Translate

Monday, September 14, 2015

የዴምህት ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስግዶም ለምን ከዱ?

(ECADF) – የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምህት) ከአርበኞች ግንቦት7፣ ከአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ እና ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ጋር ጥምረት መመስረቱን ባወጀበት ማግስት የጥምረቱ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙትና ዴምህትን ለዓመታት ሲመሩ የኖሩት አቶ ሞላ አስግዶም መክዳታቸው ታውቋል።Former TPDM chairman Mola Asgedom
ኢሳት በአጭር ሰበር ዜና ዘገባው እንደገለጸው ከሆነ አቶ ሞላ አስግዶም ድርጅታቸው ጥምረት እንዲመሰርት ፍላጎት አልነበራቸውም። ይሁንና አብዛኛው የዴህምህት አመራሮች ጥምረቱን በመፈለጋቸው ምክንያት ጥምረቱ እውን ሊሆን ችሏል።
ፋሲል የኔዓለም (የኢሳት ጋዜጥኛ) ወደ ኤርትራ ተጉዞ በነበረበት ወቅት ከአቶ ሞላ አስግዶም ጋር የመወያየት እድል አግኝቶ ነበር። የአቶ ሞላ አስግዶም መክዳት ከተሰማ በኋላ ፋሲል እንዲህ በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል፣

Thursday, September 10, 2015

ሳሞራ ወይስ ሕወሃት “ሕገመንግሥቱን” የጣሱት? ወይስ ሁለቱም?

ሳሞራ ወይስ ሕወሃት “ሕገመንግሥቱን” የጣሱት? ወይስ ሁለቱም?

samora
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ስብሰባ ባደረገበት ወቅት ሳሞራ የኑስ ህወሃትን ለብሰው፣ ህወሃትን አጥልቀው (ጫማቸውና ሌላው አይታይም እንጂ) ህወሃትን ሆነው ታይተዋል፡፡

Wednesday, September 9, 2015

ቴዲ “የፍቅር ነብዩ”ን ተውት ስለ ፍቅር ደግሞ ደጋግሞ ይዘምር… (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እረ ተዉኝ ባትነኩኝ ምናለበት
አባካችሁ ሰዎች ስራዬን ልስራበት።
ታላቁ ጥላሁን ገሠሠ
ፍቅር ሁሉንም ድል ያደርጋል !
ሸክስፒር “አስራሁለተኛው ሌሊት“ በሚለው የትያትር ፁሁፋቸው ላይ የኦርሲኖ መስፍን በአዳራሹ ተሰባስበው ለነበሩት ድምጻውያንና ሙዚቀኞች  እንዲህ በማለት ተናግረው ነበር፣ “ሙዚቃ የፍቅር ምግብ እስከሆነ ድረስ አሁንም ዘምሩ፣ በርካታ ሙዚቃዎችን ደግማችሁ ደጋግማችሁ ዘምሩልኝ…“Teddy Afro, Ethiopian popular singer
እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቅጽል ስሙ ቴዲ አፍሮ እየተባለ የሚጠራውን ቴዎድሮስ ካሳሁንን በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከብዙ ጊዜ በፊት ጀምሮ ለመንፈሳቸው እርካታ ምግብ የሆነውን የህዝቦች የፍቅር ሙዚቃ እንዳይጫወት እገዳ ሲጥልበት ቆይቷል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የቴዲን ህይወት እንደ እነርሱ በመከራ የታጀበ እንዲሆን አጥብቀው ይሰራሉ፡፡ እንደ እነርሱ “የመከራ ፍቅር ኩባንያ“ እንዲሆን ይፈለጋል፡፡
ቴዲ ግን ስለሰው ልጆች ፍቅር ደስታ እንጅ በምንም ዓይነት መልኩ ስለመከራ አይዘምርም፡፡
ቴዲ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ለማገልገል የተፈጠረ ድምጻዊ ከያኒ አይደለም፡፡ ስለመከራ እና ስቃይም አይዘምርም፡ መዘመርም አይችልም።
ቴዲ መቸውንም ጊዜ ቢሆን ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ባዶ ፕሮፓጋንዳ ማድመቂያ የሆኑትን የጥላቻ፣ የበቀል፣ ኢፍትሀዊ እና ጥልቅ ጥላቻዎችን የሚያነግሱ ሙዚቃዎችን በምንም ዓይነት መልኩ አያቀነቅንም፡፡

ሻዕቢያ ህወሃትን አስጠነቀቀ

የጦርነት አታሞ እየተመታ ነው፤ “ሳንጃም ተስሎብኛል” ብሏል

melesna isayas
ቀደም ሲል የአባትና ልጅ “አፈጣጠርና ግንኙነት” የነበራቸው ወዳጆች ሻዕቢያና ወያኔ ያልተጠናቀቀውን የባድመን ጦርነት ካካሄዱ በኋላ ለዳግም ግጥሚያ ዝግጅት እያደረጉ ነው። “የጦርነቱ ሁኔታ” ያሳሰበው ሻዕቢያ በማስታወቂያ መ/ቤቱ በኩል ለህወሃት ማጠንቀቂያ ሰጥቷል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በዘገበው መሠረት መግለጫው ህወሃት ኤርትራን እንዲወጋ የአሜሪካንን ይሁንታ አግኝቷል ብሏል።

