠፋን! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነጻነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ፤ ትምህርት በተስፋፈበትና ማንም እንደፈለገ ለመጻፍና ለማሳተም ችሎታውም ዕድሉም በማይገኝበት፣ ሳያበጥርና ሳይሰልቅ አሰር-ገሰሩን ጽፎ በአደባባይ የሚወጣውን ጥምብ-እርኩሱን አውጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው የሚያደርጉ የታወቁና የሰላ አእምሮና ብዕር ያላቸው አርታእያንና ሐያስያን (ገምጋሚዎች) ባሉበት ብዕሩን የሚያባልግ ጸሐፊ አይወጣም፤ ይህ ሁሉ ባልተሟላበት እንደኛ ባለ አገር ውስጥ ብዕርን ማባለግ እንደመብት ወይም እንደነጻነት እየታየ ነው፡፡