Monday, September 7, 2015

ከዝምታው በስተጀርባ (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ
አንዳንድ ወገኖች የወያኔ አገዛዝ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ያለበት ደረጃ መድረሱ እያበገናቸው፣በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚደርሰው ጥፋት እያስቆጫቸው የሕዝቡን ዝምታ በፍርሀት ሲገልጹት ይሰማል፡፡ አንዳንዶች እንደውም ገፋ አድርገው በቅርብ ግዜ የታየውን የአረብ አብዮት እያነሱና ተኒዚያና ግብጽን እየጠቀሱ ኢትጵያዊ በምን ያንሳል በማለት በምሬት ይናገራሉ ይጽፋሉ፡፡
የአረብ አብዮት አይነት ሰላማዊ የሕዝብ ተቃውሞና አምቢተኝነት ወያኔ አጥብቆ የሚፈራው፣ ተቀዋሚው ቢሆን የሚሻው፣ የኢትዮጵ ሕዝብ ሊያደርገው የማይችለው ነው፡፡ ሁሉም የየራሳቸው ምክንያት አላቸው፡፡ ወያኔ በሕዝብ አለመወደዱን ማወቁ፣ ለሥልጣኑ መስጋቱና ፍርሀቱ ሲሆን ፤ተቀዋሚው ለውጥ መሻቱ፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን መናፈቁ ነው፡፡ ሕዝቡ የማያደርገው ደግሞ ከጥንት እስከ ዛሬ የኖረበት ወግ ልማዱ ስላልሆነ፣ ትናንት ንጉሶች በቅርቡ ደግሞ አብዮተኞች ሥልጣን ሲነጣጠቁ ያየው በጠብ-መንጃ እንጂ በሰልፍ ስላልሆነ፣ በውርስ የተቀበለውም ሆነ በልማድ ያዳበረው ባለመሆኑ ነው፡፡

Wednesday, September 2, 2015

መለስን የገደለው መለስ ነው (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ
PM Meles Zenawiስለ ቀድሞው ጠቅላይ ምስትር መለስ ዜናዊም ሆነ በአንድ ቅኝት ሲያዘፍኑዋቸው ስለነበሩ ፓርቲዎች እንዲሁም ከተከታይነት ያለፈ ምንም ፋይዳ ስላልነበራቸው ሹማምንት ብዙ የተባለ ቢሆንም ዛሬም አድናቂ ነን ባዮች እወደድ ባዮች በመንግሥታችሁ አትርሱን ባዮች ወዘተ ታላቁ ባለ ራዕዩ ወዘተ ከማለት አልፈው አቶ መለስ ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ሲሰሩና ሲባትሉ እንደሞቱ ሊነግሩን ይዳዳቸዋል፡፡
አቶ መለስ ሀገር ከማስገንጠል ህዝብ እሰከ መነጣጠል (ያውም እንደ አሰቡት አልሆነላቸውም) ወደብ አልባ ከማድረግ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት እስከ መጣር የደረሱ ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድም ነቀርሳ የሆኑ እኩይ ድርጊቶቻቸው እንኩዋን ኢትዮጵያዊ አለም ያወቃቸው ናቸው፡፡ጥቅም ማስተዋልን ነስቶአቸው ዛሬ ስለ አቶ መለስ ተቃራኒውን የሚነግሩን ሰዎች አንድ ቀን የአቶ መለስ ትሩፋት ሲደርሳቸው ከእኛ ብሰውና ልቀው ሲኮንኗቸው እንሰማ ይሆናል፡፡
እኔ ዛሬ በትንሹ ማንሳት የምፈልገው አቶ መለስ የሞቱት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ሲለፉና ሲደክሙ ሳይሆን ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሲማስኑ እንደሆነና ራሳቸውን የገደሉት ራሳቸው መሆናቸውን ነው፡፡

የመሐል ሀገር ሰው መልዕክት ለትግራይ ሰው! (በፍቃዱ ኃይሉ)

ማስታወሻ፡- ቀጥሎ የምታነቡት ጽሑፍ በፍቃዱ ኃይሉ ከቂሊንጦ እስር ቤት ለነገረ ኢትዮጵያ የላከው ነው፡፡
Fekadu Hailu zone9 bloggerበፍቃዱ ኃይሉ
ትግራይ የኢትዮጵያ ገናና ታሪክ መሬቷ ላይ የተጻፈባት ክልል ናት፡፡ ብዙዎች ‹‹የኢትዮጵያ ራስ ናት›› የሚሉት ለዚህ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ ወደኋላ 3000 ዓመት የሚያደርሰው የአክሱም ስልጣኔ አሻራውን ትቶ የሄደው በትግራይ ክልል፣ አክሱም ከተማ ነው፡፡ ከአረቦች ተቀድቷል የሚባለውን የንግስተ ሳባ ታሪክ ‹‹ክብረ ነገስት›› በሚባለው መጽሐፍ ተርጉመው ለዚህ ትውልድ ያኖሩልን የትግራይ ሊቃውንት ናቸው፡፡
ሌላው ቀርቶ ህብረ-ብሄራዊ ቅርስ የሆነንን የሳባ ፊደል ለመላው ኢትዮጵያዊ ያወረሱት የትግራይ ሊቃውንት ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያዊነት ቀለሞች አንዱ የሆነው ያሬዳዊው ዜማ የተቀዳው ከትግራይ ምድር ነው፡፡ እነዚህና ሌሎች ያልጠቀስኳቸው እውነታዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኮራባቸው ናቸው፡፡